ጊዜ ⏱


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Art


ስማኝማ የሀገሬ ሰው
ወንድምህም ነው እኮ ሰው።

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Art
Statistics
Posts filter


ሰውዬው ድግስ ነበረበትና በሬውን አረደ

ከድግሱ እንዲቋደሱለት ዘመድ አዝማድ እና ጎረቤት መጋበዝ ፈልጎ ሴት ልጁን ጠርቶ  "ሄደሽ ጎረቤቶቻችንን እና ወዳጆቻችንን እየዞርሽ ጥሪያቸው: ከእኛ ጋር ይብሉ ይጠጡ" አላት

ሴት ልጁም የሰፈሩ መስቀለኛ መንገድ ላይ ወጥታ "እባካችሁን ጎረቤቶቻችን ቤታችን በእሳት ተያይዞ እየነደደ ነው: እባካችሁን መጥታችሁ በማጥፋት አግዙን" ስትል ጮኸች

የተወሰኑ ሰዎች የልጅቷን ጥሪ ሰምተው እየሮጡ ወደ አባትየው ቤት ሄዱ: ሌሎች ደግሞ ሰምተው ዝም አሉ

ድግሱ ተጀመረ: ምግብ መጠጡ ቀረበ :ሁሉም መደሰት ጀመረ

ሰውዬው ቅርብ የሚላቸው ወዳጆቹ  እና ጎረቤቶቹ ጋብዟቸው ባለመምጣታቸው ቅር ብሎታል

ሴት ልጁንም ጠርቶ "እዚህ የማያቸው ሰዎች በቅርቡ ወደ ሰፈራችን የመጡ ናቸው: አንዳንዶቹን ደግሞ ከነአንካቴው አላውቃቸውም:: ጎረቤቶቻችን እና የቅርብ ወዳጆቻችን የታሉ? አልጠራሻቸውም እንዴ" ሲል ጠየቃት

ልጅቱም እንዲህ አለችው

“እዚህ የምታያቸው ሰዎች ቤታችን ውስጥ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት እና እኛን ለመርዳት የመጡ ናቸው: ድግስ መኖሩን አያውቁም ነበር"

"ስለዚህ እነዚህ ናቸው ወዳጆቻችን እና ጎረቤቶቻችን: ከእነዚህ ጋር ነው ደስታችንን መካፈል እና ድግሳችንን መቋደስ ያለብን"

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@eyetaye12


አንዲት ዝሆን እና ውሻ በተመሳሳይ ግዜ አረገዙ።

ከሦስት ወራት በኃላ ውሻይቱ ስድስት ቡችላ ወለደች ።ውሻዋ ድጋሜ አረገዘች እንደገና ሌላ ስድስት ቡችላ ወለደች....

እንዲህ እንዲህ እያለ ጉዳዩ ቀጠለ...

18 ኛው ወር ላይ ዉሻዋ ዝሆኗን ጥያቄ ጠየቀች

እርግጠኛ ነሽ እርጉዝ ነሽ ...?እንደምታቂው እኔ ብዙ ቡችሎች ወልጃለሁ... አሁን ሁሉም አድገው ትልልቅ ሆነዋል ነገር ግን አንቺ እስካሁን እርጉዝ ነሽ ምን እየተካሄደ ነው...?ስትል ጠየቀች

ዝሆኗም ረጋ ብላ "የሆነ ነገር እንዲገባሽ እፈልጋለሁ ...እኔ የተሸከምኩት ነገር ቡችላ አይደለም...እኔ የተሸከምኩት ዝሆን ነው...ዝሆን ደግሞ ለመወለድ ሁለት ዓመት ይፈጅበታል...

የወለዱኩት ግዜ ደግሞ ከምድራችን ግዝፉ እንሰሳት መካከል አንዱ ይሆናል ስትል መለሰችላት ....ይባላል።

እርስዎ ያረገዙት ሀሳብ ምንድነው...?
ምን ሠራለሁ ብለው አስበዋል...?

