ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር – አዲስ አበባ ibnu Mas'oud islamic center


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


Official
ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በሰኔ ወር 2001 ዓ.ል ተመስርቶ በተቀናጀ መልኩ ለሙስሊሙ ሕብረተሰብ ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ ይገኛል

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Forward from: NESIHA TV ነሲሓ ቲቪ
Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ታላቅ የ"ነሲሓ ኮንፈረንስ" በሚሊኒየም አዳራሽ


@nesihatv


📣 ኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር በሚከተሉት የስራ ቦታዎች አአመልካቾችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል

የስራ መደብ 1:- የገቢ ማሰባሰቢያ አስተባባሪ

※ የትምህርት ደረጃ፡ ዲፕሎማ
※ የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ
※ የስራ ሁኔታ፡ የ3 ወር ኮንትራት
※ጾታ፡- ወ

🔅መስፈርት

✅ ዕርዳታ የማሰባሰብ ልምድ ያለው
✅ የኢብኑ መስዑድ / ነሲሃ ዳዕዋ እንቅስቃሴ ግንዛቤ ያለው
✅ በተለያዩ የዳዕዋ ተግባራት ላይ ተሳታፊ የሆነ
✅ ጥሩ የመግባባት ችሎታ ያለው
✅ ሱና ነጸብራቅ የሚታይበት

※ ተፈላጊ ብዛት፡ 2

※ ደሞዝ፡ በአፈፃፀሙ መሰረት ቦነስ ያለው

የስራ መደብ 2:- የእርዳታ ማስተባበሪያ ሰራተኛ

※ የትምህርት ደረጃ፡ ዲፕሎማ እና ከዚያ በላይ
※ የስራ ቦታ፡ አዲስ አበባ
※የስራ ሁኔታ፡ የ3 ወር ኮንትራት
※ ተፈላጊ ብዛት፡ 10
※ ደሞዝ፡ በአፈፃፀሙ መሰረት ቦነስ ያለው
※ጾታ፡- ወ

🔅 መስፈርት

✅ የኢብኑ መስዑድ / ነሲሃ ዳዕዋ እንቅስቃሴ ግንዛቤ ያለው
✅  በተለያዩ የዳዕዋ ተግባራት ላይ ተሳታፊ የሆነ
✅ ጥሩ የመግባባት ችሎታ ያለው
✅ የሱና ነጸብራቅ የሚታይበት

ለማመልከት:- CV በቴሌግራም @Ibnumesoud01 ላይ ይላኩ

___
🕌 ibnu Masoud islamic Center
@merkezuna


🌙 ረመዳንን እንዴት እንቀበል🌙

ለሴቶች ብቻ የተዘጋጀ ልዩ ሙሀደራ

☀️ እሁድ ጥር 25፣2017
ጠዋት ከ3:30-6:30

ከጦርሃይሎች ከፍ ብሎ 18 አካባቢ በሚገኘው
ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

@merkezuna


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📢ልዩ  ስንቅ ለታዳጊዎች የመጪው ጊዜ የኢስላም ተረካቢዎች!

⭐️ውድ ለሆኑት ትውልዶች! ለታዳጊ ተማሪዎች የተዘጋጀ  ለ 4 ቀናት የሚቆይ ድንቅ ኮርስ!

💎ኮርሱ በሶስት ደረጃዎች በእድሜ ተከፈሎ የሚሰጣቸው ሲሆን

⚡️ከቁርአን፣ ከአቂዳ እና ከተርቢያ የሚመጥናቸውን ወሳኝና ወቅታዊ ትምህርቶች
የሚያገኙበት ይሆናል።
 
▫️እድሜ ለሴቶች ከ10- 18
ለወንዶች ከ12 -18

🗓 ከጥር 26- 29፣2017

🕘ጠዋት ከ3:00-6:30

የምዝገባ ጊዜ
ከጥር 19_ 22 በአካል መጥተው አሊያም በመደወል መመዝገብ ይችላሉ ።

ለበለጠ መረጃ
1⃣ 18 ማዞሪያ የሚገኘው መርከዝ ኢብኑ መስዑድ

ለሴቶች-  0904 36 66 66
ለወንዶች- 0912 02 31 90

2⃣ ቤተል (የሴቶች ብቻ)
40 ሜትር ላይ በሚገኘው አልአፊያ ት/ቤት

+251911375952
+251911062499

⚠️ወላጆች ልጆችዎን ወደዚህ ድንቅ ዝግጅት በመላክ የህይወት ስንቅን ያውርሱ።

✔️መልዕክቱን ሼር በማድረግ የምንዳ ተካፋይ እንሁን!

