የሰለምቴዎች ቻናል


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


وَمَنْ أَحْسَنُ قَوْلًا مِّمَّن دَعَا إِلَى اللَّهِ وَعَمِلَ صَالِحًا وَقَالَ إِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينَ

ወደ አላህ ከጠራና መልካምንም ከሠራ፣ «እኔ ከሙስሊሞች ነኝ» ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው?

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


እዚህ አንቀጽ "የሚሰጥ" ለሚለው የገባው ቃል "ዩሥሊም" يُسْلِمْ እንደሆነ ልብ አድርግ! ስለዚህ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ማለት "ሁለተኛ ወይም ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ" ሳይሆን የመጀመሪያ እና ዐቢይ የዲን ቅርንጫፍ ነው፥ "ዐቂዳህ ምንድን ነው? ሲባል "እርሱ ሁለተኛ እና ንዑስ የዲን ቅርንጫፍ ነው" ብሎ ከመናገር በላይ የሚያሳፍር ነገር የለም። አምላካችን አሏህ ፈሣድን ከሚያስፋፉ ኢሕዋኑል ሙፍሢዱን ይጠብቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


ዐቂዳህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥103 የአሏህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا

"ዐቂዳህ" عَقِيدَة የሚለው ቃል "ዐቀደ" عَقَدَ ማለትም "ቋጠረ" "ያዘ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መቋጠር" "መያዝ" ማለት ነው፥ "ዐቃኢድ" عَقَائِد ደግሞ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ለሚለው ብዙ ቁጥር ነው፦
113፥4 “በየተቋጠሩ” ክሮች ላይ ተፊዎች ከኾኑት ደጋሚ ሴቶችም ክፋት፡፡ وَمِن شَرِّ ٱلنَّفَّٰثَٰتِ فِى ٱلْعُقَدِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የተቋጠሩ" ለሚለው የገባው ቃል "ዑቀድ" عُقَد እንደሆነ ልብ አድርግ! ለምሳሌ፦ የጋብቻ ቃል ኪዳን "ዑቅደቱን ኒካህ" عُقْدَةُ النِّكَاح ተብሎ ይጠራል፦
2፥237 ለእነርሱም መወሰንን በእርግጥ የወሰናችሁላቸው ስትኾኑ ሳትነኳቸው በፊት ብተፈቷቸው ካልማሩዋችሁ ወይም ያ "የጋብቻው ውል" በእጁ የኾነው ባልየው ካልማረ በስተቀር የወሰናችሁት ግማሹ አላቸው፡፡ وَإِن طَلَّقْتُمُوهُنَّ مِن قَبْلِ أَن تَمَسُّوهُنَّ وَقَدْ فَرَضْتُمْ لَهُنَّ فَرِيضَةً فَنِصْفُ مَا فَرَضْتُمْ إِلَّا أَن يَعْفُونَ أَوْ يَعْفُوَ الَّذِي بِيَدِهِ عُقْدَةُ النِّكَاحِ

እዚህ አንቀጽ ላይ "የጋብቻው ውል" ለሚለው የገባው ቃል "ዑቅደቱን ኒካህ" عُقْدَةُ النِّكَاحعُقَد ነው፥ ስለዚህ አንድ ሰው እኔን፡- "ዐቂዳህ" ምንድነው? ብሎ ቢጠይቀኝ ጥያቄው፡- በልብህ አምነህ የያዝከው እና የቋጠርከው ምንድነው? ማለቱ ነው።
ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ሸሪዓዊ ፍቺው ደግሞ "አንቀጸ እምነት" "ዶግማ" ማለት ነው፥ "ዶግማ" δόγμα የሚለው ቃል የግሪክ ቃል ሲሆን "መሠረት" "መርሕ" "አንቀጸ እምነት"creed" ማለት ነው፦
ሡነን አድ ዳርሚይ መጽሐፍ 1 ሐዲስ 231
ዐብዱር ረሕማን ኢብኑ አባን እንደተረከው፦ "የአሏህ መልእክተኛ"ﷺ":እንዲህ አሉ፦ "የሙሥሊም ልብ በሦስት ጉዳይ "አያምንም" ጀነት የሚገባበት ቢሆን እንጂ፥ እኔም፦ "ምንድን ናቸው? አልኩኝ። እርሳቸው፦ "ለአሏህ ብሎ በኢኽላስ መሥራት፣ ለአሚር ቅን ምክር መስጠት እና ጀመዓን አጥብቆ መያዝ"። عَنْ عَبْدِ الرَّحْمَنِ بْنِ أَبَانَ رَسُولِ اللَّهِ صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ قَالَ :" لَا يَعْتَقِدُ قَلْبُ مُسْلِمٍ عَلَى ثَلَاثِ خِصَالٍ إِلَّا دَخَلَ الْجَنَّةَ "، قَالَ : قُلْتُ : مَا هُنَّ؟، قَالَ : إِخْلَاصُ الْعَمَلِ لِلَّهِ، وَالنَّصِيحَةُ لِوُلَاةِ الْأَمْرِ، وَلُزُومُ الْجَمَاعَةِ،

