Abu Mahira


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


||﷽ Muslim, Student, Islamic inspiration,
Comparative religion,Islamic History,||

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


¶"የረሱል"ﷺ" ልጆች"¶

1} አል ቃሲም፦ በዚህ ልጃቸው ኩኒያ አበል- ቃሲም ተብለው ይጠሩ ነበር። ከነብይነት በፊት የተወለደ ነው። የሁለት አመት ልጅ ሲሆን ወደ ማይቀረው አኺራ ሂዷል።

2} ዐብደሏህ፦ አጥ-ጠይብ አጥ-ጧሒርም ይባላል። ምክንያቱ ከነብዩ ﷺ የነብይነት ማዕረግ በኋላ ስለተወለደ ነው። አጥ-ጠይብ አጥ-ጧሒር የተባለው ከዐብደላህ ሌላ ነውም ተብሏል። { ትክክለኛው የመጀመሪያው ነው}

3) ኢብራሒም፦ በስምንተኛው አመት በመዲና ነው የተወለደው። በአስረኛው አመት ሞቷል። የዱኒያ ቆይታው የ17 ወይም የ18 ወር ብቻ ነበር።


®"ረሱል"ﷺ" የነበራቸው ሴት ልጆች አራት ናቸው።

1} ዘይነብ(ረ.ዓ) ፦ የአክስቷ ልጅ የሆነው አቡል ዓስ ኢብኑ ረቢዓ ያገባት ናት።

2} ፋጢማ(ረ.ዓ)፦ የታላቁ ሰሓብይ ዓሊይ ቢን አቢ ጧሊብ (ረ.ዓ) ባለቤት ናት።

3} ሩቅያ (ረ.ዓ)፦ የዑስማን ኢብኑ አፋን ሚስት ናት።

4} ኡሙ ኩልሱም (ረ.ዓ) ፦ እሷም የዑስማን ኢብኑ አፋን (ረዓ) ሚስት ናት። መጀመሪያ ሩቅያን አገቡ። ከዚያ ሩቅያ ስትሞትባቸው ኡሙ ኩልሱምን አገቡ። ለዚህም ነው ዑስማን ዛ ኑረይን የተባሉት።

©"የረሱል"ﷺ" ሴት ልጆች ያለ ኺላፍ አራት ናቸው። ወንዶቹ ደግሞ በሶሒሕ ሦስት ናቸው።
¶ተሕዚብ ሢራህ ኢብኑ ሒሻም¶


«ዛሬ ላይ ስግብግብነት ሁሉን ነገር እንድናመልክ አድርጎናል። "አላህን"ﷻ" ዱኒያን እንዲሰጣችሁ ብቻ በማሰብ አታምልኩት። ይልቅ! እናንተንም ስራችሁንም እንዲወድላችሁ ብቻ በኢኽላስ አምልኩት። እሱ ከወደዳችሁ ቸር ነው ሁሉንም ነገር ሳትጠይቁት  ይሰጣችኋል።


አላህን"ﷻ"ስትለምኑ ሁሉም ነገር ገር እና ቀላል የሆነ ሕይወት እንዲሰጣችሁ አትለምኑት። ዱኒያ የፈተና መድረክ ናትና መቃረኑ አይቀርም። ይልቅ! የዱኒያን ጣጣዋን የምትጋፈጡበትን ብርታት እና ኃይል እንዲሰጣችሁ ለምኑት።
https://t.me/AbuMahira55


«አንተ ሰዎች በሚሉት ነገር ልብህ የሚጨናነቅ መኾኑን በእርግጥ እናውቃለን፡፡ ጌታህን ከማመስገንህ ጋር አጥራው ከሰጋጆቹም ኹን፡፡
[Surah Al-Ḥijr 97-98]


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
«የሐማስ ጀግኖች ጠላቶቻቸው ተገደውም ቢሆን መልካምነታቸውን ማስተባበል አልቻሉም ድንቅ ሠራዊት ናቸው።

