ወሒድ የዕቅበተ ኢሥላም መጣጥፍት"Wahid Articles of Islamic Apologetics"


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ወንድም ወሒድ በኢሥላም እና በክርስትና መካከል ያለውን ልዩነት እና አንድነት በንጽጽር የሚያስቀምጥ ወንድም ነው። ለዚህም የቋንቋ፣ የሰዋስው፣ የዐውድ፣ የተዛማች እና የሥነ አመክንዮ ሙግት በማቅረብ የሚታወቅ ተሟጋች እና ጦማሪ ነው። ለሙግቱ ነጥብ በዋነኝነት የሚጠቀምባቸው ቋንቋ ዐማርኛ፣ ግዕዝ፣ እንግሊዝኛ፣ ዐረቢኛ፣ ዕብራይስጥ እና ግሪክ ናቸው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ኩፋሮች የሚያነሱትን ጥያቄዎች ከበቂ መልስ እና ከበቂ ማብራሪያ ጋር እንዲሁ የእኛን በጨዋ ደንብ ያቀረብነውን ሙግት ይጎብኙት፦ https://t.me/wahidislamicapologetics/51131


አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ

የሃይማኖት ንጽጽር ብዙዎች ዲኑል ኢሥላምን እንዲያውቁ እና እንዲሠልሙ ምክንያት የሆነ የማስተማር ጥበብ ነው፥ ያው አጠቃቀሙ ላይ ጥቂት ሰዎች ለብሽሽቅ ቢጠቀሙበት ማለት ነው። ከዚያ ጋር ተያይዞ "ንጽጽር ይቁም" የሚል ጥቂት ድምፅ እየሰማን ነው፥ ይህ ከበስተ ኃላ ሌላ አጀንዳ አለው። የጤናም አይደለም፥ የደዕዋን መስክ ሳይገባቸው ውኃ ሊቸልስሉ የሚሞክሩ አካላት ናቸው። እንደ እኛ ግን እንደውም ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ባይ ነን፥ እንደውም የደዕዋን አድማሱን አስፍተን በይቱብ በስፋት ተከታታይ ትምህርት ለማስተማር አስበናል። ኢንሻላህ!
ይቱባችንን ስላገዱት 100 ሺህ እና ከዛ በላይ የዩቱብ ቻናል ያለው ካለ ከቻለ ሊላህ ብሎ በነጻ ይስጠን ካልቻለ እንገዛዋለን። የምትችሉ ልጆች ከዚህ በታች ያሉትን የቦርድ አባላት ማናገር ትችላላችሁ።
ኢብኑ ረሻድ https://t.me/IbunReshed
አቡ ኑዓይም https://t.me/arhmanu
አቡ ሩመይሳ https://t.me/aburumaisa037
ዐብዱ ረሕማን https://t.me/Abi_Abik
እስሚዞ https://t.me/@Esmitiz_hubi

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
በኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የተሠጠ መግለጫ!

በወቅታዊው በማኅበራዊ ሚዲያ እየተካሄደ ያለው የሃይማኖት ትንኮሳ ከማን እንደተጀመረ በግልጽ አስቀምጣችኃል፥ እውነት ነው ግለሰቡ ኦርቶዶክስን አይወክልም። ግለሰቡን በጭፍን የሚከተሉ ጀሌዎቹንም ልክ ማስገባት አለባችሁ። ሰው አመዛዝኖ ይፈርዳል በደንብ ታዝባችኃል እናመሰግናለን።

ሌሎቻችን ሼር እናድርገው!




አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ሙሥሊም ወንድሞቼ እና እኅቶቼ!

"እውን ኢየሱስ የባሕርይ አምላክ ነውን? የሚለው ይህ የንጽጽር መጽሐፍ በድጋሚ በገበያ ላይ ውሏል።

ክርስቲያኖች ሆይ!
ንጽጽር እኮ የጀመርነው እኛ ሳንሆን ፕሮቴስታንት ናቸው፥ እኛም የሰጡንን መጽሐፍ አንብበብ ማነጻጸር ጀመርን። ንጽጽር እኮ ክልክል አይደለም፥ በፕሮቴስታንት እና በኦርቶዶክስ ሥነ መለኮት ውስጥ የተካተተ ኮርስ አለ። አሳብ መሞገት እና መዝለፍ ይለያያል። የሰውን እምነት መሳደብ፣ ማበሻቀጥ እና ማነወር ካለ በሁለቱም እምነት የተወገዘ ነው።

በቅርብ "እውነተኛ አምላክ ማን ነው? አሏህ ወይስ እግዚአብሔር" በሚል በቅድስት ሥላሴ ዩንቨርስቲ አዳራሽ አስመርቀዋል፥ መጽሐፉ በሁሉም የማኅበረ ቅዱሳን መጻሕፍት መደብር ሲገኝ የእኛ መጽሐፍ ግን በየትኛውም የኢሥላማዊ መጻሕፍት መደብር ውስጥ ነገር ተፈርቶ እንዳይረከቡ ሆኗል።

ንጽጽር መጻፍ፣ መሞገት፣ መማማር፣ መወያየት በሁለቱም ሥነ መለኮት ችግር የለውም፥ በተረፈ ንጽጽር መጻፍ የሚበረታታ ነው። የኢትዮጵያ የሃይማኖት ገባኤ፦ "መስበክ፣ መማማር፣ መወያየት እና ማነጻጸር ይፈቀዳል" ብሏል፥ "ክልክል ነው" ካሉን ግን ታዛዥ ነን ከሁለታችንም ወገን ሁላችንም እናቆማለን። ኢንሻላህ!

ስንክሳሩ በተሠግዎት መቅድም እና በአንድ ታሪካዊ ሥነ መለኮት መግቢያ የተሰነደ፣ በሰባት ዐበይት ሥልታዊ ሥነ መለኮት የተሰደረ እና በአንድ ጉልኅ ማጠቃለያ የተሰነገ ነው። መልካም የንባብ፣ የጥናት፣ የምርምር እና የማነጻጸር ጊዜ ይሁንልዎ!

መጽሐፉ የሚገኝበት አድራሻ! በቴሌ ግራም ነው፦
http://t.me/merkatozon

ሌሎቻችን ሼር እናድርግ!


እኚህ ሰው ማን ናቸው?

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

15፥95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ

ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ከሕፃን እስከ አዋቂ፣ ወጣትም ሆነ አዛውንት ስለ እሳቸው ሲወራ "ጆሮ ዳባ ልበስ" የሚል የለም፥ ሁሉ ስለ እሳቸው ሲወራ አዳሜ ሆነ ሔዋኔ ጆሮውን አስግጎ ይሰማል። ከሁሉም ከሁሉም የሚገርመው ደግሞ የሚጠሏቸው ሳይቀር እንኳን ቢሆን ስለ እሳቸው ለመስማት እና ስለ እሳቸው ለማወቅ ይፈልጋሉ፥ ዝም ብለህ ሰው በተሰበሰበበት መሀል ገብተህ እና ድምፅህን ከፍ አድርገህ፦ "እከሌ" ወይም "እከሊት" ብለህ ብትጣራ ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ የሚያዞረው የጠራከውን ስም ባለቤት ብቻ ነው። ከሌለም ደግሞ ማንም ፊት እና ትኩረት የሚሰጥክ አይኖርም፥ ነገር ግን ሰው የተሰበሰበበት ስፍራ ሄደህ የእሳቸውን ስም ጠርተህ ንግግር ብትጀምር ሁሉም ፊቱን እና ትኩረቱን ወደ አንተ ያደርጋል። ትኩረት የማይሰጥህ የለም ቢባል ቅጥፈት ወይም እብለት አሊያም ግነት አይሆንብኝም፥ ስለ እሳቸው ለማወቅ የማይሰለፍ አይኖርም።

