🎓"ዕለተ ደቂቅ በሆሳዕና" የልጆች እና የወላጆች ፌስቲቫል ተካሔደ!
አዲስ አበባ ሚያዝያ 04/2017 ዓ.ም፤ በቅኔ ኮንሰልቲንግ ሥር የሚገኙት መቅድም ፎቶ እና ስቱዱዮ፣ አጋቦስ የትምህርት ማዕከል እና አቴና ሚዲያ በጋራ በመሆን ''ዕለተ ደቂቅ በሆሳዕና"በሚል ርዕስ የልጆች እና የወላጆች ፌስቲቫል አካሔዱ::
የቅኔ ኮንሰልቲንግ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሃባው ዓለሙ ከአሐዱ፡ባንክ ጋር እየሠራን ያለውን የአጋርነት ተግባር አጠናክረን እንቀጠላለን በማለት በአፅንኦት ተናግረዋል።ባንካችንም የመርሐ ግብሩ አጋር በመሆን፤በቦታው በመገኘት የሥራ ዘመቻ አከናውኗል::
በተጨማሪም በባንካችን ማርኬቲንግ እና ኮምዩኒኬሽን መምሪያ አስተባባሪነት የአሐዱ:ባንክን ዓርማ የመገጣጠም ውድድር በልጆች መካከል እንዲካሔድ በማድረግና ብላቴና የቁጠባ ሒሳብን በስፋት በማስተዋወቅ ለተወዳደሩት ሕፃናት ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል::
በመጨረሻም በተካሔደው የወላጆች ሲምፖዚየም የባንካችን የጥቃቅን አነስተኛና መካከለኛ እና ገጠር ባንኪንግ መምሪያ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ በለጠ ፋንታዬ ባንካችን ከቴሌብር ጋር በማስተሳሰር ስለጀመረው የት/ቤት ክፍያ ብድር ፣ስለ ብላቴና የቁጠባ ሒሳብ እና አክሲዮን ሽያጭ ማብራርያ ሰጥተዋል::
አሐዱ ባንክ
ከብዙዎች ከብዙዎች!
የአሐዱ፡ባንክ ማኅበራዊ ትስስር ገጾችን ይቀላቀሉ!
Website|
Facebook|
Instagram|
LinkedIn|
YouTube #AhaduBank #አሐዱ_ባንክ