4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Edutainment


እንኳን ወደ ውዱ 4-3-3 አስገራሚ እውነታዎች ቻናላችን በሰላም መጣቹ
እሄ ቻናል ያላወቀቹትን አስገራሚ ነገር በቪድዮ አልያም በፎቶ እና በፅሁፍ የምታገኙበት፣ የተለያዩ አስቂኝ የሆኑ አስገራሚ ነገሮች የምታገኙበትና እውቀትን የምትጨብጡበት ቻናል ነው።
ለማስታወቂያ ስራ - @Abusheymc & @Kiya988
Buy ads: https://telega.io/c/amazing_fact_433

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Edutainment
Statistics
Posts filter


ሁለት አይነት ምስል አይደለም

በ ራሽያዋ መዲና ሞስኮ የምድር ውስጥ ባቡር transport መንገድ ነው😯

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
መልካም በአል 🥰🥰


#ይህን_ያውቃሉ❓

🍾ጀርመናዊ ዘግነት ያላትና በጀርመናዊዎች ዘንድ Julia Güntel  በመባል የምትታወቀው Julia Gunthel Aka Zlata እንደ ኤሮፓውያን አቆጣጠር ሰኔ 05 2013 እግሮቿን በመጠቀም በ 48 ሰኮንድ ውስጥ 8 ጠርሙሶችን ቱርክ ውስጥ በመክፈት ስሟን የአለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ከማስፈሯም በተጨማሪ አለምን ጉድ ማሰኘትም ችላለች አጀብ ነው ስራዋ!!!😱

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433


ታገሱ😁 ትበላላቹ አይዟቹ😢

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

3.2k 0 14 44 151

ለመላው የቻነላችን የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ፡፡
✞ መልካም በዓል ይሁንላችሁ 🙏😊✞        

@AMAZING_FACT_433 @AMAZING_FACT_433


አሁን ሳይህ ስጋ ልበላ ተነስተሃል 😄

3.3k 0 1 19 128

✔️ሳይንቲስቶች.. ከውሀ ወጥተው መሬት ላይ መራመድ የሚችሉ ዘጠኝ የሻርክ ዝርያዎች እንዳሉ አረጋግጠዋል።

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

6.9k 0 9 39 238

Shima enaga ይባላሉ በጃፓን የሚገኙ የወፍ ዝርያ ሲሆኑ እንጨት ላይ ሲያርፋ ምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት  የተጠቀለለ ጥጥ ነው የሚመስለው

@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433


ያሱሺ ታካሃሺ ይባላል

ጃፓናዊ ሲሆን ለትዳር የሚያጫት ፍቅረኛ አለችው: የ"ታገቢኛለሽ ወይ" ጥያቄውን ማቅረብ የፈለገው ለየት ባለ መልኩ ነበር

ይህንንም አስቦ አልቀረም

ጃፓን ውስጥ 7,163 ኪሎ ሜትሮችን በእግሩ: በሳይክል: በመኪና እና በጀልባ በመዞር በካርታ መነጠቢያ ማሽን/ ጂ ፒ ኤስ ላይ "MARRY ME” የሚል ጽሁፍ እና ጦር የተሰበቀበት ልብ ቅርጽ በመስራት ሃሳቡን አሳክቷል

ይህንንም ለማሳካት ስራውን ሙሉ ለሙሉ በመተው ለስድስት ወራቶች ያህል "MARRY ME” የሚለውን ጽሁፍ ለመጻፍ ጦዟል

ይህ ጥረቱ የፍቅረኛውን "አዎ አገባሃለሁ💍” ምላሽ ብቻ አይደለም ያስገኘለት :ይልቁኑስ የአለም ድንቃድንቅ መዝገብ ላይ በጂ ፒ ኤስ የተጻፈ ትልቁ ምስል ሆኖ የክብር መዝገብ ላይ ስሙ ሰፍሯል

❤️🙌🏼


@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

8.1k 0 14 9 173

👙ራቁቷን የሆነች ሴት በ 10 ደቂቃዎች ውስጥ 1000 like🙊ታገኛለች 😡

ግን እስቲ ለዚች ምስኪን እናት ምን ያህል like ይገባታል?😢...