፨ እኚህ ሰው የእልፍ አእላፋት መጻሕፍት ርእስ በመሆን ብዙ ጸሐፊያን የከተቡላቸው ናቸው፣

፨ እኚህ ሰው በሁሉም ልብ ውስጥ በአሉታዊ ሆነ በአንታዊ በሁለት ወገን እንደተሳለ ሰይፍ ሰርስረው የገቡ ናቸው፣

፨ እኚህ ሰው አስተምህሮታቸው የተሟላ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፓለቲካዊ የሕይወት ዘይቤ በመሆኑ "የዓለማችን ተግዳሮት ነው" የተባለላቸው ናቸው፣

፨ እኚህ ሰው "የዓለማችን ቁጥር አንድ አውንታዊ እና አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ" ተብለዋል፥ ለሕሩያን አውንታ ተጽዕኖ እንዲሁ ለእኵያን አሉታዊ ተጽዕኖ አሳዳሪ ናቸው፣

፨ እኚህ ሰው ስለ እርሳቸው ማንነት የገባው ሰው፦ "ሕይወትህን መስዋዕት አርግ" ቢባል ያለ አንዳች ማቅማማት ሕይወቱን እስከ ሞት የሚያደርግላቸው ናቸው፣

፨ እኚህ ሰው በታሪክ ውስጥ እሳቸውን ለማነወር፣ ለማበሻቀጥ፣ ለማብጠልጠል ብዙ ጦማሪያን ጦምረዋል፣ ብዙ ኃያሲያን ኃይሰዋል፤ ብዙ ተቺዎች ተችተዋል፣ ብዙ ተሳላቂዎች ተሳልቀዋል። ቅሉ ግን የጦማሪያን ጦማር፣ የኃያሲያን ኂስ፣ የተቺዎች ትችት፣ የተሳላቂዎች ስላቅ ከሟቾች ጋር ሲያልፍ የእሳቸው ስም እና የሰዎችን ሕይወት የቀየሩበት መጽሐፍ እስካሁን አለ የተባለላቸው ናቸው።

እኚህ ሰው ማን ናቸው? አዎ! የዓለማቱ ጌታ የአሏህ መልእክተኛ እና የነቢያት መደምደሚያ ነቢዩ ሙሐመድ"ﷺ" ናቸው። በእርሳቸው ላይ የወረደው ሐቅ ለሰዎች የሚጠቅም ስለሆነ በምድር 1400 ዓመት ቆይቷል፥ ባጢል ቢሆን ኖሮ በእንጭጩ ኮረፋት ሆኖ ተግበስብሶ ይጠፋ ነበር፦
13፥17 እንደዚሁ አላህ ለእውነት እና ለውሸት ምሳሌን ያደርጋል። ኮረፋቱማ ግብስብስ ኾኖ ይጠፋል፥ ለሰዎች የሚጠቅመውማ በምድር ላይ ይቆያል፡፡ እንደዚሁ አላህ ምሳሌዎችን ይገልፃል"*፡፡ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْحَقَّ وَالْبَاطِلَ ۚ فَأَمَّا الزَّبَدُ فَيَذْهَبُ جُفَاءً ۖ وَأَمَّا مَا يَنفَعُ النَّاسَ فَيَمْكُثُ فِي الْأَرْضِ ۚ كَذَٰلِكَ يَضْرِبُ اللَّهُ الْأَمْثَالَ

"ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፥ ከአምላክ እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም። በእርግጥ ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ" እንዳለው ገማልያ ብዙ ሰዎችበእርሳቸው የተነሳ ከአምላክ ጋር እየተቆራረጡ ነው፦
ሐዋርያት ሥራ 5፥38-39 አሁንም እላችኋለሁ፦ ከእነዚህ ሰዎች ተለዩ ተዉአቸውም! ይህ አሳብ ወይም ይህ ሥራ ከሰው እንደ ሆነ ይጠፋልና፥ ከአምላክ እንደ ሆነ ግን ታጠፉአቸው ዘንድ አይቻላችሁም። በእርግጥ ከአምላክ ጋር ስትጣሉ ምናልባት እንዳትገኙ"።

ገማሊያ እንደተናገረው ይህ የነቢያችን"ﷺ" እሳቦት ከሰው ከሆነ ይጠፋ ነበር፥ ግን የነቢያችን"ﷺ" ግልጠተ መለኮት ከፈጣሪ ስለሆነ ገና በእንጭጭነቱ የመካህ ቁሬይሾች፣ የመዲና በኑ ቁሬይዛህ፣ የሮሙ ባዛንታይን በዕውቀት መሞገት ሲያቅታቸው በጉልበት ሊጠፉት ሞክረው አልተሳካላቸው። ከርሞም ሆነ ዘንድሮም እሳቸው ላይ ለሚሳለቁን ተሳላቂዎች አሏህ በቅቶላቸዋል፥ በእርሳቸው ላይ የወረደውን የአሏህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ቢፈልጉ እና ቢጠሉም አሏህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፦
15፥95 ተሳላቂዎችን ሁሉ እኛ በቅተንልሃል፡፡ إِنَّا كَفَيْنَاكَ الْمُسْتَهْزِئِينَ
61፥8 የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ሊያጠፉ ይሻሉ፥ ከሓዲዎቹ ቢጠሉም እንኳ አላህ ብርሃኑን ገላጭ ነው፡፡ يُرِيدُونَ لِيُطْفِئُوا نُورَ اللَّهِ بِأَفْوَاهِهِمْ وَاللَّهُ مُتِمُّ نُورِهِ وَلَوْ كَرِهَ الْكَافِرُونَ

ይህንን ብርሃን ለማጥፋት እፍ ባሉ ቁጥር እያነደዱት መሆኑን ይዘነጋሉ፥ ኢሥላም በፍጥነት መጠነ ሰፊ የእድገት መርሓ ግብር እየታየበት ያለው በምዕራባውያን መሆኑ እፍ ባሉ ቁጥር የሚያነዱበት ውጤት ነው። ሚስማር በተመታ ቁጥር እንደሚጠብቅ ዲኑል ኢሥላም በተነቀፈ ቁጥር ይስፋፋል። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣቸው! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

“ፊዳከ አቢ ወኡሚ ያ ረሡሉሏህ” فِدَاكَ أَبِي وَأُمِّي يَا رَسُول اللَّه

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


የዘካህ አወጣጥ

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ፥ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

የዘካ ገንዘብ ከተቀማጭ ላይ ከመቶ 2.5 % የሚሰጥ ነው፥ ነቢያችን”ﷺ” ከሁለት መቶ ዲርሀም 5 ዘካህ እንደሚወጣ ተናግረዋል። ያ ማለት የዘካህ ሒሳብ በመቶ ዲርሀም 2.5 ይሆናል፥ ስሌቱ 5፥2=2.5 ነው፦
ሡነን አቢ ዳውድ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 18 ዐሊይ”ረ.ዐ” እንደተረከው፦ “ነቢዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፦ ”ሁለት መቶ ዲርሀም ለአንተ በሆነች ጊዜና ዓመት ከሞላች አምስት ደራሂም ይወጣል፥ በአንተ ምንም ነገር አይሆንም ሃያ ዲናር እስኪሆን ድረስ”። عَنْ عَلِيٍّ، – رضى الله عنه – عَنِ النَّبِيِّ صلى الله عليه وسلم بِبَعْضِ أَوَّلِ هَذَا الْحَدِيثِ قَالَ ‏”‏ فَإِذَا كَانَتْ لَكَ مِائَتَا دِرْهَمٍ وَحَالَ عَلَيْهَا الْحَوْلُ فَفِيهَا خَمْسَةُ دَرَاهِمَ وَلَيْسَ عَلَيْكَ شَىْءٌ – يَعْنِي فِي الذَّهَبِ – حَتَّى يَكُونَ لَكَ عِشْرُونَ دِينَارًا