እዚህ ሐዲስ ላይ "የዕተቂዱ" يَعْتَقِدُ የሚለው "ዩእሚኑ" يُؤْمِنُو በሚል የመጣ ነው፥ ቁርኣን ላይ "ኢማን" إِيمَان የሚለው "ኢዕቲቃድ" اِعْتِقَاد ማለት ነው፦
5፥89 አሏህ በመሐላዎቻችሁ በውድቁ አይዛችሁም፥ ግን መሐላዎችን "ባሰባችሁት" ይይዛችኋል፡፡ لَا يُؤَاخِذُكُمُ اللَّهُ بِاللَّغْوِ فِي أَيْمَانِكُمْ وَلَـٰكِن يُؤَاخِذُكُم بِمَا عَقَّدتُّمُ الْأَيْمَانَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ባሰባችሁት" ለሚለው የገባው ቃል "ዐቀድቱም" عَقَّدتُّم ሲሆን "በወጠናችሁት" ማለት ነው፥ "ዐቅድ" عَقْد ማለት በልብ ውስጥ ያለ "ውጥን" ማለት ሲሆን በልብ ውስጥ የሚቀመጥ ውጥን ደግሞ እምነት ነው።
አርካኑል ኢማን "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ናቸው፥ "ዐቀዲይ" عَقَدِيّ ወይም "ዐቃኢዲይ" عَقَائِدِيّ ማለት "ዶግማዊ"dogmatic" ማለት ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ማለት "ከአሏህ በስተቀር በሐቅ የሚመለክ አምላክ የለም" ማለት ነው፥ "ኢማን" إِيمَٰن ማለት "እምነት" ማለት ሲሆን የኢማን ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው፦
ኢማም ሙሥሊም መጽሐፍ 1, ሐዲስ 60
አቢ ሁረይራህ እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ "ኢማን ከሰባ ወይም ከስልሳ በላይ ቅርንጫፎች አሉት፥ ትልቁ ቅርንጫፍ "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" ማለት ነው"። عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم ‏ “‏ الإِيمَانُ بِضْعٌ وَسَبْعُونَ أَوْ بِضْعٌ وَسِتُّونَ شُعْبَةً فَأَفْضَلُهَا قَوْلُ لاَ إِلَهَ إِلاَّ اللَّهُ

"ነፍይ" نَفْي ማለት “ማፍረስ” ማለት ሲሆን ነፍይ “ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ ነው፥ “ኢስባት” إِثْبَات ማለት “ማጽደቅ” ማለት ሲሆን ኢስባት “ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه ነው፦
2፥256 “በጣዖት የሚክድ እና በአሏህ የሚያምን ሰው ለእርሷ መበጠስ የሌላትን ጠንካራ ገመድ በእርግጥ ያዘ”፡፡ فَمَن يَكْفُرْ بِالطَّاغُوتِ وَيُؤْمِن بِاللَّهِ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ لَا انفِصَامَ لَهَا

“ላ ኢላሀ” لَا إِلَـٰهَ በጣዖት መካድ ሲሆን “ኢለል ሏህ” إِلَّا اللّٰه በአሏህ ማመን ነው፥ ከአርካኑል ኢማን አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "አመንቱ ቢላህ" آمَنْتُ بِاللَّه ነው። "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه የሚለውን ጠንካራ የአሏህን ገመድ መያዝ "ዐቂዳህ" عَقِيدَة ይባላል፦
3፥103 የአሏህን ገመድ ሁላችሁም ያዙ። وَاعْتَصِمُوا بِحَبْلِ اللَّهِ جَمِيعًا

"ያዙ" የሚለው ይሰመርበት! ይህ ገመድ ሰዎች ከጀሀነም እሳት ጉድጋድ አፋፍ ላይ እያሉ ተንጠንጥለው የሚድኑበት ገመድ ነው፦
3፥103 በእሳት ጉድጓድ አፋፍም ላይ ነበራችሁ፥ ከእርስዋም አዳናችሁ፡፡ وَكُنتُمْ عَلَىٰ شَفَا حُفْرَةٍ مِّنَ النَّارِ فَأَنقَذَكُم مِّنْهَا