7.4k 0 4 16 1.3k

ያልተዘመረለት የካራማራው ድል (የታሪክ ገጽ)

በ Youtube ቻናላችንን ይመልከቱ 👇
https://youtu.be/VVF48oNiDm8?si=wt_va8joqHLigsCZ


Repost

እንግሊዝና ጋና የሚሻሙበት የቀን ሰራተኛ ፍሪዚ ማክቦንስ ።
.........
በጠዋት ይነሳና ፡ በጋና ዋና ከተማ አክራ ውስጥ እየተገነቡ ያሉ ህንጻዎች ወዳሉበት ቦታ በመሄድ ፡ የቀን ሰራተኛ ይፈልጉ እንደሆን ይጠይቃል ። ስራ ከተገኘ ቀኑን ሙሉ ሲሚንቶ ሲሸከም ፡ ኮንክሪት ሲያቦካ ፡ በአካፋ ሲዝቅ ፡ በባሬላ ሲሸከም ይውልና ፡ ሲደክመው ፡ የእሱ ብጤ ከሆኑ ሰወች ጋር በጋራ በተከራዩት ፡ መብራት የሌለው ጨለማ ክፍል ውስጥ ሄዶ ጎኑን ያሳርፋል ።
............
ስራው ድካም አለው ፡ ተመጣጣኝ ክፍያም አያገኝም ፡ ሆኖም ሁሌም ህይወት ፊቷን አጥቁራበት እንደማትቀር ያስባል ። እና በአንድ ኢንተርቪው ላይ እንደገለፀው ፡ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አውቅ ነበር ብሏል ።
..................

🎚ፍሪዚ ማክቦንስ ፡ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ፡ አንድ ቀን ባላሰበው አጋጣሚ እንግሊዝ የመሄድ እድል አጋጠመው ፡ ሆኖም እዛ ሄዶ. ..  ቢያንስ ጋና ውስጥ እያለ የሚሰራው አይነት ፡ የቀን ስራ እንደሚያገኝ አስቦ ለንደን የደረሰው ፍሬዚ ነገሮች እንዳሰበው አልሆንለት አሉት ።
እና ለምኖ እየበላ ፡ የማክዶናልድ መደብሮች በረንዳ ስር ማደር ጀመረ ።
.........

🎚እንዲህ እንዲህ እያለ ፡ ቋንቋውን ፡ ሀገሩን እየለመደ ሲሄድ በአንድ የነጻ ጂም ውስጥ ተመዝግቦ መስራት ጀመረ ። ይህ ሁሉ ሲሆን ፡ በህልሙም በውኑም አንድ ቀን ቦክሰኛ እሆናለሁ ብሎ፡አስቦ አያውቅም ነበር ። እና በአንድ አጋጣሚ ፡ ለገቢ ማሰባሰቢያ ተብሎ በተዘጋጀ የቦክስ ግጥሚያ ላይ ተሳተፈ ። በዚህ ውድድርም በሚያስደነግጥ ሁኔታ ፡ ተጋጣሚውን በመርታት አሸነፈ ።
......
ልክ በዚያን እለትም የቦክስ አሰልጣኞች አይን ውስጥ ገባ ።
..........
ህይወት መልካም ጎኗን እንደምታሳየኝ ፡ አንድ ቀንም እንደምትስቅልኝ እያሰብኩ የኖርኩ ሰው ብሆንም ፡ በዚህ መልኩ ህይወቴ ይለወጣል ብዬ ግን አስቤ አላውቅም ፡ ነገር ግን ፈጣሪ መንገዶች እንዴት እንደሚጠርግ ያውቅ ነበርና ባላሰብኩት መንገድ አስጉዞ እዚህ አድርሶኛል ይላል ።
.........

🎚ከአመታት በኋላ ዛሬ ላይ ። ያ ፡ በፍቃደኝነትና በነጻ የውድድር መድረክ ፡ የቦክስ ጓንቱን አሟሽቶ ፡ የሪንጉን አለም የተዋወቀው ፍሪዚ ማክቦንስ ፡ በተለያዩ የቦክስ ውድድሮች ላይ ባሳየው ብቃት አብዛኛው ግጥሚያዎቹን በዝረራ እያሸነፈ ፡ እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን የሚል ስም ተሰጥቶታል ።  ባለፈው ቅዳሜ ደግሞ  በእንግሊዝ ውስጥ በተካሄደው ታላቅ የቦክስ ውድድር ላይ ካሸነፈ በኋላ የዚህ ሰው ስም ይበልጥ መግነን ጀምሯል ።

🎚በጋና የኮንስትራክሽን ግንባታዎች ላይ ባሬላና አካፋ በመዛቅ የድህነት ጥግ ውስጥ ይኖር የነበረው ፍሬዚ ማክቦንስ አንድ ቀን የአለም ሻምፒዮን እንደሚሆን እያሰበ ፡ ወደፊት መገስገሱን ቀጥሏል ። ዛሬ ጋና እና እንግሊዝ ይህን ሰው ይሻሙበታል ። እንግሊዛዊው ማይክ ታይሰን ሳይሆን ጋናዊው ነው መባል ያለበት የሚል ነገር ሁሉ ይነሳበታል ።
.............