ትልቅ ሀሳብ ያለው ሰው ሀሳቡን ከግብ ለማድረስ ግዜ ሊወስድበት ይችላል ግን ከፍፃሜ ሲደርስ ለሀገር ብሎም ለዓለም በርከት መሆን ይችላል።

ህልም እና ራዕይህ ትልቅ ይሁን።

@eyetaye12


✔️ ዱለቱን የበሉት ቄሱ እማሆይ ግን አገሱ፡፡ @eyetaye12


😂አፍንጫ ቢገተር እንደ ስልክ እንጨት ይበልጡሽ የለም ወይ እነ ጎራዲት።

Join 👉 @eyetaye12


#እሷ:- ሚስትና ልጆች እንዳሉህ ለምን አልነገርከኝም

#እሱ:- አይናፋር ነኝ ማሬ😔😔😔

@eyetaye12


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🥹😔


ይበልጠዋል ካንደበቴ ከመኖሬ ምታነበዉ 🥺


አንድ ንፁህ ሠሃን በልተዉ ከጨረሱ በኋላ የቆሸሸ ሠሃን ይሉታል😒


ልትኖር ከምትቃትት
አንዲት ደቃቃ ነፍስ የተላከዉ መልዕክት

አትያዙኝ ልዉደቅ ብዬ እየጮኩኝ
እጣ ፋንታ ሆኖኝ
መሳቅ ብርቅ ሆኖብኝ
ለማከም ስሞክር የህመሜን ቁስል
ባትኖር ምን ነበረ ባለሁበት ክልል
ሂድ ራቅ ይሸታል
የቆሰለዉ እኔነቴ ይከረፊል
መጠላት ገንዘቡ
መወደድ ርሃቡ
መፈለግ ምኞቱ
መተዉ የግል ሃብቱ
ለሆነዉ እኔነቴ
እንዴት ልንገርልህ
እንዴት ላስረዳልህ
ምንስ ልበልልህ
ለመተዉ ሚቸኩል ልቤን በምን ቃል ላስረዳዉ
ወዶሃል እያይኝ በምን ቃል ልንገረዉ
ጨነቀኝ አለሜ ምገባበት ጠፊኝ
ልኖር መጓጓቴ ይባሱኑ ጎዳኝ
የኔ ያልኩት አለም ራሴኑ አደማኝ


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አንዳንዴ እንደዚም አይነት ስሜቶች አሉ😔


ትቶ መሄድ እንዲ ቢቀል
መርሳት አንቺን እንዴት ሊቻል
ትዝታዬን የህመሜን መድኃኒት
ጠበቃዬን ዋስትናዬን አካሚዬን
መቼም አለቅሽም ውዷ ስጦታዬን 😘


መረሳት እኮ ይቻላል
ከመፈቀርም ይቀላል
አትጨክን በራስህ
ትተኋኝ ሂድ ጎበዝ ሁነህ
አትያዘኝ አትተወኝ
ሂድ ብልህም እቀፈኝ
ግና አለሜ እኔን ለህመሜ ተወኝ
እባክህ ግን እጄን አትልቀቀኝ


👆👆ጠቃሚ_መልእክት


አንድ ንጉስ አስር ተናካሽ ውሾች (Wild dogs) ነበሩት ፤ እነዚህን ውሾችም አገልጋዮቹን ‹አሽከሮቹን› ሲያጠፉ ለማሰቃየትና ለማስበላት ይጠቀምባቸዋል፡፡

ከእለታት አንድ ቀን አንደኛው አሽከሩ ትክክል ያልሆነ ሃሳብ ንጉሱን ተናገረው ፤ በዚህም ምክንያት ንጉሱ እጅግ ተቆጣበት ፤ ወዲውኑም ወደ ውሾቹ እንዲወረወር ትዕዛዝ አስተላለፈ፡፡

አሽከሩም በሀዘን "አስር አመታት አገለገልኩህ ፤ ተገዛውልህ ያልከኝን ሁሉ አደረኩልህ ፤ አሁን ግን ይህንን አደረክብኝ ፤ እባክህ ወደ ውሾች ውስጥ ከመወርወሬ በፊት አስር ቀን ስጠኝ" ብሎ ተማጸነው ንጉስም ተስማማ ‹ፈቀደለት› ፡፡

ይወረወር ዘንድ የተፈረደበት አሽከር ውሾቹን ወደሚንከባከበው ሌላኛው አሽከር ሔደና ‹እባክህ እነኝህን ውሾች ለአስር ቀን ልንከባከባቸው › ብሎ ጠየቀው፡፡ የውሾቹ ጠባቂም ግራ በመጋባት ሁኔታ ፈቀደለት ፡፡

የተፈቀደለት አሽከርም ውሾቹን መንከባከብ ጀመረ ፤ ቆሻሻቸውን ማጸዳዳት ፤ ምግባቸውን በሰአቱ ማቅረብ ፤ ማጠብና አስፈላጊውን እንክብካቤ ሁሉ አደረገላቸው ፤ አስር ቀኑም አለቀ፡፡

