EthioTube


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


ኢትዪትዩብ፦ ኢትዮጵያዊ። ነፃ። ገለልተኛ።
Follow us on other our social media networks:
Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


በግጭቱ ከ35 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰማ

በሶማሌ ክልል ፋፋን ዞን ደአወሌይ ቀበሌ ትናንት ታህሳስ 16/ 2017 ዓ/ም "በአካባቢው አርብቶ አደሮች" እና በመንግስት ሚሊሻዎች መካከል በተቀሰቀሰ የትጥቅ ግጭት ከ35 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተሰምቷል።

ግጭቱ ከዩአሌ ወረዳ የመጡ “ልዩ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች” ደአወሌይ ቀበሌ ላይ ጥቃት ማድረሳቸውን ተከትሎ  የተፈጠረ ነው ተብሏል።

በአካባቢው በሚኖሩ “ኢሳቅ እና የኦጋዴን ንዑስ ጎሳዎች” መካከል ለረጅም ጊዜ በቆየው የድንበር ግጭት የተነሳ ታህሳስ 10 ከተከሰው ግጭት የቀጠለ መሆኑንም ታውቋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


አዘርባጃን ብሔራዊ ሐዘን አወጀች

አዘርባጃን በትናትናው ዕለት በካዛኪስታን በተፈጠረ የአውሮፕላን መከስከስ አደጋ ብሔራዊ ሐዘን ማወጇ ተነገረ፡፡

የአዘርባጃን 62 መንገደኞችንና አምስት ሰራተኞችን የጫነ አውሮፕላን በካዛኪስታን አክታው ከተማ አቅራቢያ መከስከሱ ይታወቃል፡፡ኢምብሬር 190 የተባለው የበረራ ቁጥር ጄ2-8243 የአዘርባጃን አየር መንገድ ንብረት የሆነው አውሮፕላን በሩሲያ ቺቺኒያ ከባኩ ወደ ግሮዝኒ ሲበር እንደነበርም ተገልጿል፡፡

ሆኖም በግሮዝኒ ጭጋግ ምክንያት ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲዞር የተደረገ ሲሆን፥ ቢያንስ በህይዎት የተረፉ ቢኖሩም ብዙዎችን ለህልፈት የዳረገ አደጋ መሆኑ ነው የተገለጸው፡፡በዚህም አዘርባጃን የሐዘን ቀን ማወጇን የዘገበው ዥኑዋ ነው፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


ኢሰመጉ የአሰራር ጥሰት ፈፅሟል በሚል በመንግስት መታገዱ ተሰምቷል።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤን (ኢሰመጉ) ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት መሆኑ ተነግሯል።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ ተዘግቦ ተመልክተናል።

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው ጠቅሶ ዋዜማ ዘግቧል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በትናትናው ዕለት ለ5 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ሰጠ

የዩኒቨርሲቲው የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ትምህርት ሚኒስቴር በቅርቡ ካሳለፈው ጊዜያዊ እግድ ጋር አይጋጭም ወይ የሚል ጥያቄን አስነስቷል፡፡

ሚኒስቴሩ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት እንዳይሰጡ በድጋሚ ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር በዕግዱ ላይ ከታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በየትኛውም የከፍተኛ ትምህርት ተቋም የተሰጠ እና የሚሰጥ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገት ተቀባይነት እንደማይኖረውም ያትታል፡፡

የዕግዱ ምክንያትም ከጥቅምት 4/2013 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የነበረው "የአካዳሚክ ሠራተኞች የደረጃ ዕድገት መመሪያ" በመሻሻል ላይ በመሆኑ እንደሆነ ያነሳል፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በበኩሉ፤ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ዕድገቱን የሰጠው በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ''ስለ ራስገዝ ዩኒቨርሲቲ ለመደንገግ በወጣው'' አዋጅ ቁጥር 1294/2015 መሠረት መሆኑን ይገልጻል፡፡

ኢቢሲ ጉዳዩን ለማጣራት አደረኩት ባለው ጥረት ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ በመሆኑ ከላይ በተጠቀሰው አዋጅ መሰረት ዕድገቱን የመስጠት መብት እንዳለው ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ምላሽ አግኝቷል፡፡
በዚህም መሰረት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ:-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም…….  በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሠጥቷል።


