ጃዋር ሙሐመድ ስለ ሒጃብ ክልከላ ገጠመኙን በዚህ መልኩ በመጽሐፉ ላይ አስፍሮታል‼
=====================================
(የሒጃብ ጉዳይ የማይገባቸውን ድንዙዛን በዚህ መልኩ ማስረዳት ሳይጠበቅብን አይቀርም!)
||
✍ «… የሀይማኖት ተጽዕኖ መኖሩን ለመጀመሪያ ጊዜ የተረዳሁት አዳማ በምማርበት ወቅት ነበር። አንድ ቀን ትምህርት ቤት በር ላይ ስደርሰ መግቢያው ፊትለፊት ቆመው የሚያለቅሱ ሴቶችን ስላየሁ በድንጋጤ ምን እንደሆኑ ጠየኳቸው።
«ሂጃብ ካላወለቃችሁ አትገቡም አሉን» በማለት ነገሩኝ። «እናንተ ብታወልቁ ምን ችግር አለው?» ስላቸው፤ ሀይማኖታችን ይከለክለናል አሉኝ። በወቅቱ የሂጃብን አሰፈለጊነት ሰለማላውቅ ነበር የጠየኩት።
እስከማሰታውሰው ድረስ ባደኩበት አካባቢ አንዲት ሴት ጸጉሯን የምትሸፍነው ማግባቷን ለማሳየት ነው። ያላገባች ሴት ጸጉሯን አትሸፍንም፡
ሹሩባ ተሰርታ፣ ጸጉሯን አያዘናፈለች፡ የወጣቱን ልብ አያሸበረች ትሄዳለች። ስታገባ ራሷ ላይ ሻሽ ጣል ማድረግ ትጀምራለች፡ ልጆች ወልዳ ዕድሜዋ ሲገፋ ደግሞ ጉፍታ የሚባል ታስራለች። ያገባች እና ያላገባች ሴት መለየት የሚቻለው ጸጉሯን በመሸፈኗ እና ባለመሸፈኗ ነው።
የተማሪዎቹን ቅሬታ እና ሂጃብ ማውለቅ የማይችሉበችትን ሰበብ ከተረዳሁ በኋላ የትምህርት ቤቱየዲሲፕሊን ኃላፊ ጋር ሄጄ «ለምን አታስገቧቸውም? የሀይማኖት መብት ለምን ትጋፋላችሁን?› ስለው፡ «ከትምህርት
ቢሮ የመጣ መመሪያ አንጂ የትምህርት ቤቱ ውሳኔ አይደለም» አለኝ። ወደ ዳይሬክተሩ ሰሄድም ተመሳሳይ መልስ አገኘሁ። ወንድ እንደመሆኔ የሂጃብ ክልከላው በቀጥታ ባይጎዳኝም በሴት ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና በጣም አሳዘነኝ።
መታገል አለብኝ ብዬ ወሰንኩ። ከግቢ ውጪ ወዳሉት ሴት ተማሪዎች ተመልሼ «ነገ ሌሎቹንም ጨምራችሁ ሁላችሁም ሻሽ አድርጋችሁ በተመሳሳይ ሰዓት ኑ» አልኳቸው። በዕረፍት ሰዓት ሻሸ የማይለብሱ ወይም አውልቀው የገቡ ሴቶችን
ሰብሰቤ አወያየሁ። ክርስቲያን የሆኑትም ከሙስሊም አሀቶቻቸው ጋር ለመተባበር በማግሰቱ ሻሽ አስረው መምጣት
እንደሚችሉ ተወያይተው ወሰኑ። ወንድ ተማሪዎች በፊናችን ሴቶቹ እስከሚገቡ ድረሰ ውጪ ቆመን ባለመግባት
ትብብር ለማሳየት ተስማማን።
በማግስቱ እንዳቀድነው ብዙ ሴት ተማሪዎች ጸጉራቸውን ተሸፋፍነው በመምጣት አውልቁ ሲባሉ አሻፈረኝ በማለታቸው መግባት ተከልክለው ውጪ ላይ ቆሙ። ወንዶቹም ከአነሱ ጀርባ ቆመን«አናንተ እለፉና ግቡ ስንባል ሴቶቹ ካልገቡ አንገባም አልን። ለተቃውሞው ተዘጋጅተው የመጡ ብቻ ሳይሆኑ ቦታው ላይ የሰሙ ተማሪዎችም
