Psychology (ሥነ-ልቦና) Zone 🧠


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Psychology


Support channel for mental health awareness in Ethiopia. We post facts about psychology and psychological phenomenon.
''There is no health without Mental Health.''
Contact @FikrConsultSupportbot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Psychology
Statistics
Posts filter


ሙሉ ጤንነት!

ብዙ ሰዎች ለአካላዊ ጤናቸው ትልቅ ትኩረት ሰጥተው በአመት ሁለት ጊዜ የህክምና ክትትል (ቼክ አፕ) ያደርጋሉ፤ እንዲህ አይነት ልምድ እጅግ መልካም ነው። ነገር ግን የሳንባ፣ ኩላሊት፣ ጉበት፣ ጨጓራ፣ ጥርስና የመሳሰሉ አካላት ደህንነት ብቻ የጤናማነት ምልክት ሊሆን አይችልም።

የአለም ጤና ድርጅት ጤና ለሚለው ቃል ትርጉም ሲሰጥ ጤንነት ማለት "ሙሉ አካላዊ፣ አዕምሮአዊና ማሕበራዊ ደህንነት ነው እንጂ አለመታመም ብቻ አይደለም" ይላልና።

WHO defines health as well-being, “a state of complete physical, mental and social well- being and not merely the absence of disease or infirmity”.

ለመሆኑ የአዕምሮ ጤና ምንድን ነው?

አንድ ሰው የአዕምሮ ጤንነት አለው የምንለው ግለሰቡ ያልተዛነፈ አስተሳሰብ፣ ባሕርይና ስሜት ሲኖረው እንዲሁም ከማሕበረሰቡ ጋር ተቀላቅሎና በጥሩ ሁኔታ ሰርቶ መኖር ሲችል ነው።

እስቲ በዝርዝር እንመልከታቸው፦

ሀ) የአስተሳሰብ ጤንነት (cognitive health)

ጥሩ የማሰብ፣ የማስታወስ (memory)፣ የማሰላሰል፣ ፍሰት ያለው ሀሳብ የማፍለቅ፣ የትኩረት፣ የማቀድ፣ ችግሮችን የመፍታትና ውሳኔ የመስጠት ችሎታዎች የአስተሳሰብ ጤንነትን ያመላክታሉ።

ለ) የስሜት ደህንነት (emotional well-being)

አንድ ሰው የስሜት ጤንነት አለው ለማለት በብዛት በቀን ውስጥ የሚያስተናግዳቸውን ስሜቶች ማወቅ አስፈላጊ ነው። በብዛት ከአሉታዊ ስሜቶች (ለምሳሌ ንዴት፣ ጥላቻ፣ ፍርሃት፣ ቂም...ወዘተ) ይልቅ አዎንታዊ ስሜቶችን (ለምሳሌ ፍቅር፣ መገረም፣ ተስፋና ደስታ) የሚያስተናግድ መሆን አለበት።

ሐ) ጤናማ የህይወት ዘይቤ (Healthy life style)

አንድ ግለሰብ ሰናይ ባሕርያት አሉት የምንለው የሚያደርጋቸውን ነገሮች (አመጋገብ፣ አለባበስ፣ አነጋገር...ወዘተ) ተመልክተን ነው። ለምሳሌ በብዛት አትክልትና ፍራፍሬ ይመገባል፣ የአካል እንቅስቃሴ ያደርጋል፣ ሰው ይረዳል፣ አይሳደብም፣ አልኮል አይጠጣም፣ አይቅምም፣ አያጨስም፣ ነውጠኛ አይደለም...ወዘተ።

መ) ማሕበራዊ ደህንነት (social well-being)

ጥሩ አስተሳሰብ፣ አካላዊ ጤንነት፣ አዎንታዊ ስሜትና የሕይወት ዘይቤ አንድን ሰው ጤናማ ነው ለማለት መሉ መስፈርት አይሆኑም። ያ ሰው ከሰዎች ጋር ተስማምቶ መኖር፣ ሀሳቡን ማስረዳት፣ የሌሎችንም ሀሳብ መረዳት በጠቅላላው ከሌሎች ጋር በጥሩ ሁኔታ አብሮ መኖር አስፈላጊ ነው።

መደምደሚያ: ጤንነት አካላዊ ደህንነት እንዲሁም አለመታመም ብቻ አለመሆኑን ተረድተን ጤናማ የባሕርይ እና የአዕምሮ ጤንነታችንን መጠበቅ አለብን።

(ሳይኮሎጂ 101)

@melkam_enaseb


⬇️


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

መልካም በዓል!