የአዘርባጃን አየር መንገድ አውሮፕላን በካዛክስታን ተከሰከሰ

ኤምብራየር 190 በተሰኘው አውሮፕላን ውስጥ 62 ተሳፋሪዎች እና 5 የበረራ ሰራተኞች እንደነበሩ የትራንስፖርት ሚኒስቴር ዘግቧል።

የመጀመሪያ ሪፖርቶች እንዳመላከቱት በህይወት ከተረፉ 25 ሰዎች መካከል 22ቱ ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የካዛኪስታን የድንገተኛ አደጋ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በአዘርባጃን አየር መንገድ የሚተዳደረው አውሮፕላኑ በአክታዉ ከተማ አቅራቢያ ለማረፍ ሲሞክር በእሳት የነደደ ሲሆን አሁን ላይ እሳቱን ሙሉ በሙሉ መጥፋቱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል።

የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ እስካሁን አልታወቀም።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የፈረንጆችን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በመላው ዓለም የፈረንጆችን የገና በዓል ለሚያከብሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዓሉን ለሚያከብሩ በሙሉ፣ ለኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ወዳጆች፣ የዳያስፖራ ማኅበረሰብ እና የዓለም ቤተሰብ መልካም የገና በዓል እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ ብለዋል።

በዓሉ የደስታ፣ የሰላም እና የአንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን በኤክስ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት ገልጸዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


ኢትዮጵያ  የሶማሊያ መንግስት ያቀረበባትን ክስ መሰረተ ቢስ ስትል አጣጣለች

የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣዉ መግለጫ የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ኃይሎች በሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ላይ ጥቃት አድርሰዋል  በሚል ያቀረበዉን ክስ አጣጥሏል፡፡

ድርጊቱ የተፈፀመዉ ኢትዮጵያ ኃይሎች ሳሆን የሁለቱን አገራት ግንኙነት ለማበላሸት በሚፈልጉ  ሶስተኛ ወገኖች የተፈጸመ ነዉ ብሏል፡፡

ኢትዮጵያ መሰል   ትንኮሳዎችና  የሁለቱን አገራት ግንኙነት  የሚያበላሹ ድርጊቶችን ለመከላከል ቁርጠና መሆኗንም አረጋግጣለች፡፡

የሶማሊያ መንግስት  ባወጣው መግለጫ ዱሎው በተባለችው የጁባላንድ ከተማ የኢትዮጵያ ኃይሎች ጥቃት ፈፅመዋል ሲል መውቀሱ  የሚታወስ ነዉ፡፡

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚከሰቱ የመሬት መንቀጥቀጥ ክስተቶችን የሚከታተለው የአሜሪካ ጂኦሎጂካል ሰርቬይ ድረገጽ ምሽት 4:41 ላይ ከመተሐራ 13 ኪሎ ሜትር ርቀት የመሬት መንቀጥቀጥ ተከስቶ እንደነበር አመልክቷል።

መሬት መንቀጥቀጡ በሬክተር ስኬል 4.9 የተመዘገበ መሆኑን አመልክቷል።

ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ ተሰምቷል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በተለያዩ ሀገራዊ ጉዳዮች እና በልዩ ልዩ የፓርቲ አጀንዳዎች ላይ ለመወያየት፣ የብልጽግና ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ዛሬ ጠዋት ስብሰባ መጀመራቸውን ጽ/ቤቱ አስታወቀ ።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በእስር ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ "ህመማቸው እንደባሰባቸው" ቤተሰቦቻቸው ተናገሩ

በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እስር ላይ የሚገኙት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ እና የአማራ ክልል ምክር ቤት አባሉ አቶ ዮሐንስ ቧያለው "ለከፍተኛ ሕመም" መዳረጋቸውን የቅርብ ቤተሰቦቻቸው አስታወቁ።

