ISLAMIC SCHOOL️


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ኢስላም በትምህርት ቤት

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎችን ማሠር ጀምሯል!

ላለፉት አመታት በነፃነት ሲለበስ የነበረውን ኒቃብ ከልክሎ ሙስሊም ተማሪዎችን ማንገላታት የጀመረው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ወደማስፈራራት እና ማሳሰር እንደተሸጋገረ ተገልፇል:: እስካሁንም ከኦዳያ ካምፓስ አንድ ሙስሊም ተማሪ ታስሯል:: ኒቃብ ለባሽ እህቶች ግቢ መግባት አትችሉም ከተባሉ ከዛሬ ጋር 4ተኛ ቀናቸውን የያዙም ሲሆን መስጂድ ውስጥ ከተማሪዎች እና ከትምህርት ርቀው እንደሚውሉና እንደሚያድሩም ታውቋል::

  የነፃነት እና እኩልነት ጥያቄን በማስፈራራት እና በማሰር ማቆም አይቻልም::

ፍትሕ ለዲላ ዩኒቨርሲቲ ሙስሊም ተማሪዎች!
ፍትሕ ለኢትዮጵያ ሙስሊም ተማሪዎች!


@islam_in_school


ኧረ እነዚህ ሰዎች😳😳

ከሳአዲ ተልዕኮ ተቀብላቹሃል😳😳

ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው እንዳይማሩ ክልከላ አድርገዋል የተባሉት በአክሱም ከተማ የሚገኙ አራት ትምህርት ቤቶች

10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ደግሞ ከአክሱም ከተማ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በተዘረጋ የውጭ ተፅእኖ ፈተና ለመውሰድ የሚያስችላቸው ፎርም አልሞሉም። ሃቁ ይህ ሆኖ እያለ ' 159 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ከ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ምዝገባ እንዲስተጓጎሉ ተደረገ ' እየተባለ ነው የሚወራው። 142 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች በትምህርት ቤቶቻችን የሌሉ የፈጠራ ድርሰቶች ናቸው።

የተቀሩት 10 ሴት ሙስሊም ተማሪዎች ቢሆኑ ፎርም መልተው ለመፈተን ፍላጎት አላቸው ፤ ከትግራይ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፣ ከመቐለ ፣ ከአዲስ አበባ እስከ ሳውዲ ዓረብያ በየቀኑ እየተደወለ ማስፈራርያ ይደርሳቸዋል። ይህ አካሄድ ደግሞ የቆየውን አብሮነት እና መቻቻል የሚጎዳ ለህዝብ እና አገር የማይጠቅም መወገዝ ያለበት ተግባር ነው። "

... ሲሉ ትምህርት ቤቶቹ በጥምር ለቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ በላኩት የፅሁፍ ምላሽ ገልጸዋል።

ኧረ ሼር አርጉት

@islam_in_school


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እህቶቻችን ለእህቶቻችን

«አክሱም ሒጃብ ብቻ አይደለም የተከለከለው እስልምና እንጂ»‼️

@islam_in_school


ሒጃቤ ክብርና ከፍታዬ!
መገለጫና ውበቴ
ኢስላማዊ ዓርማዬ ነው

➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho

@islam_in_school


በትግራይ ክልል መቀመጫ መቐለ ከተማ በአክሱም ትምህርት ቤቶች የተጣለውን የሒጃብ ክልከላ የሚቃወም ሠልፍ ዛሬ ማክሰኞ ጥር 13/2017 እየተካሔደ ይገኛል።

@islam_in_school


ዲላ ዩኒቨርሲቲ ••• Update!

የዲላ አናብስቶች 3ኛ ቀናቸውን በእምቢታ ቀጥለዋል:: ዛሬም ኒቃብ ለብሳችሁ ከግቢ አትገቡም የተባሉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኒቃቢስት እህቶቻችን ከግቢ ውጭ ከመስጂድ አድረዋል:: በሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ግብር የተነባ የልሕቀት ማዕከል የሀገሪቱ ግማሽ የሆነውን ሙስሊም ማህበረሰብ ልጆች በእምነታቸው ሳቢያ ማደሪያ እንኳን ነፍጎ ከውጭ ያሳድራል::

በአላህ ፈቃድ ግን ይህን መሠሉ በራስ ሀገር በራስ ተቋም የሚፈፀም ግፍ ፍፃሜውን ያገኛል ••• ነፃነት በነፃ አይገኝም!

@islam_in_school


"ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ መልበስ አይቻልም!" - ዲላ ዩኒቨርሲቲ

ላለፉት 3 አመታት በዩኒቨርሲቲው ውስጥ በነፃነት ይለበስ የነበረውን ኒቃብ ያለ ሕግ እና መመሪያ ከወር በፊት ከልክሎ የነበረው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሙስሊም ተማሪዎች ጋር ግብግብ ውስጥ እንደነበር ይታወቃል:: በሰሞኑም ለብሳችሁ አትገቡም በማለቱ ሙስሊም ተማሪዎች ከግቢ ውጭ ከመስጂድ ማደራቸው ይታወሳል::

የተፈጠረውን ችግር ለመፍታትም በዛሬው እለት ከሙስሊም ተማሪዎች ተወካዮች ጋር ውይይት ያደረገው የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር "ኒቃብ ለደህንነት ስጋት ስለሆነ በግቢ ውስጥ ለብሶ መግባትም ሆነ መንቀሳቀስ አይቻልም!" የሚል መልስ እንደሰጣቸው ተማሪዎች አሳውቀዋል::

በሙስሊም ተማሪዎች ላይ ተጨባጭ ያልሆነ እና እምነቱን የሚዳፈር ምክንያት በማቅረብ የሚደረግ የመብት ጥሰት መቆም እንዳለበት:: ኒቃብንም ሆነ የትኛውንም ኢስላማዊ አለባበስ የደህንነት ስጋት አድርጎ ማሰብም ሆነ ማቅረብ ሀይማኖቱን ከማንቋሸሽ ተለይቶ አይታይም:: ኒቃብ በሐይማኖት እንዲለበስ የታዘዘ የእምነት ልብስ ሲሆን በሕግ ደግሞ የማይከለከል የነፃነት መገለጫ ነው::

በአላህ ፈቃድ መሠል ጥላቻ ተኮር የመብት ጭቆናዎች በዚህ ትውልድ ታሪክ ይሆናሉ ••• ነፃነት በትግል እንጅ በነፃ አይገኝም!

©️EHEMSU

@islam_in_school


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የቀድስ ፍልስጤማውያን  የእስረኞችን መፈታት ጣፋጮችን በማደል እየካበሩት ይገኛል።

የቁድስ ጊዜም ቅርብ ነው❤
ኢንሻ አላህ

@islam_in_school


📱 TikTok Is back 📱

✔️ TikTok በሀገረ አሜሪካ በድጋሜ ወደ ስራ ገብቷል በትራምፕ ጥሪ መሰረትም Tiktok ለቀጣይ 3ወራት ባለው ጉዳይ ላይ ስምምነት እስኪደረስ መስራቱን ይቀጥላል።የTiktok እጣ ፈንታ ምን ይመስላቿል?

   @islam_in_school              


"በዚህች ምድር ላይ የፀናው እርሱ ነው ድል ያረገው"

የቀሳም ብርጌዶች ወታደራዊ ቃል አቀባይ አቡ ዑበይዳ

➖➖➖➖➖➖
Mahi Mahisho

@islam_in_school


በአዲስ አበባ የሚገኘው የሳዉዲ አረቢያ ኤምባሲ የባህል ዘርፍ ከ አዱረቱል መክኑና የተረቢያና የቁርአን ማዕከል ጋር በመተባበር የተዘጋጀ
📚📚📚📚📚📚📚📚📚

