TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
ኑ እናንብብ

19 Jan 2021, 18:53

Open in Telegram Share Report

Forward from: ፍልስፍና ለላቀ አስተሳሰብ Philosophy
ሃይማኖተኛ የበዛባት፤ መንፈሳዊ ያነሰባት የዛሬዋ ኢትዮጵያ!
✍️እሸቱ ብሩ

ሐገራችን 98 ከመቶ የሚሆነው ህዝቧ አማኝ እንደሆነ የህዝብና የቤት ቆጠራ መረጃዎችና የተለያዩ ጥናቶች ያረጋግጣሉ፡፡ ከነዚህ ውስጥ ደግሞ በአማኝነት የአንበሳውን ድርሻ የያዙት የክርስትና እና የእስልምና እምነት ተከታዮች ናቸው፡፡ አማኝ ሲበዛ ፈሪዓ እግዚአብሔር ይኖራል፡፡ ሰው ከፊቱ የሚፈራው ነገር ካለ ራሱንም ሌሎችንም ከክፉ ይጠብቃል፡፡ የትኛውም ሃይማኖት ሰውን ሰብዓዊ እንዲሆን፣ መልካም ስነምግባር ያለው ዜጋ እንዲሆን፤ ሰው ወደበጎ ተግባር እንዲያመራ፤ ሰላም፣ ፍቅር፣ አንድነት፣ መተዛዘንና መተባበር እንዲኖር የሚሰብክ ነው፡፡ የተለየ ክፉ ተልዕኮ ያለው ሃይማኖት አለ ብዬ አላስብም፡፡ በርግጥ በየትኛውም ሃይማኖት ውስጥ ተሰግስገው ያሉና ድብቅ አጀንዳ ያላቸው ጥቂት ሃይማኖተኞች መኖራቸው አጠያያቂ አይደለም፡፡ ሃይማኖቱን ለገዛ ራሱ ፍላጎትና ክፉ ዓላማው የሚጠቀምበት ጥቅመኛና ተንኮል የተጠናወተው ሃይማኖተኛ መኖሩ ሃቅ ነው፡፡ ሃይማኖተኛ ሁሉ በጎ ዓላማ፣ ሠናይ ተልዕኮ አለው አይባልምና!

የሆነው ሆኖ ሃይማኖተኛ መብዛቱ ጥሩ ሆኖ ሳለ ከሃይማኖተኛ የሚጠበቅ መልካም ስነምግባርና በጎ ስራ እያነሰ መሆኑና እየጠፋ መሄዱ ግን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ መንፈሳዊነት የኮሰሰበት ሃይማኖተኝነት እውነተኛ ሃይማኖተኝነት አይደለም፡፡ ‹‹እምነት ያለስራ ከንቱ ናት!›› እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ ሃይማኖቱን የማይኖርበት ሃይማኖተኛ ከኢአማኙ አይለይም፡፡ እምነቱን በስራ ከማይገልጽ አስመሳይ አማኝ ይልቅ አንዴ የካደው ኢአማኝ ይሻላልና፡፡

የሃይማኖት ግቡ መንፈሳዊነት ነው፡፡ መንፈሳዊነት ማለት ሰው የስጋውን ዓለም አሸንፎ፣ ከራስወዳድና ከስግብግብ አኗኗሩ ወጥቶ፣ ስሜቱንና አምሮቱን ተቆጣጥሮ፣ ፍላጎቱን አደብ አስገዝቶ በራስ ላይ መንገስ ማለት ነው፡፡ መንፈሳዊነት፣ በፍቅር፣ በሰላም፣ በአንድነት መኖር ነው፡፡ የዛሬው አማኝ ሰው የራሱ ንጉስ ይሆን ዘንድ መንፈሳዊ ሕይወትን የሙጥኝ ማለት ሲጠበቅበት፤ እሱ ግን በዓለማዊ አምሮት፣ በስጋ ምኞት ነሁልሎ፣ በዘረኝነት አስተሳሰብ ተሸንፎ ራሱንና ሰውነቱን ዘንግቷል፡፡ የመኖር ሚስጥሩን፣ የሕይወቱን ትርጉም፣ የሰውነቱን አንድምታ ከገንዘብ ጋር ብቻ የሚያገናኝ አማኝም ይሁን ማንም ሰው ቢሆን መገንዘብ የጎደለው ነው፡፡ ገንዘብ የማይገዛው፣ ቁስ የማይተካው ነው ሰውነት ማለት!

መንፈሳዊነት ትርጉሙ ረቂቅ ነው፤ አኗኗሩ ጠሊቅ ነው፡፡ መንፈሳዊነት የሚታየውን ብቻ ሳይሆን በስጋ ዓይን መታየት የማይችለውን ሁሉ ማየት መቻል ነው፡፡ በሚታየው ዓለም በስተጀርባ ያሉትን ሚስጥራት በድብቁ ዓይን፣ በስውሩ አዕምሮ ማየት የሚቻለው በመንፈሳዊው ዓለም ልዩ ጥበብ ነው፡፡ ሳይንስ የሚታዩትን አጉልቶ ወይም አጥርቶ እንዲታይ የተለያዩ መሣሪያዎችን ፈበረከ እንጂ የማይታየውን ያይ ዘንድ አይችልም፡፡ የሳይንስ መነፅር መታየት የሚችለውን ወይም የተፈጠረን ነገር ነው የሚያሳየው፤ የመንፈሳዊ መነፅር ግን በሰው ዓይን ሊታይ የማይችለውን ሁሉ ያሳያል፡፡ የመንፈሳዊ መነፅሩ ከውስጥ ወደውጭ፤ ከውጭ ወደውስጥ ማሳየት የሚያስችል ነው፡፡ የመንፈሳዊ ዓይን የተተከለው ከውስጥ ነውና፡፡ መንፈሳዊነት ስሩ ውስጠት ነው፡፡ መነሻው በጎ ሕሊና ነው፤ መድረሻው ሰብዓዊነት ነው፡፡ መንፈሳዊነት ተቀድቶ የሚፈስሰው ከነፍስ ነው፡፡ ሰው አካል ያለው መንፈስ ነውና!

