ተአምረ ማርያም ✤የእመቤታችን ተአምር የሚነገርበት✤ የቅዱሳን ህይወት የሚተረክበት


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


... መሠረቶችዋ በተቀደሱ ተራሮች ናቸው፡፡›› (መዝ.86 ፥ 1) 
----------------✤✤✤---------------
"እነሆም፥ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት
ይሉኛል፤ "የሉቃስ ወንጌል ፩:፵፰
-----------------✤✤✤-------------
ስለእመቤታችን ተዓምሯን አማላጅነቷን እና በአምላክ ዘንድ መመረጧን የሚነገርበት
አስታየት መልዕክት ካለ @Thsion21 ይላኩልን፡፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛


🌷👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧


የዕለቱ ስንቅ

​✝ ቻይ እና ትዕግስተኛ የሆነ ሰው ይጸልያል ስለሚሰጠውም የእግዚአብሔር መልስ አይጨነቅም ። እግዚአብሔር ጸሎቱን እንደሚሰማው እርግጠኛ ነው ። ሁሉም ነገር በእግዚአብሔር ጥበብና ፈቃድ እንደሚሆን በተገቢው ጊዜና መንገድ መልስ እንደሚሰጠው በማመን ለእግዚአብሔር ፍቅር ይተዋል ። አንዳንድ ሰዎች ይህ መሰል ትዕግሥት የላቸውም ። እግዚአብሔርን መውቀስ እና ከእርሱ ስሕተት መፈለግ እንጂ መጠባበቅ አይችሉም ። እርሱን ይወነጅሉታል እርሱ  ግን እጅግ ይታገሳቸዋል ወቀሳቸውንም ይሸከማል ። እነዚህ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ እንደሚሰራ ማመን አለባቸው ።

       አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


#በዓለ_ሥሉስ_ቅዱስ (ጥር 7)

ጥር ሰባት በዚች ቀን በዓለ ሥላሴ የሚከበረው ስለ ሁለት ምክንያቶች ነው:: ቀዳሚው ሕንጻ ሰናዖርን ማፍረሳቸው ሲሆን ሌላው ደግሞ ቅዳሴ ቤታቸው ነው::

#ሕንጻ_ሰናዖር
ሰናዖር ከሺዎች ዓመታት በፊት በአሁኗ ኢራቅ አካባቢ እንደ ነበረ የሚነገርለት ግዛት ሲሆን ስሙ ለሃገሪቱም: ለንጉሡም በተመሳሳይ ያገለግል ነበር:: ከናምሩድ ክፋት በሁዋላ ሰናዖርና ወገኖቹ ከሰይጣን ተወዳጁ::

ከጥፋት ውሃ (ከኖኅ ዕረፍት) በሁዋላ በሥፍራው በአንድነት ይኖሩ ነበርና እርስ በርሳቸው "ኑ ሳንበተን ስማችን የሚጠራበትን ሕንጻ እንሥራ:: በዚያውም አባቶቻችን በውሃ ያጠፋ እግዚአብሔርን እንውጋው" ተባባሉ::

ቀጥለውም ሰማይ ጠቀስ ፎቅን ገነቡ:: ከሕንጻው መርዘም የተነሳ በጸሐይ አብስለው በልተዋል ይባላል:: ቀጥለውም ጦር እያነሱ ፈጣሪን ሊወጉ ወርውረዋል::

መቼም የእነዚህን ሰዎች ክፋትና ቂልነት ስንሰማ ይገርመን ይሆናል:: ግንኮ ዛሬ ሰለጠንኩ በሚለው ዓለም እየተሠራ ያለው ከዚህ የከፋ ነው:: ቸርነቱ ቢጠብቀን እንጂ እንደ ክፋታችንስ ጠፊ ነበርን::

ርሕሩሐን ሥላሴ ግን የሰናዖር ሰዎች የሠሩትን አይተው ማጥፋት ሲችሉ አላደረጉትም:: የባሪያቸውን የኖኅን ቃል ኪዳን አስበዋልና:: ይልቁኑ "ንዑ ንረድ ወንክአው ነገሮሙ ለከለዳውያን-ቁዋንቁዋቸው እንደባልቀው" አሉ እንጂ::

ከለዳውያን ልሳናቸው ተደበላልቆ 71 ቁዋንቁዎች ተፈጠሩ:: እነርሱም ስምምነት አጥተው ተበተኑ:: ሥላሴም ያን ሕንጻ በነፋስ ትቢያ እንዲሆን በተኑት:: ስለዚህም እስከ ዛሬ ሥፍራው "ባቢሎን (ዝሩት)" ሲባል ይኖራል::

#ቅዳሴ_ቤት
ልክ የዛሬ 324 ዓመት አድያም ሰገድ ኢያሱ በኢትዮዽያ በነገሡ በ10ኛው ዓመት (በ1684 ዓ.ም) በጐንደር ከተማ ንግሥተ አድባራት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተሰርታ ተጠናቃለች::