ከዚያም በኋላ ከንጉስ ጋር በተነጋገሩት መሰረት …አሽከሩ ተጠርቶ ወደ ተናካሽ ውሾቹ ዘንድ ይወረወር ዘንድ አዘዘ ፤ ወረወሩትም ፡፡ ወርዋሪዎቹም ይህ አሽከር እንዴት በውሾቹ ሊበላ እንደሚችል እየዘገነናቸው መመልከት እንደጀመሩ ያላሰቡትን ሁኔታ በአይናቸው አዬ ፤ ንጉሱም በሚመለከተው ሁኔታ ግራ ተጋባና «በእነዚህ ተናካሽ ውሾቼ ላይ ምን ደረሰ ? ምንስ ገጠማቸው?» ማለት እንደጀመረ… የተወረወረው አገልጋይ በውሾቹ መሃል እየተሻሼ በኩራት እየተራመደ እንዲህ አለ "እነዚህን ውሾች ለአስር ቀናቶች ብቻ መገብኳቸው ተንከባከብኳቸው እነርሱም ያደረኩላቸውን በፍጹም አልዘነጉም ፤ አንተን ግን አስር አመት ሙሉ ተገዛሁልህ አገለገልኩህ ነገር ግን በአንዲት ጥፋት ምክንያት ሁሉንም ረሳህና ለሞት አሳልፈህ ሰጠኸኝ" አለው ፡፡

ንጉሱም ሁኔታውን ሁሉ በማስተዋልና ፤ ከውሾች እንዳነሰም በመገንዘብ አገልጋዩ ነጻ እንዲሆን አዘዘ ፤ ነጻም ሆነ፡፡


  joinh አድርጉ ❤❤❤👍
የበለጠ ለማግኘት @eyetaye12 ተቀላቀሉ




😂አርጅታችሁ ጥርሳችሁ ከማለቁ በፊት ሳቁበት።😁

Join👉💕 @eyetaye12


እ ው ነ ተ ኛ   ደ ስ ታ

አንድ ባልና  ሚስት 25 ዓመታትን በትዳር ውስጥ ያለምንም ክርክር አሳልፈው አከበሩ። ሰዎች የዚህ ምስጥርን ለማወቅ ጠየቁት "በሁለታችሁ መካከል ያለምንም ልዩነት 25 አመት እንዴት አለፈ?"

ባልየውም፦ በመጀመሪያዎቹ የጫጉላ ሽርሽር ቀናቶች ወደ ገጠር ወጥተን ሁለታችንም ፈረስ እየጋለብን ነበር.. ፈረሱ ግን ሚስቴን ወደ መሬት ጣላት፤ ሚስቴም ተነስታ የፈረሱን ጭንቅላት ዳበሰችውና እንደዚህ አለችው "ይህ የመጀመሪያ ነው" ቀጥሎ በሁለተኛው ሙከራ ፈረሱ እኔን ጣለኝ፤ አሁንም አናቱ ላይ ዳበሰችውና "እናም ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ነው አለች" በሶስተኛው ሙከራም ወደቀች ሚስቴም ተረጋግታ ተነሳችና ቦርሳዋን ከፍታ ሽጉ ጥ አውጥታ የፈረሱን ጭንቅላት ላይ ተ ኩሳ ገደ ለችው።

ያየውትን ማመን ስላቃተኝ "ምንድነው ያደረግሽው አብደሻል እንዴ! ፈረሱን ለምን ገደልሽው?" ብዬ ጮውኩባት። ወደኔ ጋር መጥታ ዓይን ዓይኔን እየተመለከተች ጭንቅላቴን በእርጋታ ዳበሰችውና እንዲህ አለችኝ፦ "ናፍቀኸኛል እና ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው.."  ከዛ ቀን ጀምሮ በፍቅር፣ በሰላም፣ በደስታ እና በፍፁም መረጋጋት ውስጥ እንኖራለን። ለሁለተኛ ጊዜ አልደረስንም..😁

@eyetaye12 Share


እግር ጥሏችሁ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ብትደርሱ የዚህን ውሻ ሀውልት በአንድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ይህ ውሻ ለ10 አመታት ፍቅርን የሰበከ ታማኝነትን ያወጀ በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል ይወዱታል፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡  "Hachi: a dogs tale" በ2009 የተሰራው ፊልም ነው።

ይህ ውሻ ስሙ ሀቺኮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የፕሮፌሰር ኢዛቡሮን ውሻ ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩ ውሻውን በፍቅር አሳደጉት፡፡ ሁሌም ውሻው ጠዋት አብሮ ባቡር ጣቢያ ሄዶ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ይመለሳል ማታ 11 ሰዓት ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበለውና ቤት ድረስ አብሮ ይመጣል፡፡