አርካኑል ኢሥላም "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ናቸው፥ "ዐቂዲያህ" عَقِيدِيَّة ወይም "ዐቃዒዲያህ" عَقَائِدِيَّة ማለት "ዶግማውያን"dogmatism" ማለት ነው። ከአርካኑል ኢሥላም አንዱ የሆነው የመጀመሪያው እና ዋናው "ላ ኢላሀ ኢለል ሏህ" لَا إِلَـٰهَ إِلَّا اللَّه ነው፥ ሙሉ ሁለንተናውን ለአሏህ የሰጠ ሙሥሊም ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፦
31፥22 እርሱ መልካም ሠሪ ሆኖ ፊቱን ወደ አሏህ የሚሰጥም ሰው ጠንካራ ገመድን በእርግጥ ያዘ፡፡ وَمَن يُسْلِمْ وَجْهَهُ إِلَى اللَّهِ وَهُوَ مُحْسِنٌ فَقَدِ اسْتَمْسَكَ بِالْعُرْوَةِ الْوُثْقَىٰ






Video is unavailable for watching
Show in Telegram
◆▮አስገራሚ ትምህርት▮◆

◍በዘረኘት ሰክራችሁ ሰው እየገደሉ ላሉ ዘረኞች እጠር ያለች መልእክት።

◍ሰለ ተራዌህ ሰላት መቸ ተጀመረ እንደት ተጀመረ!?
ሌሎችም  ትምህርቶች


👉ልብን የሚያረጋጋ ቲላዋ👂


◆▮ውይይት▮◆

"ሥላሴን ባይብል አያቀውም"።
"እኛነት በቁርአን"

◍ወንድም አብዱል ከሪም 
◍ሌሎችም
           🅥🅢
◍ ከወገናችን መሠለ
◍ሌሎችም


"ረብ" رَبّ ማለት "ጌታ" ማለት ነው፥ የረብ ብዙ ቁጥር "አርባብ" أَرْبَابً ሲሆን "ጌቶች" ማለት ነው። አሏህን በአምልኮቱ እና በጌትነቱ መታዘዝ ኢሥላም ሲሆን ይህንን ሐቅ ካስተባበሉ ሑጃህ እንዲቆምባቸው እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ በሏቸው፦
3፥64 ምቢ ቢሉም፡- "እኛ ሙሥሊሞች መኾናችንን መስክሩ" በሏቸው፡፡ فَإِن تَوَلَّوْا فَقُولُوا اشْهَدُوا بِأَنَّا مُسْلِمُونَ

አምላካችን አሏህ በዲኑል ኢሥላም ያጽናን! ሙሥሊም አድርጎ ወደ እርሱ ይውሰደን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


ዲኑል ኢሥላም

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

አምላካች አሏህ በተለያየ ዘመነ መግቦት"dispensation" መልእክተኛ ልኳል፥ ያ የሚላከው ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ አማኞች ሊታዘዙት እንጂ አልተላከም፦
4፥64 ማንንም መልእክተኛ በአሏህ ፈቃድ ሊታዘዙት እንጂ አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن رَّسُولٍ إِلَّا لِيُطَاعَ بِإِذْنِ اللَّهِ

"ኢዝን" بِإِذْن ማለት "ፈቃድ" ማለት ሲሆን አንድ አማኝ የተላከው መልእክተኛ መታዘዝ የአሏህ ፈቃድ ነው፥ በዚህም ኑሕ፣ ሁድ፣ ሷሊሕ፣ ሉጥ፣ ሹዕይብ፣ ዒሣ ወዘተ "ታዘዙኝ" በማለት ይናገራሉ፦
26፥108 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥126 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥144 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥163 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
26፥169 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ
3፥50 አሏህንም ፍሩ! ታዘዙኝም፡፡ فَاتَّقُوا اللَّهَ وَأَطِيعُونِ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዘዙኝ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑኒ" أَطِيعُونِ ነው፥ አምላካችን አሏህ ተወዳጁ ነቢያችንን"ﷺ" መታዘዝ እንዳለብን ሲናገር "መልእክተኛውን ታዘዙ" በማለት ነው፦
24፥56 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፣ ምጽዋትንም ስጡ፣ መልእክተኛውን ታዘዙ! ለእናንተ ሊታዘንላችሁ ይከጀላልና፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ وَأَطِيعُوا الرَّسُولَ لَعَلَّكُمْ تُرْحَمُونَ

እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አጢዑ" أَطِيعُوا እንደሆነ አንባቢ ልብ ይለዋል። ቅሉ እና ጥቅሉ ግን ሰዎች ለአሏህ "ታዘዙ" የተባሉበት ትእዛዝ ግን ለእርሱ ብቻ አምልኮታዊ መታዘዝ ነው፦
22፥34 አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው፡፡ ለእርሱም ብቻ ታዘዙ! ለአሏህ ተዋራጆችንም አብስራቸው፡፡ فَإِلَـٰهُكُمْ إِلَـٰهٌ وَاحِدٌ فَلَهُ أَسْلِمُوا ۗ وَبَشِّرِ الْمُخْبِتِينَ

"አምላካችሁም አንድ አምላክ ብቻ ነው" ካለ በኃላ "ለእርሱም ብቻ ታዘዙ" በማለት ያስቀምጣል፥ እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ሲሆን ለእርሱ በብቸኝነት የሚቀርብ አምልኮ ነው፦
39፥54 «ቅጣቱም ወደእናንተ ከመምጣቱ እና ከዚያም የማትረዱ ከመኾናችሁ በፊት ወደ ጌታችሁ በመጸጸት ተመለሱ፡፡ ለእርሱም ታዘዙ!፡፡ وَأَنِيبُوا إِلَىٰ رَبِّكُمْ وَأَسْلِمُوا لَهُ مِن قَبْلِ أَن يَأْتِيَكُمُ الْعَذَابُ ثُمَّ لَا تُنصَرُونَ

አሁንም እዚህ አንቀጽ ላይ "ታዘዙ" ለሚለው የገባው ቃል "አሥሊሙ" أَسْلِمُوا ነው፥ "ኢሥላም" إِسْلَام ማለት እራሱ "መታዘዝ" ማለት ነው፦
3፥19 አሏህ ዘንድ ሃይማኖት ኢሥላም ነው፡፡ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلَامُ

ለአሏህ ብቻ በውጥን የሚደረግ መታዘዝ "ኢሥላም" إِسْلَام ይባላል፥ "ኢሥላም" إِسْلَام የሚለው ቃል "አሥለመ" أَسْلَمَ‎ ማለትም "ታዘዘ" "ተገዛ" "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መታዘዝ" "መገዛት" "ማምለክ" ማለት ነው።
"ዲን" دِين የሚለው ቃል "ዳነ" دَانَ ማለትም "ሃይመነ" "ደነገገ" "ፈረደ" "በየነ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ሃይማኖት" "ፍትሕ" "ፍርድ" "ሕግ" "መርሕ"doctrine" ማለት ነው፥ አሏህ ዘንድ ያለው ሃይማኖት ኢሥላም ነው። አንድ ማንነት ለአሏህ ብቻ በአምልኮ ሲታዘዝ "ሙሥሊም" مُسْلِم ይባላል፦
3፥84 «እኛ ለእርሱ ታዛዦች ነን» በል፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
2፥136 «እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» በሉ፡፡ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ
29፥46 በሉም «በዚያ ወደ እኛ በተወረደው ወደ እናንተም በተወረደው አመንን፡፡ አምላካችንም አምላካችሁም አንድ ነው፡፡ እኛም ለእርሱ ታዛዦች ነን» وَقُولُوا آمَنَّا بِالَّذِي أُنزِلَ إِلَيْنَا وَأُنزِلَ إِلَيْكُمْ وَإِلَـٰهُنَا وَإِلَـٰهُكُمْ وَاحِدٌ وَنَحْنُ لَهُ مُسْلِمُونَ

እነዚህ አናቅጽ ላይ "ታዛዦች" ለሚለው የገባው ቃል "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው፥ "ሙሥሊም" مُسْلِم ማለት በነጠላ "ታዛዥ" ማለት ሲሆን ብዙ ቁጥሩ "ሙሥሊሙን" مُسْلِمُون ነው። ታዲያ ቀደምት ነቢያት ሙሥሊሞች አይደሉምን? ዲናቸውስ "ፈጣሪ አንድ አምላክ ነው" ተብሎ ፈጣሪን ብቻ በአምልኮ መታዘዝ አይደለምን? እንዴታ።
ወደ እኛም የተወረደው እና ወደ መጽሐፉ ሰዎች የተወረደው ግልጠተ መለኮት ጭብጡ የአንድ አምላክ አስተምህሮት ነው፦
21፥25 ከአንተ በፊትም እነሆ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጅ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