ጥር 7 ቀንም ሊቁ ክፍለ ዮሐንስን ጨምሮ በርካታ ምዕመናን ሠራዊት መሣፍንትና ሊቃውንት ባሉበት ቅዳሴ ቤታቸው ተከብሯል። በዕለቱም ታላቅ ሐሴት ተደርጉዋል። ኢያሱ አድያም ሰገድ ኃያል ደግ ጥበበኛ አስተዋይ መናኝ ንጉሥ ነውና።

ቤተ ሥላሴን አስጊጿታልና ከዚህ ቀን ጀምሮ ጥር ሥላሴ በድምቀት የሚከበር ሆኗል:: ነገር ግን በተሠራች በ16 ዓመቷ ደጉ ኢያሱ ከተገደለ በሁዋላ ቤተ ክርስቲያኑ በአደጋ ፈርሷል:: ዛሬ የምናየው በ1708 ዓ.ም በልጁ በአፄ ዳዊት ሣልሳዊ የታነጸውን ነው::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

(ስንክሳር ዘተዋሕዶ)

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


ሚስት ባሏን ልትፈትን ፈለገች፣ ከኔ ተለይቶ ሲያድር ወይም ድንገት ከቤት ሲያጣኝ ምን ይሰማዋል? የሚለውን ለማወቅ አቀደችና ባለቤቷ ከሥራ በሚመለስበት ሰአት ጠብቃ አልጋ ስር ተሸሸገች።

በብጣሽ ወረቀት " ቤተሰቦቼ ጋ ሄጃለሁ። አልመጣም አትጠብቀኝ" የሚል ማስታወሻ ፅፋ ኮሞዲኖ ላይ አስቀምጣ አልጋ ስር ገባች። ባል ወደቤት ሲገባ ባለቤቱ የለችም። ወረቀቱን አነበበና እሱም መልስ ጫር ጫር አድርጎ ወረቀቱን ያገኘበት ቦታ አስቀመጠውና ልብሱን መቀያየር ጀመረ።

ልብሱን ቀይሮ እንደጨረሰ ሞባይሉን አነሳና " ሄሎ ፍቅሬ የኔ ማር እንዴት ነሽልኝ፣ ዛሬ ምርጥ ጊዜ እናሳልፋለን። ባለቤቴ ቤተሰቦቿ ጋ ሄዳለች አትመጣም። አንቺ ኮ ማር ነሽ.... እሷን ሳላገባ ባውቅሽ ኖሮ እሷን አላገባም ነበረ ... ከአምስት ደቂቃ በላይ አልቆይም ዝግጁ ሁነሽ ጠብቂኝ መጥቼ ወስድሻለሁ ባይ የኔ ጣፋጭ " ብሎ ወሬውን ጨርሶ ተነስቶ ወጣ።

ሚስት አልጋ ስር ሆና ቅጥል ብግንግን ብላለች... ልክ እንደወጣ አፍናው የቆየችውን ለቅሶዋን አፈነዳችው...... ከዚያ ምናባቱ ነው ፅፎ ያስቀመጠው... አለችና ወረቀቱን አንስታ ስታነበው .. " ቂሎ ባንቺ ቤት መደበቅሽ ነው አይደል...... እግሮችሽን ገና ስገባ ነው ያየሁት በይ እራት ገዝቼ መጣሁ እንባሽን ታጥበሽ … እሽቅርቅር ብለሽ ጠብቂኝ " ነበረ የሚለው።

ፍቅር እንዲህ ነው

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna




!ፍቅርን ለተጠማ ሁሉ ፍቅር ተወለደ

ሰላም ላጡት ሁሉ ሰላም ተወጠነ

በጨለማ ላሉ ሁሉ ብርሃን ወጣ

ለባዘኑት ሁሉ እረኛው መጣ በበረት ተኛ

ለበሽተኞች ሁሉ መድኃኒት ተገኘ

ስጦታ ለናፈቅን ሁሉ ውድ ስጦታ ተሰጠን
ስጦታውም ምድራዊ ሳይሆን ሰማያዊ ነው።
እርሱም የአብ የባሕርይ ልጅ ነው
" በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:16)


እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳይሁ !!!

