ሂዳያ መልቲሚዲያ | ʜɪᴅᴀʏᴀ ᴍᴜʟᴛɪᴍᴇᴅɪᴀ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Religion


- አንዳንድ ማስታወሻና ምክሮች
- ዳዕዋዎች እና ፈታዋዎች
- ምርጥ ግጥሞች
- አጫጭር የዳዕዋ ቪድዮዎች
- የተለያዩ ደርሶችና ታሪኮች
-ጥያቄና መልስ ፕሮግራሞች የሚጋሩበት የሆነ ቻናል ነው።
Join እና Share በማድረግ አጋርነታችሁን ግለፁ!!
🔘በተጨማሪም የዩቱብ ቻናላችን ይቀላቀሉ!
https://www.youtube.com/@hidaya_multi
🗳ለአስተያየት @annafiabot ይጠቀሙ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Religion
Statistics
Posts filter


ÄŠĒŁÄMÛ ÅĹËŸĶŰM WĖŘÊHMÊŤŮĻŁÁHÏ WĖBĒŘÊĶĀŤÛH

ቴሌግራም ገብተው ምንም አዲስ ነገር ለማግኘት ለመስማት ተቸግረዋል? ወይስ ፕሮፋይል ፎቶ ለመቀየር ተቸግረዋል?
እንግዲያውስ ኢሀው የፈለጉትን ቻናል ይዘን ቀርበናል

በማለት አባል ብቻ ይሁኑ




ሚስጢር (💎)


t.me/hidaya_multi


ሰለዋት እናብዛ !!!

ረሱል ﷺ :- "በጁሙዓ ሌሊትና ቀን በእኔ ላይ ሰለዋት ማድረግ አብዙ፤ የናንተ ሰለዋት እኔ ዘንድ ይቀርባልና" ብለዋል።

اللهم صلي على محمد وعلى آل محمد ،
كما صليت على إبراهم وعلى آل إبراهم ،إنّك حميدٌ مجيدٌ
اللهم بارك علي محمد وعلى آل محمد ،كما باركت على إبراهم وعلى آل إبراهم ،إنّك حميدٌ مجيدٌ


💎ገጠመኙን ሲተርክ እንዲ ይላል:-

❝ ወደ ስራ ስሄድ አንድ የስልክ እንጨት ላይ የተለጠፈ ወረቀት አየሁኝ: ጽሁፉ እንዲህ ይላል:-

" እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር ጠፍቶብኛል: ያገኘ ሰው ካለ እባካችህን አድራሻዬ በሚቀጥለው መንገድ በቀኝ በኩል ስትታጠፉ ያለው አሮጌ ቤት ነው:: አይኔ እንደፈለግኩኝ አያይም: እድሜዬም ገፍቷል: ልጆችም የሉኝም"

ይህንኑ ጽሁፍ ተከትዬ ወደ አሮጌው ቤት ስሄድ አንዲት ሴትዮ ደጃፍ ላይ ተቀምጠዋል: የእግር ኮቴየን ሰምተው "ማነው? ማን ልበል?" አሉኝ

"እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነው: እሱን ልሰጥ ነው የመጣሁት" ብዬ መለስኩላቸው

አሮጊቷ እንባ ቀደማቸው - "ልጄ! እስካሁን ድረስ ከ40 በላይ ሰዎች 50 ብር መንገድ ላይ ወድቆ አገኘን ብለውኝ መጥተዋል"

ቀጠሉ እማማ - "እኔ ይህንን ጽሁፍ አልጻፍኩኝም: ጽሁፍ ለመጻፍም ሆነ ለማንበብም አይኔ እሺ አይለኝም" 50 ብሩን በእጃቸው አስጨበጥኳቸው። ጽሁፉን ከስልክ እንጨቱ ላይ እንድቀደው ቢነግሩኝም አላደረግኩትም: የመጣውን ሰው ሁሉ ይህንኑ ነበር የሚሉት።

ይህንን ጽሁፍ የጻፈውን ሰው እንዴት እንዳደነቅኩት : እኚህን ሴትዮ ለመርዳት የሄደበት ርቀት በጣም ነው ያደነቅኩት!

ከሴትዮዋ ቤት ስወጣ አንዲት ወጣት ልጅ አስቆመቺኝና

"ወንድሜ! እዚህ መንገድ ላይ 50 ብር አግኝቼ ነበር: የቤቱ አቅጣጫ በየት በኩል እንደሆነ ታውቃለህ እንዴ?"

