Ethio Menzuma


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


Welcome to Ethio Menzuma! We preserve the traditional spiritual music and prayers of Ethiopia. Join us to experience the beauty and power of this spiritual music. Stay connected for daily updates, unique content, and a chance to celebrate and honor our cu

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


እስራኤላውያን እና 5 ታይላንዳውያን ታጋቾች ዛሬ ይለቀቃሉ

ሃማስ የ20 አመቷን የእስራኤል ወታደር አጋም በርገር ለአለማቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር ማስረከቡን የእስራኤል መንግስት አረጋግጧል።

እስራኤል በምትኩ 110 ፍልስጤማውያን እስረኞችን እንደምትፈታ አስታውቃለች።






Walifi foundation


Yiqalaqalun ye jema sew lamardat sew mahon bicha baqi new ye jema join yadirgu




ሱፊያ ተሳዳቢ አደለም
____

"ወሀብያ እያላችሁ ሱፊያን አታሰድቡ ፣ ሱፊያ ከስድብ የጠራ ፣ ሰዎችን በጥሩ ስነ-ምግባር የሚጣራ ነው
እንጂ ወሀብያ እያለ ሚሳደብ አደለም "  ፣ የድምፅ ብክለት እንዳላስከትል የት ሄጄ ልሳቅ 😁😁😁

ይህ አባበል ለታክሲ ጥቅስነት ከተፈለገ አሪፍ ነው ፣ ከዛ ውጪ ግን በውስጡ የያዘዉ ምንም አይነት ሀቂቃ (እዉነታ)የለውም።

ሲጀመር “ ወሀቢያ “ ማለት ስድብ ነው ያለው ማነው ?? እነርሱ በስማቸዉ አፍረው ስድብ ነው ሲሉ ሰምተህ እኛ ጋር መጥተህ ማቀርሸት ትንሽ አይከብድም ⁉️

ታላቁ ሱፊይ ሁጀቱል ኢስላም ኢማም አል- ገዛሊ ረሂመሁላህ  በተሰውፍ የዒልም ዘርፍ አቻ ያልተገኘለትን ና من لم يقرأ الإحياء فليس من الأحياء ) ኢህያእ ኪታብን ያላነበበ ህይወት እንዳለው አይቆጠርም ) የተባለለት የኢህያእ  አል- ዑሉሙዲን ኪታብ አዘጋጅ  ቢሆኑም የጥመት አንጃዎች ላይ ምላሽ ከመስጠና እነርሱን ከማጋለጥ አላገዳቸዉም ።

ለምሳሌ ያክል :-

አንደኛ : ኢልጃም አል-ዐዋም ላይ ሙተሻቢህ አንቀፆችን ብትንትን አድርገው አብራርተዋቸዋል ፣ አሏህ ሱብሀነሁ ወተዐላ ከክፍለ አካላት የተዋቀረ ( ሙረከብ ) ነው ብሎ የሚያምን ሰው በኢጅማዕ ካፊር እንደሆነ አስቀምጠዋል።

ሁለተኛ :
ተሀፋት አል-ፈላሲፋህ ወይም "የፈላስፎች ውድቀት" በሚለው የተወሰኑ መሰረታዊ የዐቂዳ ነጥቦችን የተቃረኑ ሙስሊም ፈላስፎችን አክፍረዋል

ሶስተኛ :
አል ቂስጣሱል ሙስተቂም የተሰኘ ለባጢኒያዎች ምላሽ የሆነ ኪታብ ፅፈዋል ፣ ከዚህም በተጨማሪ ኢህያእ ዑሉሙዲንን ጨምሮ ብዙ ኪታቦቻቸው ላይ የተለያዩ ፊርቃዎች ለሚያነሷቸው ከንቱ አስተሳሰቦች  መልስ ሰጥተዋል ።

ኢማም ዒዝ ቢን አብዱሰላም ከሀዲስ ልሂቁ ከኢማም ኢብኑ ሰላህ ጋር ትልቅ ትንቅንቅ ውስጥ ገብተው የነበሩት “ ድንበር አላፊ ሀናቢላዎችን ዝም"እንበል በሚለው ፈትዋቸው ነበር። ዒዝ ቢን አብዱስሰላም ዝም ማለት የለብንም ብለው ብእራቸውን ካነሱ ዑለሞች መካከል ነበሩ ።

