ከቅርብ ወራት ወዲህ በቻይናዋ Zhejiang province
ጎዳናዎች ላይ የሚታይ አንድ ድቡልቡል ጎማ የሚመስል እንግዳ ሮቦት አለ ።
...
ይህ ሮቦት አንዴ ሀይል ከተሞላ ፡ ለሀያ ሰአታት ያህል በዝግታ ወደዛ ወደዚ እየተሽከረከረ ፡ ሲለውም አማካኝ ቦታ መርጦ በመቆም ፡ በዛ ጎዳና የሚያልፈውን ሰው ሁሉ እጅግ ጥራት ባለው HD ካሜራ አይኖቹ ይቃኛል ።
.......
በዚህ መሀል ታዲያ ወንጀል የሚሰራ ወይም ፡ በፖሊስ የሚፈለግ አንድ ሰው ካገኘ በአቅራቢያው ለሚገኝ ፖሊስ ሪፖርት ያደርግና ተፈላጊውን ሰው በቅርብ ርቀት መከታተል ይጀምራል ።
በስፍራው የፖሊስ ሀይል ከሌለ ደግሞ ወንጀለኛን ለመያዝ ተብሎ በውስጡ የተገጠመውን መረብ በመተኮስ ሰውየው በመረቡ ተጠምዶ መንቀሳቀስ እንዳይችል ካደረገው በኋላ ፖሊስ መጥቶ እስኪወስደው ይጠብቃል ።
....
RT-G robot ይባላል ፡ ይህ ባለፈው አመት ወደስራ የገባው ይህ ሮቦት ፡ ከፖሊሶች ጋር በህብረት በመሆን ፡ እና ብቻውንም ሮንድ በመውጣት በተጨናነቁ የገበያ ቦታዎች እንዲሁም የፀጥታ ጥበቃ በሚያስፈልግባቸው ቦታዎች እየተዘዋወረ የአካባቢውን ደህንነት ይቆጣጠራል ።
የገበያ ቦታዎችን ከዘራፊዎች ይጠብቃል ፡ በዚህ መሀል ለዘረፋ የተሰማሩ ወንጀሎች ከሆኑና ይህንን ሮቦት ሊተናኮሉት ከሞከሩ ደግሞ እራሱን ለመከላከልና ፡ ቦታውን ከዘረፋ ለማዳን የታጠቀውን የጭስ ቦንብ በመልቀቅ ፡ ወንጀለኞቹን ከስፍራው እንዲለቁ ማድረግ ይችላል ። ከጠንካራ ቁስ ስለተሰራም በምንም ነገር ሊጎዳ አይችልም ።
...
RT-G robot የፖሊስ አጋዥ ሆኖ ፀጥታን ከማስከበር ባለፈም ፡ የተፈጥሮ አደጋዎች በሚከሰቱበት ጊዜም ወደቦታው በፍጥነት ደርሶ ፡ የነብስ አድን ስራ ይሰራል ።
ይህ ሮቦት ባለበት ሰርቆ ወይም ወንጀል ሰርቶ ማምለጥ አይታሰብም ፡ በሰአት እስከ ሰላሳ ኪሎ ሜትር እየሮጠ ወንጀለኛውን ለመያዝ ይጥራል ።
በውሀ ውስጥ ይሄዳል ፡ አስቸጋሪ የተባሉ መንገዶች ሁሉ ለሱ ምንም ማለት አይደለም ።
ይህ አስቸጋሪ በሆኑ ቦታዎች ለመሰማራት በጥቅም ላይ የዋለው ይህ ሮቦት በዚህ መሰል ስራ ላይ የተሰማራና በጥቅም ላይ የዋለ የአለማችን የመጀመሪያው ሮቦት ሆኗል
አንብበው ከጨረሱ 👍