አሏህ ከጥንት ጀምሮ "ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" ብሎ ለሚልከው ነቢይ የሚገልጠው ይህ ግልጠት ነው፥ "የምናወርድ" ለሚለው የገባው ቃል "ኑሒ" نُوحِي ሲሆን የሚወርድለት "ወሕይ" وَحْي ነው። ስለዚህ የቀደሙት ነቢያት ሙሥሊም ነበሩ፦
5፥44 እነዚያ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ነቢያት በእነዚያ አይሁዳውያን በኾኑት ላይ በእርሷ ይፈርዳሉ፡፡ يَحْكُمُ بِهَا النَّبِيُّونَ الَّذِينَ أَسْلَمُوا لِلَّذِينَ هَادُوا

በግሥ መደብ "ትእዛዝን የተቀበሉት" ለሚለው የገባው ቃል "አሥለሙ" أَسْلَمُوا ሲሆን በስም መደብ "ሙሥሊም" مُسْلِم ነው። የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፦
3፥64 በል፦ "የመጽሐፉ ሰዎች ሆይ! በእኛ እና በእናንተ መካከል ትክክል ወደ ኾነች ቃል ኑ፡፡ قُلْ يَا أَهْلَ الْكِتَابِ تَعَالَوْا إِلَىٰ كَلِمَةٍ سَوَاءٍ بَيْنَنَا وَبَيْنَكُمْ

ይህቺ የጋራ ትክክለኛ ቃል አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው፦
3፥64 እርሷም፦ "አሏህን እንጂ ሌላን ላናመልክ፣ በእርሱም ምንንም ላናጋራ፣ ከፊላችንም ከፊሉን ከአሏህ ሌላ ጌቶች አድርጎ ላይዝ ነው"። أَلَّا نَعْبُدَ إِلَّا اللَّهَ وَلَا نُشْرِكَ بِهِ شَيْئًا وَلَا يَتَّخِذَ بَعْضُنَا بَعْضًا أَرْبَابًا مِّن دُونِ اللَّهِ


"ሱረቱል ሹራ"

የአላህ ጀሚል💧


◆▮ውይይት▮◆

"የባይብል ግጭት፣ብርዘት፣ስህተቶች፣"።
እስልምና ላይ የተጠየቁ:-"መውሊድ፣ግርዛት፣የአላህ መልእክተኛ መተዳደሪያቸው ምን ነበር? "

◍ወንድም ኢምረን
◍ኡስታዝ ወሒድ
◍ወንድም አህመድ
◍ሌሎችም
           🅥🅢
◍ ከወገናችን ኪሚጽዮን
◍ ከወገናችን ውዳሴ
◍ ሌሎችም

◍ሌሎችም


Forward from: የነብያት መንገድ | طريق الأنبياء
Video is unavailable for watching
Show in Telegram


ምንታዌ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

5፥17 እነዚያ አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሢሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

"ምንታዌ" ማለት "ሁለት" "ሁለትነት" ማለት ሲሆን በ451 ድኅረ ልደት በኬልቄዶን የጸደቀው "ዲያ ፊሲስ" δυο φύσις ትምህርት ነው፥ "ዲያ" δυο ማለት "ምንታዌ" "ሁለት" ማለት ሲሆን "ፊሲስ" φύσις ማለት ደግሞ "ባሕርይ"nature" ማለት ነው። በጥቅሉ "ዲያ ፊሲስ" δυο φύσις ማለት "ሁለት ባሕርይ" ማለት ሲሆን የኬልቄዶን ጉባኤ የአውጣኬን ትምህርት በማውገዝ፦ "ኢየሱስ ከሰው ጋር እና ከአብ ጋር "በባሕርይ የተስተካከለ"consubstantial" በአንድ አካል ያለ ውላጤ፣ ያለ ሚጠት፣ ያለ ትድምት፣ ያለ ቱሳሔ፣ ያለ ቡዓዴ ሁለት ባሕርይ አለው" የሚል እሳቤ ነበር።

፨ "ውላጤ" ማለት "መለወጥ" ማለት ሲሆን "ሥጋ ወደ መለኮት ተለወጠ" ወይም "መለኮት ወደ ሰውነት ተለወጠ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ሚጠት" ማለት "መመለስ" ሲሆን "ሥጋ ከትንሳኤ ወይም ወደ ከእርገት በኃላ ወደ መለኮት ተመለሰ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ቱሳሔ" ማለት "ቅልቅል" ማለት ሲሆን "ልክ እንደ ውኃ እና ማር ብርዝ አሊያም እንደ ወተት እና ቡና ማኪያቶ ጣዕም እና መልክ በመቀላቀል ተዋሐደ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ትድምት" ማለት "መደመር" ወይም "መደረብ" ማለት ሲሆን "ልክ ልብስ በአካል እንደሚደረብ እና እንደሚለበስ መለኮት መለኮትን ሳይለቅ ሥጋ ጨመረ፣ ደረበ፣ ለበሰ" "ደመረ" የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ኅድረድ" ማለት "ማደር" ማለት ማለት ሲሆን "ልክ ቤተመቅደስ አምላክ እንደሚያድር መለኮት ሥጋ ላይ አደረበት ወይም ልክ ውኃ በማድጋ፣ ሰይፍ በሰገባ፣ መጽሐፍ በተደጎሰ ማኅደር፣ ጽላት በታቦት እንደሚያድሩ መለኮት ሥጋ ላይ አደረበት የሚል እሳቤ ነው።
፨ "ቡዓዴ" ማለት "መለየት" ማለት ሲሆን "ልክ ብረት ብረትትነቱን ሳይለቅ ከእንጨት ጋር በብሎን ተለያይቶ እንደሚተሳሰር መለኮት ከሥጋ ጋር ተለያይቶ በአንድ አካል ተሳሰረ" የሚል እሳቤ ነው።