"ምርከኞቹ እስረኛ ሳይሆኑ ቫኬሽን ከርመው የተመለሱ ይመስላሉ። ፈገግታቸው እንዳለ ሁኔታቸው በግልፅ ቋንቋ ያበራል።

"እነዚህ ምርከኞች በአቅሷ ጀግኖች አያያዝና እንክብካቤ በፍቅር ተማርከዋል። ስለ ሐማስ የተነገራቸው ጭራቃዊ ምስል እና በተጨባጭ ከሰራዊቱ ጋር የነበራቸው የ15 ወራት መልካም አኗኗር እንክብካቤ አስደምሟቸዋል።

"ሐማስ ሲማርካቸው ያደርስብናል ብለው ጠብቀውት የነበረው ጭራቃዊ በቀል ባልጠበቁትና ባላሰቡት ሁኔታ ልዩ ፍቅርና እንክብካቤን ቸራቸው። እነሱ የተሰጣቸው የሐማስ ስዕል እና እውነተኛው የሐማስ መልክ እጅግ ይለያያል።

"እነዚህ ምርከኞች ሐማስ ባስቀመጠባቸው ቦታ ከእስራኤል አየር ጥቃት ለመከላከል ጀግኖቹ ራሳቸውን ከፊት አሰልፈው ከለላ እየሆኑ የከፈሉትን መስዋትነት መካድ አልተቻላቸውም።

"ለእያንዷንዱ ላደረጋችሁልን መልካም እንክብካቤ አኗኗር እናመሰግናለን ሲሉ ለዓለም መስክረውላቸዋል። የነፍስያ እና የስሜትን ሕግ በሸሪዓ መርሕ አሸንፈዋል።

"የሐማስ ጀግኖች ምርከኞችን ለማሰቃየት ለመበቀል ተዘርዝሮ የማያልቅ የውስጥ ሕመም አላቸው። ግን ይህን የውስጥ ቁስል ዋጥ አድርገው ነፍስያቸውን አሸንፈው "እነሱ ለእኛ አርዓያ አይደሉም" ብለው እንደ እነሱ ከማድረግ ተቆጥበው የራሳቸውን ቅዱስ-መርሕ ለዓለም በማሳየት የትክክለኛ አሸባሪውንና የጭራቁን ማንነት ለዓለም ግልፅ አድርገው አሳይተዋል።

"ኃያሉ አሏህ እስከ መጨረሻው ኃይልንም ነስሩንም ይወፍቃቸው።
https://t.me/AbuMahira55


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
«ይሁንና ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ሥላሴ እንደሚያስተምሩን የሥላሴ-አካላት "የእግዚአብሔር ባሕርያት" የሆኑት ሁሉ አላቸው። እያንዳንዱ አካል ፍጹም አምላክ ነውና።
{ነገረ-መለኮት 244}

«ጥያቄ፦ ታዲያ እያንዳንዱ አካል ራሱን የቻለ በየግሉ ሁሉም "ፍፁም አምላክ" ከሆነ ሦስት አማልክት እንጂ በምን ቋንቋ "አንድ" ይባላሉ?

"ስለ "አንድ" የሆነ ነገር ሲወራ "ነው" እንጂ "ናቸው" አይባልም። "አለው" እንጂ "አላቸው" አይባልም። "አንድ አምላክ እንደሆነ" እንጂ "አንድ አምላክ እንደሆኑ" አይባልም። ክርስትና ግን ብዛታቸውን አምኖ በብዜት ቋንቋ እያወራ እንደገና ተመልሶ "አንድ" ነው ለማለት "አንድ "ናቸው" ይላል።

"የሥላሴ "አካላት" የሆኑት ሁሉም ማለትም "ሦስቱም "የእግዚአብሔር ባሕሪ" አላቸው» ይላሉ። ለእነዚህ ሦስት አማልክት የባሕሪ ምሳሌ የሆነው "እግዚአብሔር" የቱ ነው? ማንኛው ነው?