@melkam_enaseb


ትኩረት የማጣት እና የመረጋጋት ችግር (Attention Deficit hyperactivity Disorder) - ADHD

ADHD ልጆች ላይ ሊከሰት የሚችል የእድገት እክል ነው። አንዳንድ ወላጆች ልጆቻቸውን ከሌሎች በተለየ ትዕግስት የለሽ፣ ቀዥቃዣና አስቸጋሪ ሆነውባቸው መፍትሔ ሲፈልጉ ይታያሉ፡፡ እነዚህ ህፃናት የሚይዙት የሚጨብጡት የሚጠፋባቸው፣ አንድ ነገር ጀምረው አፍታም ሳይቆዩ ሌላ የሚያምራቸው፣ ለመናገርና ለመጠበቅ ትዕግስት የማይኖራቸውና ችኩል ናቸው፡፡

ይህ አይነት የስነባህሪና የስነአእምሮ ችግር ያለባቸው ህፃናት ትኩረት ያጡ፣ ትዕግስት የለሽ ቀዥቃዣነት (ADHD) ህመም ተጠቂዎች ናቸው፡፡

የእነዚህ ህፃናት መሰረታዊ መገለጫዎች፦

- አንድ ነገር ጀምረው በቀላሉ ወደ ሌላ የሚሳቡና አንድን ነገር ጀምሮ ለመጨረስ ትኩረት የሌላቸው
- በትምህርት ቤት ግዴለሽነት የሚታይባቸውና ቀላል ስህተቶችን በፈተና ላይ በተደጋጋሚ የሚሰሩ
- የማያዳምጡና የተባሉትን የማያደርጉ
- የክፍልና የቤት ስራን ጀምሮ ለመጨረስ እንኳን ትዕግስት የሌላቸው
- በተሰጣቸው ስራ ላይ ሀሳባቸውን መሰብሰብ የማይችሉ
- ዝንጉነት በእጅጉ የሚታይባቸው
- በየአቅጣጫው የሚሮጡና እረፍት የሌላቸው፣ ዛፍም ሆነ ደረጃ ላይ ለመውጣት የሚታገሉ
- እጅና እግራቸው የሚቅበጠበጥና አደብ የሌላቸው
- ከጓደኞቻቸው ጋር እየተጫወቱ ተራቸው አስኪደርስ መጠበቅ ሞት የሚመስላቸው
- በቀላሉ የሚበሳጩና የሚናደዱ ናቸው፡፡

ስለዚህም ይህ ትኩረት የለሽነታቸውና ትዕግስት አልባነታቸው የትምህርት አቀባበልና አረዳዳቸውን በእጅጉ ይጎዳዋል።

ለዚህ ህመም እንዲህ ነው የሚባል ምክንያት ባይኖርም በእርግዝና ጊዜ አልኮልና ሲጋራ መጠቀም እንደ አጋላጭነት ይጠቀሳሉ፡፡ ዓለም አቀፍ ጥናት እንደሚያሳየው ከሆነ ለትምህርት ከደረሱ ህፃናት መካከል ከ5-10 በመቶ የሚሆኑት ህፃናት ይህ ችግር ሊታይባቸው ይችላል፡፡

አብዛኛው ትኩረት የለሽ ህፃናት በስነ-ልቦና ህክምና፣ በአማራጭ ትምህርት (Special Education) እና በመድሀኒቶች በመታገዝ የሚስተካከሉና መሻሻል ሊያሳዩ ይችላሉ፡፡ ሆኖም አንዳንዶች የጎላ ችግር ያለባቸው ካደጉ በኋላም ራስን ዝቅ ማድረግና ከማህበራዊ ግንኙነቶች ማፈግፈግ ሊታይባቸው ይችላል፡፡