በልቤ እየሳቅኩኝ ቤቱን ጠቆምኳት❞

     ❤️መልካምነት ለራስ ነው❤️

t.me/hidaya_multi




🌴  የረጀብ  ዒባዳ🌴

ረጀብ መግባቱን አስመልክቶ የሚባሉ አንዳንድ ነጥቦችን ለማብራራት ያክል:

❝ ፆም ወደ አሏህ ከሚያቃርቡ ትልልቅ ዒባዳዎች መሀል አንዱ ነው።
ማንኛውም ዒባዳ ሁለት መሰረቶች አሉት ከነዚህ መሀል አንዱ ከጎደለ፣
በሸሪዓ ሚዛን ዒባዳ አይባልም!
አሏህ ዘንድም ተቀባይነት አያገኝም!

💥1ኛ/ ዒባዳውን ለአሏህ ብቻ ብሎ በኢኽላስ መስራት (ለይዩልኝና ለይስሙልኝ ሳይሆን)

💥2ኛ/ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸው የሰሩት ወይም ስሩት ብለው ያዘዙት፣ ወይም ሲሰራ አይተው ዝም ያሉት መሆን አለበት።
👉🏻 ከዚህ ውጪ ዒባዳ ሊባልና ወደ አሏህ ሊያቃርብ የሚችል ነገር የለም::

🔸 የረጀብን ጾም ነቢዩ ሙሐመድ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም እራሳቸውም አልጾሙም፣ ጹሙ ብለውም አላዘዙም ፣ሰሃቦችም አልጾሙትም::

💥በረጀብ ወር የሚሰሩ ምንም ዓይነት ልዩ ዒባዳዎች የሉም!

በዚህ ዙሪያ የሚሰራጩ ሐዲሦች በሙሉ ደዒፍና ነቢዩ ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም ላይ የተዋሹ መሆናቸውን 📂አል_ሓፊዝ ኢብኑ ሐጀርን ጨምሮ ሌሎችም የሐዲሥ ሊቃውንት  ገልጸዋል
ደጋግ ቀደምቶች፥ " ከናንተ በፊት ያለፉ ቅን ትውልዶችን መንገድ ተከተሉ አዲስን ነገር አትፍጠሩ " ይሉ ነበር
ዘወትር ሰኞና ሀሙስ ሌሎችንም የተለያዩ የሱና ጾሞችን የሚጾም ሰው ግን ረጅብም ላይ ይህ ስራው ላይ ቢቀጥል ምንም ችግር አይኖረውም
የሚከለከለው *ረጅብ ስለሆነ* ብቻ ተብሎ በጊዜያዊነት የሚሰራ ዒባዳ ብቻ ነው! ❞

✍ኡስታዝ አሕመድ ሼኽ ኣደም
ረጀብ 10/7/1439 ዓ.ሂ
@ዛዱል መዓድ




📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الثاني والأربعون

عن أنس بن مالك رضي الله عنه قال: سمعت رسول اللهﷺ يقول: «قال الله تعالى؛ يا ابن آدم! إنك ما دعوتني ورجوتني غفرت لك على ما كان منك ولا أبالي، يا ابن آدم! لو بلغت ذنوبك عنان السماء ثم استغفرتني، غفرت لك ولا أبالي، يا ابن آدم! لو أتيتني بقراب الأرض خطايا ثم لقيتني لا تشرك بي شيئا، لأتيتك بقرابها مغفرة.»

رواه الترمذي، وقال: حديث حسن صحيح

📘ሐዲስ ቁጥር 42

አነስ ኢብኑ ማሊክ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና; የአላህን መልእክተኛ ﷺእንዲህ ሲሉ ሰምቻለሁ ብለዋል; «አላህ እንዲህ ብሏል፦ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! አንተ እኔን (ማረኝ ብለክ)እስከለመንክና (ምህረትን) ከኔ እስከከጀልክ ድረስ ወንጀልክ ምንም ያክል ቢሆን እምርካለሁ ምንም አይጨንቀኝም፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ወንጀልክ የሠማይ ጣራ ቢደርስና ማረኝ ብትለኝ እምርልካለሁ ምንም አይጨንቀኝም፤ አንተ የአደም ልጅ ሆይ! ዱንያን ሊሞላ በሚቀርብ ወንጀል እኔ ጋር ብትመጣና በኔ ላይ ሳታጋራ ብትገናኘኝ እኔም እሷን(ምድርን) ሊሞላ በሚቀርብ ምህረት እመጣልካለሁ።»