¶"በድር" ¶

® «የበድር ዕለት በእርግጥም እውነት ከሐሰት የተለየበት ዕለት ነበር። የእውነትና የሐሰት ኃይላት ከዚያ በፊት በይፋ ጦር ተማዝዘው እያውቁም ነበር። የበድር ዕለት ጦር ተማዘዙ። ከሐሳብ ጦርነት ባሻገር ምድር ላይ ግንባር ለግንባር ተሞሻለቁ። ግዙፉ የሐሰት ኃይል ተንኮታኮተ እውነት ግልጽና ይፋ ወጣ።

® «ከዚያ በፊት ሙስሊሞች ከጠላቶቻቸው ጋር ጦር እንዲማዘዙ አልተፈቀደላቸውም ነበር። በትዕግስት እንዲጠባበቁ የሚደርስባቸውን ጥቃት ሁሉ እንዲሸከሙ ነበር የታዘዙት። የበድር ዕለት ግን ይህ ዘመን የማብቃቱ ዜና በተግባር ታወጀ። የጡንቻ ግብግብ ተጀመረ።

® "ኢስላም መንፈሳዊ ብቻ ሳያይሆን፥ ምድርን ከግፍና ጭቆና ሥረዓት ለማጽዳትና የሰውን ልጅ እውነተኛ ነጻነት ለማጐናፀፍ የመጣ ሃይማኖት (ዲን) እንደመሆኑ በሰበካ ብቻ ሊወሰን እንደማይችል የትጥቅ ትግል እንደሚያሻው የተረጋገጠበት ዕለት ነበር።

® "በድር"፦ ኢስላም ለዚህ ቅዱስ ዓላማ የሰው ልጆችን የሕይወት መርሕ ሥረዓት ለመዘርጋት ሲንቀሳቀስ በሥጋት ለሚያዩትና እንቅፋት የሚሆኑበትን ኃይላት ሁሉ በኃይል ማንበርከክ ግዴታ እንደሆነ የተገለፀበት ዕለት ነው። በዚህ የተጨባጭ ትርጉሙ ነው የበድር ዕለት “የውመል ፉርቃን" የተባለው።

® «በሰው ልጅ ታሪክ ላይም “የመለያ ቀን” ወሳኝ ሊሆን ይችላል "በድር"፡፡ ከዚህ ዕለት በፊት የሰው ልጅ ባጠቃላይ ኢስላማዊውን ሥርዓት በተሟላ መልኩ አላየውም አያውቀውም። በወቅቱ ዓለም በጃሒሊያ መንግሥታትና ጨቋኝ ሥርዓቶች ትመራ ነበር። ከበድር ዕለት በኋላ ግን በመለኮታዊ እምነትና አመለካከት ላይ የታነፀ አዲስ ሥርዓት አዲስ ሕገ-መንግሥት ለዓለም ይፋ ሆነ።፡

® «የሰው ልጅ "ለድል" ያለው ግንዛቤም የተስተካከለበት ዘመቻ በመሆኑም “የውመል ፉርቃን” ሊሰኝ ችሏል። ሙስሊሞች በሁሉም ምድራዊ ሚዛን ለሽንፈት በሚያበቃቸው ሁኔታ ውስጥ ነበሩ። በቁጥር እጅግ አናሳ፣ ሁነኛ የጦር መሣሪያም ያልታጠቁ ነበሩ።

"በአንጻሩ ከሓዲያን በምድራዊ መስፈርት ለድል የሚያበቃቸውን የሰው ኃይልም ሆነ የመሣሪያ ጥንካሬ ነበራቸው። አላህ ጦርነቱን በዚህ ተጨባጭ እንዲከናወን አደረገው፡፡ የድል ሰበቡ የጡንቻ ጥንካሬ ሳይሆን የእምነት ፅናት፣ የዓላማ አንድነት እንደሆነ በውጤቱ አሳየ። የዚህ ዲን ተከታዮች ከጠላቶቻቸው ጋር በሚያደርጉት ፍልሚያ የሚያደርጉት አቢይ ዝግጅትም ምን ሊሆን እንደሚገባ በተጨባጭ ያስተማረ ዕለት ነበር፡፡