ወላጆች እንዲህ አይነት ባህሪ ያላቸውን ህፃናት በአግባቡ በማሳከምና በቤት ውስጥ ድጋፍና አንክብካቤ በማድረግ ችግራቸውንና የትምህርት አቀባበላቸውን ቀስ በቀስ ማስተካከል ይችላሉ፡፡

በዶ/ር ሄኖክ ዘውዱ (የህፃናት ህክምና ስፔሻሊስትና የልጅ በእድሉ አይደግ መፅሀፍ ደራሲ)

@melkam_enaseb


⬇️


Certificate Course on Trauma Focused CBT Group Therapy         

Key areas of the training:

- Trauma and our brain functioning
- Coping and self-regulation skills
- Cognitive restructuring
- Gradual trauma processing
- Resilience and moving forward
- Assessment in trauma
- Group engagement

Training Date – April 29 – May 1, 2025,

Register using the link to secure your spot!  https://forms.gle/dgcxJdiMghBR7eHh9

(Aha Psychological Services)

@melkam_enaseb


"ልጅነት የነገ ታሪክ ተቀርፆ የሚቀመጥበት መዝገብ ነው!"

እኛ ወላጆች የነጋችንን ለማወቅ ዛሬ እዚያ ልጅነት መዝገብ ላይ የከተብነውን ማንበብ ነው የሚጠበቅብን። ነጋችንን ለማድመቅ ዛሬ እዚህ መዝገብ ላይ የምናሰፍረውን ማጤን አለብን።

እኛ ዛሬ እየኖርን ያለነው ወላጆቻችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ በልጅነታችን መዝገብ ያሰፈሩብንን በልጅነታችን ማሳ ላይ የዘሩትን አይደል? በልጅነት መዝገብ ላይ በዘፈቀደ የተሳለ ኹሉ የኃላ ኃላ ጅራቱ እና አናቱ የማይለያዩበት ቅዠት ያስታቅፋል።

በልጆቻችን ላይ የምናሳድረው ተጽእኖ የወደፊት ህይወታቸውን እንዴት እንደሚቀርጽ ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። ልክ እንደ ትንቢት መዝገብ፣ በልጅነታቸው የተቀረጹት ነገሮች የነገ ህይወታቸው መሰረት ይሆናሉ።

ልጆቻችንን ስናሳድግ፣ በቃላችንም ሆነ በድርጊታችን፣ በምናስተምራቸው እሴቶችና በሚሰማቸው ስሜቶች፣ በልጅነታቸው መዝገብ ላይ ታሪክ እየጻፍን ነው። ይህ ታሪክ ወደፊት ህይወታቸውን ይቀርጻል፣ ባህሪያቸውን፣ አመለካከታቸውን እና ስኬቶቻቸውን ይወስናል።

ልጆቻችንን ስናሳድግ፣ የምንሰጣቸው ትምህርት፣ የምናሳያቸው ፍቅር፣ የምንፈጥርላቸው እድሎች እና የምንመራበት መንገድ ሁሉም የነገ ህይወታቸው ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይኖረዋል። ስለዚህ፣ ዛሬ በልጆቻችን ላይ የምንዘራው ዘር ነገ የምናጭደውን ፍሬ ይወስናል።

በልጅነት ጊዜ የሚደረጉ ነገሮች፣ የሚሰሙ ቃላት፣ አልፎ ተርፎም የሚሰማቸው ስሜቶች በልጆች ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ሊኖራቸው ይችላል። በዘፈቀደ የሚደረግ አስተዳደግ፣ ያለ እቅድና ያለ መመሪያ የሚሰጥ እንክብካቤ ልጆች ወደፊት ህይወታቸው ላይ ችግር ሊያስከትል ይችላል።