2 ተኛ ዙር

ሀገር አቀፍ የወንዶች እና የሴቶች ሀዲስ ሂፍዝ ዉድድር

1446ሂ -2025 ዓ ል

መስፈርቶች

1,ተወዳዳሪዎች ኢትዮጵያ ዉስጥ መሆን ይጠበቅባቸዋል
2,እድሜ ከ 40 አመት በታች የሆኑ
3, ወደፊት በሚገለፀዉ የፈተና ቀን ሰዓት እና ቦታ መገኘት ይኖርባቸዋል
4,ከአዲስ አበባ ዉጪ መተዉ ለሚወዳደሩ ተወዳዳሪዎች የምግብ የማደሪያ የትራንስፖርትና ማንኛውም ወጪ በራሳቸው የሚሸፍን ይሆናል
5,የፈተናና የዉጤት ቀናት በቀጣይ የሚገለፅ ይሆናል
6,ዉድድሩ የሚሆነው ቡሉገል መራም ሚን አዲለቲል አህካም
ዝግጅት አህመድ ኢብኑ አልይ ኢብኑ ሀጀር አል አስቀላኒ
ቅንብር ሰሚር ኢብኑ አሚር አልዙሀይሪ
የመፅ ሀፉ ኮፒ https://down.ketabpedia.com/files/bkb/bkb-ha1853-ketabpedia.com.pdf

7 የመወዳደሪያ ደረጃዎች (በአንድ ደጃ ብቻ ይወዳደሩ)

1,57 ሀዲሶችን መሐፈዝ
1-57

2,108 ሀዲሶችን መሐፈዝ
1-108

3,150 ሀዲሶችን መሐፈዝ
1-150
4,203 ሀዲሶችን መሀፈዝ
1-203

ለመመዝገብ በዋትስ አፕ ቁጥር
ለወንዶች +251928933333
ለሴቶች +251945777744
+251945777755




በመንገዱ መታሰር ቀርቶ ነፍሱን ለመስጠት የተዘጋጀ ፍልስጤማዊ ጎልማሳ ነው። ሀዲ አል-ሀምሸሪ ይሰኛል። ከዓመታት በፊት ሽማግሌ ልኮ ኒካሁ እንደታሰረ ነበር ዘብጥያ የወረደው። ለድፍን 16 አመታት እስር ቤት ማቀቀ። የሚስቱ ዕድሜ በወቅቱ አስራ ሰባት ነበር። ደመወዙን እያጠራቀመች ቦታ ገዛች ቤት ገነባች። እነሆ ከአምስት ቀን በፊት ከእስር ተለቀቀ። ጎጇቸውን በፍቅር ቀልሰው ኑሯቸውን ጀመሩ።

➖➖➖➖➖➖
©️Mahi Mahisho
➖➖➖➖➖➖


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
እንደዚህ ነው

@islam_in_school


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አዲስ የእሳት አደጋ በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ግዙፍ #የኤሌክትሪክ_ኃይል ማከፋያ ጣቢያ ላይ!!
___
ከሰሞኑ እሳት እየፈተናት ባለችው የአሜሪካዋ ካሊፎርኒያ ግዛት አሁንም አዲስ የእሳት አደጋ እንዳጋጠማት ተነግሯል።

አዲሱ የእሳት አደጋ በካሊፎርኒያዋ ሞንቴሪ በሚገኝ ግዙፍ የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋያ ጣቢያ ላይ የጠከሰተ ሲሆን፤ መንገዶች ተዘገተዋል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችም ከስፍራው እንዲለቁ ታዘዋል።

@islam_in_school


የአክሱም ሙስሊም ሴት ተማሪዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እየፈፀሙ ካሉ መካከል አንዱ ስዩም ካሕሳይ ይህ ነው። በጥላቻ ያበደ ሸይጣን (ሰይጣን) ይሉታል ተማሪዎቹ። በሙስሊም ተማሪዎች ላይ የሚያንፀባርቀው ንቀት፣ ጥላቻ እና ዘለፋ ለመግለፅ ይከብዳል። በምን አይነት የትምህርት ካሪኩለም ቢቀረፅ ነው እንዲህ በጥላቻ የሰከረው?

@islam_in_school


Update‼️

በትግራይ ክልል አክሱም ከተማ የሚገኙ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የትምህርት ቢሮን አዲስ ውሳኔ ተከትሎ ወደ ትምህርት ቤት ቢያመሩም፤ ወደ ቅጽ ግቢ መግባት ስላልተፈቀደላቸው ዳግም ከበር እንዲመለሱ ተደርገዋል። ዛሬም በሒጃባቸው ምክንያት የትምህርት ቤት በሮች ተዘግቶባቸዋል። ከአጥር ውጪ ሆነው ሲማሩባቸው የነበሩ ትምህርትቤቶች አሻግረው ሲመለከቱ ታይተዋል። ጓደኞቻቸው ወደ ክፍል ሲገቡ እነሱ ግን በር ተዘግቶባቸው ቆመው ሲመለከቱ ነበር። በጥበቆች ተባረዋል።

የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሐሙስ ጥር 8/2017 ለአክሱም ከተማ ትምህርት ቢሮ የተማሪዎችን አለባበስ በተመለከተ በጻፈው ደብዳቤ ከትምህርት ገበታ ውጪ የተደረጉ ተማሪዎች ቀድሞ የነበረውን ወይም ለመከልከላቸው ምክንያት የሆነው አለባበስ ተጠቅመው ትምህርት እንዲቀጥሉ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

ነገር ግን ዛሬም እነ ወይዘሮ ፀጋ፣ እነ መምህር ስዩም ካሕሳይ በተማሪዎቹ ላይ ሲሳለቁ ታይተዋል! ምንም ዐይነት ውሳኔ አልደረሰንም ብለው ተማሪዎቹ መልሷቻዋል። ለመማር ሰፍ ብለው የመጡ ሒጃብ የለበሱ ሙስሊም ሴት ተማሪዎች የመማር እድል ተነፍገዋል።

@islam_in_school


በሀገረ ማሌዥያ የሚገኘው ትልቁ አል ቡሃሪ ኢንተርናሽናል ዩኒቨርስቲ የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት ሙሉ ወጪያቸውን ተሸፍኖላቸው መማር ለሚፈልጉና በጦርነት ለተጉዱ አካባቢ ተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል አዘጋጅቶል ነበር ።

መስፈርቱን ያሟሉ 5 የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች ዛሬ ማሊዢያ ተጉዘዋል።ይህንን ዕድል ያገኙት አምስት የትግራይ ክልል  ሙስሊም ተማሪዎች በመቐለ ዩኒቨርስቲ እና በመቐለ የቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ይህንን ዕድል እንዳገኙ ኢንጂነር ሷሊህ እና ሌሎችም በመተባበር ያሳኩት መሆኑ ተገልጿል።

ተማሪዎቹ ትምህርታቸውን ተምረው ራሳቸው፣ ህዝባቸውንና ሀገራቸው እንደሚጠቅሙ ተስፋ የተጣለባቸው ሲሆን በሂደቱ ላይ በሀሳብ፣ በገንዘብ፣ በጊዜያቸውና በሌላም የተባበሩን ግለስቦችና ተቋማት ምስጋና ቀርቧል።

በዚህ ወቅት የትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች ከነዩኒፎርማቸው  ጋር ተመሳሳይ የሆነ ሒጃብ ለብሰው ለማማር የተከለሉ ሲሆን የ12ኛ ክፍል ተማሪዎቹም ፎርም የመሙላት እድል ተነፍገው እንደሚገኙ የሚታወቅ ነው።

እነዚህ የውጭ የትምህርት ዕድል አግኝተው ወደ ማሌዥያ ያቀኑ የትግራይ ክልል ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ ውጪ ለተደረጉ ተማሪዎች የስነልቦና ከፍታ ይሆናሉ ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ተማሪዎችን እንዳይማሩ ላደረጉ አካላት ደግሞ ሂጃብ ምንም ማድረግ እንደማይከለክል ማሳያ ይሆናሉ ተብሏል።

@islam_in_school


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የማይሰበር ትውልድ!
አላህ ከሸሂዶች ይመድባቸው!

@islam_in_school


እስራኤል እና ሀማስ በኩል ከ1 አመት ከ3 ወር በላይ ሲደረግ የቆየው ጦርነት በስምምነት መጠናቀቁን የሀማስ ባለስልጣናት ገልጸዋል።

በዚህም የመጀመሪያ ዙር የድርድር ሂደት ሀማስ ምርኮኞችን የሚለቅ ሲሆን እስራኤልም ፍልስጤማውያን እስረኞችን የምትለቅ ይሆናል።

የሰላም ስምምነቱ ዘላቂ የተኩስ አቁም ስምምነትን እና በጋዛ ሰብዓዊ እርዳታዎችን ለማስገባት ወሳኝ መሆኑም ተገልጿል።

@islam_in_school

20 last posts shown.