«ሐቂቃ የትግራይ መጅሊስና መሻይኾች ታላቅ ክብርና ምስጋና ይገባቸዋል። አርዓያም ናቸው። ሕዝብን ከፊት ሁኖ ታግሎ ማታገል እንዲህ ነው። ይህ ችግር የትግራይ ችግር ብቻ እንዳልሆነ ሁላችንም እናውቃለን።

«የሒጃብ ጉዳይ ሀገሪቱ ላይ ለረጂም ጊዜ ስር የሰደደ እና በየ ጊዜየው ደስ ባላቸው ጊዜና ቦታ ጥቁር ጥላቻቸውን ከሚገልፁበት መንገድ የሒጃብ ጉዳይ በጣም ትንሿ ማሳያ ናት።

«አሁንም ቢሆን ትግራይ ላይ ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱ ላይ ባለው የትምህርት ስረዓትና ረቂቅ አዋጅ ጭምር ተፈትሾ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር ውይይትም ካስፈለገ መንገዱን ማመቻቸት ግድ ነው።

"የሕግ-ባለሙያዎች ተዋቅረው የእህቶቻችን ሒጃብ መልበስ ከሴሰኞች እና ጭፍን ጥላቻን ካረገዙት ውጭ ሌላ ማንንም እንደማይነካ አስረግጠው ካሳመኑ በኋላ እንደ ሀገር ቋሚና ዘላቂ የሆነ ሕጋዊ መፍትሔና ድንጋጌን ይፈልጋል።

"አለዚያ የማንም ወፈፌና ሰካራም ደስ ባለው ጊዜ እየተነሳ ሲከለክለን እነሱም ጥላቻቸው ወደር የለውምና አያርፉም ለእኛም እያረፉ ለቅሶ እንጂ ዘላቂ መፍትሔ አይኖረውም።


«ለትዳር የማይሆኑ 5 ሴቶች»

1] «ስለ እንያንዳንዷ ነገር በዝርዝር ስሞታ የምታበዛ፣ ማለፍን የማታውቅ አዎንታዊ ዕይታ የሌላት፣ በቃ ሁሉም ነገር የማያስደስታት ባሏ ሲወጣም ሲገባም እያሟረተች የምታማርር ናት።

2] «በቧሏ ላይ ሁሌም የምትመፃደቅና የምትኮፈስ ናት። «በምን ወንጀሌ ነው አንተ ላይ የጣለኝ? እኔኮ ለአንተ የምገባህ ሴት አልነበርኩም» ባይ ናት።

3] «ዓይኗ ያረፈበትን ነገር ሁሉ ሰፍ የምትልና የምትመኝ መብቃቃት የጎደላት። ጓደኛዋም ቤት ከሄደች የጓደኛዋን ዕቃ አንድ በአንድ ቆጥራ ትመጣና ለባሏ እከሌ እኮ እንትን አላት እያለች ባሏን ለአላስፈላጊ ወጭ ትጋብዛለች። ሱፐር ማርኬት ከሄደች እንዳለ ሙሉን መረከብ ያምራታል።

4] «የራሷን ውበት ቁንጅናዋን ጥበቃ ላይ ብቻ ቢዚ የሆነች የባሏንም ሆነ የቤቷን ኃላፊት የረሳች ናት። ከየ ማስታወቂያው አመድና ዱቄት እየፈለገች በመግዛት መለቃለቅና መበጃጀት እንጂ ሌላ ስራ የላትም።

5] «ይችኛዋ ደሞ ዝም የምትልበት ሰዓት በጣም ትንሽ ነው የምትለፈልፍበት ሰዓት ደሞ ብዙ ነው። ምላሷ ረጂም እንደ ጦር የምትፈራ ናት። ንግግሯና ጩኸቷ ከጀመረች ማቆሚያ የለውም። ለጎረቤትም ይተርፋል። በጮኸችና ተናዳ በለፈለፈች ቁጥር ሁሉንም ጎረቤት ያውካል።