🚯መራር እውነታ ቢሆንም

የኛ ሀገር  የታላላቅ አሊም ልጆች በቲንሹ አንዱ ወሀብያ ነው ፣
ስም እየጠቀስኩ እገሌ  እገሌ ማለት እችላለሁ ግን ጥቅም የለውም። አንተ ዝም ብትል ልጆችህ ላይ የሚሰራ ፣ በብዙ ነገር የተደራጀ ፣ ታላቅ የሆነ ሚዲያ የገነባ ፣ከላይ እስከታች በሀብታም ሀገሮች የሚደገፍ፣ውሸት በመቅጠፍና በፕሮፓጋንዳ የሚስተካከለው የሌለ እንደው እንደ ስድብ አትቁጠሩብኝ እንጂ  ዱርዬ የሆነ የባጢል ጭፍራ አለ።

ይህን ቡድን በሀላጅና በኢብኑ አረቢ እንዲሁም በሩሚ አለፍ ሲል ደግሞ በመጅኑኑ ለይላ ቂሷ ፣  በመንዙማ  እቋቋመዋለሁ አሸንፈዋለሁም ካልክ ቀጥልበት ፣ ይህ አካሄድ ባለፋት ሰላሳ አመታት ሱፊያውን ማህበረሰብ ምን ያክል ዋጋ እንዳስከፈለው ግን አትርሳ ፡ ከገሀዱ አለም በላይ ትክክለኛ ፈራጅ የለምና ።

በሀቅና ባባጢል መሀከል በሚደረግ ጦርነት ላይ ሰበብ ሳታደርስ ከራማ ብቻ የምትፈልግ ከሆነ የበድር  ጦርነት ፣የኡሁድ ጦርነት ፣ሂጅራና ሌሎችም ከፍተኛ ትግሎች  ጥቅም ከንቱ ነበሩ ማለት ነውን ⁉️ የሙእጂዛ ባለቤት የሆኑት ፣ እጃቸውን ቢያነሱ ዱዐቸው የማይመለሰው ውዱ ነቢያችን ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም ይህን ያክል ከለፋ ፡ ቀሳሱል ከራማ ( ቁጭ ብለው የወልዮችን ከራማ የሚተርኩ ) ምን ያክል መልፋት እንዳለባቸው ማሰብ አይከብድም።

🚯በጣም የሚያስቀኝ ነገር ቢኖር ሌሎች ጋር የአቂዳ ኡስታዛቸዉን ፡” የአቂዳ አንበሳ “ ፣ “ የእነ  እገሌ ራስ ምታት “ ፣ የእነ እገሌ ውጋት 😁😁ወዘተ በሚል ስም ይጠራሉ ።

እኛ ጋር ደግሞ ባለችህ አቅም የባጢል ባለቤቶችን ስትታጋል የማይወጣልህ ስም የለም ፡ በቅርቡ ስሙን መጥቀስ የማልፈልገው የቲቪ ጣቢያ “ ኡስታዝ ኢሳን  “ ማቅረብ ፈልገው ነገር ግን ከወሀብያ ጋር ሰለሚመላለስ ማቅረብ እንደማይፈልጉና እራሳቸውን ማስበላት እንደማይፈልጉ ነገሩኝ።

ይህ የድድብና ጥግ ነው ምንም ሳይከፈለው፣ እራሱን አደጋ ላይ ጥሎ ለዲኑ አንዳች ነገር ላበርክት ያለን ሰው በዚህ ልክ መንካት ከሞራልም ከዲንም አንፃር የተወገዘ ነው።ደግሞ እነዚሁ ሰዎች መልሰው የሆነ ወሀብያ እንዲህ አለኝ ብለው ኡስታዝ ኢሳ ጋር መደወላቸው ገርሞ ይገርማል።


✍ዘ.ሐ


ማጋዝ ምትፈልጉ በኮሜንት ያውሩን


sefaricom የትኛውንም ጥያቄ በዝህ በኩል ይጠይቁ
https://t.me/official_safaricomet_bot?start=wqjj5AunLRntCkRTFzfhDq