🎚ገንዘብና ዝና ከስር ከስሩ የሚከተሉት. ... በእንግሊዝና አለም አቀፍ ሚዲያዎች ስሙ እየገነነ የመጣው የ32 አመቱ ፍሬዚ ማክቦንስ. ....

  በእጆቼ የሲሚንቶ መዛቂያ አካፋ ይዤ ፡ አንድ ቀን ህይወት እንደምትስቅልኝ አስብ የነበረው ነገር እንደተሳካ አውቄያለሁ ፡ ባልታሰበ አጋጣሚ ወደቦክስ ስፖርት አለም የገባሁት እጅግ ዘግይቼ ነው ።  ነገር ግን . ..... 
ዘግይቼ ጀመርኩ ማለት .... አልችልም ማለት አይደለም ። አንተም የዘገየህ ቢመስልህ እንኳን ማድረግ አትችልም ማለት አይደለምና ፡ የተሻለ ነገር ለመስራት ፡ የተሻለ ህይወት ለመኖር ዛሬውኑ ተነስ ። ሲል ይመክራል ።

..........

🛒@Amazing_fact_433
🛒@Amazing_fact_433

8.4k 0 16 4 124

ፈረጃ : ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ

| በህዝብ መዋጮ የሚሰራዉና በኢትዮጵያ የመጀመርያዉ (croudfunding) ፊልም የሆነዉ ፈረጃ የተሰኘዉ የቦክስ ፊልም ከብዙ ዝግጅትና አድካሚ ጉዞ በኋላ የታሰበዉ በጀት ባይሞላም ቀረፃዉ ሚያዝያ 20 ሊጀመር ነዉ።

አርቲስት ሄኖክ ወንድሙ ሂደቱ ከባድ እንደነበር ተናግሮ የቦክስ ፊልም እንደመሆኑ ለቀረፃዉ ብዙ ሰው እንደሚያስፈልግና በተሳትፎ እንዲያግዙት ወጣቱን ኃይል ጠይቋል።

በገንዘብና በሀሳብ ላገዙት ሰዎች በሙሉ ትልቅ ክብርና ምስጋናዉንም አቅርቧል።


@AMAZING_FACT_433
@AMAZING_FACT_433

9.4k 0 10 10 287

አልበርት አንስታይን የካቲት 5 1930 ዓ.ም ላይ ለልጁ እንዲህ የሚል ደብዳቤ ላከለት፦

“ህይወት ብስክሌት እንደመንዳት ናት ሚዛንህን ለመጠበቅ መንቀሳቀስህን መቀጠል አለብህ። የስኬት ሰው ብቻ ለመሆን አትሞክር ይልቅ ዋጋ ያለው ሰው ለመሆን ሞክር። ምክንያቱም ስኬት የሚለካው በምትወስደው ነገር ሲሆን ዋጋ የሚለካው ደግሞ በምትሰጠው ነገር ነው።

ሞኝ ማለት አንድ አይነት ነገርን ደጋግሞ ሰርቶ የተለየ ውጤት የሚጠብቅ ነው። የተለየውን መንገድ ተከተል አዲስ ነገር ታገኛለህ። አትቀመጥ ምክንያቱም ምድራችን አደገኛ የሆነችው በክፉ ሰዎች ስራ ሳይሆን ምንም በማይሰሩ ሰዎች ውጤት ነው።

ትምህርት እውነትን አያስተምርም ይልቅ የአእምሮ አስተሳሰብን ማበልጸጊያ ልምምድ ነው። የሌሎች ጫጫታ የአንተን የውስጥ ድምፅ እንዲውጠው ማድረግ የለብህም። ማንም ሰው ባንተ ላይ ገደቦች እንዲጥል አትፍቀድ፤ ገደብህ በራስህ ያወጣኸው የህይወት መመርያ መሆን አለበት


🛒@Amazing_fact_433
🛒@Amazing_fact_433

9.3k 0 70 4 129

ፕሮፌሰሩ

ፕሮፌሰሩ ክፍል ውስጥ የተሰበሰቡትን ተማሪዎች እንዲህ ብሎ ይጠይቃል "86,400 ብር አላችሁ እንበል፤ አንድ ሰው ይመጣና 1ዐብር ይዞባቹ ይሮጣል፤ እና ለዛች 1ዐብር ብላቹ 86,390ብሩን ትታቹ ሰውየውን ተከትላቹ ትሮጣላቹ ወይስ የቀረውን 86,390ብር ይዛቹ መንገዳችሁን ትቀጥላላቹ?"