ይህንን የሁለት ባሕርይ እሳቤ የሚያራምዱት ካቶሊክ፣ የምሥራቅ ኦርቶዶክ እና ፕሮቴስንታንት ናቸው፥ ይህ ሁሉ ውዝግብ ግን በባይብል ላይ የለም። ከዚያ ይልቅ አምላክ እና ሰው ሁለት ለየቅል ባሕርዮት ሲሆኑ በአንድ ማንነት"person" አይኖሩም፥ ባሕርይ አንድ ሳይሆን አካል"person" አንድ አይሆንም፦
ኢሳይያስ 31፥3 ግብጻውያን ሰዎች እንጂ አምላክ አይደሉም። וּמִצְרַ֤יִם אָדָם֙ וְֽלֹא־אֵ֔ל
ሕዝቅኤል 28፥2 ነገር ግን ልብህን እንደ አምላክ ልብ ብታደርግም አንተ ሰው ነህ እንጂ አምላክ አይደለህም። וְאַתָּ֤ה אָדָם֙ וְֽלֹא־אֵ֔ל וַתִּתֵּ֥ן לִבְּךָ֖ כְּלֵ֥ב אֱלֹהִֽים׃

"አምላክ" መለኮታዊ ኑባሬ ከሆነ "ሰው" ሰዋዊ ኑባሬ ከሆነ ሰው እና አምላክ ሁለት ለየቅል ማንነት እና ምንነት ናቸው፦
ሆሴዕ 11፥9 እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና። כִּ֣י אֵ֤ל אָֽנֹכִי֙ וְלֹא־אִ֔ישׁ

"እኔ" እያለ የሚናገር አንድ ነጠላ ማንነት በምንነቱ ሰውነት ስለሌለበት "እኔ አምላክ ነኝ እንጂ ሰው አይደለሁምና" በማለት እንቅጩን ፍርጥ አርጎ ይናገራል። አምላክ በማንነት አንድ ስለሆነ አንድ አምላክ አለ፥ ሰው ግን በማንነት ብዙ ስለሆነ ብዙ ሰዎች አሉ፦
1ኛ ቆሮንቶስ 8፥4 ከአንዱም በቀር ማንም አምላክ እንደሌለ እናውቃለን። καὶ ὅτι οὐδεὶς Θεὸς εἰ μὴ εἷς.
1 ጢሞቴዎስ 2፥5 አንድ አምላክ አለና፥ በአምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛው ደግሞ አንድ አለ፥ እርሱም ሰው የሆነ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው። εἷς γὰρ Θεός, εἷς καὶ μεσίτης Θεοῦ καὶ ἀνθρώπων, ἄνθρωπος Χριστὸς Ἰησοῦς,

በአንድ አምላክ እና በሰዎች መካከል ያለው መካከለኛ ከአንዱ አምላክ እየሰማ የሚያስተላልፍ ሰው ነበር፦
የሐዋርያት ሥራ 2፥22 ከአምላክ ዘንድ ለእናንተ የተገለጠ ሰው ነበረ። ἄνδρα ἀποδεδειγμένον ἀπὸ τοῦ Θεοῦ εἰς ὑμᾶς.
ዮሐንስ 8፥40 ነገር ግን አሁን ከአምላክ የሰማሁትን እውነት የነገርኋችሁን ሰው ልትገድሉኝ ትፈልጋላችሁ። νῦν δὲ ζητεῖτέ με ἀποκτεῖναι, ἄνθρωπον ὃς τὴν ἀλήθειαν ὑμῖν λελάληκα, ἣν ἤκουσα παρὰ τοῦ Θεοῦ·

