➠ ሸዋልን አስመልክቶ አጠር ያሉ አህካሞች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
⓵ ከአቢ አዩብ አል'አንሳሪይ ረዲየሏሁ ዓንህ ተይዞ ነብዩ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
مَنْ صَامَ رَمَضَانَ ثُمَّ أَتْبَعَهُ سِتًّا مِنْ شَوَّالٍ كَانَ كَصِيَامِ الدَّهْرِ
“ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለው አመት እንደመፆም ነው።” [ሙስሊም፡ 1164]
⓶ ከሸዋል ስድስት ቀን መፆሙ ትሩፋቱ ምንድነው ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- እንዲህ አሉ : ❝ረመዷንን ፁሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ማስከተል ልክ አመት እንደመፆም ነዉ❞
📂الفتاوى ❪٢٠/١٧❫.
⓷ ከሸዋል ወር ስድስቱን ቀናት መፆም ሴቶችንም ወንዶችንም ያጠቃልላል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝አዉ ሴቶችንም ወንዶችንም ያጠቃልላል❞
⓸ ረመዷን ላይ የነበረበትን ቀዷ (ዕዳ) ሳይፆም የሸዋልን ስድስቱን ቀን የፆመ ሰዉ የሸዋል አጅር ይኖረዋል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- ❝የሸዋልን ስድስት ቀን ፆም አጅር ረመዳንን ጨርሶ ቀዷ ሳይኖርበት የቀጠለ እንጂ ቀዷዉን ትቶ የፆመ አጅሩን አያገኝም❞ (የሸይኽ ኢብኑ ባዝ አቋምም ነዉ)
📂الفتاوى ❪١٨/٢٠❫.
- ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ ረሂመሁላህ ደግሞ ይቻላል ብለዋል ❝በረመዳን ያፈጠረባቸውን (ያልፆመባቸውን) ቀናት ቀዷእ ካወጣ በኋላ ከዚያም ስድስቱን ከፆመ ይሄ መልካም ነው። ይህንንም ያንንም ማድረግ የማይችል ከሆነ ግን ነብዩ ﷺ “ረመዳንን ፆሞ ከዚያም ከሸዋል ስድስት ያስከተለ ልክ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ነው” ያሏትን ስድስቷን (አስቀድሞ) ሊፆም ይችላል። ለምን ይህን አልን? ምክንያቱም የቀዷው ጊዜ ከስድስቷ ፆም በተለየ (ወቅቱ) ሰፊ ስለሆነ ነው። (ስድስቷ ግን) ከሸዋል ውጭ ጊዜ የላትም። የቀዷእ ወቅት ግን ከዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ እንደመጣው እንዲህ ብላለች፡ ‘በሸዕባን (ወር) እንጂ ቀዷየን አላወጣም ነበር።’ ምክንያቱም በአላህ መልእክተኛ ﷺ ጉዳይ ትጠመድ ስለነበር ነው።❞
➦ የብዙሀን ኡለማዖች ፈትዋ የሚያመለክተዉ ግን መፆም እንደሚቻል ነዉ። ከቀዷ አስቀድሞ ሸዋልን መፆም ይቻላል።
⓹ የሸዋል ስድስቱ ቀን እንዴት ነዉ የሚፆመዉ ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ ሙዕሚኑ ከሸዋል ሙሉ ወር (ከ30 ቀኑ) ዉስጥ የፈለገዉን ይመርጣል፣ ከፈለገ ከመጀመሪያው አንስቶ ይፆማል፣ ከፈለገ ከመሀከል ይቀጥላል፣ ከፈለገ ከመጨረሻ አከባቢ ይፆማል፣ ከፈለገ ነጣጥሎ ወይም ቀጣጥሎ መፆም ይችላሉ❞
📂الفتاوى ❪٣٩٠/١٥❫
➅ የሸዋል ስድስቱ ቀናት አጿጿም አስመልክቶ በላጩ ምንድነው ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ አከታትሎ ከወሩ መጀመሪያ አንስቶ መፆሙ በላጭ ነዉ❞
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- ❝ የሸዋል ስድስቱ ቀናት አጿጿም አስመልክቶ በላጩ ከዒድ በኋላ እና በማከታተል መፆም ነዉ❞
📂الفتاوى ❪٢٠/٢٠❫.
⓻ የሸዋልን ስድስት ቀን የፆመ ሰዉ በየ አመቱ በቋሚነት የሸዋልን ስድስት ቀን መፆም ዋጂብ (ግዴታ) ይሆንበታል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ ከአመታት በኋላ እየፆመ በሌላ አመት ከተወም ችግር የለዉም ሱና እንጂ ዋጂብ አይደለም።❞
📂الفتاوى ❪٢١/٢٠❫.
➇ የሸዋልን ስድስቱን ቀን የሚፆም ሰዉ ግዴታ ኒያዉን ለሊት ላይ ማሳደር(መነየት) አለበት ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ ፆሙ እንዲሟላ ግዴታ ከፈጅር በፊት ግዴታ መነየት አለበት❞
📂الفتاوى ❪١٨٤/١٩❫.
➈ የሸዋልን ፆም ቢድዓ ነዉ ሚባለዉ ልክ ነዉ ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ይሄ ዉድቅ ንግግር ነዉ(ቢድዓ ፈፅሞ አይደለም)።
📂الفتاوى ❪٣٨٩/١٦❫
⓾ የሸዋልን ስድስት ቀን ከ-ከፋራ (ማሳበሻ) ቅጣት ፆም አስቀድሞ መፆም ይቻላል ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ ግዴታዉ ከፋራን አስቀድሞ መፆም ነዉ። ከፋራ ሳይፆም ሸዋልን መፆም አይቻልም። ምክንያት ሸዋል ሱና ነዉ ከፋራ ዋጂብ ነዉ፣ በአስቸኳይ መሆንም አለበት።❞
📂الفتاوى ❪٣٩٤/١٥❫.
