አዋጭ እና አሚጎስ በጋራ በመሆን የቅድመጥናት ወርክሾፕ አዘጋጁ፡፡
ከኢትዮጵያ ኀብረት ሥራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አምባሳደር ሽፈራው ሽጉጤ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በሀገራችን የሚገኙትን የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ሥራ ማኅበራት እድገት እና ተግዳሮቶችን በስፋት በመዳሰስ የወደፊት አቅጣጫን ለማስቀመጥና ፍኖተካርታ ለመንደፍ የሚያስችል የቅድመ ጥናት ወርክሾፕ አዋጭ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ከአሚጎስ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበር ጋር በመተባበር ካዛንቺስ በሚገኘው ጁፒተር ሆቴል አካሂዷል፡፡
ለውይይቱ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት መተላለፉን ተከትሎ የገንዘብ ቁጠባና ብድር ኅብረት ስራ ማህበራት ተግዳሮቶችና የወደፊት የትኩረት አቅጣጫን በሚመለከት የኢትዮጵያ ኅብረት ስራ ኮሚሽን የፋይናንስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ብረሃኑ ዱፌራ ጥናታዊ ፅሑፍ አቅርበዋል፡፡
የአዋጭ እና የአሚጎስ የጥናት ባለሙያዎች በበኩላቸው የየኅብረት ስራ ማኅበራቸውን እድገት እና አሁናዊ ሁኔታ ለመድረኩ ተሳታፊዎች ግልፅ አድርገዋል፡፡ በተጨማሪም በቅድመ ጥናት ወርክ ሾፑ ላይ ጥናቱን የሚያካሂደውን አካል የመለየትና ስለጥናቱ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ ተሰርቷል፡፡
በዚህ ወርክ ሾፕ ላይ የኢዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የኢኮኖሚክስ ዲፓርትመንት ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አጥናፉ ገ/መስቀል፣ የሁለቱም ኅብረት ስራ ማህበራት ከፍተኛ ኃላፊዎች፣ በዘርፉ ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ የኅብረት ስራ አባቶችን ጨምሮ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