ቀን 17/05/2017ዓ.ም
ደሴ/ኢትዮጵያ
ለመምህር አካለ ወልድ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች በሙሉ፦
✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️✔️
እንደሚታወቀዉ የ2017ዓ.ም የመጀመሪያዉ መንፈቀ አመት የማጠቃላያ ፈተና የሚሰጠዉ ትምህርት ቢሮ ባወረደዉ የትምህረት ካላንደር መሰረት ከጥር 19 እስከ ጥር 23 መሆኑን በተደጋጋሚ በተለያዬ የመረጃ ምንጮት አሳወቀናችኋል። በመሆኑም ሰኞ በ19/05/2017ዓ.ም ለፈተና ስትመጡ ማሟላት ያለባችሁ ነገሮች፦
1. ሁሉም ተማሪ ፀጉሩን ተሰተካክሎ መምጣት የግድ ነዉ።
2. ሁሉም ተማሪ ፈተና ከመጀመሩ 30 ደቂቃ በፊት በት/ቤት ውስጥ መገኘት ይጠበቅባችኋል።
3. በተመደባችሁበት ክፍል ፈታኙ በሚሰጣችሁ አቅጣጫ መሰረት ወደ ፈተና ክፍል በመግባት በቦታቸው መቀመጥ ይጠበቅባችኋል፡፡
4.ከእስክሪብቶ፣ እርሳስ፣ ላጲስ፣ መቅረጫ ውጪ ወደ መፈተኛ ክፍል ይዘው መግባት የተከለከለ ነዉ።
5.በፈተና ሰዓት መኮረጅ ወይም ማስኮረጅ ፈተና የሚያሰርዝ በመሆኑ በስርዓት የራሳችሁን ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት በማድረግ መፈተን ይጠበቅባችኋል።
6.ለፈተናው የተሰጣችሁን ሰዓት በአግባቡ መጠቀም ይኖርባችኋል።ማለትም ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ ቀድሞ መዉጣትም ሆነ መግባት የተከለከለ ነዉ።
7.በፈተና ሰዓት ምንም አይነት ድምፅ ማሰማት፣ እንቅስቃሴ ማድረግ፣ አላስፈላጊ ወረቀት(ደብተር) ይዞ መገኘት፣ ረብሻ መፍጠር ፣ወረቀት መወርወር በጥብቅ የተከለከለ ነዉ።
8.ሁሉም ተፈታኝ ተማሪዎች አስፈላጊውን መረጃ፣ ስም፣ተራ ቁጥር፣ ፆታ ፣ክፍል እና ሴክሽን የመሳሰሉትን በአግባቡ መሙላትና የፈተናውን መልስ መሟላቱን በማረጋገጥ ለፈታኝ መምህሩ በጠየቀው ሰዓት መመለስ ይጠበቅባችኋል።
9. ሁሉም ተፈታኞች ማንኛውም ጥያቄ ሲጠየቁ በስርዓት እጅ በማውጣት መሆን ይኖርበታል።
10.ሁሉም ተፈታኞች አቴንዳንስ ላይ በዕለቱ በተፈተኑበት ትምህርት ስር መፈረም ይኖርባቸዋል።
11.የተለያዬ ጌጣጌጦች ይዞ መምጣት የተከለከለ ነወ።በተለይ ሴቶች
12.ሞባይል ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
13.የተለያዪ ኤሌክትሮኒክስ ነገሮች፣ስለታማ ነገሮች፣ ሳይንቲፊክ ካልኩሌተሮች ፣ዘመናዊ የ እጅ ስአቶች ይዞ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
14.ዩኒፎርም ለብሶ መምጣት ይጠበቅባችኋል።
15.የ12 ኛ ክፍል ፈተና በሞዴል እስታንዳርድ በመሆኑ እርሳ ላፒስ እና መቅረጫ ይዞ መምጣት የግድ ነዉ።
16. ሁሉም ተፈታኞች ፈተና ከጨረሱ በኃላ የተፈተኑት የመልስ መስጫ ወረቀት ለፈታኙ በጥንቃቄ መስጠት ይናርባችኋል።
17.ሁሉም ተፈታኝ ፈተና ጨርሶ ከክፍል ከወጣ በኋላ ምንም አይነት ድምፅ ማሰማት የተከለከለ ነዉ።
18.የትኛዉም ተፈታኝ የጥያቄ ወረቀቱን ክፍል ውስጥ ወይም ከክፍል ዉጭ ጥሎ ወይም ቀዶ መሄድ በጥብቅ የተከለከለ ነዉ።
19.የትኛዉም ተማሪ ለተለያዩ ጉደዮች ለማጠራት አስተባባሪዎ ወይም የፈተና ኮሚቴዎች ወይም ፈታኞች መታወቂያ ከጠየቁ ማሳየት የግድ ነዉ።
20.የትኛዉም ተማሪ ወደ ትምህርት ቤት ሲመጣ የትምህርት ቤት መታወቂያ ይዞ መምጣት የግድ ነዉ።
21.የትኛዉም ድምፅ የሚያወጡ ነጠላ ጫማ እና የመሳሰሉት ለብሶ መምጣት የተከለከለ ነዉ።
ማሳስቢያ፦
1. ዉድ የተማሪ ወላጆች ተማሪዎች ወደ ፈተና ስትልኩ በእናንተ በኩል ያላችሁ የግንዛቤ ማስጨበጫ የምክር አገልግሎት አ አሰጥጣ ከጥር 19 እስከ ጥር 23 ለሚሰጠዉ የማጠቃላያ ፈተና እናንተም አንድ የትምህርት ባለድርሻ አካል ስለሆናችሁ የተማሪዎች ዉጤት የተሻለ እንዲሆን ሀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪ እያስተላለፍን።
2. ተማሪዎች በስአቱ ወደ ትምህርት ቤት እንድትልኳቸዉ በጥብቅ እናሳስባለን።
3.የትምህር ቤታችን የወላጅ ተወካዬች የፈተና ሰርአቱን ትምህርት ቤት በመገኘት እንድታስተባብሩ ጥሪ እናስተላልፋለን።
ት/ቤቱ