በዚህ ሐዲስ መሠረት የአንድ ሰው ካፒታል 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ዘካህ ይወጅበታል። በሸሪዓህ የዘካህ አነስተኛ የክፍያ መጠን “ኒሷብ” نِصاب ይባላል፥ ይህም ኒሷብ የሚለካው 20 ዲናር ወይም 200 ዲርሀም ሲሆን ነው። “ዲናር” دِينَار‎ ማለት “የወርቅ ሳንቲም”gold coin” ማለት ሲሆን “ዲርሀም” دِرْهَم‎ ማለት ደግሞ “የብር ሳንቲም”silver coin” ማለት ነው። ይህ በጥንት ጊዜ የሸቀጥ ገንዘብ”commodity money” ነው። “ዲናር” እና “ዲርሀም” የሚለኩት በሚስቃል ነው፥ “ሚስቃል” مِثْقَال የሚለው ቃል “ሰቀለ” ثَقَلَ ማለትም “ከበደ” ከሚል ሥርወ-ቃል የመጣ ሲሆን “ክብደት” ማለት ነው።
1 ሚስቃል ወርቅ 4.25 ግራም ነው፥ 20 ሚስቃል ወርቅ ደግሞ 4,25x 20 = 85 ግራም ወርቅ ይሆናል ማለት ነው።
1 ሚስቃል ብር 2.975 ግራም ነው፥ 200 ሚስቃል ብር ደግሞ 2.975x 200= 595 ግራም ብር ይሆናል ማለት ነው።

በዘካህ ላይ የሚወጅበው ኒሷብ 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ነው።
አንድ ሙሥሊም ያስቀመጠው ካፒታል ዓመት ከሞላው እና ያም ካፒታል 85 ግራም ወርቅ ወይም 595 ግራም ብር ያክል ከሆነ ዘካህ ማውጣት ግዴታው ነው።
ዘካቱል ማል የሚወጣበት አነስተኛ ዋጋ የብር ኒሷብ ስለሆነ አብላጫው ምሁራን የብር ኒሷብን መሠረት ባደረገ መልኩ ከዚያ እንዲወጣ ፈትዋ ሰተዋል፥ ስለዚህ አንድ ሰው ዓመት የተቀመጠ 148,750 ብር(ገንዘብ) እና ከዛ በላይ ካለው ዘካህ ማውጣት ግዴታ አለበት።

እንዴት? ካላችሁ የብር ኒሷብ ወደ ወረቀት ገንዘብ”Fiat money” ለመቀየር ብርን ዛሬ ባለው የወቅቱ ግብይት ለናሙና ያክል መሥራት ይቻላል። በኢትዮጵያ አንድ ግራም ብር"silver" አሁን ባለኝ መረጃ 250 ብር"ገንዘብ" ነው፥ ስናሰላው 250×595= 148,750 ብር(ገንዘብ) ይሆናል።
ለምሳሌ፦ እኔ 200 ሺህ ብር ቢኖረኝ ከ 200 ሺህ ብር ላይ 2.5 % ዘካህ ሲሰላ 5,000 ይወጅብብኛል፥ ስናሰላው 200,000×2.5፥100= 5,000 ይሆናል። ስለዚህ ዓመት የሞላው 148,750 ብር እና ከዛ በላይ ዘካህ ማውጣት ስለሚወጅብ ዘካህን መስጠት አንርሳ፦
2፥110 ሶላትንም አስተካክላችሁ ስገዱ፡፡ ዘካንም ስጡ፡፡ وَأَقِيمُوا الصَّلَاةَ وَآتُوا الزَّكَاةَ

ተውሒድ ኢሥላማዊ ጥሪ ማኅበር በመጅሊሥ ፈቃድ የሚንቀሳቀስ ተቋማችን ሲሆን ለተቸገሩ ሠለምቴዎች የዘካን ሐቅ ለመስጠት ስለተዋቀረ መስጠት የምትፈልጉ ከዚህ በታች ያሉትን የቦርድ አባላት ማናገር ትችላላችሁ።
ኢብኑ ረሻድ https://t.me/IbunReshed
አቡ ኑዓይም https://t.me/arhmanu
አቡ ሩመይሳ https://t.me/aburumaisa037
ዐብዱ ረሕማን https://t.me/Abi_Abik
እስሚዞ https://t.me/@Esmitiz_hubi

አምላካችን አሏህ ዘካን ከሚሰጡ ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም






«ለአደም ስገዱ»

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» በማለት አዘዛቸው፦
2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

የአዳም እና የሔዋን ታሪክ ላይ ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ፦
"ሚካኤልም ወጥቶ መላእክቱን ሁሉ ጠራ፡- "ጌታ አምላክ እንዳዘዘው ለአምላክ መልክ ለአዳም ስገዱ" አለ።
Life of Adam and Eve Chapter XIV(14) Number 1

ቀሌምንጦስ ዘሮም"Clement of the Rome" ከጴጥሮስ የተቀበለው ንግግር ተብሎ በሚታመነው መጽሐፍ ላይ እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ ወደ አዳም ራሳቸውን አዘንብለው ለአዳም እንደሰገዱ ይናገራል፦
ቀሌምንጦስ 1፥41 አራዊት፣ እንስሳት፣ ወፎች እና "እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ወደ አዳም ተሰበሰቡ ከፊቱም ቁመው ራሳቸውን አዘነበሉ "ለ-"አዳም ሰገዱ"።

"እግዚአብሔር የፈጠረው ሁሉ" ማለት መላእክትን ይጨምራል፥ ምክንያቱም መላእክት ፍጡራን ኑባሬዎች ናቸውና፥ ፍጥረት ሁሉም ለአዳም ይታዘዝ እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር፦
ቀሌምንጦስ 1፥42"ፍጥረት ሁሉም ለአዳም "ይታዘዝ" እና ቃሉንም ይጠብቅ ነበር።

አምላካችን አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ሲል ለኢብሊሥ "ስገድ" አለማለቱን አያሳይም፥ ምክንያቱም አሏህ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» ብሎታልና፦
7፥12 አላህ፦ «ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ?» አለው፡፡ قَالَ مَا مَنَعَكَ أَلَّا تَسْجُدَ إِذْ أَمَرْتُكَ

“ባዘዝኳችሁ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" ሳይሆን “ባዘዝኩህ ጊዜ ከመስገድ ምን ከለከለህ" አለው፥ “ባዘዝኩህ” የሚለው ኃይለ ቃል "ለአደም ስገድ" ብሎ አዞት እንደነበር ቁልጭና ፍንትው አድርጎ ያሳይል። ለምሳሌ፦ ፈጣሪ አዳምን "መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ" ብሎት ነበር፦
ዘፍጥረት 2፥17 ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ።

ጥቅሱ ላይ "አትብላ" እንጂ "አትብሉ" አላላቸውም፥ ነገር ግን ሔዋን፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም" ያህዌህ ብሎናል ብላለች፦
ዘፍጥረት 3፥3 ነገር ግን በገነት መካከል ካለው ከዛፉ ፍሬ፥ ያህዌህ አለ፦ "እንዳትሞቱ ከእርሱ አትብሉ አትንኩትም"።

