Forward from: Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
ከ"ዘመናዊ" የጥንቆላ ወጥመዶች እንጠንቀቅ
~
በዚህ ዘመን ጥንቆላ መልኩን እየቀየረ እየመጣ እንደሆነ እያየን ነው። በእርግጥ የቀደመው ዓይነት ጥንቆላም ቢሆን ብዙም ገበያው አልቀዘቀዘም። የሺርክ እንቁላል የሚጥሉ በርካታ ጠንቋዮች ከገጠር አልፈው በየከተማው መሽገዋል። በሌላ በኩል "ለተማረው" እና ለሚያነበው የማህበረሰብ ክፍል ታልመው የሚቀርቡ የጥንቆላ ዓይነቶች መቅረብ ከጀመሩ ቆይተዋል። ጋዜጦችና መጽሔቶች እንዲሁም የሬዲዮ ፕሮግራሞች ሳይቀሩ ቁም ነገር አገኛለሁ ብሎ ለሚከታተላቸው ወገን ጥንቆላን ሲያቀርቡ ማየት የሚያሳዝን ነገር። ዛሬ ደግሞ እንደ ፌስቡክ ያሉ ፕላትፎርሞችን በመጠቀም የሰዎችን ህይወት፣ ሙያ፣ እድሜ፣ ጋብቻ፣ የኳስ ውድድር ውጤቶችን፣ ወዘተ ቀድመው "የሚተነብዩ"፣ የጥንቆላን ስራዎችን የሚያቀርቡ አካላት አሉ። እነዚህ ነገሮች በሸሪዐ ሚዛን እንደዋዛ መዝናኛ ተብለው የሚታለፉ አይደሉም። ውጤታቸውም ኢማንን የሚነካ ጥፋት ነውና መጠንቀቅ ይገባል። እነዚህን አፖችና ድረ ገፆች መጎብኘት ጠንቋይ ዘንድ እንደ መሄድ ነው። የሚያቀርቡትን "ትንበያ" ማመን ደግሞ ልክ በጠንቋይ ንግግር እንደማመን ነው።
ሃሳቤን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ በመፅሄቶች ላይ የሚቀርቡ ጥንቆላዎችን አስመልክቶ ሸይኽ ሷሊሕ ኣሊ ሸይኽ የተናገሩትን አቀርባለሁ። ሸይኹ እንዲህ ይላሉ፡-
“በዚህ ዘመን ብዙ ሰው ቢዘነጋውም በግልፅ ከኮከብ ቆጠራ ጥንቆላ ውስጥ የሚገባው በመፅሄቶች በብዛት የሚለቀቀው ኮከብ ቆጠራ (astrology) እየተባለ የሚጠራው ነው። ጋዜጦች ላይ አንድ ገፅ ወይም ከዚያ ያነሰ ይመድቡለታል። ሊዮ፣ እስኮርፒዮን፣ ታውረስ፣ ወዘተ እያሉ የአመቱን ኮከብ ንድፍ ይሰራሉ። ከእያንዳንዱ ኮከብ ፊት ይከሰታል ብለው የሚያስቡትን ይፅፋሉ። ይሄ የከዋክብትን እንቅስቃሴና ሁኔታ ተመልክቶ ምድር ላይ የሚደርሰውን ማወቅ ይቻላል የሚል ትምህርት ነው። ይሄ ከጥንቆላ አይነቶች አንዱ ነው። በመፅሄቶችና ጋዜጦች ላይ ይሄ ነገር ከኖረ ጥንቆላ አለባቸው ማለት ነው። ስለዚህ ሺርክ፣ የሩቅ እናውቃለን የሚል ሙግት፣ ጥንቆላና ኮከብ ቆጠራ ስለሆነ የያዘው ሊቃወሙት ይገባል። እያንዳንዱ ሙስሊም እንዲህ አይነቱን ነገር ከቤቱ ሊያስገባ አይገባም። ማንበብና መከታተልም የለበትም። ምክንያቱም ይህን ኮከብ ቆጠራና በውስጡ ያለውን መከታተል ማለት እንዲሁ ለማወቅ ብቻ ቢሆን እንኳን የተከለከለ ነው። ምክንያቱም ላይቃወም ጠንቋይ ዘንድ መሄድ ነውና።
የተወለደበትን ኮከብ ሊያውቅ ወይም ከሱ ጋር የሚሄደውን ኮከብ ሊያውቅ አስቦ የኮከብ ቆጠራ ያለበትን ገፅ ያነበበ ሰው ልክ ጠንቋይ እንደጠየቀ ነው። ስለዚህ አርባ ቀን ሶላቱ ተቀባይነት የለውም። በነዚህ የኮከብ ቆጠራ ውስጥ ያለውን ካመነ ደግሞ በሙሐመድ ﷺ ላይ በወረደው ያለጥርጥር ክዷል።” [ኪፋየቱል ሙስተዚድ፡ 193]
=
የቴሌግራም ቻናል፡-
https://t.me/IbnuMunewor