ታድያ ከእለታት ሁሉ በአንዱ ከፉ ቀን በግንቦት 21 - 1923 ዓ.ም ውሻው ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ቢጠብቃቸው ሰውዬው ለካ በልብ ድካም ሞተው ኖሯል ሳይመጡ ቀሩ፡፡

ውሻው ግን ይመጣሉ ብሎ ፕሮፌሰሩን ጠበቀ 1 ቀን ብቻ አደለም ጥቂት ወራትም አደለም ድፍን 10 አመት እንጂ እሳቸውን ጥበቃ እዛችው ባቡር ጣቢያው ጋር 10 አመት ጠብቆ እዛው ሞተ፡፡ እናም ሀቺኮ ወዳጁን 10 አመት በፅናት መጠበቁ አያስደንቅም
?

😌ሀቺኮ

@eyetaye12


Nafkshngal😊


🤗


ከአድናቆት የምናገኘው ትምህርት ..🤔

ከአድካሚ ውሎ በኋላ አንድ ቀን ምሽት ላይ እናቴ ለቤተሰቡ እራት አዘጋጀች። ለአባቴ በጣም ያረረ ዳቦ የተጠበሰ እንቁላል እና ሰላጣ አቅርባለት ነበር ። የቀለበውን ምግብ ስለመለከት ትኩረቴን ወዲያውኑ ወደ ዳቦው አረፈ። አባቴ ሐዘን፣ ንዴት ወይም የብስጭት ስሜት ይሰማዋል ብዬ በማሰብ እራሴን አዘጋጀሁ።

የሚገርመው ግን ፈገግ ብሎ መብላት ጀመረ። እንቁላሉን በዳቦው ውስጥ በደስታ እየጠቀለለ ስለ ውሏችን ይጠይቀንና ያጫውተን ጀመር።

እናቴ ስላረረው ዳቦ ይቅርታ ስትጠይቅ አባቴ የሰጠውን ሞቅ ያለ ምላሽ ግን ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ- "ውዴ፣ ፍጹም ደህና ነው። የምወደው ዳቦ እንዲህ ሲያር ነው።"

የዚያን ዕለት ምሽት አልጋ ላይ ተኝቼ ሳለ አባቴ ሊይናግረኝ መጣ። የማወቅ ጉጉት ስላደረብኝ ስለ ዳቦው የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ጠየቅሁት ። እቅፍ አድርጎ ከጎተተኝ በኋላ እንዲህ አለኝ- "እናትህ ረጅም፣ አድካሚ ቀን አሳልፋለች፣ ነገር ግን ለኛ ምግብ ለማዘጋጀት ድካሟ አላገዳትም። ያረረ ዳቦ መብላት እሷ ካሳየችው ፍቅርና ጥረት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።"

በዚያች ቅጽበት፣ ስለ ምስጋና እና በትንሽ ነገሮች ውስጥ ያለውን ውበት ስለማየት ጠቃሚ ትምህርት ተማርኩኝ።

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏

@eyetaye12


21 ማህበራዊ ህግጋት  👌

1. ይሰለቹሃል 

አስሬ አትደውል፤ ሰዎች ጋር ከሁለቴ በላይ አይደወልም። ተሰልቺ ትሆናለህ!

2. ሼም ነው

የሚከፍለው ሌላ ሰው ነው ብለህ ከፍ ያለ ዋጋ ያለው ምግብና መጠጥ አትዘዝ!

3. አይባልም 

.. እንዴ እስካሁን አላገባሕም? ለምንድነው እስካሁን ያልወለድሽው? እንዴት ዲግሪሽን እስካሁን ሳትይዢና ሳትይዝ ወዘተ..." አይባልም።

4. ክፈል 

አብሮህ ላለው ሰው ታክሲ ላይም ሆነ የትም ቦታ አግባብ ነው ብለህ ስታምን ቀድመህ ክፈል። ገና ለገና ይከፍላል ብለህ ከሱ ስትጠብቅ ደምህን እያሯሯጥክ ትሰቃያለህ።

5. ነውር ነው 

ሰው እየበላም ይሁን በማንኛውም ሰዓት ከሰዎች ጋር ካለህ ጥርስህን አትጎርጉር፣ አፍንጫህንና ሌሎች ያልተገቡ ቦታዎችንም አትነካካ።

