በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን
📖መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ላንብብ📖
ክፍል ፮
#የመጽሐፍ #ቅዱስ #ዘይቤ
ዘይቤ ማለት የአነጋገር ስልት ማለት ነው።መጽሐፍ ቅዱስ ራሱን የቻለ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዘይቤ አለው።ዘይቤያዊ አነጋገር እና አገላለጹ የሚመጣውን እንዳለፈ ያለፈውን እንደሚመጣ በማድረግ ይገላጻል። ዘይቤያዊ አነጋገርና አገላለጽን ማወቅ በመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ውስጥ ትልቅ ሚና አለው።
1. #የሚመጣውን #እንዳለፈ #መናገር
የሚመጣውን ነገር እንደሚመጣ ሲናገር ይህ ትንቢት ይባላል። በመጽሐፍ ቅዱስ አገላለጽ ግን የሚመጣውን እንደሚመጣ በመግለጽ እና ያልተፈጸመውን ትንቢት ሲገልጽ እንመለከታለን።ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘይቤ ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ እጆቹና እግሮቹ በመስቀሉ ላይ ከመቸንከራቸው አስቀድሞ በ900 ዓመተ ዓለም የተናገረውን ትንቢት ስንመለከት "እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ አጥንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ...ልብሴን ለራሳቸው ተከፋፍለው በቀሚሴ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ" መዝ 21፡17 በመዝሙረ ዳዊት የተጠቀሰውን የትንቢት ቃል ስንመለከት ቀጥታ ነገሩ እንደተፈጸመ ያመለክታል። ትንቢቱ ግን በብሉይ ኪዳን ተነግሮ በሐዲስ ኪዳን መፈጸሙን ማቴ 27፡1 ጀምሮ ማንበብ እንችላለን። ይህንን የመሰሉ ሌሎች ጥቅሶችም አሉ፦ መዝ 68፡21፣ ት. ኢሳ 53፡4፣ ት. ኢሳ 9፡6 ገና ሊሆን ያለውን ትንቢት በመግለጽ መጽሐፍ ቅዱስ የሚመጣውን እንዳለፈ(እንደመጣ) በመናገር ሲገልጽ እንመለከታለን።
2. #ያለፈውን #እንደሚመጣ #መናገር
መጽሐፍ ቅዱስ የሚመጣውን እንዳለፈ አድርጎ የመናገር ዘይቤ እንዳለው ሁሉ በቀራንዮ ያለፈውን፣የሆነውን ወይም የተፈጸመውን ገና እንደሚመጣ አርጎ የመናገር ዘይቤ አለው። በይሁዳ መልዕክት 1÷7 "እንዲሁም እንደእነርሱ ዝሙትን ያደረጉና ሌላ ስጋ የተከተሉ ሰዶምና ገሞራ በዙሪያቸው የነበሩ ከተሞች በዘላለም እሳት እየተቀጡ ምሳሌ ሆነዋል"
ይህ በይሁዳ የተነገረውን ረጋ ብለን ስናጤነው ድርጊቱ ከተፈጸመ ብዙ ሺህ አመታትን አስቆጥሯል። አነጋገሩ ግን አሁንም ወደፊት እየተደረገ እንዳለ ይመስላል። ይህ ከተከናወነ ግን 2000 ዓመታት አልፈውታል። "እየተቀጡ" የሚለው ቃል የመጽሐፍ ቅዱስን ያለፈውን እንደሚመጣ አድርጎ የመናገር ዘይቤ ያስተምራል። በዕብ 7፡25 "ስለ እነርሱ ሊያማልድ (ሊያስታርቅ) ዘወትር በሕይወት ይኖራል" ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረው ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። የአገላለፁ ዘይቤ ግን ያለፈውን እንደሚመጣ በማድረግ ነው። የተገለጸው ግን ፍፃሜ ያገኘው በዕለተ ዓርብ በቀራንዮ አደባባይ ነው። በዕብ 9፡28 "ሁለተኛ ጊዜ ያለ ኃጢአት ይታያቸዋል" የቅዱስ ጳውሎስን አገላለጽ ስንመለከት ቃሉ ስለሰዎች ኃጢአት ዳግመኛ መከራ ሊቀበል ይመጣል ማለቱ ሳይሆን በዳግም ምፅዓት በእርሱ ሕይወት ላገኙት ይገለጥላቸዋል ማለቱ ነው። አብዛኛውን ጊዜ ስህተቶች የሚመጡት መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ማንበብ እንዳለብን ካለማወቅ ነው። መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ መሪ ያስፈልጋል የሐዋ 8፡30 "ፊሊጶስም ሮጦ የነቢዩን የኢሳይያስን መጽሐፍ ሲያነብ ሰማና በውኑ የምታነበውን ታስተውላለህን አለው። እርሱም የሚመራኝ ሳይኖር እንዴት ይቻላል? አለው" በውስጡ ያሉትን ነጠላ ትርጉም፣ምሳሌያዊ ትርጉም፣ምስጢራዊ ትርጉም፣የሕይወት ትርጉም ዘይቤያዊ አነጋገርን ማወቅ የግድ ነው።
በቀጣይ
📖መጽሐፍ ቅዱስን በጊዜና በሰዓት ከፋፍሎ የማንበብ ስልት እናያለን
የመጨረሻዉ ክፍል ይቀጥላል