ዜና፡ የ #አክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት ሂጃብ ባገዱ ትምህርት ቤቶች ላይ የተመሰረተውን ክስ ውድቅ አደረገ፤ ተማሪዎች ውሳኔውን አወገዙ
የ #ትግራይ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፤ ሙስሊም ተማሪዎች ሂጃብ ለብሰው ወደ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ እንዳይገቡ በከለከሉ ትምህርት ቤቶች ላይ የተከፈተውን ክስ የአክሱም ወረዳ ፍርድ ቤት መዝጋቱን አስታወቀ።
ፍርድ ቤቱ ክሱን ወደ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የማስተላለፍ 'ሥልጣን እንደሌለ' በመግለጽ ጉዳዩ 'ሽምግልና ወይም በአስተዳደር ሂደት' መፈታት እንዳለበት መወሰኑን የክልሉ እስላምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤቱ አስታውቋል።
የምክር ቤት ፀሐፊ ሀጂ መሐመድ ካህሳይ ውሳኔው የተላለፈው ቀደም ሲል በትምህርት ቤቶች ውስጥ ሂጃብ መልበስ እንዳይከለከል የወሰነው ዳኛ ከኃላፊነቱ ተነስቶ በሌላ ሰው መተካቱን ተከትሎ ነው ብለዋል።
@islam_in_school