"እነዚህ ለወንድ ልጅ ሰላምና ምቾትን የማይሰጡ በጣም አስቸጋሪ ባህሪያት ናቸው።

ለትዳር የማሆኑት ወንዶቹስ እንዳትሉኝ። የወንዶቹን እናንተ ሴቶቹ ተናገሩ ፈቅደናል😀


¶ዘካ¶
«ዘካ" ከኢስላም መሠረቶች አንዱና ዋነኛው ምሰሶ ነው። የክፍፍል ሥርዓቱም ለስምንት ዓይነት የኅብረተሰብ ክፍሎች ይሰጣል፦

1) «”ድሆች" {ፉቀራእ}፦ እነዚህ መሠረታዊ ፍላጐታቸውን በምንም መልኩ በትንሽም ማሟላት የተሳናቸው ናቸው፡፡

2) «ችግረኞች» {መሳኪን}፦ እንደ መጀመሪያዎቹ ድሆች ሆነው 'ግን ችግራቸውን ለሰው ለማካፈል የማይደፍሩና ከድሆች በትንሹ የተሻሉ ናቸው፡፡ አላቸው ግን ለመሠረታዊ ነገር በቂ አይደለም።

3) «በርሷ ላይ ለሚሠሩ ሰዎች»፦ ዘካን የመሰብሰቡንና የማከፋፈሉን ተግባር የሚያከናውኑ ወገኖች ናቸው፡፡

4) «ልቦቻቸው (ኢስላምን) እንዲላመዱ የሚከጀሉ ወገኖች»፦ አዲስ ኢስላም የተቀበሉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ልባቸው በኢስላም ላይ እንዲፀና ዘካ ይሰጣቸዋል። ወይም ለኢስላም ጥሩ አመለካከት እንዲኖራቸውና ሸራቸውን ለመከላከል ወይም እንዲሰልሙ የሚከጀሉ ወገኖች ሊሆኑም ይችላሉ።

5) «ለባሪያዎች›፦ ይህ ድንጋጌ የባሪያ አሳዳሪ ሥርዓት ዓለም አቀፋዊ ሥርዓት በነበረበት ወቅት የወረደ ነው፡፡ ዘካ የባሪያ ሥርዓቱ እንዲከስምና እንዲጠፋ ታላቅ ሚና ተጫውቷል። በተመሳሳይ ሁኔታ የጦር ምርኮኞችን ነጸ ለማውጣትም የዘካ ገንዘብ ጥቅም ላይ ይውላል።

6) «ባለዕዳዎች»፦ ዕዳቸውን ይከፍሉና እፎይ ይሉ ዘንድ ከዘካ ገንዘብ ይሰጣቸዋል።

7) «በአላህ መንገድ ለሚደረግ ትግል»፦ በአላህ መንገድ የሚደረግ ትግል ዘርፈ ብዙ ነው፡፡ በሰይፍ ፣ በጠመንጃ፣ ወይም በብዕር፥ ወዘተ ... ሊሆን ይችላል።

8) «ስንቅ ያለቀበት መንገደኛ»፦ ለሀገሩ መዳረሻ የሚያበቃውን ያህል ገንዘብ ከዘካ ላይ ይሰጠዋል።

«ዘካ በርካታ ማኅበራዊ ችግሮችንና ቀውሶችን በመቅረፍ ረገድ እጅግ ጠቃሚ ሚናን ይጫወታል። አሁን ላይ ዘካ ምን እንደ ሆነ የማያውቅ ማህበረሰብ ተፈጥሯል። ነገር ግን ያሉብንን ብዙ ማህበረሰባዊ ቀውሶችን እንደ ዑማ ለመቅረፍ ዘካ ትልቁን ድርሻ ይወስዳል። የግል ሐያታችንም በረካ ይኖረዋል።


«ጂሐድ እና ሶሓቦች»

«እነዚያም ለጉዞ የሚሆን እንስሳ የጠየቁህና ላገኝላችሁ አልችልም" ያልካቸው ለጂሃድ የሚያውሉት ገንዘብ ሊያገኙ ባለመቻላቸውም እጅግ አዝነውና ዓይኖቻቸው እንባ እየረጩ የተመለሱትንም ወቀሳ የለባቸውም፡፡ (9/92)

