"What lies behind us and what lies before us are tiny matters compared to what lies within us." – Ralph Waldo Emerson
___
ተፈጥሮን 'የማረም' አባዜ አለብን... መሆንን አንቀበልም - መሆንን አናደንቅም... ይልቁን 'እንዲሆን በምንፈልገው' ውስጥ እንጠፋለን... 'እንዲህ መሆን' ነበረበት እያልን እንቆጫለን...
___
በዙሪያችን ያሉ ዕጽዋት፣ ወንዞች፣ ተራራ፣ መንገዶች፣ ሰዎች ሳይቀር 'እንዲሆኑ በምንፈልገው' ሁኔታ ግዴታ ውስጥ ወድቀው ተፈጥሮአዊነት ተሰልበዋል...
አንድ የ Landscape Architect ወዳጄ እንደነገረኝ የወንዞችን ውበት በመጠበቅ ስም የወንዙን ውሃ ከከባቢው ጋር የሚኖረውን መስተጋብር የሚቀንሱ ግንባታዎችን መስራት፣ ለወንዙ መጥፋት የመጀመሪያው እርከን ነው... የሲሚንቶ ግድግዳ ሰርተህ ውሃውን ከአፈሩ ስትነጥለው ወንዙ መድረቅ ይጀምራል...
የወንዙ ውሃ ከአፈሩ ጋር መስተጋብር አለው፣ በዙሪያው ከሚበቅሉ ዛፎች፣ በውስጡ ካሉ ነፍሳት፣ ከሚቀላቀሉት ኬሚካሎች... ወዘተ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት አለው...
"Look deep into nature, and then you will understand everything better." – Albert Einstein
ሌላ ወዳጄ ደግሞ አንድ ከተማ በአስፓልት ብቻ እየተሸፈነች የምትሄድ ከሆነ የከርሰ ምድር ውሃ እጥረት እንደሚገጥማት አውግቶኛል... የክረምት ዝናብ ወደ አፈር ውስጥ መስረግ አለበት... ይህ ካልሆነ ሁለት ጉዳት አለው... ከተማዋ - ክረምት በጎርፍ ትጠቃለች፣ በበጋ ከፍተኛ የውሃ እጥረት ያሰቃያታል...
የተፈጥሮን መስተጋብራዊ ዑደት መረዳት ተፈጥሮን ለመቅረብ የመጀመሪያው መስፈርት ነው... እርስ በእርሱ በተሳሰረ ዓለም ውስጥ የትም ቦታ የሚሆን አንድ ነገር ለሌላኛው የሚያተርፈው ጉዳትና ጥቅም አለ...
ሁሌም ቢሆን ተፈጥሮን እንዲሆን በምትፈልገው እሳቤህ ውስጥ ከመጨቆንህ በፊት ሊሆን የሚገባውን ለማሰብ ጊዜ መውሰድና ጠቢባኑን ማድመጥ ግዴታህ ነው...
"Nature does not hurry, yet everything is accomplished." – Lao Tzu
ይህን ሃሳብ ይዘን ወድ ሰው እንምጣ...
መልክ የሌለው የፍጹማዊነት ህመም አለብን... እንከን የለሽ ሆነን ለመታየት እንሻለን... ይህ እንዴት ይሆናል? ኑረት - ፍጹማዊነት የሚል ቃል ከመዝገበ ቃላቷ ውስጥ የለም... እኛ ነን ይህን የፈጠርነው... ሕይወት ሕብራዊት ናት... [Yin እና Yang] ወይም ነገሩን ገልብጠን በሌላ አውድ ብንረዳው ተፈጥሮ እንደወረደች ውብ ናት፤ ጉድለትን የፈጠርነው እኛ ነን...
"Nature knows no indecencies; man invents them." – Mark Twain
ሴቲቱ መልኳ 'እንዲሆን በሚፈለገው' ግዴታ ውስጥ ወድቆ ወርቅ ቅብ ሆናለች... አለባበሰዋ በማሕበረሰብ ድንጋጌ ተመትሮ ከላይ እስከ ታች ብልጭልጭ ብላለች... ገላዋ በዘመን የውበት ሚዛን ተሸልቶ በአርተፊሻል ገላ ተለብጣ ትውላለች... ተፈጥሮአዊ ሴት ማየት ሲያምርህ ይቀራል... ራሷን የተቀበለች ሴት ማግኘት ልዩ ጸሎት ይጠይቃል...
"To be beautiful means to be yourself. You don’t need to be accepted by others. You need to accept yourself." – Thich Nhat Hanh
ዝነኞች፣ መሪዎች፣ አርቲስቶች... ወዘተ 'እንደሚጠበቅባቸው' እንጂ እንደ ወረደ ተፈጥሮአቸው Act ስለማያደርጉ የማይጋባ ሳቅ ይስቃሉ፣ ለልብ የማይጥም ቃል ይደረድራሉ፣ ዘመን መላቅጡን ባሳጣው አለባበስ ተጨቁነው ይቀርባሉ...
"To be yourself in a world that is constantly trying to make you something else is the greatest accomplishment." – Ralph Waldo Emerson
____
የሆነን እንደመሆኑ ካልተቀበሉት የዕድሜ ልክ ሕመምን፣ ብሎም የመጥፊያ ቅመምን ያዘጋጃል...
ፊትህ ላይ የወጣብህን ማድያት መቀበል የየዕለት ሕመምህን ያስቀረዋል... አለመቀበል ግን በራስ የመተማመን አቅምህን ከመስለብ በዘለለ ማጥፊያ የመሰለህን ሁሉ ከፊትህ እየዶልክ ዥንጉርጉር ገጽ እንድትላበስ ያደርግሃል...
የሰውነትሽን 'እንከን' አለመቀበል በአደባባይ እንዳትቆሚ ማድረጉ ብቻ አይደለም ችግር... አቅምሽን፣ ጸጋሽን፣ መቻልሽን ሁሉ ነጥቆ ተሰባብረሽ በተደበቅሽበት ለሌላ ሕመም ምንጭ ሆኖ ይቀጭሻል...
"You are imperfect, permanently and inevitably flawed. And you are beautiful." – Amy Bloom
___
የሆነን መቀበል የአድናቆት ድርቅ እንዳይመታን ብቻ አይደለም - ከሆነው በላይ እንዳይሆንብንም ዋስትና ነው...
____
'Acceptance' በሚል ርዕስ የጫርኳት ማስታወሻ ላይ የተጋራሁዋችሁን የገጣሚት ሰናይት አበራ “በየፈርጁ” የምትል ጥልቅ ግጥም እዚህም ልድገም...
____
".. ለምን እንጨነቅ
ለምን እንሳቀቅ
የእርጥብ ቅል ክብደቱ – ነውና እስከሚደርቅ
ለምን እንሳቀቅ
.. ሁሉም በየፈርጁ
ሁሉም በያይነቱ
የፊቱን ፈንጣጣ – በፈርጥ ቢመስለው
ያንገቱን ስር እንቅርት – በውቅርት ቢያስጌጠው
ሁሉን ተቀብሎ…
እንደ አዶከበሬ – አሜን አሜን ቢለው
ለተመልካች እንጂ – ለያዘው ቀላል ነው።"
[እኛ - 1988]
____
ይህ ጽሑፍ የሚነበብ ፊርማ አለው...
እነሆ:
"There is no need to be perfect to inspire others. Let people get inspired by how you deal with your imperfections." – Anonymous
____
@bridgethoughts