ስለዚህ: ወላጆች ልጆቻቸውን በጥንቃቄ እና በእቅድ ማሳደግ አለባቸው። ለልጆቻቸው ፍቅር፣ ድጋፍ እና መመሪያ መስጠት አለባቸው። ልጆቻቸው ራሳቸውን እንዲያውቁ፣ ችሎታቸውን እንዲያዳብሩ እና ለህይወት እንዲዘጋጁ መርዳት አለባቸው። ምክንያቱም፣ የልጅነት ጊዜ የነገ ታሪክ የሚጻፍበት መዝገብ ነውና።

(ሴጅ ኢትዮጵያ)

@melkam_enaseb


⬇️


April 2: አለምአቀፍ የኦቲዝም የግንዛቤ ማስጨበጫ ቀን ነው!

በኦቲዝም ጥላ ስር የሚኖሩ ልጆች እንድናውቅላቸው የሚፈልጓቸው 10 ነገሮች፦

1. ካለብኝ ኦቲዝም ይልቅ ትኩረታችሁ እንደማንኛውም ልጅ/ሰው መሆኔ ላይ ይሁን።

2. በስሜት ህዋሳት አማካኝነት የማገኛቸው መረጃዎች ከአብዛኛዎቻችሁ በተለየ ሊረብሹኝ ይችላሉ።

3. አንዳንድ ነገሮች እንደተነገሩኝ ወዲያውኑ ላልረዳቸው እና ምላሽ ላልሰጥ እችላለሁ።

4. በየእለቱ በድግግሞሽ የሚደረጉ ነገሮችን መረዳት ይቀለኛል። ድግግሞሽ የምማርበት መንገድ መሆኑን እወቁልኝ።

5. ከሌሎች ልጆች ጋር አታነፃፅሩኝ።

6. እጃችሁን እየጎተትኩ የምፈልገውን የማሳያችሁ በቃላት ሀሳብን እንዴት እንደምገልፅ ስለማላውቅ ነው።

7. ስታስተምሩኝ በቃላት ብቻ ከምትነግሩኝ ይልቅ ብታሳዩኝ እና ብታስነኩኝ በቀላሉ ነገሮችን መረዳት እችላለሁ።

8. ከሚያቅተኝ ነገር ይልቅ የምችለው ላይ አተኩሩ።

9. ከሌሎች ጋር መሆን እፈልጋለሁ ግን እንዴት ማድረግ እንዳለብኝ አስተምሩኝ።

10. ያለምክንያት ውደዱኝ ይገባኛልና።

World Autism Awareness Day!

በመአዛ መንክር (ክሊኒካል ሳይኮሎጂስት)

@melkam_enaseb


⬆️ በአክብሮት ተጋብዛቹሃል!

እሁድ መጋቢት 28

(ነህምያ ኦቲዝም ማዕከል)

@melkam_enaseb


ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

የኦቲዝም ግንዛቤ ማስጨበጫ ወር በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ17ተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ደግሞ ለ23ተኛ ግዜ ይካሄዳል!

የፊታችን ረቡዕ መጋቢት 24/2017 ዓ.ም ሳር ቤት ቫቲካን ኤምባሲ አካባቢ በሚገኘው ጆይ ኦቲዝም ማዕከል የአለም አቀፍ ኦቲዝም ግንዛቤ ቀን መሰናዶ ላይ ሁላችሁም ተጋብዛችኋል!

(ኒያ ፋዉንዴሸን ጆይ ኦቲዝም ማዕከል)

@melkam_enaseb


የ “trauma” ትርጉም

'trauma' ለሚለው ቃል እቅጩን የሆነ የአማርኛ መተኪያ ቃል ለማግኘት ቢያስቸግርም፣ “የስሜት ቀውስ”፣ “የስ-ልቦና ስቃይ”፣ እና የመሳሰሉትን ገላጭ ሃሳቦች መጠቀም እንችላለን፡፡