ተማሪዎቹም ቀላል ጥያቄ ይሆንባቸውና "የቀረውን ብር ይዘን እንቀጥላለን እንጂ!" ብለው መለሱ።

ፕሮፌሰሩም እንዲህ አላቸው "ይሄውላቹ በቀን ውስጥ 86,400 ሰከንዶች አላችሁ። እናም አንድ ሰው በ1ዐ ሰከንድ ውስጥ ለተናገራቹ ነገር ቀኑን ሙሉ ስትበሳጩ፣ ስታዝኑ፣ ስትናደዱ የምትውሉ ከሆነ 86,390 ሰከንዶቹንም ታጣላቹ።

ሰው አሉታዊ ነገር የሚናገራቹ ከራሱ አንፃር ነው። እናም መንገዳችሁን ቀጥሉና የቀሩትን 86,390 ሰከንዶችን አትርፉ!"

(ከማህበራዊ ሚዲያ
)

@Amazing_fact_433
@Amazing_fact_433

9k 0 123 5 282

ከቅርብ ወራት ወዲህ በቻይናዋ Zhejiang province
ጎዳናዎች ላይ የሚታይ አንድ ድቡልቡል ጎማ የሚመስል እንግዳ ሮቦት አለ ።
...
ይህ ሮቦት አንዴ ሀይል ከተሞላ ፡ ለሀያ ሰአታት ያህል በዝግታ ወደዛ ወደዚ እየተሽከረከረ ፡ ሲለውም አማካኝ ቦታ መርጦ በመቆም ፡ በዛ ጎዳና የሚያልፈውን ሰው ሁሉ እጅግ ጥራት ባለው HD ካሜራ አይኖቹ ይቃኛል ።
.......
በዚህ መሀል ታዲያ ወንጀል የሚሰራ ወይም ፡ በፖሊስ የሚፈለግ አንድ ሰው ካገኘ በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ሪፖርት ያደርግና ተፈላጊውን ሰው በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራል ።

በስፍራው የፖሊስ ሀይል ከሌለ ደግሞ ወንጀለኛን ለመያዝ ተብሎ በውስጡ የተገጠመውን መረብ በመተኮስ ሰውየው በመረቡ ተጠምዶ መንቀሳቀስ እንዳይችል ካደረገው በኋላ ፖሊስ መጥቶ እስኪወስደው ይጠብቃል ።
....
RT-G robot ይባላል ፡ ይህ ባለፈው አመት ወደስራ የገባው ይህ ሮቦት ፡ ከፖሊሶች ጋር በህብረት በመሆን ፡ እና ብቻውንም ሮንድ በመውጣት በተጨናነቁ የገበያ ቦታዎች እንዲሁም የፀጥታ ጥበቃ በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች እየተዘዋወረ የአካባቢውን ደህንነት ይቆጣጠራል ።
የገበያ ቦታዎችን ከዘራፊዎች ይጠብቃል ፡ በዚህ መሀል ለዘረፋ የተሰማሩ ወንጀሎች ከሆኑና ይህንን ሮቦት ሊተናኮሉት ከሞከሩ ደግሞ እራሱን ለመከላከልና ፡ ቦታውን ከዘረፋ ለማዳን የታጠቀውን የጭስ ቦንብ በመልቀቅ ፡ ወንጀለኞቹን ከስፍራው እንዲለቁ ማድረግ ይችላል ። ከጠንካራ ቁስ ስለተሰራም በምንም ነገር ሊጎዳ አይችልም ።
...

RT-G robot የፖሊስ አጋዥ ሆኖ ፀጥታን ከማስከበር ባለፈም ፡ የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜም ወደቦታው በፍጥነት ደርሶ ፡ የነብስ አድን ስራ ይሰራል ።

ይህ ሮቦት ባለበት ሰርቆ ወይም ወንጀል ሰርቶ ማምለጥ አይታሰብም ፡ በሰአት እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር እየሮጠ ወንጀለኛውን ለመያዝ ይጥራል ።
በውሀ ውስጥ ይሄዳል ፡ አስቸጋሪ የተባሉ መንገዶች ሁሉ ለሱ ምንም ማለት አይደለም ።
ይህ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ለመሰማራት በጥቅም ላይ የዋለው ይህ ሮቦት በዚህ መሰል ስራ ላይ የተሰማራና በጥቅም ላይ የዋለ የአለማችን የመጀመሪያው ሮቦት ሆኗል


አንብበው ከጨረሱ 👍

9k 0 15 4 307



የscholarship እድል የሚያስገኘው የALX Pathway ፕሮግራም ምዝገባ ሊያልቅ 4 ቀን ብቻ ቀረው!