እዚህ አንቀጽ ላይ ላኪ "አምላክ" ባለቤት ተላኪ "ሰው" ተሳቢ መሆኑ እና በባለቤት እና በተሳቢ መካከል "የሰማሁት" የሚል ተሻጋሪ ግሥ መሆኑ በራሱ አምላክ እና ሰው ሁለት የተለያዩ ማንነቶች መሆናቸውን ቁልጭ አርጎ ያሳያል፥ ከዚያም ባሻገር አምላክ በኑባሬ ከሰው በምንነት ስለሚለያይ አምላክ የተባለው ላኪ እና ሰው የተባለው ተላኪ ሁለት የተለያዩ ምንነቶች መሆናቸውን ፍንትው አርጎ ያሳያል። ስለዚህ መሢሑ ሰው፣ ነቢይ፣ መልእክተኛ ሆኖ ሳለ አምላክ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፦
5፥17 እነዚያ አሏህ እርሱ የመርየም ልጅ አልመሢሕ ነው ያሉ በእርግጥ ካዱ፡፡ لَّقَدْ كَفَرَ الَّذِينَ قَالُوا إِنَّ اللَّهَ هُوَ الْمَسِيحُ ابْنُ مَرْيَمَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይስጠን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የረመዳን ፈታዋ 1 ||ኡስታዝ አሕመድ አደም |Hadis Amharic Ramadan | ሀዲስ በአማርኛ ፈትዋ | Ustaz ahmed adem


📜"ሱረቱል ዩኑሥ"

ወንድም ሙሐመድ🎙


◆▮ውይይት▮◆

"እስልምና ከጥንት የነበረ እንጅ በነብያችን የተጀረ አይደለም"።
"ሥላሴ"

◍ወንድም ጀማል
◍ወንድም ኢስሐቅ
◍ወንድም ኢብራሂም
◍ወንድም አቡ በክር
◍ሌሎችም
           🅥🅢
◍ ከወገናችን እዩ
◍ ከወገናችን Mፍቅር
◍ሌሎችም


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


የውኃ ጥምቀት

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥138 የአሏህን መንክር ያዙ! በመንከርም ከአሏህ ይበልጥ ያማረ ማነው? "እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን" በሉ፡፡ صِبْغَةَ اللَّهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُونَ

"ባፕቲዝማ" βάπτισμα የሚለው ቃል "ባፕቲዞ" βᾰπτῐ́ζω ማለትም "ነከረ" "አጠለቀ" "አጠመቀ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "መንክር" "ጥልቀት" "ጥምቀት" ማለት ነው፦
ማርቆስ 1፥4 ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ የንስሐንም ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት እየሰበከ መጣ። ἐγένετο Ἰωάνης ὁ βαπτίζων ἐν τῇ ἐρήμῳ κηρύσσων βάπτισμα μετανοίας εἰς ἄφεσιν ἁμαρτιῶν.

ዮሐንስ የሚያጠምቀው ጥምቀት የንስሐ ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት ሲሆን ሰዎች ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር፦
ማርቆስ 1፥5 ኃጢአታቸውንም እየተናዘዙ በዮርዳኖስ ወንዝ ከእርሱ ይጠመቁ ነበር።

ኢየሱስም የንስሐ ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ፥ ሲጠመቅ ጸሎት ይጸልይ ነበር፦
ማርቆስ 1፥9 በዚያ ወራትም ኢየሱስ ከገሊላ ናዝሬት መጥቶ ከዮሐንስ በዮርዳኖስ ወንዝ ተጠመቀ።
ሉቃስ 3፥21 ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ።

የተጠመቀበት ምክንያት ጽድቅን ሁሉ ለመፈጸም ነው፥ ጽድቅ አምላክ ያዘዘው ትእዛዝ መታዘዝ ሲሆን ዓመፃ ደግሞ አምላክ የከለከለውን ማድረግ ነው። ኢየሱስ ጽድቅን በወደድ እና ዓመፃን በመጥላት የአምላኩን ትእዛዝ ለመጠበቅ እና ለማድረግ ተጠመቀ፦
ማቴዎስ 3፥15 "ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና"
ዕብራውያን 1፥9 "ጽድቅን ወደድህ ዓመፅንም ጠላህ"
ዮሐንስ 14፥31 "አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ"
ዮሐንስ 15፥10 "እኔ የአባቴን ትእዛዝ እንደ ጠበቅሁ"