ኢማም ነወዊ እንዲህ ይላሉ

«ዚክር በቀልብ አሊያም በምላስ ሊደረግ ይችላል፡፡ በላጩ ግን በምላስ እና በቀልብ
አንድ ላይ ሲደረግ ነው፡፡ ከሁለት አንዱን መምረጥ ግድ ከሆነ ግን በቀልብ ማድረጉ
የተሻለ ነው፡፡ ሪያእ ይሆንብኛል ብሎ በመስጋት በምላስና በቀልብ አንድ ላይ ዚክር
ማድረግን መተው ተገቢ አይደለም፡፡»

📚«አል-አዝካር አን-ነወዊ»


ከ50 አመታት በላይ በበጎፈቃድ መቃብር የሚቆፍረው የናይጀሪያ ቤተሰብ
በጎፈቃደኞቹ "ወላጆቻችን ፈጣሪን ከሚያስደስተው ስራ በሰማይ ዋጋ ታገኙበታላችሁ" እያሉ አሳድገውናል ይላሉ
በናይጀሪያ ሰሜናዊ ክፍል ካዱና ከተማ አንድ ቤተሰብ ከ50 አመታት በላይ ከባድ ሃላፊነት ተቀብሎ እየሰራ ነው፤ የሞቱ ሰዎችን ገንዞ፣ መቃብራቸውን ቆፍሮ መቅበር።
አድካሚው ተግባር በከተማዋ ነዋሪዎች ቤተሰቡን ታዋቂና ተመስጋኝ ያድርግ እንጂ እንደ ስራ ከታየ ክፍያ የለውም ማለት ያስደፍራል።
የአብዱላሂ ቤተሰብ ሰዎችን በመቅበር ተግባር የተሰማራው በ1970ዎቹ ነው። ኢብራሂም እና አዳሙ የተባሉ ወንድማማቾ የጀመሩት በጎ ስራ በልጆቻቸው ቀጥሎ አሁንም ድረስ ዘልቋል።
"ወላጆቻችን ፈጣሪ ይህን አገልግሎት እንደሚወደውና በአለማዊው ህይወት ክፍያ ባይኖረውም በሰማይ ግን ዋጋው ከፍ ያለ መሆኑን እየነገሩ ነው ያሳደጉን" ይላል የኢብራሂም አቡድላሂ ትልቅ ልጅ ማጋጂ ከቢቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ።


JUUMA MUBAREK


ጁዑማ ሙበራክ


የጋዛ ነዋሪዎች የቤተሰቦቻቸውን አስከሬን ከፍርስራሽ ውስጥ እያወጡ በስርአት እየቀበሩ ነው።
እስራኤል እና ሀማስ መካከለኛው ምስራቅን ያመሰቃቀለውንና ለ15 ወራት የዘለቀውን ጦርነት የሚያስቆም የተኩስ አቀም ስምምነት ላይ ደርሰዋል።
ይህን ተከትሎ ቤተሰቦቻቸውን ያጡ በርካታ የጋዛ ነዋሪዎች በእስራኤል የአየር ጥቃት ከፈራረሱ ህንጻዎች ውስጥ በመፈለግ ላይ ናቸው።


በሎስ አንጀለስ አቅራቢያ አዲስ ሰደድ እሳት ተቀሰቀሰ !!


በሰዓታት ውስጥ ከ3 ሺህ 800 ሄክታር በላይ መሬት የሸፈነው ይህ ሰደድ እሳት ነዋሪዎችን ከመኖሪያ ስፍራቸው እያፈናቀለ መሆምኑ ተገልጿል።

ይህንንም ተከትሎም 31 ሺህ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ትዕዛዝ የተላለፈ ሲሆን ለ23 ሺህ ሰዎች ደግሞ በተጠንቀቅ ላይ እንዲሆኑ ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷል።

ደረቅ አየርና አደገኛ ንፋስ ለሰደድ እሳቱን መዛመት ምክንያት መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወደ ሌላ አካባቢ እንዳይስፋፋም ተሰግቷል።

በፍጥነት እየተስፋፋ ያለውን ሰደድ እሳት ለማስቆምም በርካታ የእሳት አደጋ መከላከያ አውሮፕላኖች እንዲሁም በሺዎች የሚቆጠሩ የእሳት አደጋ ሰራተኞች ጥረት እያደረጉ መሆኑም ተገልጿል።