በእንተ ነገረ ልደት በአፈ አበው ሲገለፅ

“ ክርስቶስ ከእለት ከሰዐት አስቀድሞ የነበረ ቀዳማዊ ሲሆን የሰዎችን ልደት ዛሬ ተወለደ፤ ሰው ሆይ ስጋ ያልነበረው እርሱ ለአንተ ብሎ ስጋን ተዋሀደ፤ ሰው ሆይ በመለኮቱ የማይዳሰስ የነበረ አምላክ ለአንተ ብሎ ተዳሰሰ ፤በመለኮቱ ጥንት የሌለው እርሱ ጥንት ያለውን ፍፁም ስጋ ተዋሀደ፤ አይታይ የነበረ እርሱ የሚታይ ስጋን ተዋሃደ፤ የማይለወጥ እርሱ በሚለወጥ ስጋ ተዳሰሰ የማይለወጥም አደረገው፤ ባዕል የሆነ  እርሱ ከሌዊ ወገን በተወለደች ድንግል ማህፀን አደረ ፤ሰማይን በደመና የሚሸፍን እርሱ በጨርቅ ተጠቀለለ፤ የነገስታት ንጉስ የሆነ እርሱ በበረት ተኛ “                                    
             ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አስጢፎስ
ከሶስቱ አካል አንዱ አካል በእመቤታችን  በንፅሕት ድንግል ማርያም  ማኅፀን  አደረ ፤ ስለ መለኮት ተዋህዶ በዚህ የምንናገረው በወልድ ያለውን ነው ፡፡ ስለ አብ ስለ መንፈስ ቅዱስ አይደለም ፈፅሞ አብ መንፈስ ቅዱስ ሰው ለመሆን በድንግል ማኅፀን አደሩ አንልም ፡፡
        ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ አግናጥዮስ
ሰዎች መለኮትን ያዩት ዘንድ የበቁ እሰኪሆኑ ድረስ በሰው ባሕርይ ተገለጠ በስጋ ዘመዳችን ሆኖ ባየነው ጊዜ በአብ ቸርነት የወልድን ጌትነት እናመስግናለን ፡፡
              ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ጎርጎርዮስ


እግዚአብሔር ቃል ወደዚህ ዓለም ይመጣ ዘንድ ከንፅሕት ድንግል ማርያም ስጋን ይዋሐድ ዘንድ ምን አተጋው ? በጨርቅ ይጠቀለል  በበረትም ይጣል ዘንድ  ከድንግል ጡት ወተትን ይጠባ ዘንድ ምን አተጋው ?   በፍዳ ተይዘን የነበርን እኛን ያድነን ዘንድ ለእኛ ብሎ አየደለምን  ፡፡
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ እለእስክንድሮስ
ከህሊናት ሁሉ ለራቀ ለዚህ ድንቅ ሚስጢር አንክሮ ይገባል ፤ከምድራዊት ሴት ሰው የሆነ እግዚአብሔር ቃልን ወለደችው ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው እርሱም እናቱን ፈጠረ፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤፍሬም

እርሱ በላይ በዙፋኑ ሳለ በድንግል ማሕፀን ተወሰነ ከእርስዋም ተወለደ ፤በእናቱ ክንድ ላይ ሳለ  በነፋስ ይመላለስ ነበር ፤መላእክትም ይሰግዱለት ነበር፡፡
ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ኤራቅሊስ
ዳግመኛም ዛሬ እግዚአብሔር ቃል ከቅድስት ድንግል ተወልዶ ታየ ፡፡ድንግልም እንደ ቀድሞዋ በድንግልና ፀንታ ኖረች ፤እናትም ተባለች፡፡
ሃይማኖተ  አበው ዘ ቅዱስ ቴዎዶጦስ
  
አምላክ ከሾማቸው ከመምህራን አባቶች    ይህን ረቂቅ ትምህርት አግኝተናል ፡፡ይህም ትምህርት ለማያምኑ  የተሰወረ ለምእመናን ግን የተገለፀ ነው፤ ፃድቃን ያውቁታል ኃጥአን ግን አያውቁትም ተብሎ እንደተፃፈ ፡፡
 

እንኳን አደረሳችሁ
መልካም የልደት በዓል ይሁንላችሁ !!!

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna




ኵሉ ዘገብራ ለጽድቅ ጻድቅ ውእቱ
ወዘያከብር ሰንበተ። ኢይበል ፈላሲ ዘገብአ ኀበ
እግዚአብሔር ይፈልጠኒኑ እምሕዝቡ። ኵሉ
ዘገብራ ለጽድቅ፣ ጻድቅ ውእቱ ወዘያከብር
ሰንበተ።(፪ ሮ፸፭)


ጽድቅን የሠራ ሰንበትን ያከበረም ሰው ሁሉ
ጻድቅ ነው። ወደ እግዚአብሔር አምልኮት የገባ
ከምዕመናን ይለየኝ ይሆን ፈጽሞ አይበል።
ጽድቅን የሠራ ሰንበትን ያከበረም ሰው ሁሉ
ጻድቅ ነው።