6. አታቋርጥ 

ግዴለህም አብሮህ ያለው ሰው አውርቶ ይጨርስ። ጥልቅ እያልክ አታቋርጥ።ከባሕልም ከስልጣኔም ውጪ ነው።

7. አታብሽቅ 

ሆን ብለህ የማናደድ ባሕሪ ካለህ ተው። ሰዎች ለመባል የማይወዱትን ተው።ሰዎች ብዙ የማይናገሩትና የተሸከሙት የራሳቸው ብሽቀት ስላለባቸው ለተሻለውና ለሚበረቱበት ሕይወታቸው አድናቆት ስጥ።

8. አመሥግን 

ለተደረገልህ ማንኛውም ቅንጣት ነገር አመሥግን።

9. ያለስስት አድንቅ 

ሰዎችን በይፋ አድንቃቸው፣ መልካም ያልሆነ ነገራቸውን ግን በግል አውራቸው።

10. ክፉ አስተያየትህን ቆጥብ 

ያልሆነ ነገር ብታይ እንኳን አፍህ በበጎ ቃላት ይቀይረው። ወፍሮ ያየኸውን ሰው ኤጭ ተዝረጠረጥክ ከማለት ተቆጠብ።

11. ካልሆኑ ጥያቄዎች ታቀብ 

ሰዎች የሕክምና ቀጠሮ ሄደው መምጣታቸውን ነግረውህ ይሆናል። የውጤቱን
ምንነት ለማወቅ ግን በጥልቀት አትጠይቅ። በነገሩህ ልክ መልካሙን ተመኝላቸው። በቻልከው መጠን በመረጃና በጥቆማ አግዛቸው እንጂ ድንበር አትዝለል።

12. ስነ-ስርዓት 

ሰዎች ከስልካቸው ላይ ፎቶ እንድታይ ቢሰጡህ ከፈቀዱልህ ውጪ ሌላ ፎቶ ካላየሁ ብለህ ስልክ አትፈትሽ። ሁሉም ሰው ታልፎ እንዲገባበት የማይፈልገው የራሱ አጥር አለው።

13. ክብር ለሁሉም 

ከላይ ጫፍ ላለ የሥራ ኃላፊና ከታች ዝቅ ባለ ስራ ላይ ለሚገኘው ሰው እኩል ክብር ስጥ። እንደውም ከላይ ካለው ይልቅ ታች ላለው ሰው የሰጠኸው ክብር ብዙ እውቅና አለው። ለንቀትህ ግን የማንንም አድናቆትና ጭብጨባ አታገኝም።

14. ስልክህን አስቀምጥ 

ሰዎች በቀጥታ ላንተ እያወሩ ስልክህን የምትነካካ ከሆነ ቀሽምነት ነው። ከሰው
ሰራሹ ይልቅ ራሱ ሰው ትልቅ ዋጋ አለው።

15. አድብ 

ሰዎች ካልጠየቁህና ካልፈቀዱልህ በስተቀር በራሳቸው ሕይወትና ሥራ ጣልቃ አትግባባቸው።

16. ተቆጠብ 

ከረጅም ጊዜ በኋላ ያገኘሃቸውን ሰዎች አስጨናቂ ጥያቄ አትጠይቃቸው። ሰዎች ቆይታቸውን እንዲሁም ዕድሜና ደሞዛቸውን ጨምሮ የመናገርና ያለመናገር ብቸኛ ባለመብት ራሳቸው እንደሆኑ እወቅ።

17. መነጽርህን አውልቅ 

ከሰዎች ጋር በዓይንህ አውራ። ከማንም ጋር በመንገድ ላይ ተገናኝተህ ስታወራ መነጽርህን ከዓይንህ ማንሳት እንዳለብህ አስታውስ። ክብርም ነው!

18. አትሳሳት 

በድኅነት አስተሳሰብ ሆነህ ስለሀብታሞች ምንነትና ማንነት አታውራ፤ ልጅ ሳይኖርህ ስለልጅና ልጅ ስላላቸው ሰዎች ባሕሪ አትፍረድ።

19. ለስልክ መልዕክት ምላሽ መስጠት 

በስልክህ የጽሑፍ መልዕክት ሲደርስህ አንብበህ ዝም ማለት ነውር ነው።ተገቢውን ምላሽ በበጎነት ቃል መመለስን ልማድህ አድርገው።

20. ዕቃ መልስ 

የወሰድከውን ማንኛውም ቁስ ባለቤቱ ሳይጠይቅህ በፊት ቶሎ መልስ።

21. አማራጭ ሐሳቦች ሁሌም አሉ 

የያዝከውን ሐሳብ ሳትፈራ አውጣው። አንተም ሐሳብህም ትጎለብታላችሁ።

ዶ/ር ምህረት ደበበ ✍️


Share Share Share @eyetaye12

20 last posts shown.