ለሁለቱም ግን "አትብሉ" ያለበት ትእዛዝ አለመገለጹ ግን "አላላቸውም" እንደማንል በተመሳሳይ "ስገድ" ያለበት ጥቅስ አለመኖሩ "ስገድ አላለውም" አያሰኝም። ሲቀጥል "መላእክት" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ "ብቻ" በሚል መረዳት የለብንም፦
7፥179 ”ለ”እነርሱ ልቦች አሏቸው፥ ግን አይገነዘቡበትም፣ “ለ”እነርሱም ዓይኖች አሉዋቸው፥ ግን ዐያዩበትም፣ “ለ”እነርሱም ጆሮዎች አሉዋቸው ግን አይሰሙበትም፡፡ لَهُمْ قُلُوبٌ لَّا يَفْقَهُونَ بِهَا وَلَهُمْ أَعْيُنٌ لَّا يُبْصِرُونَ بِهَا وَلَهُمْ آذَانٌ لَّا يَسْمَعُونَ بِهَا

"እነርሱ" የተባሉት ከሰው እና ከጂኒ ያመጹ ከሓድያን ሲሆኑ "እነርሱ" በሚል ቃል መነሻ ቅጥያ ላይ "ለ" የሚለውን መስተዋድድ ስላለ "ልቦች" "ዓይኖች" "ጆሮዎች" ያሉአቸው ኩፋሮች ብቻ ናቸው እንደማንል ሁሉ "ለመላእክት" የሚለውም ለኢብሊሥ እንዳልተባለ ማስረጃ አይሆንም፦
2፥34 ሁሉም ወዲያውኑ ሰገዱ፥ ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር። "እምቢ" አለ ኮራም ከከሓዲዎቹም ኾነ፡፡ فَسَجَدُوا إِلَّا إِبْلِيسَ أَبَىٰ وَاسْتَكْبَرَ وَكَانَ مِنَ الْكَافِرِينَ

“ኢብሊሥ ብቻ ሲቀር” በሚለው ኃይለ ቃል ላይ “ሲቀር” የምትለዋን ይዘን "ኢብሊሥ ከመላእክት ነበር" ማለት አሁንም የቁርኣንን ሰዋስው ካለመረዳት የሚመጣ ጥራዝ ነጠቅ ዕውቀት ነው፦
26፥77 «እነርሱም ለእኔ ጠላቶች ናቸው፡፡ ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር እርሱ ወዳጄ ነው»፡፡ فَإِنَّهُمْ عَدُوٌّ لِّي إِلَّا رَبَّ الْعَالَمِينَ

ኢብራሂም፦ “ለእኔ ጠላቶች ናቸው። ግን የዓለማት ጌታ ሲቀር” ማለቱን አስተውል! “ሲቀር” የሚለውን አፍራሽ ቃል ይዘን ከዓለማቱ ጌታ ውጪ ለኢብራሂም ሁሉም ጠላት ነውን? አማንያን፣ ነቢያት፣ መላእክት፣ እንስሳትስ ጠላት ናቸውን? አይ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ የአሏህን ወዳጅ ለመሆን የገባ እንጂ “ሁሉን ጠላት ናቸው ከአሏህ በቀር” ማለቱን አያሳይም ከተባለ እንግዲያውስ “በቀር” የሚለው በአንጻራዊ ደረጃ ኢብሊሥ ብቻ አለመታዘዙን እንጂ መላእክት ውስጥ መካተቱን አያሳይም።

ዲያብሎስ ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን "እምቢ" ብሏል፦
2ኛ መቃብያን 9፥3 ክሣደ ልቡናውን በማጽናት እና ራሱን በማኩራት ፈጣሪው ለፈጠረው ለአዳም መስገድን እምቢ ብሏልና።

ዲያብሎስም ከማዕረጉ የወረደው "ለአዳም አልሰግድም" በማለቱ እንደሆነ በጸጸት ተናግሯል፦
3ኛ መቃብያን 1፥15 "ለአዳም አልሰግድም በማለቴ እግዚአብሔር ስለ አባታቸው ስለ አዳም ከማዕረጌ አዋርዶኛልና።

አሏህ ለመላእክት«ለአደም ስገዱ» ማለቱን አክብሮቱን ያሳያል እንጂ "አደምን አምልኩ" የሚለውን አያሲዝም። እንደዛማ ቢሆንማ ፈጣሪ በኢየሱስ ለፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚያሰግድ ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። ἰδοὺ ποιήσω αὐτοὺς ἵνα ἥξουσιν καὶ προσκυνήσουσιν ἐνώπιον τῶν ποδῶν σου, καὶ γνῶσιν ὅτι ἐγὼ ἠγάπησά σε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ነው፥ እና ፈጣሪ ኤጲስ ቆጶሱን እያስመለከ ነው? "ኸረ በፍጹም" ካላችሁ እንግዲያውስ ከላይ ያለውን እሳቤ በዚህ መልክ እና ልክ መረዳት ቀላል ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የግብፅ ኦርቶዶክስ፦ "ድንግል ማርያም ከአዳም የመጣው ድቀተ ባሕርይ አግኝቷቷል" ሲሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ደግሞ፦ "ድንግል ማርያም ከአዳም ከመጣው ድቀተ ባሕርይ ተጠብቃለች" የሚል እምነት አላቸው፥ የግብፅ ኦርቶዶክስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ላይ ውስጥ ውስጡን እየሠሩ እንደሆነ በቂ መረጃዎች እየወጡ ነው።


"በግ ሁልጊዜ "ይበላኛል" ብሎ የሚፈራው እና የሚጠነቀቀው ተኩላን ነው፥ ነገር ግን አሳድጎ፣ አስብቶ እና ተንካባክቦ አርዶ የሚበላው በሚያምነው እና በሚታመንለት በገዛ እረኛው ነው። ከውጪ ከሚመጣ የኩፋሮች ጥቃት ይልቅ ጉያችሁ ሥር ያሉትን ሙናፊቃን እንጠንቀቅ! ከኩፍር ይልቅ ኒፋቅ ዲንን የሚሰረስር ዝገት ነው። አሏህ ከኒፋቅ ሸር እና ደባ እንዲሁ ከሙናፊቃን ተንኮል እና ሴራ ይጠብቀን! አሚን።"

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom


እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ነው። የእስር ቤት ዘበኛው ለጳውሎስ እና ለሲላስ ሰግዷል፦
የሐዋርያት ሥራ 16፥29 መብራትም ለምኖ ወደ ውስጥ ሮጠ፥ እየተንቀጠቀጠም ከጳውሎስ እና ከሲላስ ፊት ተደፋ። αἰτήσας δὲ φῶτα εἰσεπήδησεν καὶ ἔντρομος γενόμενος προσέπεσεν τῷ Παύλῳ καὶ Σιλᾷ,

የአክብሮት ስግደት ባይኖር ኖሮ በፊታቸው ሲሰግድ ዝም ይሉት ነበር? ራእይ የፊላድልፍያ ጉባኤ ኤጲስ ቆጶስ ለሆነው ሰው እንደሚሰገድለት ይናገራል፦
ራእይ 3፥9 እነሆ መጥተው በእግሮችህ ፊት "ይሰግዱ" ዘንድ እኔም እንደ ወደድሁህ ያውቁ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ። ἰδοὺ ποιήσω αὐτοὺς ἵνα ἥξουσιν καὶ προσκυνήσουσιν ἐνώπιον τῶν ποδῶν σου, καὶ γνῶσιν ὅτι ἐγὼ ἠγάπησά σε.