@ewuntegna
@ewuntegna
❤️❤️❤️❤️


በነበር ጊዜን መጨረስ ጽድቅ አይደለም።
ብየ ነበር፣አስቤ ነበር፣ቢሆን ጥሩ ነበር፣እንዲህ መሆኑን አውቄ ቢሆንማ እንዲህ አደርግ ነበር፣ነበር..በነበር ትችት ጊዜያችን አለቀ። በነበር ጊዜን መጨረስ ጥቅሙ ምንድን ነው? ምንም።ወቃሽ ህሊናን ለማስተኛት ብቻ ይጠቅም ይሆናል።
ለነፍስም ለሥጋም የሚጠቅም ተግባርን ካልሠራንበት የነበር እድሜ ዕዳ ነው።
ነበር እያሉ መውቀስ እና ማማረር  ስንፍናን እና ውሳኔ አልባነትን በራስ ላይ ማጽደቅ ነው።
ተግባር በሌለው ንግግር ነበር እያሉ ብቻ መናዘዝ የጽድቅ ትሩፋት ሊሆን አይችልም።
የአባታችን የቅዱስ ጳውሎስ ምክሩ ግን ይች ናት፦"ምክንያትን ከሚፈልጉቱ ምክንያትን እቆርጥ ዘንድ አሁን የማደርገውን ከዚህ ወዲህ ደግሞ አደርጋለሁ።"፪.ቆሮ.፲፩፥፲፪ ብሎ ምክንያተኞች እንዳያመካኙ ከተግባረ ወንጌል አለመለየቱን ነግሮናል።
ሌሊት በድንኳን ስፌት ቀን በትምህርት የተጋ ሁኖ ኑሯልና።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna




ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ

ለምስጋና ሁለተኛ ለፍጥረት ሦስተኛ ቀን ነው በዚህም ቀን እመቤታችን ትመጣለች የብርሃን ምንጣፍ ይነጠፋል፡፡ የብርሃን ድባብ ይዘረጋል ከዚያ ላይ ሁኖ ሰላም ለከ ኦ ፍቁርየ አፍሬም ትለዋለች : እርሱም ታጥቆ እጅ ነስቶ ይቆማል፡፡ ወድስኒ ትለዋለች በዕለት ሰኑይ ክርክር አልቋልና ባርከኒ ይላታል፣፣ በረከተ ወልድየ ወአቡሁ ወመንፈስ ቅዱስ ይኅድር በላዕሌከ ትለዋለች፡፡ ተባርኮ ምስጋናዋን ይጀምራል፡፡ ውዳሴ ዘሠሉስ ውዳሴሃ ለእግዝእትነ ማርያም ድንግል ወላዲተ አምላክ ዘይትነበብ በዕለተ ሠሉስ ይላል ቃለ ጸሓፊ ነው፡፡ እርሱ ግን አክሊለ ምክሕነ ብሎ ይጀምል፡፡

አክሊለ ምክሕነ፡፡

አክሊል የወዲህኛው ፤ ምክሕ የወዲያኛው::

ወቀዳሚት መድነኒትነ፡፡

ቀዳሚት የወዲህኛው ፡ መድኃኒት የወዲያኛው።

ወመሠረተ ንጽሕነ፡፡

መሠረት የወዲህኛው፤ ንጹሕ የወዲያኛው፡፡

ኮነ በማርያም ድንግል።

በማርያም ድንግል ሆነልን አለ፡፡ ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም በዚህ ቀን ከነገሥታት ዳዊትን ፤ ከመሳፍነት ኢያሱን ፤ ከደናግል ኢሊያስን አስከትላ መጥታለች፡፡ ዳዊት ምንም ንጉሠ ነገሥት ብትባል የመመኪያችንን ዘውድ ማምጣት አልተቻልህም፡፡ ኢያሱም መድኃኒት ብትባል የድኅነታችን መጀመሪያ መሆን አልተቻለህም፡፡ ኤሊያስም ንጹሕ ድንግል ብትባል ፣ የንጽሕናችን መሠረት መሆን አልተቻለህም፡፡ የመመኪያችን ዘውድ የድኅነታችን መጀመሪያ ፤ የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናት ሲል ነው፡፡ አንድም አክሊሎሙ ለሰማዕት እንዲለው አክሊለ ሰማዕት የሚባል ጌታ፡፡

ጥንተ ሕይወቶሙ እንዲለው ጥንተ ሕይውት የሚባል ጌታ  አኃዜ ዓለም በአራኈ ኩሉ እኁዝ ውስተ እዴሁ መሠረት ዓለም !ይጸውር ድደ ወይነብር ፈረ እንዲል፤ መሠረተ ዓለም የሚባል ጌታ ፣ በድንግል ማርያም ተሰማልን፡፡ ትላንት ስሟን አላነሳም ዛሬ ስሟን አነሣ በአንግዳ ልማድ እንግዳን ዕለቱን ስሙን እየጠሩትም ፣ ከዋለ ካደረ በኋላ ስሙን ይጠሩታል በዚያ ልማድ ፣ ማርያም ማለት ፍጽምት ማለት ነው : ለጊዜው መልክ ከደም ግባት አስተባብራ ተግታለች፡፡ ፍጻሜው ግን ንጽሐ ሥጋ ከንጽሐ ነፍስ ድንጋሌ ሥጋ ከድንጋሌ ነፍስ አስተባብራ ተገኝታለችና፡፡