በሎስ አንጀለስ ከተማ እና አካባቢው ከ16 ቀናት በፊት ከተቀሰቀሰው እሳት ውስጥ ከባድ የተባሉት የኢቶንና ፓላሲደስ እሳቶች አሁንም እየነደዱ መሆኑን ቢቢሲ ዘግቧል ።




አሏህ ሱብሀነሁ ወተአላ ቀለምን ፣ ጣእምን ፣ ሽታን ፣ ሙቀትን ፣ ቅዝቃዜን ፣ እርጥበትን ፣ ደረቅነትን ፣ ትልቅነትና ትንሽነት በመሳሰሉ በማንኛውም ከይፊያዎች አይገለፅም

  ሸርህ አል-ዐቃኢድ አንነሰፊያህ


💫ረመዳን ከረመዳን በፊት

ለረመዳን ዝግጅት እንዴት እናድርግ ከተባለ ኢማሙ ነወዊ ረሂመሁላህ ረመዳን ብቻ ሳይሆን ሂወታችንን እንዴት መዘጋጀት እንዳለብን ታዋቂ በሆነው ኪታባቸው ሪያዱ ሷሊሂን መፀሐፍቸው ላይ አስቀምጠውታል ።እኛም ለረመዳን መዘጋጃ ፍኖተ ካርታ ሪያዱ ሷሊሂንን ብናደርግ ትልቅ የመለወጥ ምክንያት ይሆነናል ።


1:-ነያን ማድረግና ንያን ማስተካከል
2:-ተውበት በትክክል ማድረግ
3:-የተሟላ ትግዕስት ማድረግ
4:-እወነተኛ መሆን
5:-እራስን መግዛት
6:-ተቅዋ የአሏህን ፍራቻ ማምጣት
7:-በአሏህ ላይ እርግጠኛ መሆነን
8:-ፅናት በሁሉ ነገር ላይ
9:-ማስተንተን
10:-በመልካም ስራ መቻኮል
11:-እራስን መታገል
13:-በመጨረሻው ሰአት ላይ ስራን መጨመር
14:-የመልካም ስራ በሮችን ሁሉ በቻሉት አቅም ማንኳኳት
15:-መሀከለኛ መሆን
16:-ስራውችን መጠባበቅ
17:-በሁሉም ስራ ላይ አደብ መጠበቅ
18:-ታዛዥነት
19:-ፈጠራ ነገሮችን መጠንቀቅ
20:-ጥሩ ፈለጎችን መከተል


ፈረንሳይ በቀድሞው የሶሪያ ፕሬዝዳንት በሽር አል አሳድ ላይ ሁለተኛውን የእስር ማዘዣ አወጣች።
የፈረንሳይ የወንጀል መርማሪ ቡድን አሳድ የሶሪያ ጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ በነበሩበት ወቅት በደራ ከተማ በ2017 ንጹሃን ያለቁበትን የቦምብ ጥቃት እንዲፈጸም አዘዋል በሚል ነው የእስር ትዕዛዙን ያወጣው።
የቀድሞው ፕሬዝዳንት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቅ ተግባር በመፈጸም ተጠርጥረው የእስር ማዘዣው መውጣቱንም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ግለሰብን ዋቢ አድርጎ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቧል።


በእሳት አደጋ 76 ዜጎቿን ያጣችው ቱርክ ብሄራዊ የሀዘን ቀን አወጀች
ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶሃን በአሰቃቂው አደጋ ህይወታቸው ላለፈ ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተው እለቱ ብሄራዊ የሀዘን ቀን እንዲሆን አውጀዋል።
በምዕራባዊ ቱርክ የጎብኝዎች መዳረሻ በሆነው ቦሉ ተራሮች በሚገኘው ግራንድ ካርታል ሆቴል በደረሰው አደጋ የሟቾች ቁጥር 76 የደረሰ ሲሆን፥ ከ50 ሰዎች በላይ ቆስለዋል።
የ45ቱ ሟቾች አስከሬን ለቤተሰቦቻቸው መተላለፉን ያስታወቁት የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳዮች ሚኒስትር አሊ የርሊካያ፥ የቀሪዎቹን ሟቾች ማንነት ለመለየት ምርመራ እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

20 last posts shown.