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω በ King James Version ላይ "worship" ብሎታል፥ "ዎርሺፕ" የሚለው ቃል "ዋጋ"worth" እና "ነት"ship" ከሚል ቃል የመጣ ሲሆን "ዋጋነት"worthy-ship"፣ "ማክበር" እና "አክብሮት" ማለት ነው። ዮሐንስ ለመልአኩ ሁለት ጊዜ ሰገደለት፦
ራእይ 19፥10 ልሰግድለትም በእግሩ ፊት ተደፋሁ። καὶ ἔπεσα ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν αὐτοῦ προσκυνῆσαι αὐτῷ.
ራእይ 22፥8 በመልአኩ እግር ፊት እሰግድ ዘንድ ተደፋሁ። ἔπεσα προσκυνῆσαι ἔμπροσθεν τῶν ποδῶν τοῦ ἀγγέλου

ሁለት ጊዜ ሰግዶለት ሁለት ጊዜ "እንዳታደርገው ተጠንቀቅ፥ ለአምላክ ስገድ" ብሎ አስጠንቅቆታል፥ እንደ ጴጥሮስ ለትህትና ይሆን? የሐዋርያት ሥራ 10፥25 ጴጥሮስም በገባ ጊዜ ቆርኔሌዎስ ተገናኝቶ ከእግሩ በታች ወደቀና ሰገደለት። ጴጥሮስ ግን፦ “ተነሣ፤ እኔ ራሴ ደግሞ ሰው ነኝ፥” ብሎ አስነሣው።

ምናልባት በንያው የአምልኮ ስግደት ሰግዶ ይሆን? አናውቅም። አብርሃም እና ሎጥ ለመላእክት ይሰግዱ ሰግደዋል፦
ዘፍጥረት 18፥2 ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፤ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ።
ዘፍጥረት 19፥1 ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፤ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ፤ ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ።

መላእክት ወደ ሰዎች ሲመጡ እና ሰዎች ሲገናኙ መስገድ የአክብሮት ስግደት ነው፥ ነገር ግን መላእክት እና ሰዎች የችሎታ፣ የዕውቀት፣ የማየት እና የመስማት ውስንነት ስላለባቸው በአካል ሳይገናኙ በገይብ ለእነርሱ መስገድ የአምልኮ ስግደት ነው። በተጨማሪ በላይ በሰማይ ያሉትን የመላእክትን ምስል ሆነ በታች በምድር የሰዎችን ምስል ሠርቶ መስገድ ሆነ ማምለክ የተከለከለ ነው፦
ዘጸአት 20፥4 በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ። አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም።

ለመላእክት ሆነ ለሰዎች "የአክብሮት ስግደት" እያላችሁ የአምልኮ ስግደት የምትሰግዱ እንዲሁ የተቀረጸ ምስል ለሆኑት ለመስቀል እና ለስዕል የጸጋ ስግደት የምትሰግዱ ቶሎ ብላችሁ በንስሓ ወደ አሏህ እንደትመለሱ ጥሪያችን ነው። እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፦
41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


የአክብሮት ስግደት

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

"ሻኻህ" שָׁחָה የሚለው የዕብራይስጥ ቃል፣ "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω የሚለው የግሪክ እና "ሡጁድ" سُّجُود የሚለው የዐረቢኛ ቃል "ስግደት"prostration" ማለት ነው፥ ለአንድ አምላክ በሁሉም ስፍራ የሚቀርበው ስግደት የአምልኮ ስግደት ሲሆን ለፍጡራን በአካል ሲገናኙ ለሰላምታ የሚቀርበው ስግደት የአክብሮት ስግደት ነው፦
ዘፍጥረት 23፥7 አብርሃም ተነሣ፥ "ለ-"ምድሩ ሕዝብ እና "ለ-"ኬጢ ልጆች "ሰገደ"። וַיָּ֧קָם אַבְרָהָ֛ם וַיִּשְׁתַּ֥חוּ לְעַם־הָאָ֖רֶץ לִבְנֵי־חֵֽת׃

እዚህ አንቀጽ ላይ አብርሃም ለ-"ምድሩ ሕዝብ እና ለ-"ኬጢ ልጆች ያቀረበውን የአክብሮት ስግደት "ሻኻህ" שָׁחָה ሲሆን በግሪክ ሰፕቱአጀንት "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω በዐረቢኛ "ሡጁድ" سُّجُود ነው። ስለዚህ "አሏህ ለመላእክት ለአደም ስገዱ" ሲል "የአክብሮት ስግደት ነው" ስንል እርር እና ምርር ብላችሁ የሚያንጨረጭራችሁ እና የሚያንተከትካችሁ ምን ይውጣችሁ ይሆን? እንቀጥል፦
ዘፍጥረት 27፥29 አሕዛብ ይገዙልህ ሕዝብም "ይስገዱልህ"። יַֽעַבְד֣וּךָ עַמִּ֗ים [וְיִשְׁתַּחוּ כ] (וְיִֽשְׁתַּחֲו֤וּ ק) לְךָ֙ לְאֻמִּ֔ים

እዚህ አንቀጽ ላይ ይስሐቅ ያዕቆብን “ይስገዱልህ” ሲለው "ያምልኩህ" ማለቱ ነው? የዮሴፍም ወንድሞች ለዮሴፍ በምድር ላይ በግምባራቸው ተደፍተው ሰገዱለት፦
ዘፍጥረት 42፥6 የዮሴፍም ወንድሞች በመጡ ጊዜ በምድር ላይ በግምባራቸው ተደፍተው "ሰገዱለት"። וַיָּבֹ֙אוּ֙ אֲחֵ֣י יֹוסֵ֔ף וַיִּשְׁתַּֽחֲווּ־לֹ֥ו אַפַּ֖יִם אָֽרְצָה׃

ለዮሴፍ እንደተሰገደለት ተጨማሪ ጥቅስ ዘፍጥረት 43፥26 ዘፍጥረት 43፥28 ዘፍጥረት 44፥14 ተመልከቱ! ሩት ለቦኤዝ በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦
ሩት 2፥10 በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት። וַתִּפֹּל֙ עַל־פָּנֶ֔יהָ וַתִּשְׁתַּ֖חוּ אָ֑רְצָה

ከዚህ ሁሉ የሚገርመው ከአንዱ አምላክ ከያህዌህ ጋር ለእሴይ ልጅ ለንጉሡ ለዳዊት ራሳቸውን አዘንብለው ሰገዱ፦
1ኛ ዜና 29፥20 ራሳቸውንም አዘንብለው ለያህዌህ እና ለንጉሡ ሰገዱ። וַיִּקְּד֧וּ וַיִּֽשְׁתַּחֲו֛וּ לַיהוָ֖ה וְלַמֶּֽלֶךְ׃

"ሰገዱ" በሚል በአንድ ግሥ እና "እና" በሚል መስተጻምር ተጫፍሮ መጥቷል፥ ስግደቱ ለያህዌህ የአምልኮት ለዳዊት ደግሞ የአክብሮት ነው። በእስራኤል ባህል ለሰላምታ እርስ በእርስ በግምባር ተደፍቶ መስገድ የተለመደ ነው፥ 1ኛ ሳሙኤል 20፥41 1ኛ ሳሙኤል 25፥23 2ኛ ሳሙኤል 18፥28 2ኛ ሳሙኤል 19፥18 1ኛ ነገሥት 1፥23 ተመልከት!