አንድም ጸጋ ወሀብት ማለት ነው ለጊዜው ለናት ላቲ ጸጋ ሁና ተስጥታለች ፍጻሜው ግን ለሰው ሁላ ጸጋ ሁና ተስጥታለችና አንድም መርሕ ለመንግስተ ሰማያት ማለት ነው፡፡ምእመናን መርታ ገነት መንግስተ ሰማያት አግብታለችና::

አንድም ልዕልት ማለት ነው፡፡ ሮም አርያም ማለት ልዑል ማለት እንደ ሆነ፡፡ እርሷንም መትሕተ ፈጣሪ መልዕልተ ፍጡራን ይላታልና፡፡ አንድም ማኅበረ መሐይምናን ሕዝብ ተለአኪተ እግዚአብሔር ወሰብእ ተፈሥሒ ቤተ እስራኤል ፤ ወተሐሰዩ ቤተ ይሁዳ ማለት ነው፡፡ አንድም ማርያም ማለት እግዝእተ ብዙኃን ማለት ነው፡፡ አብርሃም ማለት አበ ብዙኃን ማለት እንደሆነ፡፡

እንተ ወለደት ለነ ዘእግዚአብሔር ቃለ፡፡

መመኪያነቷን በቅጽል አመጣው  አካላዊ ቃልን በወለደች በድንግል ማርያም ተገኘልን፡፡

እኛን ስለማዳን ሰው የሆነ፣፣

ዘኮነ ሰብእ በአንተ መድኃኒትነ፡

እምድኅረ ኮነ ሰብአ ጥዩቀ አምላክ ፍጹም ውእቱ፡፡

ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው፡፡ ሐራ ጥቃቃል ሥጋ ኮነ ያለውን ይዘው ወደ ታች ተለወጠ ይላሉና ሰውም ከሆነ በኋላ ፍጹም አምላክ ነው አለባቸው::

ስለዚህ ነባር ማኅተመ ድንግግልናዋ ሳይለወጥ ወለደችው፡፡

ወበእንተዝ ወለደቶ እንዘ ድንግል ይእቲ፡፡

መንክር ኅያለ ወሊዶታ ዘኢይትነገር፡፡

ድንቅ የሚሆን የመውለዷ ሥራ የማይመረመር ነው፡፡ የማይመረመር የመውለዷ ሥራ ድንቅ ነው፡፡

ሰአሊ ለነ ቅድስት፡፡

በማይመረመር ግብር ከወለድሽው ልጅሽ ጽንዕት በድንግልና  ስርጉት በቅድስና እመቤታችን ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሣን ለምኝልን፡፡አይምዕሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን
::

@ewuntegna
@ewuntegna


አንተ ብቻ በእግዚአብሔር መስመር ላይ ትክክለኛ መንገድ ላይ ሁን እንጅ እግዚአብሔር ቆየ ማለት አላየም ማለት አይደለም።እግዚአብሔር ዘገየ ማለት እያማረና እየተዋበ ነው።ብቻ ትክክለኛው መንገድ እና አቅጣጫ ውስጥ ሆነህ ጠብቀው እንጅ እሱ በትክክለኛው ሰዓት ትክክለኛ ዋጋህን ሊሰጥ ይመጣልና ምንግዜም ታምነህ ጠብቀው።
@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna




Forward from: ࿇EL҉O҉H҉E҈ P҉I҉C҉T҉U҉R҉E҈S҉࿇
✨ ELOHE PICTURE

“ ቅዱስ ገብርኤል ፲፱ ”

የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ገብርኤል የስሙ ትርጓሜ ‹‹እግዚእ ወገብር፤ አምላክ ሰው ሆነ ሰው አምላክ ሆነ›› ማለት ነው። በዕለተ እሑድ መላእክት መኑ ፈጠረነ ሲሉ ዲያቢሎስ እኔ ፈጠርኳችሁ ብሉ ፈጥሮ ለማሳየት እጁን ከእሳት ከትቶ አቃጥሎት መላእክት በተረበሹ ጊዜ በያለንበት እንቁም ብሎ ያረጋጋቸው መላእክ ነው። በዚህም ምክንያት ጌታ " ወበእንተዝ ይደልዎ ከመ ይጹር ዜናሃ ለማርያም እንዲል ሥጋዌውን ለድንግል እንዲያበስር አድሎታል ። ከዚህም በኃላ ደጋግ ሰዎችን ለመርዳት የሚወጣ የሚወርድ ሆኗል ።


