#ብፅዕት_ነሽ
ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
አምነሽ የተቀበልሽ ብፅዕት ነሽ ድንግል (2)
በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት ዓለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልአክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ሰላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ ሥላሴ
ክብርን የተመላሽ ምልዒተ ውዳሴ
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ትወልጂያለሽ ጌታን በመንፈስ ቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነግሣል ዘላለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሰማዩ ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ከእግዚአብሔር ተልኮ የነገረሽን ቃል
አምነሽ የተቀበልሽ ብፅዕት ነሽ ድንግል (2)
በገሊላ ሳለሽ በናዝሬት ከተማ
ከመላዕክት ዓለም ከሰማይ ከራማ
ብርሃናዊው መልአክ ተሸክሞ ዜና
ደስታን አበሰረሽ በታላቅ ትህትና
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ሰላም ለኪ ማርያም ድንግል ሆይ አትፍሪ
መዓዛሽን ወዷል እግዚአብሔር ፈጣሪ
ሞገስ አግኝተሻል በቅድመ ሥላሴ
ክብርን የተመላሽ ምልዒተ ውዳሴ
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ትወልጂያለሽ ጌታን በመንፈስ ቅዱስ
ትጠሪያለሽ ስሙን ብለሽ ኢየሱስ
በያዕቆብ ወገን ይነግሣል ዘላለም
ለመንግስቱ ሽረት ፍጻሜ የለውም
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
ዘመድሽ ኤልሳቤጥ ሳትወልድ የኖረች
በእርጅና ዘመኗ ወንድ ልጅ ጸነሰች
እያለ ሲነግርሽ የሰማዩ ምስጢር
ይሁንልኝ ብለሽ ተቀበልሽ በክብር
እኔም ላመስግንሽ ማርያም ድንግል
እንደ ብስራታዊው እንደ ገብርኤል
እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን( መዝ 150 - 6 )
የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መዝሙሮችን ለማግኘት
ይሄን link በመንካት ይቀላቀሉን 👇👇👇
@ney_ney_emye_maryam
#ሼር
🙏🙏🙏🙏🙏
🕊ለወዳጅ ለዘመዶ ያካፍሉ🕊