ኢየሱስ የተጠመቀው የውኃ ጥምቀት ብሉይ ኪዳን ላይ ያለ ጥምቀት ነው። የብሉይ ኪዳን ሰዎች የውኃ ጥምቀት ለኃጢአት ስርየት ይጠመቁ ነበር፥ ይህንን የውኃ ጥምቀት የዕብራውያን ጸሐፊ ጥምቀት ይለዋል፦
ዘኍልቍ 8፥7 ታነጻቸው ዘንድ እንዲህ ታደርግላቸዋለህ፤ ኃጢአትን የሚያነጻውን ውኃ እርጫቸው።
ዕብራውያን 9፥10 እስከ መታደስ ዘመን ድረስ ስለ ምግብ፣ ስለ መጠጥ፣ ስለ ልዩ ልዩ "መታጠብ" የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና። μόνον ἐπὶ βρώμασιν καὶ πόμασιν καὶ διαφόροις βαπτισμοῖς, δικαιώματα σαρκὸς μέχρι καιροῦ διορθώσεως ἐπικείμενα.

እዚህ አንቀጽ ላይ "መታጠብ" ለሚለው የገባው ቃል "ባፕቲዝሞስ" βαπτισμός ሲሆን "ጥምቀት" ማለት ነው፦
ዕብራውያን 6፥2 እርሱም ከሞተ ሥራ ንስሐ፣ በአምላክ እምነት፥ ስለ ጥምቀቶች፣ እጆችንም ስለ መጫን፣ ስለ ሙታንም ትንሣኤ እና ስለ ዘላለም ፍርድም ትምህርት ነው።

እዚህ አንቀጽ ላይ "ጥምቀቶች" ለሚለው የገባው ቃል "ባፕቲዝሞን" βαπτισμῶν ሲሆን ይህ የውኃ ጥምቀት እስከ መታደስ ዘመን ድረስ ማለትም ኢየሱስ እስኪመጣ ድረስ የነበረ የብሉይ ሕግ ነው፥ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ስለ የውኃ ጥምቀት ምንም አላስተማረም። ቅሉ ግን እንደተናገረ አስመስለው አስዋሽተውታል፦
ማርቆስ 16፥16 ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።

የሚገርመው የማርቆስ ወንጌል የጥንት ዐበይት የግሪክ ዕደ ክታባት ኮዴክስ ቫቲካነስ እና ኮዴክስ ሲናቲከስ የሚጨርሰው ማርቆስ 16፥8 ላይ ነው፥ New International Version፦ "ከ 9-20 ያሉትን አናቅጽ ጥንታውያን እደ ክታባት እና ሌሎች የጥንት ምስክሮች የላቸውም"The earliest manuscripts and some other ancient witnesses do not have verses 9–20" በማለት ሐቁን ሳይሸሽግ ተናግሯል። አብዛኞቹ የአዲስ ኪዳን ምሁራን ከ 9-20 ያሉት የማርቆስ የመጀመሪያ ጽሑፎች ክፍል እንዳልነበሩ ነገር ግን በኋላ የተጨመሩ እንደሆነ ይስማማሉ። ኢየሱስ "የውኃ ጥምቀት አጥምቁ" ብሎ አላዘዘም። ቅሉ ግን እንደተናገረ አስመስለው አስዋሽተውታል፦
ማቴዎስ 28፥19 “እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው።

"በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው" የሚለው በግሪክ ዕደ ክታባት ላይ የተጨመረ ሲሆን ማቴዎስ በጻፈው በመጀመርያው በዕብራይስጥ የተቀመጠው ቃል ግን "አሕዛብን ሁሉ በስሜ ደቀ መዛሙርት አድርጉ" የሚል ነበር፥ ይህንን አሽቀንጥረው ስለጣሉት የሚያሳዝነው ይህ ንግግር ጠፍቷል። በዚህ ዙሪያ ከዚህ ቀደም የጻፍኩት መጣጥፍ ስላለ እንድትመለከቱት በትህትና እጠይቃለው፦ https://t.me/Wahidcom/3585

ስናጠቃልልለው ውስብስብ እና ውዝግብ የሌለበትን የአሏህን የተፈጥሮ ጥምቀት እንድትይዙ ጥሪያችን ነው፦
2፥138 የአሏህን መንክር ያዙ! በመንከርም ከአሏህ ይበልጥ ያማረ ማነው? "እኛም ለእርሱ ብቻ ተገዢዎች ነን" በሉ፡፡ صِبْغَةَ اللَّهِ ۖ وَمَنْ أَحْسَنُ مِنَ اللَّهِ صِبْغَةً ۖ وَنَحْنُ لَهُ عَابِدُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! እኛንም በተፈጥሮ ጥምቀት ጸንተው ከሚሞቱ ሙሥሊም ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


ቁርአን የልብ ብርሃን 🎧

ወንድም ሁሴን

20 last posts shown.