በአዲስ ኪዳን የአክብሮት ስግደት ቀጥሏልን? እንዴታ ያለ ጥርጥር ቀልሏል፥ ሐዋርያት ለኢየሱስ የአክብሮት ስግደት ሰግደውለታል፦
ሉቃስ 24፥52 እነርሱም፤ ሰገዱለትና በብዙ ደስታ ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። καὶ αὐτοὶ προσκυνήσαντες αὐτὸν ὑπέστρεψαν εἰς Ἰερουσαλὴμ μετὰ χαρᾶς μεγάλης,

እዚህ አንቀጽ ላይ "ስግደት" ለሚለው የገባው ቃል "ፕሩስኩኔኦ" προσκυνέω ሲሆን ኢየሱስ በሰጠው ምሳሌ ውስጥ ዕዳውን መክፍል ያልቻለው ባሪያ ለጌታው መስገዱ በእስራኤል ባህል ስግደት አክብሮትን ለማመልከት እንደሚመጣ ጉልኅ ማሳያ ነው፦
ማቴዎስ 18፥26 ስለዚህ ባሪያው ወድቆ "ሰገደለትና"፦ ጌታ ሆይ፥ ታገሠኝ፥ ሁሉንም እከፍልሃለሁ" አለው። πεσὼν οὖν ὁ δοῦλος προσεκύνει αὐτῷ λέγων Μακροθύμησον ἐπ’ ἐμοί, καὶ πάντα ἀποδώσω σοι.


ዛሬ ላይ ዐበይት ክርስትና በሚባሉት በካቶሊክ፣ በምሥራቅ ኦርቶዶክስ"Eastern Orthodox" እና በጽባሕ ኦርቶዶክስ"Oriental Orthodox" ለመላእክት፣ ለነቢያት፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት "የአክሮት ስግደት" እየተባለ የሚሰገደው ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነው፥ ምክንያቱም ዱዓእ እራሱ ዒባዳህ ነው፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 34, ሐዲስ 2
አን-ኑዕማን ኢብኑ በሺር እንደተረከው፦ “የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ "ዱዓእ ዒባዳህ ነው"። عَنِ النُّعْمَانِ بْنِ بَشِيرٍ، قَالَ قَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ إِنَّ الدُّعَاءَ هُوَ الْعِبَادَةُ ‏”‏ ‏.‏

"ዱዓእ" دُعَآء የሚለው ቃል “ደዓ” دَعَا ማለትም “ለመነ” “ጠራ” “ጸለየ” “ተማጸነ” ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን “ልመና” “ጥሪ” “ጸሎት” “ተማጽንዖ” ማለት ነው፥ ከፈጠረን አምላክ ከአሏህ ውጪ "ድረሱልን እርዱን" የሚባሉት ፍጡራን ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ሰሚ እና ሁሉን ተመልካች መለኮት ስላልሆኑ አያውቁም፣ አይሰሙም፣ አያዩም፦
7፥194 እነዚያ ከአላህ ሌላ የምትጠሯቸው እንደ እናንተ አምላኪዎች ናቸው፥ እውነተኞችም እንደሆናችሁ ጥሩዋቸው ለእናንተ ይመልሱላችሁ። إِنَّ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ عِبَادٌ أَمْثَالُكُمْ ۖ فَادْعُوهُمْ فَلْيَسْتَجِيبُوا لَكُمْ إِن كُنتُمْ صَادِقِينَ
46፥5 እስከ ትንሣኤ ቀን ድረስም ለእርሱ የማይመልስለትን ከአሏህ ሌላ ከሚጠራ ሰው ይበልጥ የተሳሳተ ማነው? እነርሱም ከጥሪያቸው ዘንጊዎች ናቸው፡፡ وَمَنْ أَضَلُّ مِمَّن يَدْعُو مِن دُونِ اللَّهِ مَن لَّا يَسْتَجِيبُ لَهُ إِلَىٰ يَوْمِ الْقِيَامَةِ وَهُمْ عَن دُعَائِهِمْ غَافِلُونَ

በትንሣኤ ቀን አሏህ ከእርሱ ሌላ በዱዓእ የሚያመልኳቸውንም ይሰበስብና እያወቁ «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ?» ብሎ ይጠይቃቸዋል፦
25፥17 እነርሱን እና ከአሏህ ሌላ የሚያመልኳቸውንም የሚሰበስብባቸውንና «እናንተ እነዚህን ባሮቼን አሳሳታችሁን ወይስ እነርሱው መንገድን ሳቱ?» የሚልበትን ቀን አስታውስ፡፡ وَيَوْمَ يَحْشُرُهُمْ وَمَا يَعْبُدُونَ مِن دُونِ اللَّهِ فَيَقُولُ أَأَنتُمْ أَضْلَلْتُمْ عِبَادِي هَـٰؤُلَاءِ أَمْ هُمْ ضَلُّوا السَّبِيلَ
25፥18 «ጥራት ይገባህ፤ ከአንተ ሌላ ረዳቶችን ልንይዝ ለእኛ ተገቢያችን አልነበረም፥ ግን እነርሱን እና አባቶቻቸውን መገንዘብን እስከተዉ ድረስ አጣቀምካቸው፡፡ ጠፊ ሕዝቦችም ኾኑ» ይላሉ፡፡ قَالُوا سُبْحَانَكَ مَا كَانَ يَنبَغِي لَنَا أَن نَّتَّخِذَ مِن دُونِكَ مِنْ أَوْلِيَاءَ وَلَـٰكِن مَّتَّعْتَهُمْ وَآبَاءَهُمْ حَتَّىٰ نَسُوا الذِّكْرَ وَكَانُوا قَوْمًا بُورًا
35፥14 ብትጠሩዋቸው ጥሪያችሁን አይሰሙም፡፡ ቢሰሙም ኖሮ ለእናንተ አይመልሱላችሁም? በትንሣኤም ቀን ማጋራታችሁን ይክዳሉ፡፡ እንደ ውስጠ ዐዋቂው ማንም አይነግርህም፡፡ إِن تَدْعُوهُمْ لَا يَسْمَعُوا دُعَاءَكُمْ وَلَوْ سَمِعُوا مَا اسْتَجَابُوا لَكُمْ ۖ وَيَوْمَ الْقِيَامَةِ يَكْفُرُونَ بِشِرْكِكُمْ ۚ وَلَا يُنَبِّئُكَ مِثْلُ خَبِيرٍ

መላእክት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን እና ሰማዕታት በትንሣኤም ቀን ማጋራታቸውን ይክዳሉ፥ ከእነርሱ ስም በስተኃላ አምልኮውን የሚጋሩት ሸያጢን ናቸው።
ክርስቲያኖች ሆይ! "የአክሮት ስግደት" እያላችሁ የምሰግዱት ስግደት ጸሎት፣ ልመና፣ ተማጽኖ ስላለበት የአምልኮ ስግደት ነውና የአምልኮ ሐቅ ገንዘቡ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን በብቸኝነት እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


ሡጁዱ አት ተሒያህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

"ተሒያህ" تَحِيَّة የሚለው ቃል "ሐያ" حَيَّا ማለትም "አከበረ" "ሰላም ሰጠ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አክብሮት" "ክብር" "መከባበር" ማለት ነው፦
25፥75 እነዚያ በመታገሳቸው የገነትን ሰገነቶች ይመነዳሉ፥ በእርሷም ውስጥ "አክብሮት" እና ሰላምታን ይስሰጣሉ፡፡ أُولَـٰئِكَ يُجْزَوْنَ الْغُرْفَةَ بِمَا صَبَرُوا وَيُلَقَّوْنَ فِيهَا تَحِيَّةً وَسَلَامًا
33፥44 በሚገናኙት ቀን "መከባበሪያቸው" ሰላም መባባል ነው፥ ለእነርሱም የከበረን ምንዳ አዘጋጅቶላቸዋል፡፡ تَحِيَّتُهُمْ يَوْمَ يَلْقَوْنَهُ سَلَامٌ ۚ وَأَعَدَّ لَهُمْ أَجْرًا كَرِيمًا