ለዚህ ነው ሲኤስ ሊዊስ፡-

‹‹አንተ ነፍስ የለህም፡፡ አንተ ራስህ አካል ያለህ ነፍስ ነህና!›› የሚለን፡፡

አዎ! የሚታየውን ተፈጥሮን መመርመር ቁሳዊ ምርምር ነው፡፡ እሱ ሳይንስ ይባላል፡፡ ሳይንስ የሚታየውን ዓለም ይመረምራል፡፡ መንፈሳዊነት ግን የማይታየውን ዓለም ነው የሚመረምረው፡፡ ሳይንስ የሰው ልጅ አካላዊ ተፈጥሮ ይመረምራል፤ አካሉም ሲታወክ ያክማል፡፡ መንፈሳዊ ጥበብ ግን የሰው ሕይወትን ይመረምራል፣ አስተሳሰቡን ይመዝናል፣ የአመለካከት ስብራቱን ይጠግናል፤ የወደቀውን ሰውነት ያነሳል፣ የጨለመውን ልቦና እንደገና አብርቶ ያዋቅራል፤ አዕምሮ በአዲስ ብርሃን ያጥለቀልቃል፡፡ መንፈሳዊነት የሰው ፍላጎቱን መርምሮ፣ ስሜቱን ፈትኖ፣ በራሱ ላይ ባለስልጣን እንዲሆን ሃይልን ይሰጣል፡፡

መንፈሳዊነት የሚታየውን ትዕይንተ ዓለም ተሸክሞ የያዘው የማይታየውን ሃይል መረዳት ነው፡፡ የተፈጥሮ ህጉን ከመረዳት አልፎ ከህጉ በስተጀርባ ያለውን ቀመር መገንዘብም ጭምር ነው መንፈሳዊነት ማለት፡፡ የተፈጥሮን ህግ አክብሮ መኖርንማ ዓለማዊውም ሳይወድ በግዱ ተገዝቶ ይኖርበታል፡፡ መንፈሳዊነት ግን ከዛ ያለፈና ጉዞው የረቀቀና የጠለቀ ነው፡፡ መንፈሳዊነት የተፈጥሮ ህጉንና ቀመሩን ተረድቶና አክብሮ መኖር ብቻ ሳይሆን የቀመሩን ባለቤትም ፈልጎ ማግኘት ነው፡፡

ማነው ፀሐይና መሬት ሳይገፋፉ ተጠባብቀውና ተቻችለው እንዲኖሩ ያደረገው ብሎ መጠየቅና ለጥያቄ መልስ መፈለግም ጭምር ነው መንፈሳዊነት፡፡ ማነው ሰውና እፅዋቱ ተስማምተው እንዲኖሩ ይህን ውብ ዓለም የፈጠረው ብሎ መፈለግ ነው መንፈሳዊነት፡፡

ሰው ሜርኩሪና ቬነስ ላይ ልኑር ቢል አይችልም፤ ምክንያቱም ሙቀቱ ይፈጀዋል፡፡ ጁፒተር፣ ማርስ፣ እና ሌሎች ከመሬት ውጪ የሆኑ የዓለም ማዕከላት ላይ ልኑር ቢል ብርዱና ቅዝቃዜ ይገድለዋል፡፡ ማርስ ላይ መኖር ይቻላል የሚሉ የጥናት መላምቶች ነገር ግን በተግባር ገና ያልተረጋገጡ ምርምሮች እንዳሉ ሳይዘነጋ! ታዲያ ማን ነው ይሄን ሰፊ፣ ግዙፍና ረቂቅ ትዕይንተዓለም ከሚደንቀው ከሰው ልጅ ውስጣዊ ውስብስብ የአዕምሮ ስርዓትና አካላዊ አወቃቀር ተፈጥሮ ጋር እንዲስማማና የምንኖርባትን መሬት ለሰው እንድትመች፣ ለምግቡና ለመጠጡ፣ ለደስታውና ለፍስሃው እንድትሆን አድርጎ የፈጠረው ብሎ ማሰስ ነው መንፈሳዊነት፡፡ መንፈሳዊነት የተፈጥሮን አናጢና ሰሪ ብቻ በመፈለግ አያበቃም፡፡ ልክ እንደቡድሂስቱ ራስን ፈልጎ ማግኘትም ነው መንፈሳዊነት፡፡ ወደውስጥም ወደውጪም መመጥለቅ ነው መንፈሳዊነት፡፡ ፍላጎትን መግደል፣ ምኞትን መቅበር፣ ስጋን ማሸነፍ፣ በራስ ላይ መንገስ፣ ራስን መግዛት ሁሉ መንፈሳዊነት ነው፡፡ ሃይማኖት ግቡ መንፈሳዊ ሰውነትን መፍጠር ነውና፡፡

3.9k 0 15
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot