#ምን_ላይ_ነህ?
አንድ አስገራሚ እና እውነተኛ ታሪክ ላጫውትህ...
ቫዮሊን ተጫዋቹ፤ ኒውዮርክ በሚገኝ የባቡር ጣብያ ውስጥ ለአርባ አምስት ደቂቃዎች ያህል ቫዮሊን ተጫወተ። ከአጠገቡ ሙዚቃውን የወደዱ ሰዎች ገንዘብ እንዲለግሱት፤ ወደ ላይ አፉን የከፈተ ሳጥን አስቀምጧል።
በነዚያም አርባ አምስት ደቂቃዎች አንድ ሰው ብቻ ቆሞ አጨበጨበለት፤ ሃያ ዶላር ያህልም መሰብሰብ ቻለ።
በነጋታው ምሽት ላይ ይኸው ቫዮሊን ተጫዋች በእጅጉ በታወቀ እና መግቢያው ለአንድ ሰው መቶ ዶላር በሆነበት... ሺዎች በታደሙበት ግዙፍ አዳራሽ ውስጥ ተመሳሳይ ሙዚቃ አቀረበ... ቫዮሊኑን ዳግም ተጫወተ። የማያባራ ጭብጨባንም ተቀበለ።
ይህ ታሪክ አንድ እውነታ ያሳየናል - እኛ ማብራት እና መታየት በማንችል ስፍራ ላይ ስንሆን ዋጋችን እናጣለን። በእርያዎች መሃል ያለ እንቁ ከድንጋይነት የተረፈ ዋጋ የለውም።
ብዙ አቅም ያላቸው ሰዎች በማይገባቸው ቦታ ሆነው፤ ክብርን አጥተዋል። ሆኖም ግን ይህንን ሲረዱና ያሉበትን የቆሸሸ ስፍራ ለቀው ሲወጡ፤ ማደግም መፍካትም ይጀምራሉ። ያኔም ልከኛ ዋጋቸውን ያገኛሉ።
በማይገባህ ስፍራ ስትገኝ ሰዎች ረግጠውህ ያልፋሉ፤ አንተ ለእነርሱ ልዩ አይደለህምና። እናም እባክህን መገኘት ያለብህ ቦታ መገኘትህን እርግጠኛ ሁን!
Join us.....
@Ab_book