ቲርሚዚይ ዘግበውታል፥ ሐዲሱን ሐሠንም ሶሂህም ብለውታል።

🧷ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍ኢስቲግፋር የሚደረገው ወደ አላህ መሆኑን

📍የአላህን ምህረተ ሰፊነት ምንም ወንጀል ቢሆን እምራለሁ ስላለ

📍ኢስቲግፋር ማድረግ እንደሚገባ

📍የተውሂድን ደረጃ፦ ካላጋራክ ምድርን ሚሞላ ወንጀል ብትሰራ እምርካለሁ ስላለ

📍ሺርክ የማይማር ወንጀል መሆኑን(በሱ ላይ ከሞተ)

📍ዱዓእና ረጃእ(ከአላህ መከጀል)ኢባዳ መሆናቸውን


والله أعلم

تم بحمد لله

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الحادي والأربون

عن أبي محمد عبد الله بن عمرو بن العاص رضي الله عنهما قال: قال رسول اللهﷺ: «لا يؤمن أحدكم حتى يكون هواه تبعا لما جئت به.»حديث حسن صحيح، رويناه في كتاب: الحجة بإسناد صحيح

📗ሐዲስ ቁጥር 41

አቡ ሙሐመድ ዐብዲላህ ኢብኑ ዓምር ኢብኑል ዓስ አላህ ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ ብለዋል; የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል; «አንዳችሁ ስሜቱ እኔ ለመጣሁበት ነገር ተከታይ እስካልሆነ ድረስ አላመነም።»

ሐዲሡ ሀሠንም ሶሂህም ነው፥ አል ሁጀህ ላይ ሶሂህ በሆነ ሰነድ ዘግበነዋል።

📌ማስታወሻ

አላመነም ሲባል፦ ኢማኑ አይሟላም ይጎላል(ይቀንሳል) ለማለት ነው


📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍መልእክተኛው ይዘውት ለመጡት ነገር ተከታይ መሆን ግዴታ መሆኑን

📍መልእክተኛው ይዘውት የመጡትን ነገር  መቃረን ሐራም መሆኑን እና ኢማንን እንደሚያጎድል

📍ኢማን የተሟላ የሚሆነው ነቢዩን በመከተል መሆኑን

📍ኢማን እንደሚጨምርና እንደሚቀንስ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الأربعون

عن ابن عمر رضي الله عنهما قال: أخذ رسول الله بمنكبي، وقال: «كن في الدنيا كأنك غريب، أو عابر سبيل.»

وكان ابن عمر رضي الله عنهما يقول: «إذا أمسيت فلا تنتظر الصباح، وإذا أصبحت فلا تنتظر المساء، وخذ من صحتك لمرضك، ومن حياتك لموتك.» رواه البخاري.

📕ሐዲስ ቁጥር 40

ኢብኑ ዑመር አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና እንዲህ አሉ; የአላህ መልእክተኛﷺ ትከሻዬን ያዙኝና እንዲህ አሉኝ; «ዱንያ ውስጥ ልክ እንደ እንግዳ፥ ወይም መንገደኛ ሁን»

ኢብኑ ዑመር እንዲህ ይሉ ነበር; «ስታመሽ ንጋትን አትጠባበቅ፤ ስታነጋ ምሽትን አትጠባበቅ፤ በጤንነትክ ለህመምክ የሚሆንክን ያዝ፤ በህይወትክ ለሞትክ የሚሆንክን ያዝ።»

ቡኻሪ ዘግበውታል።

🔗ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነግሮች

📍ነቢዩ ትከሻውን መያዛቸው፥ ለሚነግሩት ነገር ትኩረት እንዲሰጥ ነው፦ ይህ ደግሞ አንድ አስተማሪ ተማሪዎቹ ለትምህርቱ ትኩረት እንዲሰጡ መጨነቅና ሰበቦችን ማድረስ እንደሚገባው እንይዛለን

📍እንደ እንግዳ ሁን ማለት፦ እንግድነት የሄድክበት ቤት እንደማትዘወትረውና እንደፈለክ እንደማትሆነው፥ ዱንያ ላይም እንደማትዘወትር እና ያንተ እንዳልሆነች እወቅ ማለት ሲሆን;