መግባቱን ትተው ተቀለላቀሉን። እኛን ለማናደድ እና ሰሜት ውስጥ ለማስገባት በሚመስል መልኩ የግቢው ጥበቃ ባለፈው ከተማሪዎቹ የሰበሰበውን ሻሽ ማቃጠል ጀመረ። ተማሪዎቹ ሰሜት ውስጥ አንዳይገቡ አረጋግተን ዓላማውን አከሸፍነው።
በሩ ላይ ግርግር በዝቶ ፓሊሶች ተጠርተው ሲመጡ ሄጄ ያለውን ነገር አሰረዳኋቸው። ምንም ዓይነት ፀብ እንደማንፈልግና ያለንን ቅሬታ በሰላማዊ መንገድ ብቻ እንደምናቀርብ ቃል ገብቼ አሳመንኳቸው። አዚያ የነበረው ፖሊስ አዛዥ ረብሻ ፈጥራችሁ በሰው እና በንብረት ላይ ጉዳት አሰካላደረሳችሁ ድረስ አንነካችሁምን በማለት ፓሊሶች ከእኛ ራቅ ብለው መንገድ ተሻግረው አንዲቆሙ አዘዘ። ጥበቃው እንዲያባርሩን ሄዶ ቢነግራቸውም ፖሊሶቹ እሺ አላሉም።
የት/ቤቱ ዳይሬክተር መጥቶ ጥቂቶቻችንን ለብቻ አናገረን። «መመሪያው የመጣው ከላይ ነው፡ ምን ማድረግ አንችላለን?» ብሎ ተማጸነን። እኛም «ከላይም ይምጣ ከታች ትክክል ያልሆነ እና የተማሪውን መብት የሚጋፋ ነገር
ሥራ ላይ መዋል የለበትም» ብለን ሞገትነው። ሊያሳምነን ሞክሮ ሲያቅተው ትቶን ሄደና ትንሽ ቆይቶ እንደተመለሰ
«ይህን ጉዳይ ተረጋግተን በውይይት እናሰተካክላለን። ለአሁኑ ሁላችሁም ወደ ክፍል ግቡ፡ ሴቶቹም ሻሻቸውን ሳያወልቁ
ይግቡ» አለን። ሁሉም ተማሪዎች ገብተን መደበኛው ትምህርት ቀጠለ።
ዕረፍት ሰዓት ላይ የትምህርት ቤቱ የሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ በጉዳዩ ላይ ለመወያየት በማግስቱ ቀጠሮ መያዙ ተነገረን። በታቀደው ውይይት ላይ ሂጃብ መከልከል እንደሌለበት ኮሚቴውን ማሳመን የምንችልበትን ነጥብ አዘጋጅተን እኔ
አንዳቀርበው ተወሰነ። ሰብሰባው ላይ መምህራን፣የተማሪ ተወካዮች፣ ወላጆች እና የትምህርት ቢሮ ተወካዮች ተሳትፈዋል። ከሥነ-ሥርዓት ኮሚቴ ውስጥ አንድ መምህር ከትምህርት ቢሮ የመጣውን መመሪያ አነበበ። መመሪያው ሂጃብ የተከለከለበት ምክንያት የተማሪዎችን የጸጉር ንጽሕና ለማረጋገጥ፣ በሀይማኖት መካከል የሚፈጠር ልዩነት እና
ግጭት ለማስቀረት አንዲሁም ጽንፈኝነት አንዳይሰፋፋ ለመከላከል እንደሆነ ይዘረዝራል።
ምላሽ ለመስጠት ዕድሉ ሲሰጠኝ ተነሳሁና «በሀገራችን ሕገ-መንግሥት እና ዓለም አቀፍሕጎች መሠረት አንድ ድርጊት፣ ቃልና ምልክት ትምህርት ቤት ውስጥ መከልከል የሚችለው ሁለት ጉዳቶችን የሚያስከትል ከሆነ ነው'’ አልኩ።