https://t.me/darulhadis18


በአላህ ፈቃድ በቅርቡ ልዩ የነሲሓ ኮንፈረንስ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል.. ለመሳተፍ ይዘጋጁ!

____
🕌 ibnu Masoud islamic Center
@merkezuna


በወሎና አካባቢዋ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የ 4.7 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ተደረገ

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ከተለያዩ የሃገራችን አካባቢዎች ተፈናቅለው ወሎ ደሴ ገራዶ፣ ሀርቡ፣ ደጋንና አርጎባ ሰንቀሌ ለሚገኙ 2,300 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞችና የሸሪዓ እውቀት ተማሪዎች የ 4,700,ዐዐዐ ብር የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል። በዚህ ኸይር ስራ የተሳተፉ በጎ አድራጊዎችን ሁሉ አላህ የመልካም ስራ ምንዳቸውን እጥፍ ድርብ አድርጎ እንዲከፍላቸው እንለምነዋለን።

ታህሳስ 15/ 2017

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

____
🕌 Ibnu Mas'oud islamic Center
@merkezuna


سعد مركز ابن مسعود الإسلامي بأديس أببا اليوم الخميس ١٩/٥/١٤٤٦ هے بزيارة القائم بأعمال سفارة دولة الكويت لدى إثيوبيا معالي الأستاذ عبد العزيز محمد حمادة - حفظه الله - والتقى بمدير المركز السيد إلياس أول وبنخبة من مشايخ المركز وأساتذته.

وقام سعادته خلال زيارته بجولة تفقدية في مكتب قناة النصيحة ومعهد دار الحديث وفصوله الدراسية ومكتبته العلمية، كما استمع إلى تقرير موجز عن أنشطة المركز وبعض إنجازاته العلمية والخيرية، وأبدى انبهاره لذلك، كما أبدى استعداد السفارة للوقوف مع المركز في تحقيق أهدافه.

حفظ الله دولة الكويت حكومة وشعبا ونشكر معاليه على هذه الزيارة ونسأل الله له التوفيق والسداد، والحمد لله رب العالمين.


___
🕌 ibnu Mas'oud islamic Center @merkezuna


🎓 በጉራጌ ዞን ጉብርዬ ከተማ በሚገኘው ነሲሓ መድረሳ  ለ3 ተከታታይ አመታት ሲያስተምራቸው የቆየውን ዱዓቶች በልዩ ድምቀት በማስመረቅ ላይ ይገኛል። በፕሮግራሙ ላይ ታላላቅ መሻይኾችና የነሲሓ ዳዕዋ አጋሮች ተገኝተዋል። አልሐምዱሊላህ!

አላህ ተመራቂዎቹን እውቀትን ይጨምራለቸው፣ ሙስሊሙን ማህበረሰብ የሚጠቅም ኸይር ስራ ሁሉ ያግራቸው።

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር
ጥቅምት 17/2017 ዓ.ል

____
🕌 ibnu Mas'oud islamic Center
@merkezuna


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አሰላሙዓለይኩም ወራሕመቱላሂ ወበረካትሁ

"ኑ-የጉራጌ ዞን ዳዕዋ ህያው እናድርግ" በሚል መርህ በጉብርየ ነሲሓ የዱዓት ማሰልጠኛ ተቋም ላለፉት 3 አመታት በከፍተኛ የዒልም ደረጃ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ  ብርቅዬ የሆኑ ዱዓቶች እና ኡስታዞች ለማስመረቅ ተዘጋጅተናል። አልሓምዱሊላህ!