♡ ㅤ  ⎙ㅤ    ⌲        ✉️    Lᶦᵏᵉ   ˢᵃᵛᵉ    ˢʰᵃʳᵉ    ᶜᵒᵐᵐᵉⁿᵗ
ቶሎ ቶሎ እንድንለቅ ሪያክሽን እንዳይረሳ ❤️
     ➪ ꌗꃅꍏꋪꍟ ꌩꂦꀎꋪ ꎇꋪꀤꍟꈤꀸ

🔻🔻ይቀላቀሉን 🔗🔗⏰
https://t.me/+Ci5F1FcleWtlZThk


#ሊቀ_መላእክት_ቅዱስ_ገብርኤል (#ታኅሣሥ_19)

ታኅሣሥ ዐስራ ዘጠኝ በዚህች ቀን ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ሠለስቱ ደቂቅ ያዳነበት ነው፡፡ ንጉሥ ናቡከደነፆር ከአባታቸው ከይሁዳው ንጉሥ ከኢዮአቄም ጋር የማረካቸው አናንያ፣ ሚሳኤልና አዛርያ እግዚአብሔር በዚህች ዕለት መልአኩን ልኮ ታላቅ ተአምር አድርጎላቸዋል፡፡

ንጉሥ ናቡከደነፆር እነዚህን ወጣቶች በቤተ መንግሥቱ ውስጥ ጥበብን እያስተማረ ካሳደጋቸው በኋላ በባቢሎን ሀገሮች ሁሉ ውስጥ ሾማቸው፡፡ ከዚህም በኋላ ንጉሡ የወርቅ ምስል በሠራ ጊዜ መኳንንቱንና በግዛቱ ውስጥ ያሉ ሁሉ ለዚያ ምስል እንዲሰግዱ አዘዘ፡፡ በዚህም ጊዜ ለጣዖቱ ባለመስገድ እግዚአብሔርን ብቻ በማምለክ የጸኑት እነዚህ ሦስት ወጣቶች ብቻ ነበሩ፡፡ ስለ እነርሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዲህ ተብሎ ነው የተጻፈው፡-
‹‹ንጉሡ ናቡከደነፆር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድስት ክንድ የሆነውን የወርቁን ምስል አሠራ፤ በባቢሎንም አውራጃ በዱራ ሜዳ አቆመው፡፡ ንጉሡም ናቡከደነፆር መኳንንትንና ሹማምቶችን፥ አዛዦችንና አዛውንቶችን፥ በጅሮንዶችንና አማካሪዎችን፣ መጋቢዎችንም፣ አውራጃ ገዦችንም ሁሉ ይሰበስቡ ዘንድ፣ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ይመጡ ዘንድ ላከ፡፡ በዚያን ጊዜም መኳንንቱና ሹማምቶቹ፣ አዛዦቹና አዛውንቶቹ፣ በጅሮንዶቹና አማካሪዎቹ፣ መጋቢዎቹና አውራጃ ገዦቹ ሁሉ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ምስል ምረቃ ተሰበሰቡ፤ ናቡከደነፆርም ባቆመው ምስል ፊት ቆሙ፡፡ አዋጅ ነጋሪውም እየጮኸ እንዲህ አለ፡- ‹ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የምትናገሩ ሆይ! የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ፣ ተደፍታችሁ ንጉሡ ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቁ ምስል እንድትሰግዱ ታዝዛችኋል፡፡ ተደፍቶም የማይሰግድ በዚያን ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል፡፡› ስለዚህ በዚያን ጊዜ አሕዛብ ሁሉ የመለከቱንና የእንቢልታውን፣ የመሰንቆውንና የክራሩን፣ የበገናውንና የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰሙ ጊዜ፣ ወገኖችና አሕዛብ በልዩ ልዩ ቋንቋም የተናገሩ ሁሉ ተደፉ፤ ንጉሡም ናቡከደነፆር ላቆመው ለወርቅ ምስል ሰገዱ፡፡

