AWACH SACCOS Ltd.


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Economics


ኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚያከናውናቸው ተግባራት
የቁጠባ እና የብድር አገልግሎት
አነስተኛ የብድር መድህን አገልግሎት
የትምህርት ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት
+251-11-557-97-98
+251-11-557-88-89
+251-11-557-98-99
+251-11-868-47-44
saccawach@gmail.com
https://www.facebook.com/AWACHSACCOS
@awachsaccos

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Economics
Statistics
Posts filter


  አዋጭ ፋውንዴሽን ከአዲስ አበባ ት/ቢሮ ጋር በጋራ የሚሠራ በመሆኑ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ባደረገው ጥቆማ መሰረት አፄ ናኦድ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት አድራሻ አራዳ ክ/ከ/ወ/06 በመሄድ ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ወልደመላክ መርዓነህ ጋር ውይይት ተደርጎ በጣም አስፈላጊ የሆኑ ዕቃዎች ብቻ ተጠንተው እንዲቀርቡ ስምምነት በተደረገው መሰረት፣ ለትምህርት ቤቱ አስፈላጊ የሆኑ የትምህርት መሳሪያዎች ድጋፍ ተደርገዋል ፡፡ በትምህርትቤቱ 434 ወንድ እና 598 ሴት በድምሩ 1,032 ተማሪዎች እየተማሩ  የሚገኙ ሲሆን ትምህርት ቤቱ ያለበትን  የግብዓቶች እጥረት  በማየት  33 የመፅሃፍት አይነት እና 29 የላብራቶሪ እቃዎች   አዋጭ ፋውንዴሽን ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ አድርጓል ፡፡










አዋጭ እና አሚጎስ በጋራ በመሆን የቅድመጥናት ወርክሾፕ አዘጋጁ፡፡

ከኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሀገራችን የሚገኙትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እድገት እና ተግዳሮቶችን በስፋት በመዳሰስ የወደፊት አቅጣጫን ለማስቀመጥና ፍኖተካርታ ለመንደፍ የሚያስችል የቅድመ ጥናት ወርክሾፕ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል አካሂዷል፡፡
ለውይይቱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ተግዳሮቶችና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫን በሚመለከት የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን የፋይናንስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብረሃኑ ዱፌራ ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል፡፡
የአዋጭ እና የአሚጎስ የጥናት ባለሙያዎች በበኩላቸው የየኅብረት ስራ ማኅበራቸውን እድገት እና አሁናዊ ሁኔታ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ግልፅ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም በቅድመ ጥናት ወርክ ሾፑ ላይ ጥናቱን የሚያካሂደውን አካል የመለየትና ስለጥናቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡
በዚህ ወርክ ሾፕ ላይ የኢዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አጥናፉ ገ/መስቀል፣ የሁለቱም ኅብረት ስራ ማህበራት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በዘርፉ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ የኅብረት ስራ አባቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡






በህብረት ስራ ማህበራችን የዲያስፖራ አካውንት ለመክፈት ህጋዊ የሆነ የኢትዮጵያ ፓስፖርት ወይም በትውልድ ኢትዮåያዊ ለመሆኖ የሚያረጋግጥ የመኖሪያ ፍቃድ'መታወቂያ ካርድ፣ ወይም ሌላ የውጭ ሀገር ነዋሪነትዎን የሚያረጋግጥ ሰነድ እና የመጀመሪያ ተቀማጭ ገንዘብ ያስፈልግዎታል ። በውጭ ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያዊ መሆንዎን ለማረጋገጥ ሁሉንም አስፈላጊ ሰነዶች በማቅረብ በአዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኃላፊነቱ የተወሰነ መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበር ሜክሲኮ ቅርንጫፍ በኩል ማመልከት ይችላሉ።
መስፈርቶች ;
• ኢትዮጵያዊ መሆንዎን ማረጋገጫ - ትክክለኛ ፓስፖርት ወይም መታወቂያ ካርድ
• የውጭ ሀገር ነዋሪ መሆኖትን የሚገልጽ ማረጋገጫ - የመኖሪያ ፈቃድ ወይም ሌላ ከኢትዮጵያ ውጭ እንደሚኖሩ የሚያሳይ ሰነድ
• የማመልከቻ ቅጽ - ከኅብረት ሥራ ማህበራችን የሚላክሎትን የማመልከቻ ቅጽ ይሙሉ
• የመጀመሪያ ተቀማጭ ገንዘብ፡ ሒሳቡን ለመክፈት በህብረት ስራ ማህበራችን የሚፈለገው ዝቅተኛ የተቀማጭ ገንዘብ ማስገባት ።










Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


Video is unavailable for watching
Show in Telegram



18 last posts shown.