ፕሮግራሙ በጉብርየ ከተማ እሁድ ጥቅምት 17 ቀን 2017 ዓ.ል ከጠዋቱ 3:00 ጀምሮ ይካሄዳል።

_
🕌 ibnu mas'oud islamic center
@merkezuna


በትናንትናው ዕለት በመርካቶ ልዩ ስሙ "ሸማ ተራ" በሚባለው አካባቢ በደረሰው ከባድ የእሳት አደጋ ግምቱ ከፍተኛ የሆነ ንብረት ወድሟል። ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለይሂ ራጂዑን!

በአደጋው በንብረታቸው ላይ ጉዳት ላደረሰባቸው ሁሉ መፅናናት፣ ትዕግስትና ብርታትን እንመኛለን።

ፈተናዎችን በፅናት ማለፍ የ ቅን የአላህ ባሮች መገለጫ ነው!

አላህ እንዲህ ብሏል፤

﴿ وَلَنَبْلُوَنَّكُمْ بِشَيْءٍ مِنَ الْخَوْفِ وَالْجُوعِ وَنَقْصٍ مِنَ الْأَمْوَالِ وَالْأَنْفُسِ وَالثَّمَرَاتِ وَبَشِّرِ الصَّابِرِينَ * الَّذِينَ إِذَا أَصَابَتْهُمْ مُصِيبَةٌ قَالُوا إِنَّا لِلَّهِ وَإِنَّا إِلَيْهِ رَاجِعُونَ * أُولَئِكَ عَلَيْهِمْ صَلَوَاتٌ مِنْ رَبِّهِمْ وَرَحْمَةٌ وَأُولَئِكَ هُمُ الْمُهْتَدُونَ ﴾

[ከፍርሃትና ከረኃብም በጥቂት ነገር፣ ከገንዘቦችና ከነፍሶችም፣ ከፍራፍሬዎችም በመቀነስ በእርግጥ እንሞክራችኋለን፡፡ ታጋሾችንም አብስር፡፡ እነዚያን መከራ፤ በነካቻቸው ጊዜ «እኛ ለአላህ፤ ነን እኛም ወደርሱ ተመላሾች» ነን የሚሉትን (አብስር)፡፡
እነዚያ በእነርሱ ላይ ከጌታቸው የኾኑ ምሕረቶች ችሮታም አልሉ፡፡ እነርሱም ተመሪዎቹ እነርሱ ናቸው!
[البقرة:155- 157]

ከአላህ የሚሰጠን ፀጋና ሲሳይ ብዙ ነውና
የጠፋ ንብረታችሁን በተሻለ እንዲተካ፣ ከተለያዩ ፀጋዎቹም በብዙ እንዲለግሳችሁ አላህን እንለምነዋለን። አሚን!

ማክሰኞ ጥቅምት 12/2017

ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር


_
Ibnu Mas'oud islamic center
@merkezuna


من ضيوف مركز ابن مسعود الإسلامي، يشرع فضيلة الشيخ الدكتور عبدالرحمن آل نابت -حفظه الله- اليوم الجمعة ٢٤ ربيع الأول ١٤٤٦ هـ بعد صلاة العصر في شرح "منظومة سلم الوصول إلى علم الأصول في توحيد الله واتباع الرسول" للحافظ الحكمي رحمه الله بمسجد بلال في مدينة بيشوفتو (دبرزيت)، وتستمر الدورة إلى يوم يوم الأحد ٢٦ ربيع الأول ١٤٤٦ هـ.

نسأل الله تعالى أن يجزي الشيخ خير الجزاء وأن ينفع به الإسلام والمسلمين

____
🕌 ibnu Mas'oud islamic Center @merkezuna


يقيم فضيلة الشيخ الدكتور عبدالرحمن حامد آل نابت -حفظه الله- درسا في شرح (منظومة أصول الفقه)  للشيخ العثيمين رحمه الله، وذلك بمسجد رحماء في مدينة كمبولتشا شمال إثيوبيا.

والشيخ أحد ضيوف مركز ابن مسعود الإسلامي في دورة ميراث الأنبياء الرابعة التي أقيمت في هذا الشهر.