• “trauma” ማለት “ለአሰቃቂ ክስተት የሚሰጥ ስሜታዊ ምላሽ” ማለት ነው፡፡

• ሰዎች ባጋጠማቸው “ይጎዳኛል” ወይም “ያስፈራል” ብለው በሚያስቡት የአካል ወይም የስሜት አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ የ “trauma” ልምምድ ውስጥ ሊገቡ ይችላሉ፡፡

• አንድ ሰው በ “trauma” ልምምድ ውስጥ ካለፈ በኋል የጉዳት ስሜቱና ምልክቱ በአጭር ጊዜ ውስጥ ወይም ከረጅም ጊዜ በኋላ ሊከሰት ይችላል፡፡

• ከዚህ ልምምድ በኋላ ሰዎች ከአቅም በላይ የሆነ ነገር እንደተከሰተ የመሰማት ሁኔታ፣ አቅመ-ቢስነት ወይም ድንጋጤ ሊሰማቸው ይችላል።

• አንድ ሰው የደረሰበትን “trauma” በሚገባ መፍትሄ ካላገኘለትና ሁኔታው ከተባባሰ የአእምሮ ጤንነትን ወደማወክ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፣ ወይም ደግሞ post-traumatic stress disorder (PTSD) ወደተሰኘው ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡

የ “trauma” መነሻ የሚሆኑ ልምምዶች

ከዚህ በታች በሁለት ክፍል ተለይተው የተዘረዘሩትን የ “trauma” አይነቶች ለመንደርደሪያነት በመጠቀም ሌሎች ለዚህ ስሜት ተጋላጭ እንድንሆን የዳረጉንን ሁኔታዎች መለየት እንችላለን፡፡

የልጅነት “trauma” ምሳሌዎች

- ለእድሜ የማይመጥን ስራን ሰርቶ ማደግ፣ ጨዋታን ተከልክሎ ማደግ፣ በቤተሰብ (በአሳዳጊ) ስድብንና የቃላት ጥቃትን አስተናግዶ ማደግ፣ ከፍተኛ አደጋ አይቶ ማደግ፣ የወሲብ ጥቃትን ወይም ሙከራን አስተናግዶ ማደግ፣ አካላዊ ድብደባን አስተናግዶ ማደግ፣ ጉልበተኝነት (bullying) አስተናግዶ ማደግ ይጠቀሳሉ።

የአዋቂነት “trauma”

- የዘረኝነት ጥቃት፣ ጦርነት አካባቢ መኖር ወይም መገኘት፣ የአስገድዶ መደፈር ጥቃት፣ አሰቃቂ የትራፊክ ወይም የተፈጥሮ አደጋ፣ ለሕይወት አስጊ የሆኑ የጤና ሁኔታዎች፣ የሚወዱትን ሰው በድንገት ማጣት፣ የሽብርተኝነት ድርጊቶች ይጠቀሳሉ።

(ዶ/ር እዮብ ማሞ)

@melkam_enaseb


⬇️


#March30
#WorldBipolarDay

ባይፖላር ዲስኦርደር ምንድነው?

ባይፖላር ዲስኦርደር የምንለው ከፍተኛ (ማኒያ) ወይም ዝቅተኛ (ድብርት) ስሜቶችን የሚያካትት የአዕምሮ ጤና ህመም ሲሆን ማኒክ ዲፕሬሽን በመባልም ይታወቃል።

ለባይፖላር ህመም መንስኤ ከምንላቸው ውስጥ በጥቂቱ

- በዘር ባይፖላር ያለበት ቤተሰብ ካለ
- በአንጎላችን ውስጥ ያለው ኬሚካል ምጥን መዛባት
- የኑሮ ጫና ከፍተኛ ጭንቀት ያለባቸው ክስተቶች (ለምሳሌ የአንድ ቅርብ ሰው ሞት)