📍እንደ መንገደኛ ሁን ማለት ደግሞ፦ ይልቁንስ ዱንያ ምትረማመድባት መንገድ አርገህ ያዛት ማለት ነው።

📍ከዐብዲላህ ኢብኑ ዑመር ንግግር ደግሞ፦ 1. ዱንያ ላይ ምኞትን ማስረዘም እንደማይገባ
            2. የአኸራ ስራን ነገ ከነገ ወዲያ እሰራለሁ እያሉ ማዘግየት እንደማይገባ
           3. ኸይር ስራን ለመስራት አመቺ የሆነባቸውን ሰአታትና ሁኔታዎች ሳይልፉን ልንጠቀምባቸው እንደሚገባ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ማክሰኞ | ታህሳስ 22/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ






📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث التاسع والثلاثون

عن ابن عباس رضي الله عنهما - أن رسول الله ﷺ قال: «إن الله تجاوز لي عن أمتي الخطأ والنسيان وما استكرهوا عليه.» حديث حسن رواه ابن ماجة، والبيهقي في السنن، وغيرهما.

📔ሐዲስ ቁጥር 39

ከኢብኑ ዓባስ አላህ መልካም ስራቸውን ይውደድላቸውና; የአላህ መልእክተኛ እንዲህ ብለዋል; «አላህ ለኔ ከህዝቦቼ ተሳስተው፤ ረስተውና ተገደው የሚሰሩትን ወንጀል ምሮልኛል።»

ሐዲሱ ሀሠን ነው። ኢብኑ ማጃህ: በይሀቂይ ሱነናቸው ላይ: እና ሌሎችም ዘግበውታል።

🖇ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍አላህ ለነቢዩ የዋለውን ውለታ

📍የነቢዩ ኡመት የታዘነለት ኡመት መሆኑን

📍የሰው ልጅ ተሳስቶ፣ ረስቶና ተገድዶ በሚሰራው ነገር እንደማይጠየቅ

📍የአላህ እዝነት ሰፊ መሆኑን


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ረቡዕ | ህዳር 2/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث الثامن والثلاثون

عن أبي هريرة رضي الله عنه قال: قال رسول اللهﷺ: إن الله تعلى قال: « من عادى لي وليا فقد آذنته بالحرب، وما تقرب إلي عبدي بشيئ أحب إلي، مما افترضته عليه، ولا يزال عبدي يتقرب إلي بالنوافل حتى أحبه، فإذا أحببته، كنت سمعه الذي يسمع به، وبصره الذي يبصر به، ويده التي يبطش بها، ورجله التي يمشي بها، ولئن سألني لأعطينه، ولئن استعاذني لأعيذنه. »رواه البخاري

📓ሐዲስ ቁጥር 38

አቡ ሁረይራህ እንዲህ ብለዋል; የአላህ መልእክተኛ ﷺእንዲህ ብለዋል; «አላህ እንዲህ ብሏል; ❝የኔን ወዳጅ ጠላት አርጎ የያዘ፥ በሱ ላይ ጦርነትን አውጄበታለሁ፤ ባሪያዬ እኔ ዘንድ የተወደደ በሆነ ባንዳችም ነገር ወደኔ አይቀርብም፥ ግዴታ ያረኩበትን ነገር በመፈፀም ቢሆን እንጂ፤ ባሪያዬ ሱና ዒባዳዎችን በመፈፀም ወደኔ ከመቃረብ አይወገድም፥ እኔ ብወደው እንጂ፤ እኔ ከወደድኩት፥ መስሚያ ጆሮው፤ የሚያይበት አይኑ፤ የሚሰራበት እጁ፤ የሚሄድበት እግሩ እሆንለታለሁ፤ ቢጠይቀኝ እሰጠዋለሁ፤ ጥበቃዬን ቢፈልግ እጠብቀዋለሁ።❞»ቡኻሪ ዘግበውታል።

📌ማስታወሻ

- ጆሮው፣ አይኑ፣ እጁ፣ እግሩ እሆነዋለሁ ማለት፦ በነዚህ አካላት ኸይርን እንጂ ሌላ ነገር እንዳይሰራ አደርገዋለሁ ማለት ነው።

-ወሊይ(የአላህ ወዳጅ) የሚባለው፦ ማንኛውም አማኝ የሆነና አላህን የሚፈራ ሰው ነው።


📎ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍የአላህ ወዳጆች ያላቸው ደረጃና እነሱን ጠላት አርጎ መያዝ ያለውን አደጋ