نسأل الله تعالى أن يجزي الشيخ خير الجزاء وأن ينفع به الإسلام والمسلمين

____
🕌 ibnu Mas'oud islamic Center
@merkezuna


በ2017(1446/47)ቁርአን እና የዲን ትምህርት ፈላጊዎች ልዩ እድል

    በኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ስር የሚገኘው ዳሩል ሐዲሥ ኢንስቲትዩት ለአዋቂ ወንዶች የተመላላሽ የቁርኣን ሒፍዝ ፕሮግራም እና ኪታብ ትምህርት ፕሮግራም በማዘጋጀት ምዝገባ ጀምሯል። ከታች የተቀመጡትን መስፈርት የምታሟሉ  ተማሪዎች ከመስከረም  3 -መስከረም 9 ድረስ በኢብኑ መስኡድ ኢስላሚክ ሴንተር ዋና መርከዝ 18 አደባባይ በአካል በመቅረብ እንድትመዘገቡ ያስታውቃል።

 1. ለቁርአን ሒፍዝ ፕሮግራም
ቁርአን ነዘር በተጅዊድ የጨረሰ እና ቢያንስ 3ጁዝ የሀፈዘ የዲን ትምህርት እየተማረ የሚገኝ(መሰረታዊ የዲን ኪታቦችን የጨረሰ)
እድሜው ከ18 እስከ 25 የሆነ
     
2. በጀማሪ ጧሊበል ኢልም ደረጃ 
ቁረኣንና መሰረታዊ የአቂዳና ፊቅህ ኪታቦችን የቀራ

3. በመካከለኛ ጧሊበል ኢልም ደረጃ
በፊቅህ ፣ በአቂዳ፣ በነህው በሶርፍ መሰረታዊ መትኖችን የቀራ እና ዐረብኛ ማንበብ የሚችል
 ለሁሉም እርከኖች የጋራ መስፈርቶች
በጥሩ ስነ-ምግባር የታነጸ ለዚህም መረጃ ማቅረብ የሚችል።

የመርከዙን ደንቦች አክብሮ ለመማር ዝግጁ የሆነ።

ከተማረ በኋላ ዑማውን ለማገልገል ዝግጁ የሆነ።

መግቢያ ፈተና ማለፍ የሚችል።

ተያዥ ማቅረብ የሚችል።

👉 ትምህርቱ የሚሰጥበት ቦታ፡‐ 18 አደባባይ አካባቢ የሚገኘው ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር 

👉 ትምህርቱ የሚሰጥባቸው ቀናት
👉 ለቁርአን በሳምንት 6 ቀናት፤ ከሰኞ እስከ ቅዳሜ
👉 ለኪታብ በሳምንት 4 ቀናት ከሰኞ እስከ ሐሙስ
👉 ትምህርቱ የሚሰጥበት ሰዓት፡‐ ከጠዋቱ 3:00 እስከ 6:00 
👉 ለምዝገባና ለበለጠ መረጃ:- ስልክ 0912617007
                      
 ኢብኑ መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር

____
Ibnu Mas'oud islamic center
https://t.me/merkezuna


Forward from: ዳሩል ሀዲስ ኢንስቲትዩት Darul Hadith institute
📣የመዝጊያ ፕሮግራም

በኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር የዳሩል ሐዲስ የሸሪዓና የቋንቋ ኢንስቲትዩት ባለፈው አንድ ዓመትና በዚህ ክረምት ወራት ለወንድ ታዳጊዎችና ወጣቶች ሲሰጥ የቆየውን ትምህርት መጠናቀቅ ምክኒያት በማድረግ የተዘጋጀ ፕሮግራም

በዕለቱም

⚡️በተለያዩ ዳዒዎች የሙሀደራ ፕሮግራም

⚡️በተማሪዎች የሚቀርቡ  ልዩ ልዩ ፕሮግራሞች ይኖራሉ

🗓 አሁድ ጷጉሜ  03/2016

⏰ ከጠዋቱ 3:00-6:30 ጀምሮ

🕌 18 በሚገኘው ኢብን መስዑድ ኢስላሚክ ሴንተር ነሲሃ መስጂድ

https://t.me/darulhadis18

14 last posts shown.