የባይፖላር ህመም ምልክቶች በMania ምዕራፍ

1. ከልክ በላይ የሆነ ደስታ: የታላቅነት ወይም የብስጩነት ስሜት (Euphoric, expansive, or irritable mood)
2. በኃይል መሞላት (Excessive energy)
3. ራስን መኮፈስ (Grandiosity)
4. መተኛት አለመፈለግ (Decreased need for sleep)
5. ወሬኝነት (Talkative)
6. ከሃሳብ ሃሳብ መዝለል/ የሃሳብ እሽቅድምድሞሽ (Flight of idea/Racing thoughts)
7. የሃሳብ መሰረቅ (Distractibility)
8. የበዛ ግብ ያለው እንቅስቃሴ (Increased goal directed activity)
9. ህመም የሚያስከትሉ ተግባራት (involved in Pain resulting activities)

ከእነዚህ በትነሹ ሶስት (3) ምልክቶች በተከታታይ ለአንድ ሳምንት በተደጋጋሚ የሚሰማችሁ ከሆነ የባይፖላር ህመም ሊሆን ስለሚችል በቶሎ የአእምሮ ህክምና ስፔሻሊስት ያማክሩ።

ለማማከር ይደውሉልን: 0995011035
አጭር ቁጥር: 8187

(Sitota Mental Health Care & Rehabilitation Center)

@melkam_enaseb


ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1446ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ!

@melkam_enaseb


የባለትዳሮችን ግንኙነት የሚያጠናክሩ ነጥቦች!

በፍቅር ጓደኝነት የተጀመረ ወዳጅነት ወደ ትዳር ከፍ ሲል ተቋማዊ መልክን ይይዛል፡፡ በዚህ ጊዜ በሁለት ጥንዶች መካከል ከህይወት ውጣ ውረድ፣ ከልማድ፣ ከፍላጎት መለያየት እና ከሌሎችም ምክንያቶች የተነሳ ጥል እና መጨቃጨቅ ይከሰታል፡፡

ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ውጤታማ ልማዶች ታዲያ በትዳር አጋሮች መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እንደሚያግዙ ባለሙያዎች ይመክራሉ።

1.የጋራ ፍላጎቶችን መፍጠር

ባለትዳሮች በጋራ የሚዝናኑባቸውን እና አብረው ጊዜ የሚያሳልፉባቸውን ለሁለቱም ተስማሚ የሆኑ ቦታዎች እና ሁነቶችን ሊፈጥሩ ይገባል፡፡ እነዚህ ተደጋጋሚ ልማዶች ጤናማ እና ደስተኛ ግንኙነት ለመገንባት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ፤ በተጨማሪም የመተዋወቅ እና ስሜትን የመጋራት ሁኔታን ይፈጥራሉ፡፡

2. አብሮ መመገብ

ማዕድ መጋራት ወይም አብሮ መመገብ ምንም እንኳን ቀላል ነገር ቢመስልም በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ በጋራ ገበታ ላይ መቀመጥ የባለትዳሮችን አብሮነት ከፍ የሚያደርግ ነው፡፡ ምንም እንኳን በቀን ውስጥ ሁሉንም ሰአት አብሮ መመገብ የማይቻል ቢሆንም በተገኘው አጋጣሚ በምግብ ዙርያ የሚወሩ ወሬዎች ስለ ቀን ውሎ ለመነጋገርና ሀሳብ አሰተያየት ለመጋራት እድል ይሰጣሉ።

3.ከዘመድ እና ወዳጅ ጋር በቤት ውስጥ አብሮ ማሳለፍ

በተቻለ አቅም ከቤተሰብ እና ከጓደኛ ጋር የጋራ ጊዜን ማሳለፍ፣ የህይወትን አጋጣሚዎች፣ በጋራ ማጣጣም እና ማክበር ቢቻል በጥንዶች መካከል የእኔነት ስሜትን ይፈጥራል፡፡ እንደ ባልና ሚስት የመግባባት ስሜት ከማሳደጉም ባለፈ ከጓደኞች እና ቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ ውብ ትውስታዎችን በመፍጠር ግንኙነቱን ያጠናክራል፡፡