«የዚችን አንቀጽ መውረድ በተመለከተ ከኢብን ዐባስ (ረዐ) የተላለፈው ዘገባ እንዲህ ይለናል፦

«የአላህ መልዕክተኛ "ﷺ" ሰዎችን ስንቅና ትጥቃቸውን አዘጋጅተው ከርሳቸው ጋር እንዲዘምቱ አዘዙ። ከባልደረቦቻቸው ከፊሎቹ የጉዞ እንስሳ ሊጠይቋቸው ከርሳቸው ዘንድ ቀረቡ። ዐብደላህ ኢብን ሙገፈል አል-ማዚኒ አብሯቸው ነበር።

«የአላህ መልዕክተኛ ሆይ! ለጉዞ የሚሆነን እንስሳ ይስጡን» በማለት ጠየቁ መልዕክተኛውም፦፡ «“በአላህ እምላለሁ አላገኝላችሁም» አሏቸው፡፡ እያለቀሱ ተመለሱ። ምክንያቱም ከጂሃድ መቅረት ለእነሱ በእጅጉ ከባድና የሞት ሞት ነበር።

«አላህﷻ ለእርሱና ለመልዕክተኛው"ﷺ" ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር በመመልከት ይህችን አንቀጽ በማውረድ ስሜታቸውን አከመ። ታሪኩ የሰሓቦችን ሐቅን ለመርዳትና የበላይ ለማድረግ የነበራቸውን ከፍተኛ ጉጉትና ጥልቅ የጂሃድ ስሜት በጉልህ ያሳያል።

«በእንዲህ ዓይነት መንፈስ በሚደረግ ትግል ነው ድሮ ኢስላም ለድልና ለበላይነት የበቃው። ተራው ሕዝብ ኢስላምን እንዳይሰማና እንዳያውቅ እንቅፋት የነበሩ ኃይሎችን ያንኮታኮተውና ዓለምን ለዘመናት በበላይነት የመራውም በእነዚህና መሰሎቻቸው ጀግኖቹ ነበር፡፡

«በወቅቱ የነበሩ ግዙፎቹን የሮማንና የፐርሺያን ኢምፓየሮች ጭምር በአጭር ጊዜ ውስጥ ያንበረከከው በዚህ መንፈስና ወኔ ነበር፡፡

«ዛሬ ላይ “ሙስሊሞች” ከዚህ ስሜት ጋር ምን ያህል ተራርቀናል? የሚለው ለማንም ግልፅ ነው። ያለንበትም የውርደት አዘቅጥና የበታችነት ስሜት ጂሐድን ችሎ መኖር ብለን እንድንተረጉም አድርጎናል። አሁን ላይ ከዲኑ ላይ ይቅርና ከነፍሳችን ላይ በምላሳችን እንኳን ዲፋዕ ማድረግ አቅቶናል።

«ታዲያ ዛሬ ላይ ይህ ለጂሐድ የምንሰጠው ትርጓሜ እና ኢስላም ዓለምን ከመራበት ትርጓሜ አንጻር ሲታይ እጅጉን ይለያል። ከዚህ ዑማ ግን አሕሉ -ገዛ ይለያሉ። ጥንታዊው ጂሐድ ትርጉሙንም መንፈሱንም የተረዱ ወኔውንም የታጠቁ ናቸው ብንል ማጋነን አይሆንም። እንደ እነርሱ መሆን ቢያቅተን እንኳ እነሱን ማድነቅና ለእነሱ ነስርን መመኘት ከኢማን ነው። አላህ ቀልባችንን ለጂሐድ ሕያው ያድርግልን።

«ይህንን የጀግኖች ጥምር ፎቶ አይቶ በቀልቡ እንኳ መቀላቀልን ያልተመኘች ቀልብ አላህ ድጋሚ ሩሕ ይዝራባት።
https://t.me/AbuMahira55




