የሆነልህን እንጂ የሆነብህን አትቁጠር
ሳታሸንፍ በፍጹም እዚህ አልደረስክም፡፡ አንተ የአሸናፊዎች ምሳሌ እንጂ በፍጹም የተሸናፊዎች ምልክት አይደለህም፡፡ የአየሩን መለዋወጥ፣ የኢኮኖሚውን ከፍና ዝቅ ማለት፣ ከሰዎች የሚሰነዘርብህን ደስ የማያሰኙ ሁኔታዎች … አልፈህ እዚህ ደርሰሃል፡፡ ከአሁን ወዲያ ደግሞ ከተሳሳትካቸው ነገሮች ትምህርትን፣ ከተሳኩልህ ጉዳዮች ደግሞ ድፍረትን በመያዝ ወደፊት የመሄድ ሃላፊነት አለብህ፡፡
ማታ እቤት ስትገባ በሰላም መግባትህን አስብ እንጂ ከኪስህ የጠፋውን ገንዘብ ወይም የሞባይል ቀፎ በማሰብ፣ ወይም በመንገድ ላይ ያበሳጨህን ሰው በማሰላሰል አእምሮህን አትሙላው፡፡ ውስጥህን በይሆናልና በይቻላል መሙላት ከአንተ በፊት ያለፉ ሰዎችን አስደናቂ ፈለግ የመከተል አስገራሚ እርምጃ እንጂ የቅዠት ምልክት አይደለም፡፡ የሆነልህን መልካም ነገር አእምሮህ ውስጥ ስፍራን ስጠውና በመኮትኮት አሳድገው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ጤና ቢሱን ሃሳብ ስፍራ በመንፈግ አስርበውና እንዲሞት አድርገው፡፡
“ከሃዘኖችህ ይልቅ ሃሴቶችህን፣ ከጠላቶችህ ይልቅ ደግሞ ወዳጆችህን ቁጠር” - Irish Proverb
ስለሚወዱህ ሰዎች ከማሰላሰልና ስለሚጠሉህ ሰዎች ከማሰብ የትኛው ጥሩ ስሜት ይሰጥሃል? የሚወዱህ ሰዎች የነገሩህን የፍቅርና የአክብሮት ቃል ከማሰብና የሚጠሉህ ሰዎች የነገሩህን ስሜትን የሚወጋ ቃል ከማሰላሰል የቱ ይሻልሃል? ምርጫው የአንተ ነው፡፡
ቁጭ ብለህ የማይቀበሉህ ሰዎች ማን ማን እንደሆኑ ከመቁጠር፣ የሚወዱህንና የሚቀበሉህን ሰዎች መቁጠር በስኬትህ ላይ ታላቅ ተጽእኖ አለው፡፡ ጨለማን በብርሃን አሸንፍ እንጂ በጨለማ አትሸነፍ፡፡
Join us.....
@Ab_book