4. ከግጭት በኋላ ስሜትን መገላለጽ

በጥንዶች መካከል መዋደድ እና መፋቀር እንዲሁም ጥሩ ጊዜዎች እንዳሉ ሁሉ መጣላት፣ መጨቃጨቅ፣ በሀሳቦች ያለመስማማትም በግንኙነት ውስጥ የሚያጋጥም ነው፡፡ ግጭት ተፈጥሯዊ ቢሆንም ጥሉን ለመፍታት ሰዎች የሚከተሉት መንገድ ጤናማነት ግንኙነቱን ለማስቀጠል እና መግባባትን ለመፍጠር ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህም ግጭቱን ስለፈጠረው ምክንያት በእርጋታ መመካከር ስለመፍትሄው መወያየት እና ከማንኛውም አለመግባባት በኋላ ሁለቱም ወገኖች ይቅርታ በመጠየቅ ህይወታቸውን ሊቀጥሉ ይገባል፡፡

በተጨማሪ: ባህላዊ እና ሀይማኖታዊ ሁነቶች ላይ በጋራ መታደም፣ የስፖርት እና የዳንስ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ፣ ስነጥበባዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ልምድን ማዳበር የባለትዳሮችን ጥምረት ለማጠናከር ይረዳሉ ተብለው ከተጠቀሱ ነጥቦች መካከል ናቸው፡፡ Via: Alain

@melkam_enaseb


⬇️


የድባቴ ህመም (Major Depressive Disorder)

ድባቴ ምንድነው?

ድባቴ የምንለው በተከታታይ ሁለት ሳምንታት በላይ የሚቆይ የመደበር እና ደስታ የማጣት ስሜት ነው።

ለድባቴ ህመም መንስኤ ከምንላቸው ውስጥ በጥቂቱ?

- የመጠጥ ወይም አደንዛዥ ዕፅ ሱስ
- አካላዊ ወይም ፆታዊ ጥቃት
- የሚወዱትን ሰው በሞት ማጣት
- የተወሰኑ የህክምና መድኃኒቶች
- ብቸኝነት ሰው ማጣት
- የንጥረ ነገር መዛባት (ለምሳሌ የSerotonin መቀነስ)

የድባቴ ህመም ምልክቶች

1. ከዚ በፊት ማድረግ የሚወዱትን ነገር አሁን ማድረግ ካስጠላቸው
2. ባዶነት መሰማት፣ ማዘን፣ እለት ተእለት የመደበር ስሜት መሰማት
3. እንቅልፍ ማጣት ወይም ረዥም ሰዓት መተኛት
4. ትኩረት ማጣት፣ ነገሮችን መርሳት
5. ምክንያት የሌለው ክብደት መቀነስ ወይም መጨመር
6. የድካም ስሜት
7. ለራስ ዋጋ አለመስጠት
8. የምግብ ፍላጎት መቀነስ ወይም በጣም መጨመር
9. በተደጋጋሚ ስለ ራስን ማጥፋት ማሰብ

ከእነዚህ ምልክቶች ቢያንስ አምስት እና ከዛ በላይ በተከታታይ ለሁለት ሳምንት በተደጋጋሚ የሚሰማችሁ ከሆነ የድባቴ ህመም ልንል እንችላለን።

መፍትሔው 

በደንብ እርግጠኛ ለመሆን እና ሳይባባስ መፍትሔ ለማግኘት ከአዕምሮ ህክምና ስፔሻሊስቶች ጋር መነጋገር፤ ሳይኮሎጂስቶችን ማማከር ያስፈልጋል።

ይደውሉልን: 0995011035
አጭር ቁጥር: 8187

(Sitota Mental Health Care & Rehabilitation Center)

@melkam_enaseb


ኧረ ሌላ መውጫ እንፈልግለት!

ፌስቡክ መጠቀም ከጀመርክ ስንት ሰአት ሆነህ? ከእንቅልፍህ ከተነሳህስ? በየ46 ሰከንዱ በአለማችን አንድ ሰው ራሱን ያጠፋል። ኢትዮጲያ ውስጥ ደግሞ በየአንድ ሰአቱ። በሀገራችን በአመት ከ8ሺ በላይ ሰዎች ራሳቸውን ያጠፋሉ።

ሰዎች ራሳቸውን የሚያጠፉት ጨንቋቸው ነው። ከከፍተኛ መከፋትና ጭንቀት ሌላ መውጫ አልታይ ቢላቸው ለመገላገል ራሳቸውን ያጠፋሉ።

ከጭንቀትና ከመከፋት ሌላ መውጫ መንገድ አለ። የአእምሮ ህክምና እንዲሁም "አለሁልህ" ብሎ ጭንቀትን መካፈል። ለተጨነቁ ሰዎች ሌላ መንገድ እንዳለ እናሳያቸው።

ያለ አእምሮ ጤና፤ ጤና የለም!