በዚያን ጊዜም ከለዳውያን ቀርበው አይሁድን ከሰሱ፡፡ ለንጉሡም ለናቡከደነፆር ተናገሩ እንዲህም አሉ ‹ንጉሥ ሆይ! ሺህ ዓመት ንገሥ፡፡ አንተ ንጉሥ ሆይ የመለከትንና የእንቢልታን፣ የመሰንቆንና የክራርን፣ የበገናንና የዋሽንትን፣ የዘፈንንም ሁሉ ድምፅ የሚሰማ ሰው ሁሉ ተደፍቶ ለወርቁ ምስል ይስገድ፤ ተደፍቶም የማይሰግድ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ይጣላል ብለህ አዘዝህ፡፡ በባቢሎን አውራጃ ሥራ ላይ የሾምሃቸው ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም የሚባሉ አይሁድ አሉ፤ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ትእዛዝህን እንቢ ብለዋል፤ አማልክትህን አያመልኩም፥ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል አይሰግዱም፡፡› ናቡከደነፆርም በብስጭትና በቍጣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም ያመጡ ዘንድ አዘዘ፤ እነዚህንም ሰዎች ወደ ንጉሡ ፊት አመጡአቸው፡፡ ናቡከደነፆርም ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ሆይ! አምላኬን አለማምለካችሁ ላቆምሁትም ለወርቁ ምስል አለመስገዳችሁ እውነት ነውን? አሁንም የመለከቱንና የእንቢልታውን የመሰንቆውንና የክራሩን የበገናውንና የዋሽንቱን የዘፈኑንም ሁሉ ድምፅ በሰማችሁ ጊዜ ተደፍታችሁ ላሠራሁት ምስል ብትሰግዱ መልካም ነው፤ ባትሰግዱ ግን በዚያ ጊዜ በሚነድድ እሳት እቶን ውስጥ ትጣላላችሁ፤ ከእጄስ የሚያድናችሁ አምላክ ማን ነው?›› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም መለሱ ንጉሡን ‹ናቡከደነፆር ሆይ! በዚህ ነገር እንመልስልህ ዘንድ አስፈላጊያችን አይደለም፡፡ የምናመልከው አምላካችን ከሚነድደው ከእሳቱ እቶን ያድነን ዘንድ ይችላል፤ ከእጅህም ያድነናል፡፡ ነገር ግን ንጉሥ ሆይ! እርሱ ባያድነን አማልክትህን እንዳናመልክ ላቆምኸውም ለወርቁ ምስል እንዳንሰግድለት እወቅ› አሉት፡፡

የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም ላይ ቍጣ ሞላበት፡፡ የፊቱም መልክ ተለወጠባቸው፡፡ እርሱም ተናገረ የእቶንም እሳት ይነድድ ከነበረው ይልቅ ሰባት እጥፍ አድርገው እንዲያነድዱት አዘዘ፡፡ ሲድራቅንና ሚሳቅንም አብደናጎንም ያስሩ ዘንድ ወደሚነድድም ወደ እቶን እሳት ይጥሉአቸው ዘንድ በሠራዊቱ ውስጥ ከነበሩት ኃያላን አዘዘ፡፡ የዚያን ጊዜም እነዚህ ሰዎች ከሰናፊላቸውና ከቀሚሳቸው ከመጐናጸፊያቸውም ከቀረውም ልብሳቸው ጋር ታስረው በሚነድድ በእቶን እሳት ውስጥ ተጣሉ፡፡ የንጉሡም ትእዛዝ አስቸኳይ ስለሆነ የእቶኑም እሳት እጅግ ስለሚነድድ፣ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም የጣሉአቸውን ሰዎች የእሳቱ ወላፈን ገደላቸው፡፡ እነዚህም ሦስቱ ሰዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም ታስረው በሚነድደው በእቶኑ እሳት ውስጥ ወደቁ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ናቡከደነፆር ተደነቀ ፈጥኖም ተነሣ፤ አማካሪዎቹንም ‹ሦስት ሰዎች አስረን በእሳት ውስጥ ጥለን አልነበረምን?› ብሎ ተናገራቸው፡፡ እነርሱም ‹ንጉሥ ሆይ! እውነት ነው› ብለው ለንጉሡ መለሱለት፡፡ እርሱም ‹እነሆ እኔ የተፈቱ በእሳቱም መካከል የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለሁ፤ ምንም አላቈሰላቸውም፤ የአራተኛውም መልክ የአማልክትን ልጅ ይመስላል› ብሎ መለሰ፡፡ የዚያን ጊዜም ናቡከደነፆር ወደሚነድደው ወደ እሳቱ እቶን በር ቀርቦ ‹እናንተ የልዑል አምላክ ባሪያዎች ሲድራቅና ሚሳቅ አብደናጎም! ኑ ውጡ› ብሎ ተናገራቸው፡፡ ሲድራቅና ሚሳቅም አብደናጎም ከእሳቱ መካከል ወጡ፡፡

መሳፍንቱና ሹማምቶቹም አዛዦቹና የንጉሡ አማካሪዎች ተሰብስበው እሳቱ በእነዚያ ሰዎች አካል ላይ ኃይል እንዳልነበረው፣ የራሳቸውም ጠጕር እንዳልተቃጠለች ሰናፊላቸውም እንዳልተለወጠ፣ የእሳቱም ሽታ እንዳልደረሰባቸው አዩ፡፡ ናቡከደነፆርም መልሶ ‹መልአኩን የላከ ከአምላካቸውም በቀር ማንም አምላክ እንዳያመልኩ ለእርሱም እንዳይሰግዱ ሰውነታቸውን አሳልፈው የሰጡትን የንጉሡንም ቃል የተላለፉትን በእርሱ የታመኑትን ባሪያዎቹን ያዳነ፣ የሲድራቅና የሚሳቅ የአብደናጎም አምላክ ይባረክ፡፡ እኔም እንደዚህ የሚያድን ሌላ አምላክ የለምና በሲድራቅና በሚሳቅ በአብደናጎም አምላክ ላይ የስድብን ነገር የሚናገር ወገንና ሕዝብ በልዩ ልዩም ቋንቋ የሚናገሩ ይቈረጣሉ፣ ቤቶቻቸውም የጕድፍ መጣያ ይደረጋሉ ብዬ አዝዣለሁ› አለ፡፡ የዚያን ጊዜም ንጉሡ ሲድራቅንና ሚሳቅን አብደናጎንም በባቢሎን አውራጃ ውስጥ ከፍ ከፍ አደረጋቸው፡፡›› ትንቢተ ዳንኤል 3፡1-30፡፡

