የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎትን ለማሳደግ ከክፍያ ነፃ የሆነ ዌብሳይትን ይጠቀሙ
የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የተማሪዎችን እንግሊዝኛ ቋንቋን ለማሻሻል የሚያግዝ ፖርታል አዘጋጅቷል፡፡
ፖርታሉ ከቅድመ አንደኛ (O ክፍል) ጀምሮ በሁሉም የክፍል ደረጃዎች የተዘጋጁ ሁኔታንና አውድን ያገነዘቡ እያዝናኑ የሚያስተምሩ ግልጽና በቀላሉ ለመረዳት የሚያስችሉ በድምጽ በጽሁፍና በምስል የተቀናበሩና የእንግሊዝኛ ቋንቋን የሚያሻሽሉ መረጃዎች ለማግኘት ያስችላል።
ፖርታሉን ለመጠቀም ኢንተርኔት ማብራት የሚያስፈልግ ቢሆንም ኢንተርኔቱ ገንዘብ የማይቆርጥ ሲሆን በስማርት ስልክ፣ ስማርት ቴሌቪዥን፣ በታብሌትና በኮምፒውተር በማንኛውም ብሮዘር መጠቀም ይቻላል፡፡
ፖርታሉን
https://learn-english.moe.gov.et/ በመንካት መክፈትና መጠቀም ይችላሉ።