አቶ ክርስቲያን እና አቶ ዮሐንስ ቀዶ ሕክምና ከተደረገላቸው በኋላ "የማያቋርጥ የደም መፍሰስ እንዳጋጠማቸው" ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ቤተሰባቸው ነግረውኛል ሲል ቢቢሲ በዘገባው ጠቁሟል።

አንድ የአቶ ክርስቲያን የቅርብ ቤተሰብ "ቁስሉም አልደረቀም እና ደግሞ ደም እየፈሰሳቸው ነው፤ ሐኪሞቹም ተናግረዋል፤ ደም መፍሰስ ሊያጋጥም እንደሚችል እና ይህ ሲያጋጥምም እንድታመጧቸው ብለው ነበር" ብለዋል ያለው ዘገባው ነገር ግን ከቀዶ ሕክምናው በኋላ ወደ ሆስፒታል አለመወሰዳቸውን ነግረውኛል ብሏል።

ሕክምናውን ተከትሎ ለሚከሰተው የደም መፍሰስ ማስታገሻ እንደተሰጣቸው ያስታወሱት የቤተሰብ አባላቱ "ሕመሙን ለማስታገስ ቶሎ ቶሎ እየወሰዱት ስለነበር የተሰጣቸው የማስታገሻ መድኃኒትም አልቆባቸዋል። " ሲሉ ተናግረዋል ።

የአቶ ዮሐንስ ቤተሰብ አባል፤ "ትላንት ማስታገሻ ይዘን ስንሄድ መግባት አትችሉም ተባልን፤ ለምንድን ነው ስንል? ሊቀየሩ ነው አሉን። እስከ ትናንት ግን እነሱ አይሄዱም ብለውን ነበር። ትናንት በድንገት ተነስተው ሊወጡ ስለሆነ ምንም ምግብ ማስገባት አትችሉም መድኃኒትም አይገባም ብለው ከለከሉን" ማለታቸውንም ዘገባው አካቷል።

የአቶ ክርስቲያንም የቤተሰብ አባል በተመሳሳይ "ትላንትና ምግብም ማስታገሻም ይዘን ስንሄድ የሚያስገባን ስለሌለ ተመለስን" ሲሉ መናገራቸውን አስታውቋል።




አሜሪካ የራሱዋን ተዋጊ ጄት በቀይ ባህር ላይ መትታ ጣለች

ትናንት ማምሻውን የአሜሪካ ባህር ኃይል F/A-18 ተዋጊ ጄት የሁቲ ዒላማዎችን ለማጥቃት በመጓዝ ላይ እያለ በዩኤስኤስ ጌቲስበርግ ተመቶ ወድቋል።

ሁለቱም አብራሪዎች በተሳካ ሁኔታ ተወርውረው በሕይወት ተርፈዋል፤ ነገር ግን አንደኛው ቀላል ጉዳት ደርሶበታል ሲል የአሜሪካ ማዕከላዊ እዝ ገልጿል።

የቱሩማን ኬሪየር ስትራይክ ግሩፕ አካል የሆነው ዩኤስኤስ ጌቲስበርግ ከሳምንት በፊት ወደ ቀጠናው የገባ ሲሆን አውሮፕላኑ ላይ ተኩስ ከፍቷል። F/A-18 አውሮፕላን የተነሳው ዩኤስኤስ ሂሪ ኤስ ትሩማን ከተሰኘው አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ነው።

አሜሪካ ከዩናይትድ ኪንግደም ጋር በመሆን የሁቲ አማፂያን ለፈጸሙት ጥቃት የአጸፋ ምላሽ በየመን ሰነአ በቡድኑ ኢላማዎች ላይ ከቅዳሜ ጀምሮ የአየር ድብደባ አድርሰዋል።

ሁቲዎች ለፍልስጤማውያን ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት ከእስራኤል ጋር ግንኙነት አላቸው ተብለው በሚታመኑ መርከቦች ላይ ጥቃት የመሰንዘር ፖሊሲ አውጀዋል።

Facebook.com/EthioTube
Twitter.com/EthioTube
Youtube.com/EthioTube
Instagram.com/EthioTube
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