⓵⓵ የቀዷን ፆም ከጨረሱ በኋላ ከሸዋል ፆም ጋር አከታትሎ (ቀጥሎ) መፆም ይቻላል ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ ትክክለኛዉ አቋም እንደሚቻል (ችግር እንደሌለዉ) ነዉ❞
📂الفتاوى ❪٣٩٦/١٥❫.
⓵⓶ የሸዋል ስድስት ቀን ያመለጠዉ ሰዉ በዙል ቂዕዳ ወር የሸዋልን ስድስቷን ቀን ቀዷ ማዉጣት ይችላል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- ❝ ለምሳሌ አንድ ሰዉ ሙሉ የረመዳን (30 ቀን) ቀዷ ካለበት ፣ በመንገድ ጉዞ ምክንያት ወይም በ ኒፋስ ምክንያት ሙሉ ቀዷ አለበት ካልን ከዛ ይህ ሰዉ ቀዷዉን ሙሉ በሸዋል ወር አወጣና የሸዋል ስድስቱ ቀን ካመለጠዉ የዛኔ በዙል ቂዕዳ ወር የሸዋልን ስድስቷን ቀን ቀዷ ማዉጣት ይችላል።
➦ ነገር ግን በችላ ባይነት ቀዷ ሳያወጣ ዘግይቶ ከዛ በሸዋል ወር ያለበትን የረመዳን ቀዷ አዉጥቶ ሸዋልን ስድስቷን በዙል ቂዕዳ አወጣለዉ ካለ አያብቃቃዉም(አይሆንም)።
📂لقاءات الباب المفتوح لقاء ❪١١٧❫
⓵⓷ የስለት ፆም ይቀድማል ወይስ ሸዋል ስድስቱን መፆም ?
➦ ሸይኽ አብዱል ዓዚዝ ኢብኑ ባዝ -ረሂመሁላህ- ❝ በመጀመሪያ የስለት ፆም ይቀድማል ከዛን ስድስቷን ሸዋል ከተቻለ። ምክንያቱም ሸዋል ሱና ነዉ የስለት ፆም ግዴታ ነዉ
📂موقع الشيخ
⓵⓸ ሱና የሆነ ፆም ኒያን ሳያስቀድሙ መፆም ይቻላል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ የሸዋልን ስድስት ቀን የሚፆም ሰዉ ከፈጅር በፊት ትቶ ከዙህር በኋላ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ኒያዉን ከነየተ ቀን ሙሉ እንደፆመ አይፃፍለትም።ለምሳሌ የመጀመሪያዉን ቀን ፆም ከነጋ በኋላ ነይቶ ፆሞ ከዛ አምስቱን ቀን በትክክል ከፆም ይህ ሰዉ ስድስቱን ቀን ፆመ አይባልም። ምክንያቱም አምስት ቀን ከግማሽ ነዉ የፆመዉ። ማስረጃዉም የነቢያችን (ﷺ) ኒያን አስመልክቶ የተናገሩት ሀዲስ ነዉ።
*📂فتاوى نور على الدرب ش ❪٢٩٦❫
⓵⓹ ሸዋልን መፆም ሂክማዉ ምንድነዉ ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ ከፆም የተጓደለብንን ለማሟላት ነዉ። ስድስቱ የሸዋል ሱና ፆም ማለት ልክ ከዋጂብ ሰላት በኋላ እንደምንሰግዳቸዉ ሱናዎች ነዉ፤ የተጓደለብንን ይሞሉልናል (ከአጅሩ በተጨማሪ)።
📂فتاوى نور على الدرب شريط ❪٧٥❫
⓵⓺ ከሸዋል ስድስቱ ቀን መካከል ሶስት ብቻ ወይም አራት ብቻ የፆመ (ያላሟላ) አጅር ይኖረዋል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ አዎን ይኖረዋል ግን ሀዲሱ ያመለከተዉን ያክል አይደለም። ረሱል (ﷺ) አመት እንደፆመ ይቆጠራል ባሉት ሀዲስ ስር አይገባም ግን አጅር አለዉ❞
⓵⓻ የሸዋልን ስድስት ቀናት ከ ሰኞ እና ሀሙስ ፆም ጋር በአንድ ኒያ አቆራኝቶ መፆም ይቻላል ?
➦ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን -ረሂመሁላህ- : ❝ ቀናቱ ከተጋጠሙለት ይቻላል። ሸዋልንም ነይቶ የሰኞ ወይም የሀሙስ ቀንን ፆም ነይቶ አንድ ላይ ቢፆም የሁለቱንም አጅር ያገኛል❞
📂الفتاوى ❪٢٠/ ١٨-١٩❫
የፈትዋ መመለሻዎች :
➠ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ ረሂመሁላህ
➠ ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚን ረሂመሁላህ
➠ ሸይኽ ሙቅቢል አል'ዋዲዒይ ረሂመሁላህ
ሰፊ ማብራሪይ በዚህ ሊንክ :
https://t.me/IbnuMunewor/5630
𝐓𝐞𝐥𝐞𝐠𝐫𝐚𝐦 : https://t.me/hidaya_multi