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በመልአኩ አማላጅነት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


"ልጆቻችሁን ይዛችሁ ወደ ቤተክርስቲያን ኑ። ብቻችሁን አትምጡ። ብቻችሁን ከመጣችሁ ወደ ሌላ ይሔዳሉ ፣ እናንተ እዚህ መጥታችሁ የምትሰሩትን አያውቁም ። ወዴት እንደሔዳችሁ አያውቁም ። ወራሾቻችሁ አይሆኑም ። ስለዚህም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡ ልጆቻችሁን ይዛችሁ ኑ። አሳዩአቸው ሥዕሉን ይሳሙ ፣ ቅዳሴ ጠበል ይጠጡ ፣ በእምነት አሻሹአቸው መስቀል እንዲስሙ አስተምሯቸው ፣ ዕጣኑን ያሽትቱ ፣ ሥጋ ወደሙን ይቀበሉ ፣ ቃጭሉን ይስሙ ፣ ደውል ሲደውል ይስሙ ፣ ቄሳቸው ማን እንደሆነ ቤተ ክርስትያናቸው ምን እንደሆነች ፣ በውስጧ ምን ምን እንደሚሰራ ያጥኑ ፣ ይማሩ ። ወደ ሰንበቴው እጃችሁን ይዘው ይከተሉ ፣ ወደ ማኅበር ስትሔዱም ይዛችኋቸው ሒዱ ፣ ቆሎውን ዳቦውን ተሸክመው ወደ ሰንበቴው ይምጡ ይማሩ ። እነርሱም ነገ ይሄን እንዲወርሱ የነገ ባለአደራዎች መሆናቸውን እንዲያውቁ ።"

       አቡነ ጎርጎሪዮስ ካልዕ

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna


ጌታ ሆይ አንተ ለራስህ አድርገኸናል፤
በአንተ እስኪያርፍ ድረስ ልባችን እረፍት የለውም

የአውግስጢኖስ ኑዛዜ 1፡1


" ክፉ የሆነች ልማድ ሳበችኝ፣ በታዘዝኩላት ጊዜም በማይፈታ ማሰሪያ አሰረችኝ፡፡ ማሰሪያውም በእኔ ዘንድ የተወደደ ነው፤ ልማድ፣ በወጥመዷ ፈጽማ አሰረችኝ፡፡ በታሰርሁ ጊዜም ፈጽሞ ደስ ይለኛል፡፡ በማዕበሉም ያሰጥመኛል፤ በዚህም ደስ ይለኛል፡፡ ጠላት ሰይጣንም ዘወትር ማሰሪያዬን ያድስልኛል፤ በመታሰሬ ፈጽሞ ስደሰት አይቶኛልና፡፡ ኅፍረትና ጉስቁልኛ ሸፈነኝ፤ እኔ በፈቃዴ ታሰርሁ፤ ማሰሪያዬንም በቅጽበት በመበጣጠስ ከወጥመድ መውጣት እችላለሁ፡፡ ነገር ግን አልሻም፤ እኔ በቸልተኝነትና በስንፍና የተያዝኩ ነኝና፡፡ ክፉ ለሆነች ልማድም የተገዛሁ ነኝና፡፡ እኔ ጎስቋላ በሆነ ስቃይ የታሰርሁና ለበጎ ነገር የማልጠቅም ሰነፍም ነኝ፡፡ እኔ አሁን ወደ አንተ ካልተመለስኩ እንደምትፈርድብኝ አውቃለሁና ወደ እኔ ትመለስ ዘንድም በእንባ እለምንሃለው፡፡ ስለዚህም ቁጣህን ከእኔ አዘግይ፤ ወደ አንተ መመለሴን፣ ንስሐ መግባቴንም ጠብቅ፤ አንተ ማንኛውም ሰው በእሳት እንዲቃጠል አትሻምና!! እንኪያውስ በምሕረትህ እታመናለው፣ በይቅርታህም እጸናለሁ፡፡ "

@Ewuntegna
@Ewuntegna
@Ewuntegna



20 last posts shown.