ዶ/ር ዮናስ ላቀው (የአእምሮ ህክምና ስፔሺያሊስት) 

@melkam_enaseb


ከወላጅ የመለየት ፍራቻ!

ከወላጅ የመለየት ፍራቻ ሁሉም ልጆች ላይ በሚባል ደረጃ የሚፈጠር እጅግ የተለመደ የእድገት ሂደት ነዉ። ከተወለዱ ከ6 - 8 ወራት ጊዜ ዉስጥ ይጀምራል፤ ከ10 - 18 ወር ላይ ከፍተኛ ደረጃ ይደርሳል፤ 4 ወይም 5 ዓመት አካባቢ ልጆች በራስ የመተማመን አቅማቸው ስለሚጨምር የመለያየት ፍርሀቱ በሂደት ይከስማል።

ልጆች ምን አይነት ባህርይ ሊያሳዩ ይችላሉ?

- ማልቀስ፣ ከመጠን በላይ መጣበቅ፣ ወይም ወላጆቻቸው ጋር ሲለያዩ ከመጠን ያለፈ ብስጭት።
- ሌሎች ሰዎች ሲያባብሏቸዉ አለመቀበል።
- ለአጭር ጊዜም ቢሆን ለብቻ መሆንን መፍራት
- የመለያያ ሰዐት ሲደርስ የህመም ስሜት (ሆድ ቁርጠት፣ ራስ ምታት) እየተሰማቸዉ እንደሆነ መናገር።
- የወላጅ እቅፍ ዉስጥ ወይም አጠገብ ካልሆኑ ለመተኛት መቸገር ናቸዉ።

ወላጆች ምን ማረግ አለባቸዉ?

- በአጭር ደቂቃ መለያየትን በመጀመር ቆይቸታዉን ቀስ በቀስ በማያስታዉቅ መልኩ መጨመር
- ወላጆች ተደብቆ መሄድን ማቆም። መለያያ ሰዐት ሲደርስ ለጥቂት ደቂቃ አዋርቶ እንደሚመለሱ ነግረዉ መሰናበትን ባህል ማድረግ።
- የወላጅን ፍርሀት ልጆች በቀላሉ ማወቅ ስለሚችሉ የፍርሀት ስሜትን ከፊት ላይ ማስወገድ እና በሙሉ የራስ መተማመን እና መረጋጋት መቅረብ
- የመለያያ ሰአት ላይ የልጆችን ምቾት ለመጨመር የሚወዱትን መጫወቻ ማቅረብ።
- የልጆችን የፍርሀት ስሜት በደንብ መረዳትና በሚያረጋጉ ቃላት መልስ መስጠት።
- ወላጆች በተቻለ መጠን እንመጣለን ባሉት ሰዐት ለመመለስ መሞከር እና የመዉጫ መግቢያ ሰአትን ቋሚ ማድረግ።
- በዚ ሁሉ ሂደት ዉስጥ ልጆች የሚያሳዩትን ለዉጥ እና ጥንካሬ በትንንሽ ሽልማቶች ማበረታታት።

ነገር ግን ምልክቶቻቸዉ ለተራዘመ ጊዜ ከቆዩና በእለት ተእለት እንቅስቃሴ ላይ እክል መፍጠር ከጀመሩ የባለሙያ እገዛ ሊያስፈልግ ይችላል!

ዶ/ር ሚካኤል ከፍያለዉ
(Sitota Mental Health Care & Rehabilitation Center)

@melkam_enaseb

20 last posts shown.