እነዚህ አናቅጽ ላይ "አክብሮት" "መከባበር" ለሚለው የገባው ቃል "ተሒያህ" تَحِيَّة ነው፥ በጥቅሉ "ሡጁዱ አት ተሒያህ" سُجُود الْتَحِيَّة ማለት "የአክብሮት ስግደት" ማለት ነው። ይህንን ከተረዳን ዘንዳ አምላካችን አሏህ ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ያለው ስግደት የአክብሮት ስግደት ነው፦
2፥34 ለመላእክትም «ለአደም ስገዱ» ባልን ጊዜ አስታውስ ፡፡ وَإِذْ قُلْنَا لِلْمَلَائِكَةِ اسْجُدُوا لِآدَمَ

ቁርኣን ከመውረዱ በፊት የአክብሮት ስግደት በሩቅ ሳይሆን በአካል የአክብሮት ስላምታ መስገድ ሐላል ነበረ፥ የዩሡፍ እናት እና አባት እንዲሁ ወንድሞቹ የአክብሮት ስግደት ለዩሡፍ ሰግደዋል፦
12፥4 ዩሡፍ ለአባቱ፡- «አባቴ ሆይ! እኔ አሥራ አንድ ከዋክብትን፣ ፀሐይን እና ጨረቃን በሕልሜ አየሁ፥ ለእኔ ሰጋጆች ሆነው አየኋቸው» ባለ ጊዜ አስታውስ፡፡ إِذْ قَالَ يُوسُفُ لِأَبِيهِ يَا أَبَتِ إِنِّي رَأَيْتُ أَحَدَ عَشَرَ كَوْكَبًا وَالشَّمْسَ وَالْقَمَرَ رَأَيْتُهُمْ لِي سَاجِدِينَ
12፥100 ወላጆቹንም በዙፋኑ ላይ አወጣቸው፡፡ አለም፦ ለእርሱም ሰጋጆች ኾነው ወረዱለት፡፡ «አባቴም ሆይ! ይህ ፊት ያየኋት ሕልሜ ፍች ነው፡፡ ጌታ በእርግጥ እውነት አደረጋት፡፡ وَرَفَعَ أَبَوَيْهِ عَلَى الْعَرْشِ وَخَرُّوا لَهُ سُجَّدًا ۖ وَقَالَ يَا أَبَتِ هَـٰذَا تَأْوِيلُ رُؤْيَايَ مِن قَبْلُ قَدْ جَعَلَهَا رَبِّي حَقًّا

የጸጋ ስግደት"Graceful prostration" ከአሏህ በስጦታ የተቸረ የአክብሮት ስግደት ሲሆን ነገር ግን ይህ የአክብሮት ስግደት ሲለጠጥ ለመላእክት፣ ለነቢያት፣ ለጻድቃን እና ለሰማዕታት መለኮት ባልሆኑበት ሁኔታ ሰዎች እየተለማመኑ ሲሰግዱ ወደ የአምልኮ ስግደት እየተቀየረ ሲመጣ ቁርኣን ሲወርድ ተከለከለ፥ አሏህም "እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ" ብሎናል፦
41፥37 ሌሊት እና ቀን ፀሐይ እና ጨረቃ ከምልክቶቹ ናቸው፥ ለፀሐይ እና ለጨረቃ አትስገዱ! ለእዚያም ለፈጠራቸው ለአሏህ ስገዱ፡፡ እርሱን ብቻ የምታመልኩ እንደ ኾናችሁ ለሌላ አትስገዱ፡፡ وَمِنْ آيَاتِهِ اللَّيْلُ وَالنَّهَارُ وَالشَّمْسُ وَالْقَمَرُ ۚ لَا تَسْجُدُوا لِلشَّمْسِ وَلَا لِلْقَمَرِ وَاسْجُدُوا لِلَّهِ الَّذِي خَلَقَهُنَّ إِن كُنتُمْ إِيَّاهُ تَعْبُدُونَ

ተወዳጁ ነቢያችንም"ﷺ" በሐዲስ ላይ የአክብሮት ስግደትን ከልክለዋል፦
ሡነን ኢብኑ ማጃህ መጽሐፍ 9, ሐዲስ 1926:
ዐብደላህ ኢብኑ አቢ ዐውፋ እንደተረከው፦ ”ሙዓዝ ኢብኑ ጀበል ከሻም ምድር በተመለሰ ጊዜ ለነቢዩ”ﷺ” ሰገደ፥ እሳቸውም፦ “ሙዓዝ ሆይ! ይህ ምንድነው? አሉት። እርሱም፦ “ሻም ምድር ሄጄ ነበር፥ ለኤጲስ ቆጶሳቶቻቸው እና ለጳጳሳቶቻቸው ሲሰግዱ ተመለከትኩ። ይህንን ለእርሶ በራሴ ልሠራው ተመኘሁ” አለ። የአሏህ መልእክተኛም”ﷺ” አሉ፦ “ይህንን በፍጹም እንዳትሠሩ!”። عَنْ عَبْدِ اللَّهِ بْنِ أَبِي أَوْفَى، قَالَ لَمَّا قَدِمَ مُعَاذٌ مِنَ الشَّامِ سَجَدَ لِلنَّبِيِّ ـ صلى الله عليه وسلم ـ قَالَ ‏”‏ مَا هَذَا يَا مُعَاذُ ‏”‏ ‏.‏ قَالَ أَتَيْتُ الشَّامَ فَوَافَقْتُهُمْ يَسْجُدُونَ لأَسَاقِفَتِهِمْ وَبَطَارِقَتِهِمْ فَوَدِدْتُ فِي نَفْسِي أَنْ نَفْعَلَ ذَلِكَ بِكَ ‏.‏ فَقَالَ رَسُولُ اللَّهِ ـ صلى الله عليه وسلم ـ ‏”‏ فَلاَ تَفْعَلُوا


ሡጁዱል ዒባዳህ

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

18፥110 «በጌታውም "አምልኮ" አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ዒባዳህ" عِبَادَة የሚለው ቃል "ዐበደ" عَبَدَ ማለትም "አመለከ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "አምልኮ" ማለት ነው፦
18፥110 «በጌታውም "አምልኮ" አንድንም አያጋራ» በላቸው፡፡ وَلَا يُشْرِكْ بِعِبَادَةِ رَبِّهِ أَحَدًا

"ሡጁድ" سُجُود የሚለው ቃል "ሠጀደ" سَجَدَ ማለትም "ሰገደ" ከሚል ሥርወ ቃል የመጣ ሲሆን "ስግደት" ማለት ነው፥ በጥቅሉ "ሡጁዱል ዒባዳህ" سُجُود الْعِبَادَة ማለት "የአምልኮ ስግደት" ማለት ነው፦
6፥56 «እኔ እነዚያን ከአሏህ ሌላ የምትጠሩዋቸውን ከማምለክ ተከልክያለሁ» በላቸው፡፡ قُلْ إِنِّي نُهِيتُ أَنْ أَعْبُدَ الَّذِينَ تَدْعُونَ مِن دُونِ اللَّهِ
7፥206 እነዚያ እጌታህ ዘንድ ያሉት መላእክት እርሱን ከማምለክ አይኮሩም፥ ያወድሱታልም፡፡ ለእርሱ ይሰግዳሉ፡፡ إِنَّ الَّذِينَ عِندَ رَبِّكَ لَا يَسْتَكْبِرُونَ عَنْ عِبَادَتِهِ وَيُسَبِّحُونَهُ وَلَهُ يَسْجُدُونَ ۩