እነሱም፣
1. የተማሪውን እና የአስተማሪውን መብት እና ደኅንነት አደጋ ላይ የሚጥል ከሆነ እና
2. የመማር ማስተማሩን ሂደት የሚያስተጓጉል ከሆነ።
የመጀመሪያውን ነጥብ ብዙ ማብራራት አላስፈለገኝም። «ጸጉር መሸፈን በትምህርት ቤት ውስጥ የደህንነት ችግር እንደማይፈጥር ግልጽ ነው። ሴቶች ሻሽ ሰላሰሩ የተፈጠረ የሀይማኖት ግጭት አላየንም አልሰማንም። ሻሽ ግጭት
ፈጥሯል የሚል ሰው ካለ ይናገር» ብዬ አዳራሹ ውስጥ ስመለከት ሐሳብ የሚሰጥ ጠፋ።
ሁለተኛው ነጥብ ወሳኝ ስለሆነ እና መመሪያውን ለማክሸፍ ስለሚጠቅም ተዘጋጅቼበታለሁ።
ከአኔ ጋር የሚማሩ ሁለት ሴት ተማሪዎችን አንዷ በሂጃብ አንድትሸፋፈን፡ ሌላኛዋ እንደ ከተማ ዱርዬ ከጉልበት በታች ተቆርጦ ያጠረ ዩኒፎርም
አንድትለብስ አድርጌ ወደ አዳራሹ አስገባሁ።
ሁለቱን ልጃገረዶች ጎን ለጎን አሰቁሜ በጣቴ ሂጃብ ወደለበሰችው ልጅ እየጠቆምኩኝ ከተሳታፊዎች መሀል አንዱን
ተማሪ «ይህቺ ልጅ ክፍል ውስጥ አጠገብህ ከተቀመጠች ወይም ግቢ ውስጥ ፊት ለፊትህ ከቆመች ትረብሽካለችን»
አልኩት። «ምኗን አይቼ ነው የምትረብሸኝ» ብሎ እንደመቀለድ አለ።
ቀጥሎ አጭር ልብስ የለበሰችዋን አሳይቼው
«ይህቺ ልጅ ሂጃብ ከለበሰችው አጠገብ ክፍል ውስጥ ፊትለፊትሀ ብትቆም የትኛዋ ናት የበለጠ የምትረብሽህ?› ብዬ ሰጠይቀው ልጁ እንደማፈር ብሎ አቀረቀረ፡ አዳራሹ ውስጥ የነበሩ ተሳታፊዎች ነገሩ ገብቷቸው ቤቱን በሳቅ
አናጉት። ዕድሜው ለገፋ አንድ አስተማሪም ለተማሪው ያቀረብኩለችን ጥያቄደገምኩለት «ሂጃብ የለበሰች ልጅ ክፍል
ውስጥ ማየትሀ የማስተማር ሥራህን ያውካል?›» ስለው «አሷን ካፈናት ነው አንጂ የሚረብሽ ነገር የለውም» አለ።
አጭር ልብስ የለበሰችውን፤ አሥነስቼ ስጠይቀው ደግሞ «አኔ ሽማግሌ ነኝ አይረብሸኝም። ለአንዳንተ ያለ ጎረምሳ
ግን አደጋ ነው፡ ጭኗን አንጂ ሰሌዳ አታዩም› ብሎ ሰውን አሳቀው።
«እንደምታዩት ጸጉርን መሸፈን የመማር ማስተማሩን ሂደት እንደማያውክ ተማሪውም አስተማሪውም መስክሯል።
መጀመሪያ ሕገ-መንግሥቱን ጠቅሼ እንደተናገርኩት አንድ ድርጊትም ሆነ አለባበስ ሊታገድ የሚችለው የመማር
ማስተማሩን ሂደት ካወከ ስለሆነ ሂጃብ የሚከለከልበት ምክንያት የለም። ከትምህርት ቢሮ የመጣው መመሪያም
ስሕተት ነው» ብዬ ቁጭ አልኩ።
በቀረቡት አስተያየቶች ላይ ውይይት ተደርጎ ሂጃብ አንዳይከለከል ስምምነት ላይ
ተደርሶ ለትምህርት ቢሮ አንዲገለጽ ተወሰነ።»
Via ሙራድ ታደሰ
@islam_in_school