የALX ‘Pathway’ ፕሮግራምን በመውሰድ፣ የአለምአቀፍ ዲግሪ እና ሙሉ ስኮላርሺፕ እድል ለማግኘት ይመዝገቡ። የዚህ ስኮላርሺፕ እድል በጥቅሉ በአመት የ85,000 አሜርካን ዶላር፣ ወይም የ11 ሚሊዮን የኢትዮጵያ ብር፣ ተመጣጣኝ ዋጋ አለው።

ALX ከ14 በላይ ታዋቂ ዓለም አቀፍ ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የትብብር ስምምነት አለው። አብዛኛዎቹ ዩኒቨርሲቲዎች የሚገኙት America ሲሆን፣ በEurope እና South Africa የሚገኙም አሉ።

የዚህ የትብብር ስምምነት ዋና ይዘት፣ የALX Pathway ኘሮግራምን በስኬት የሚጨርሱ ልጆች፣ በእነዚህ ታዋቂ ዩኒቨርሲቲዎች ተቀባይነት እና የስኮላርሺፕ እድሎች የሚያገኙበትን መንገድ ማስፋት ነው።

የምዝገባውን ሂደት ደረጃ በደረጃ ማብራሪያ ለማየት፣ እንዲሁም ምዝገባውን በተሳካ ሁንያ ለማጠናቀቅ፣ ይህንን የቴሌግራም ቻናል ተቀላቀሉ፡- https://t.me/ALXScholarship2ndBatch.

ወደ ምዝገባው ቀጥታ ለመሄድ ይህንን ተጫኑ - https://www.alxafrica.com/join-pathway/

9.1k 0 17 26 19

Old Group ካላችሁ ታማኙ አቡሼ አለላችሁ ?👍

2022 - 500 ብር
2021 - 500 ብር
2020 - 500 ብር
2019 - 500 ብር
2018 - 500 ብር

ያላችሁ መሸጥ ከፈለጉ ያዋሩኝ👉 @Abushe433

History Clear ያሎነ ትክክለኛ Old ብቻ ነው ምፈልገው ልታደክሙኝ አትምጡ🫡


የቻይና ወጣቶች ቤት ተከራይቶ ከመኖር ይልቅ በሆቴሎች ማደር እየመረጡ ነው

#Ethiopia | በቻይና ቤት ተከራይቶ ወይም ገዝቶ ከመኖር ይልቅ በሆቴሎች በቋሚነት መኖርን የሚመርጡ ወጣቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል::

ወጣቶቹ በሀገራቸው ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ አንጻር ሆቴሎችን ምርጫቸው አድርገዋል::

በተለይ ደግሞ ቀለል ያለ ህይወትን ልመምራት እና ጭንቀትን ለማስወገድ ሆቴል ተመራጭ እየሆነ ነው::

መኖርያ ቤት መከራየት ማለት ተቀማጭ ሊሆን የሚችልን ገንዘብ እንደመክፈል ነው:: በዛ ላይ በየወሩ የውሃ የመብራት እንዲሁም የኤሌክትሪክም ክፍያዎች መከፈል አለበት።

በሆቴል ውስጥ ግን ይህንን ሁሉ ክፍያ አንዴ ነው የምንከፍለው በማለት ሆቴል እንደሚሻላቸው ወጣቶቹ መናገራቸውን ኦዲቲ ሴንትራል ዘግቧል።

ከቤታቸውም የሚሰሩት ስራ ያላቸውም ሆኑ በየጊዜው ስራ እና አካባቢን የሚቀይሩ ቢሆኑ ይሄ አኗኗር ተስማምቷቸዋል።

ይሄን የኑሮ ዘይቤ በኮቪድ 19 በተነሳበት ጊዜ እንደተጀመረ እና ሆቴሎችም ብዙ እንቅስቃሴ ስለሌላቸው በጊዜው ዋጋቸው ቅናሽ ስለነበር አብዛኛውን ሆቴሎች ለረጅም ጊዜ የሚቆዩ ደንበኞችን ይቀበሉ ነበር።

ታድያ እድሜ ለኮቪድ ይሁንና የሚሉት ቻይናውያን ወጣቶች ጠባብ መኖርያ ቤትን ከሚከራዩበት ባነሰ ዋጋ ጥሩ በሚባሉ ሆቴሎች መኖር ምርጫቸው ሆኗል።

20 last posts shown.