የባሕርይ ስግደት"Ontological Prostration" ለአንዱ አምላክ ብቻ የሚቀርብ የአምልኮ ስግደት ሲሆን ለአንዱ አምላክ ለአሏህ ብቻ የሚቀርብ መጎባደድ፣ መተናነስ፣ ማሸርገድ፣ መዋረድ ነው፦
22፥77 እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! በሶላታችሁ አጎንብሱ፣ "በግንባራችሁም ተደፉ"፣ ጌታችሁንም አምልኩ፣ ትድኑ ዘንድ መልካምን ነገር ሥሩ፡፡ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا ارْكَعُوا وَاسْجُدُوا وَاعْبُدُوا رَبَّكُمْ وَافْعَلُوا الْخَيْرَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ ۩

"በግንባራችሁም ተደፉ" ለሚለው የገባው የግሥ መደብ "ኢሥጂዱ" اسْجُدُوا ሲሆን በሶላት ውስጥ ያለው ሡዱድ ለአሏህ ብቻ የሚቀርብ ሡጁዱል ዒባዳህ ነው፥ የትም ሆነን ሁሉን ለሚችል፣ ሁሉን ለሚያውቅ፣ ሁሉን ለሚያይ፣ ሁሉን ለሚሰማ መለኮት የሚቀርብ ስግደት የአምልኮ ስግደት ነው። ፍጡራን ግን ሁሉንም የመቻል፣ የማወቅ፣ የማየት እና የመስማት ባሕርይ ስለሌላቸው ለእርሱ በሩቅ የሚቀርብ ስግደት ሺርክ ነው፦
35፥18 የምታስጠነቅቀው እነዚያን ጌታቸውን በሩቅ የሚፈሩትን፣ ሶላትንም አስተካክለው ያደረሱትን ብቻ ነው፡፡ إِنَّمَا تُنذِرُ الَّذِينَ يَخْشَوْنَ رَبَّهُم بِالْغَيْبِ وَأَقَامُوا الصَّلَاةَ

መላእክት፣ ነቢያት፣ ጻድቃን እና ሰማዕታት መለኮት ስላልሆኑ ሁሉን ቻይ፣ ሁሉን ዐዋቂ፣ ሁሉን ተመልካች እና ሁሉን ሰሚ ስላልሆኑ ለእነርሱ በሩቅ የሚቀርበው ስግደት ሺርክ ነው፦
4፥36 አሏህንም አምልኩ! በእርሱም ምንንም አታጋሩ፡፡ وَاعْبُدُوا اللَّهَ وَلَا تُشْرِكُوا بِهِ شَيْئًا

አምላካችን አሏህ ነባቢ መለኮት ነው፥ "እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ" ይለናል፦
21፥92 ይህቺ ኡማህ አንዲት ኡማህ ስትሆን በእርግጥ ኡማችሁ ናት፥ እኔም ጌታችሁ ነኝና አምልኩኝ፡፡ إِنَّ هَـٰذِهِ أُمَّتُكُمْ أُمَّةً وَاحِدَةً وَأَنَا رَبُّكُمْ فَاعْبُدُونِ
21፥25 ከአንተ በፊትም "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ወደ እርሱ የምናወርድለት ቢኾን እንጂ ከመልእክተኛ አንድንም አልላክንም፡፡ وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ مِن رَّسُولٍ إِلَّا نُوحِي إِلَيْهِ أَنَّهُ لَا إِلَـٰهَ إِلَّا أَنَا فَاعْبُدُونِ

ከጥንት ጀምሮ "እነሆ ከእኔ ሌላ አምላክ የለምና አምልኩኝ" በማለት ነቢያትን ሲልክ የነበረውን አንዱን አምላክ አሏህ ማምለክ ምንኛ መታደል ነው? እናንተ ሰዎች ሆይ! ቅጣትን ትጠነቀቁ ዘንድ እናንተን እና እነዚያንም ከእናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን አምልኩ፦
2፥21 እናንተ ሰዎች ሆይ! ቅጣትን ትጠነቀቁ ዘንድ እናንተን እና እነዚያንም ከእናንተ በፊት የነበሩትን የፈጠረውን ጌታችሁን አምልኩ፡፡ يَا أَيُّهَا النَّاسُ اعْبُدُوا رَبَّكُمُ الَّذِي خَلَقَكُمْ وَالَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

ክርስቲያኖች ሆይ! የአምልኮ ሐቅ ገንዘቡ የሆነውን አንዱን አምላክ አሏህን እንድታመልኩ ጥሪያችን ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም


አሥ ሠላሙ ዐለይኩም ያ ጀመዓህ ይህንን ቻናል የዲኑል ኢሥላም የብርሃን አድማስ ለማስፋት እና ለኩፋሮች ተደራሽነት እንዲሆን ሊንኩን በየቻናሉ፣ በየግሩፑ፣ በየኮሜንት መስጫ እንድታጋሩልን ከታላቅ ትህትና ጋር እንደጠቃለን። ኢንሻላህ
https://t.me/Wahidcom




አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነው!

በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው።

65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

አምላካችን አሏህ ሁሉንም "ነገር" ዐዋቂ ነው፥ "ሸይእ" شَيْء ማለት "ነገር" ማለት ሲሆን ይህም ነገር አጠቃላይ ፍጥረትን ሁሉ ያጠቃልላል፦
65፥11 "አሏህም ነገሩን ሁሉ ዐዋቂ ነው"፡፡ وَاللَّهُ بِكُلِّ شَيْءٍ عَلِيمٌ

ይህ ሆኖ ሳለ ሚሽነሪዎች "ዐሊመሏህ" عَلِمَ اللَّه የሚለው ቃል ወስደው "አሏህ ሁሉን ዐዋቂ ነውን? ብለው ይጠይቃሉ፦
2፥235 አሏህ እናንተ በእርግጥ የምታስታውሷቸው መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ سَتَذْكُرُونَهُنَّ
2፥187 አሏህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ

"አሏህ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም አለማወቁን በፍጹም አያሳይም፥ ምክንያቱም አሏህ ዘንድ አላፊ እና መጻዒ ጊዜ ስለሌለ በአሁናዊ ግሥ "አሏህ ዐወቀ" የሚለው ጭራሽ አሏህ ሁሉን ዐዋቂ እንደሆነ ያሳያል። ተመሳሳይ የሰዋስው አወቃቀር ከባይብል በንጽጽር እንመልከት! "የደ ኤሎሂም" יֵּ֖דַע אֱלֹהִֽים ማለት በአሁናዊ ግሥ "አምላክ አወቀ" ማለት ነው፦
ዘጸአት 2፥25 አምላክ የእስራኤልን ልጆች አየ፥ አምላክ በእነርሱ ያለውን ነገር "አወቀ"። וירא אלהים את בני ישראל וידע אלהים׃

"አምላክ ዐወቀ" ማለት ጥንቱንም አለማወቁን በፍጹም አያሳይም፥ ምክንያቱም አምላክ ዘንድ አላፊ እና መጻዒ ጊዜ ስለሌለ በአሁናዊ ግሥ "አምላክ ዐወቀ" የሚለው ጭራሽ አምላክ ሁሉን ዐዋቂ እንደሆነ ያሳያል" ካላችሁ እንግዲያውስ የቁርኣኑን አናቅጽ በዚህ መልክ እና ልክ ተረዱት! በሰፈሩት ቁና መሰፈር ይሉካል እንደዚህ ነው። አምላካችን አሏህ ሂዳያህ ይስጣችሁ! ለእኛም ጽናቱን ይወፍቀን! አሚን።

✍ከዐቃቢ ኢሥላም ወሒድ
https://t.me/Wahidcom

ወሠላሙ ዐለይኩም

20 last posts shown.