ውሎ ከስደተኞች ጋር
"…ዛሬ በዕለተ ቀዳሚት ሰንበት ወደ ጎንደር ሄደን ቀበሮ ሜዳ በተባለ አሰቃቂ የጎንደር ዐማራ ተፈናቃይ የስደተኛ ካምፕ ነው የምውለው። ቀበሮ ሜዳ ከሚገኙ ተፈናቃይ የጎንደር ዐማራ ስደተኞች ጋር ነው የምንውለው። ከወለጋ፣ ከቤኒሻንጉል፣ ከወልቃይት፣ ከትግራይ በግፍ ተፈናቅለው ባዶ እጃቸውን ቤሳቤስቲ ሳይዙ ተባረው ከመጡ የጎንደር ዐማራ ስደተኞች ጋር ነው የምንለው።
"…ተፈናቃይ ስደተኞቹ በነበሩበት ስፍራ ሀብት ንብረት አፍርተው የነበሩ። በረታቸው በከብት፣ ጋጣቸው በበግና በፍየል። ወተት፣ አሬራ፣ እርጎ፣ ቅቤ፣ እንቁላሉ ከማዕዳቸው የማይጠፋ፣ ማሳቸው ያማረ፣ ጎተራቸውም ማዕዳቸውም ሙሉ የሆነ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ባማረ አልጋ ላይ ንፁሕ አንሶላና ፍራሽ ላይ የሚተኙ፣ እንግዳ ተቀባይ፣ ፍሪዳ አርደው የሚያስተናግዱ፣ ልጆቻቸውን የሚያስተምሩ ነበሩ። ግን ዐማራ ስለሆነ ተፈናቀሉ። ተባረሩ። በአንድ ጀንበር የደሀ ደሀ ሆኑ።
"…ዛሬ ከእነዚህ ስደተኞች ጋር ነው የምንውለው። ነገም በመረጃ ቲቪ የሚጎድላቸውን በሙሉ ድንጋይ ተሸክሜ እናንተን እየለመንኩ ሳሟላላቸው ነው የምውለው። ብዙም ሰው የሚያስፈልገው አልነበረም። በጥቂት ሰዎች ብቻ የሚሟላ ነገር ነው ጉድለታቸው። እሱን ስናሟላላቸው እንውላለን። ማርያምን ትል ከሰውነታቸው ውስጥ ሲወጣ አሳያችኋለሁ። መፈጠራችሁን ነው የምትጠሉት። መፈጠራችሁን አልኳችሁ። ጎንደር በዚህ ልክ ሲሰቃይ ማየት ያማል።
"…ተፈናቃዮቹ ሕጋዊ የባንክ ደብተር አላቸው። ያውም በመንግሥት የተፈቀደ የባንክ ደብተር። በእሱ ላይ ነው በቀጥታ የምናስገባላቸው። ከእኔ ጋር አይነካካም። ከዚህ በፊት እንደማደርገው ሁሉ ነው አሁንም የማደርገው። ዘመዴ ብሩን በላው እንዳትሉኝ ሳይሆን የሚሉ ስላሉ የእነሱንም አእምሮ ከመጠበቅ አንፃር እኔ በእኔ በኩል በግሌ ሰብስቤ ስለማላውቅ አሁንም በቀጥታ ከተጎጂዎቹ ጋር ነው የማገናኛችሁ። ባንኩ ስዊፍት ኮድም ስላለው ካላችሁበት ሀገር ቀጥታ በባንክም ትልኩላቸዋላችሁ ማለት ነው። አለቀ።
"…በመጀመሪያ ዛሬ የምናደርገው መጪውን አዲስ ዓመት ደስስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ በዓሉን እናሳምርላቸዋለን። ቀጥሎ በስደተኛ ካምፕ ውስጥ በቋሚነት የጎደላቸውን እናሟላላቸዋለን። ለምሳሌ እንደትምህርት ቤት ያለውን እንገነባላቸዋለን። ሰሞኑን ከኮሚቴዎቹ ጋር ስለዚህ ጉዳይ ነበር በዝርዝር ስንወያይ የከረምነው። ሁሉንም በባለሙያ አስጠንተው ልከውልኛል። አንዱም አይቀረኝ ሁሉንም ለምኜ አሟላላቸዋለሁ። በቅድሚያ ግን አዲሱ ዓመት በደስታ የሚያሳልፉበትን ነው የማስቀድመው።
"…መንግሥት ለወር ብሎ 15 ኪሎ በቆሎ ነው ለስደተኞቹ የሚያድለው። 15 ኪሎ በቆሎ። እሱን ነው በልተው የሚኖሩት። በቆሎው በዚያው ይቀጥል። እኔ ግን ለአዲስ ዓመት ለቅዱስ ዮሐንስ ለእንቁጣጣሽ ነጭ ማኛ አንደኛ ደረጃ ጤፍ አስፈጭቼ ነው ሰንጋ ጥዬ፣ ለስላሳ፣ ውኃ ገዝቼ አንበሽብሼ የማውላቸው። ጥብሱን፣ ቁርጡን ነው የማማርጣቸው። በደስታ ነው ሳስለቅሳቸው የምውለው። የትአባቴንስና።
"…ለበዓሉ የሚያስፈልጋቸው በዝርዝር ተነግሮኛል። እነሱ 3 ሰንጋ ይበቃናል ነው ያሉት እኔ ግን ለመጠባበቂያ 4 አደርግላቸውና አምስተኛ ሰንጋም እጨምርበታለሁ። አምስተኛውን ሰንጋ ደግሞ እዚያው ጎንደር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአእምሮ ውስንነት ያለባቸው ልጆችን የሚረዱ አሉ ለእነሱ እናበረክትላቸዋለን። በጤና ምክንያት የበሬ ሥጋ ለማይበሉና እንዲሁም በመጠለያ ጣቢያው ውስጥ ለሚገኙ ለሙስሊም ወንድም እህቶቻችን ደግሞ 5 ሙክት ፍየል ያስፈልገናል ብለዋል። እሱን እኔ ራሴም ቢሆን ከራሴ ጦሜን አድሬ አሟላላቸዋለሁ። የሚረዳኝ ካገኘሁ መልካም ነው። ከሌለም እሱ አያቅተኝም።
"…50 ሎሚ ለአንድ ሰው ሸክሙ ነው። ለ50 ሰው ግን ጌጥ ነው። እንደምታስቡት አይደለም። የነገው መርሀ ግብሬ ላይ ላይ በዛ ያለ ሰው ያስፈልገን ይሆናል እንጂ ለዛሬው መርሀ ግብሬ በጣም ጥቂት ሰው ነው የሚያስፈልገኝ። በጣም ጥቂት ሰው። ቃል ትገባላችሁ። ያን ቃላችሁን ትልኩልኛላችሁ። እኔ ደግሞ የባንክ አካውንታቸውን እልክላችኋለሁ በዚያ ቀጥታ ታስገቡላቸዋላችሁ። በነገው ዕለት ግን ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአቅሙ ይሳተፍ ዘንድ የባንክ አካውንታቸው በይፋ በቴሌግራም ገፄም፣ በመረጃ ቴሌቭዥንም ይለጠፋል።
• ዝግጁ ሆናችሁ ጠብቁኝ መጣሁ። ከጤፉና ከሰንጋው ነው የምንጀምረው።
በመምህር ዘመድኩን 👇👇
https://t.me/ZemedkunBekeleZ