+ ትህትና +
👉 ለአንድ መነኩሴ ሰይጣን የብርሃን መልአክ መስሎ ተገለጸለትና "እኔ ገብርኤል ነኝ ወደ አንተ ተልኬ መጣኹ" አለው::
በዚኽ ጊዜ መነኩሴው "እስኪ ወደ ሌላ ተልከኽ እንደኾነ ልብ አድርግ፤ እኔ እንኳንስ አንተን የገዛ ኃጢኣቴን እንኳ ለማየት የበቃኹ አይደለኹም" አለው::
ይኽን ሲሰማ ከትሕትናው ፊት መቆየት የተሳነው ጠላት እንደ ትቢያ በኖ ጠፋ::
በእግዚአብሔር ፊት የተዋረደ ስብዕናን አላብሶ ፀሎታችንን ምፅዋታችንን ፆማችንን እና ድካማችንን ተቀባይነት የሚያሳጣው ትዕቢት ነው። እግዚአብሔር እንደ ትዕቢት የሚፀየፈው ነገር የለም። በዚህ ምክንያት ነው ከዛ ተመፃዳቂ ፈሪሳዊ ይልቅ ያንን ልቡ የተሰበረ ኃጢያተኛ ፀሎት የተቀበለው።
ትህትና እግዚአብሔር እስከ መፀነስ ያበቃች ታላቅ መንፈሳዊ ልብስ ናትና እሷን እንልበስ። የለበስነውም የትዕቢት ልብስ ለባለቤቱ ለዲያብሎስ እንመልስ ያኔ በእግዚአብሔር ፊት ሞገስ አግኝተን መሻታችን ይፈፀማል።
"ሰው ሳይወድቅ በፊት ልቡ ከፍ ከፍ ይላል፥ ትሕትናም ክብረትን ትቀድማለች።" ምሳ.፲፰፥፲፪
ወስብሐት ለእግዚአብሔር🙏
https://t.me/Abalibanos333