ከኮሪደር ልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ 3 አመራሮች

በ አዲስ አበባ መንግስትና ህዝብ የጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከኮሪደር ልማት የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅማቸው ሊያውሉ የሞከሩ 3 አመራሮች በከተማው የፀጥታ አካላት በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የከተማ አስተዳደሩ አስታወቀ።

በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮቹ፤ የየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ራሄል ኃ/ኢየሱስ ጨምሮ የወረዳው ስራ አስኪያጅ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ደበበ ጉልማ፣ የወረዳው የፋይናስ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ግዛቸው መሆናቸውን የከተማ አስተዳደርሩ ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 በካዛንችስ የኮሪደር ልማት ላይ ባልተገባ አካሄድ የፍርስራሽ ግምት ለግል ጥቅም ለማዋል በመሞከር ላይ እያሉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ ከከተማ እስከ ክ/ከተማ የፀጥታ መዋቅሩን በመጠቀምና ክትትል በማድረግ መሆኑን ተገልጿል።

በዚህም መሠረት የወንጀል ማጣራት ሂደቱ በሚመለከተው አካል እየተካሄደ ይገኛል ያለው መግለጫው አስተዳደሩ ሌብነትና ብልሹ አሰራር የልማታችን ዕንቅፋት እንዳይሆን ተገቢውን እርምጃ ወስዷል ብሏል፡፡

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በመዲናዋ በስድስት ክፍለ ከተሞች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ

በአዲስ አበባ ከተማ ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ ሲባል ለቀጣይ 5 ወራት በስድስት ክ/ከተሞች በተመረጡ ወረዳዎች የስምና ንብረት ዝውውር ታገደ።

የከተማዋ መሬት ይዞታ ምዝገባና መረጃ ኤጄንሲ ለፋና ዲጂታል እንዳስታወቀው፥ ከመሬት ይዞታ ጋር ተያይዞ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ ነው።

ለዚህም ዘመናዊ ሁለገብ ካዳስተር ግንባታ ስርዓት በመዲናዋ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ለማድረግ ሥራ መጀመሩን አመልክቷል፡፡

አሁን ላይ ከአዲስ አበባ ጠቅላላ የቆዳ ስፋት ውስጥ 54 በመቶ ለሚሆነው የመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራ መሰራቱ ተጠቁሟል።

በተያዘው በጀት ዓመት ለመጨረሻ ጊዜ በ136 ቀጠናዎች የሚገኙ ይዞታዎችን አረጋግጦ ለመመዝገብ እየተሰራ ነው ተብሏል።

በዚህ መሠረትም የይዞታ ማረጋገጥ ስራው በተመረጡ ስድስት ክ/ከተሞች በቀጣይ አምስት ወራት ውስጥ እንደሚከናወን ተጠቅሷል።

ክፍለ ከተሞችም የካ፣ ለሚ ኩራ፣ አቃቂ ቃሊቲ፣ ንፋስ ስልክ ላፍቶ ፣ቦሌ እና ኮልፌ ቀራኒዮ መሆናቸው ተመላክቷል።

ለመሬት ይዞታ ማረጋገጥ ሥራው ሲባልም ምዝባ በሚካሄድባቸው የክ/ከተሞቹ ወረዳዎች እስከ ቀጣየዩ ሚያዝያ ወር መጨረሻ አካባቢ የስምና ንብረት ዝውውር መታገዱ ተገልጿል።

ባለይዞታዎች ከታሕሣሥ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 ቀናት የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እንዲያቀርቡም ጥሪ ቀርቧል።

Facebook.com/EthioTube   
Twitter.com/EthioTube    
Youtube.com/EthioTube   
Instagram.com/EthioTube   
https://t.me/ethiotube
https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L


በእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ሊቨርፑል መሪነቱን አጠናክሯል።

ዘንድሮ ዋንጫውን ማን ያነሳል?

#PremierLeague #Liverpool #Chelsea #Arsenal


በዋትስአፕ ቻናላችን ኢትዮትዩብን ይከተሉ፡
Follow the EthioTube channel on WhatsApp:
👇🏾 https://whatsapp.com/channel/0029VaCq8Gs2kNFzFeZTGh3L



17 last posts shown.