📍ግዴታ ዒባዳዎች ከምንም እንደሚበልጡና ወደ አላህ እንደሚያቃርቡ

📍ሱና ዒባዳዎች የአላህን ውዴታ እንደሚያስገኙ

📍አላህ ለወደደው ባሪያው ምን እንደሚያደርግለት

📍አንድ ሰው አላህ እንደወደደውና እንዳልወደደው በምን እንደሚያውቅ



والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ሰኞ | ህዳር 30/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ


اصبر فوالله إن الله أرحم بك من نفسك، والله سبحانه وتعلى لا يمكن أن يبتليك بشر إلا لحكمة منه،

إذًا الله عز وجل من رحمته ما يجعل حياتك كلها بلاء. إن أخذ منك الشيء أعطاك أشياء أخرى. لا يمكن، هذا هو من رحمة الله، ولذالك...
قال النبي ﷺ: « إنَّ عِظَمَ الجَزَاءِ مَعَ عِظَمِ الْبَلَاءِ، وَإنَّ اللهَ إذَا أَحَبَّ قَومًا ابتِلاهُم، فَمَن رَضِيَ فَلَهُ الرِّضا، وَمَن سخِطَ فَلَهُ السُّخْطُ »
أخرجه الترمذي، وابن ماجه

ታገስ! አላህ ላንተ ካንተ ነፍስ የበለጠ አዛኝ ነው። አላህም አንተን በመጥፎ አይፈትንህም ለጥበብ ቢሆን እንጂ።

አላህ በእዝነቱ ሙሉ ሀያትህን በላእ አያደርግብህም። የሆነ ነገርን ቢይዝብተህ(ቢወስድብህ) ብዙ ነገራትን ሰጥቶሀል(ትቶልሀል)። ለዚህም ሲባል ነብዩ ﷺ እነዲህ አሉ: ❝የአጅር መብዛቱ ከበላእ መብዛቱ ነው። አላህ የሆኑ ሰዎችን በወደዳቸው ጊዜ ይፈትናቸዋል። ወዶ የተቀበለ(ሰብር ያደረገ)ለሱ የአላህ ውዴታ አለቀለት። የተቆጣ(ያማረረ) ደግሞ ለሱ የአላህ ቁጣ አለበት።❞

ቲርሚዚይና ኢብኑ ማጃ ዘግበውታል

@hidaya_multi


እነሆ ዲመሽቅ ተከፍታለች‼

ታሪካዊ ቀን‼

አንዱና ዋነኛው የዐረብ አብዮት ውጤት‼

🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾🇸🇾

أيتها الأمة العظيمة.... الليلة فُتحت دمشق

2024/12/8.

من ثمر ربيع العربي

በመጨረሻው ዘመን ሃገረ ሻም የኢስላምና የሙስሊሞች መሸሸጊያ ትሆናለች‼

አቢ ኡማማህ (አላህ መልካም ሥራውን ይውደድለትና) ውዱን ነቢይ ﷺ ስለ ኑብዋቸው አጀማመር ሲጠይቃቸው «የአባቴ የኢብራሂም ዱዓእ፣ የዒሳ ብስራት (ነኝ)። እናቴ የሻምን ግንቦች ያበራ ኑር ከርሷ ሲወጣ አይታለች።» አሉ።

[ሲልሲለቱ-ል-አሓዲሢ-ስ'ሶሒሓህ: 1545]


ኢብኑ ከሢር በተፍሲራቸው ላይ «በኑራቸው መታየት ሻምን ለብቻ ለይተው መጥቀሳቸው፤ በሻም ምድር ላይ ዲናቸውና ነቢይነታቸው ዘውታሪ ሆኖ እንደሚቀጥል ማሳያ ነው!
ለዚህም ሲባል ሻም በመጨረሻው ዘመን የኢስላምና ባለቤቶቹ መሸሸጊያ ትሆናለች። በርሷም ውስጥ የመርየም ልጅ ዒሳ ይወርዳል። (ደጃልንም ይገድላል!)» ብለዋል።

[ተፍሲር ኢብኑ ከሢር: 1/444]

وعن أبي أمامة رضي الله عنه قال: قلت : يا نبي
الله! ما كان أوّل بدء أمرك؟ قال: "دعوة أبي إبراهيم، وبشرى عيسى، ورأت أُمّي أنه يخرج منها نور أضاءت منها قصور الشام"

قال ابن كثير رحمه الله : "وتخصيص الشام بظهور نوره : إشارة إلى استقرار دينه، ونبوته ببلاد الشام .
ولهذا تكون الشام في آخر الزمان معقلاً للإسلام وأهله، وبها ينزل عيسى ابن مريم" انتهى .


© Murad Tadese

https://t.me/hidaya_multi

🤲አላህ ለሙስሊሞችናቸዉ ለሙስሊም ሀገራት ድልን ይወፍቃቸው!


🔷መሰል መልእቶች ለማግኘት ተ🀄️ላ🀄️ሉ

📢 t.me/hidaya_multi

🔕 𝔧𝔬𝔦𝔫 𝔞𝔫𝔡 𝔲𝔫𝔪𝔲𝔱𝔢


📚#የሀዲስ_ትምህርት

📖الحديث السابع والثلاثون

عن ابن عباس - عن رسول الله - فيما يرويه عن ربه تبارك وتعلى قال: «إن الله كتب الحسنات والسيئات، ثم بين ذلك، فمن هم بحسنة فلم يعملها، كتبها الله عنده حسنة كاملة، وإن هم بها فعملها، كتبها الله عنده عشر حسنات إلى سبع مئة ضعف، إلى أضعاف كثيرة، وإن هم بسيئة فلم يعملها، كتبها الله عنده حسنة كاملة، وإن هم بها فعملها، كتبها الله عنده سيئة واحدة.» رواه البخاري ومسلم في صحيحيهما بهذه الحروف.

📘ሐዲስ ቁጥር 37

ከኢብኑ ዓባስ እንደተላለፈው; የአላህ መልእክተኛﷺ ከጌታቸው በሚዘግቡት ነገር(ሐዲስ አል ቁድስ) ውስጥ; አላህ እንዲህ ብሏል; «አላህ መልካም እና መጥፎ ስራዎችን(ከምንዳቸው ጋር) ደንግጓል፤ ከዛም ይህን ተናግሯል፤ መልካምን ለመስራት ያሰበና የወሰነ ከዛም ያልሰራው፥ አላህ እሱ ዘንድ የተሟላ አጅርን ይፅፍለታል፤ እሷን(መልካም ስራን ለመስራት) ወስኖ የሰራት፥ አላህ እሱ ዘንድ ከ10 - 700 እጥፍ ከዛም በላይ(አጅሩን) ያበዛለታል፤ መጥፎ ስራን ለመስራት ያሰበና የወሰነ ከዛም ያልሰራው፥ አላህ እሱ ዘንድ የተሟላ አጅርን ይፅፍለታል፤ እሷን(መጥፎ ስራን ለመስራት) ወስኖ የሰራት፥ አላህ እሱ ዘንድ አንድ ወንጀል ይፅፍበታል።»

ቡኻሪና ሙስሊም ሶሒሓቸው ላይ በዚህ መልኩ ዘግበውታል።


📌ማስታወሻ

- መልካምን ለመስራት ወስኖ ያልሰራ ሲባል፦ በዑዝር ምክንያት ለማለት እንጂ ሐሣብ ቀይሮ ማለት አይደለም

- መጥፎን ለመስራት ወስኖ ያልሰራ ሲባል፦ አላህን በመፍራት ከተወው እንጂ ስላልተመቻቸለት ያልሰራ አይደለም

🔗ከሐዲሱ የምንይዛቸው ቁምነገሮች

📍መልካምና መጥፎ ስራዎች(ከነ ምንዳቸው) የተፃፉ መሆናቸውን

📍የኒያን ደረጃ፦ አንድ ሰው መልካምን ለመስራት አስቦና ወስኖ በዑዝር ምክንያት መስራት ባይችል በኒያው አንድ አጅር ስለሚፃፍለት

📍ወንጀልን ለአላህ በሎ መተው ምንዳን እንደሚያስገኝ

📍አላህ ችሮታው ሰፊ መሆኑን፥ መልካም ስራ ስንሰራ እጥፍ አርጎ መክፈሉ።

📍መልካም ስራ ያለውን ደረጃ

📍የአላህን እዝነት፦ ወንጀልን የሰራ ሰው በአንድ ብቻ መፃፉ


والله أعلم

© ሂዳያ መልቲሚዲያ

🗓 ጁሙዓ | ህዳር 27/2017

♡     ⎙ ㅤ ⌲         🔕           📢
ˡⁱᵏᵉ  ˢᵃᵛᵉ   ˢʰᵃʳᵉ    ᵘⁿᵐᵘᵗᵉ    ᶜʰᵃⁿⁿᵉˡ



20 last posts shown.