እስልምና ላይ የሚቀርቡ ጥያቄዎችንና በሀይማኖት ንጽጽር ዙሪያ የሚሰሩ ስራዎችን ጥልቅ በሆነ መልኩ ስራዎችን ለመስራት እንዲያግዝ በማሰብ ሒዳያ ኢስላማዊ ማዕከል በስሩ የጥናትና ምርምር ዘርፍ አቋቁሟል።

በዚህ ዘርፍ ውስጥ የንጽጽር ዱዓቶችን ጨምሮ ተተኪ ወንድምና እህቶች ሰፊ ጊዜዎችን በመውሰድ ስራዎችን እንዲያጠኑ፣ በየቋንቋቸው የጥናት ውጤታቸውን እንዲያዘጋጁ በማመቻቸት ላይ ይገኛል።

ለስራውም በአማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ አረብኛ እና እንግሊዝኛ የተጻፉ መጽሀፍትን ለማሟላት ጥረት እየተደረገ ሲሆን ለዚህ የሚያግዙ እናንተ ጋር የተቀመጡና ለተቋማችን ይጠቅማል የምትሏቸው መጽሀፍት ካሉ በሚከተለው ስልክ ቁጥር ለአስተባባሪዎች በመደወል መስጠት የምትችሉ ሲሆን ቢሮ መጥቶ መስጠት የሚችሉም ይበረታታሉ።

አድራሻ፦ ቤተል
ስልክ፦ 0910858830


◇ «ከሙስሊሙ ዓለም የፈሰሰው የደም ጅረት አጠቃላይ በአሜሪካ እጅ ነው። የዚህ የአንድ አመት የጋዛ ጦርነት እንኳ እስራኤል መዶሻ ብትሆንም መዶሻውን ይዛ ቀጥቃጯ እና ሚናውን የምትጫወተው አሜሪካ ናት።

◇ «"ባለፈው Jan 4 New York Post ባስነበበው ዘገባ ላይ አሜሪካ ለእስራኤል የ8,ቢሊዬን ዶላር የጦር መሳሪያ ሽያጭ ዕቅድ መያዟን አስነብቧል። ይህ ዕቅድ ለተፈፃሚነት የምክር ቤት እና የሴኔት አባላቱን ውሳኔ በመጠባበቅ ላይ እንደሚገኝም ገልጿል።

◇ «አሜሪካ ይህንን ሁሉ የምታደርገው ለእነሱ እስራኤል የያዘችው ጦርነት ከሙስሊሞች ጋር ስለሆነ ሙስሊሙን ዓለም ማጥፋት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሳይሆን ራስን የመከላከል የሕልውና ውጊያ ነው ብለው ስለሚያኑ ነው።

◇ «አሁንም አሜሪካ እስራኤል የያዘችውን የማጥቃትና የንጹሓን ጭፍጨፋ ሒደቱ እንድትቀጥል እንደምትፈልግ ብዙ ማሳያ አለ።

◇ «እንደ New York Post ዘገባ መሠረት ከጦርነቱ መቆራቆስ ጅማሮ እስካሁን በዚህ አንድ አመት ውስጥ አሜሪካ ለእስራኤል የ22,ቢሊዬን ዶላር የጦር ድጋፍ አድርጋለች።

◇ «ባለፈው ነሐሴ ወር ላይ ብቻ ለእስራኤል የ20,ቢሊዬን ዶላር የጦር መሳሪያ ጭያጭ አፅድቃለች። ድጋሚ ሕዳር ወር ላይ የ 680,ሚሊዬን የጦር መሣሪያ ሽያጭ አፅድቃለች።

◇ "ይህ ሁሉ ርብርብና ዝግጅት በኃያልነታቸው ተኮፍሰው ንጹሓንን ለመፍጀት ብቻ ነው። ትራምፕ ጋዛን ጀሐነም እናደርጋታለን ብሎ በዛተ በ24 ሰዓት የአሏህ"ﷻ" ፍርድ ቀደመ። ጀሐነምን የሚያውቁት በሰው ቀዬ የለኮሱትን እሳት የሚያዩት በቲቪ ነበር። አሁን ደሞ ዐዲል የሆነው አላህ"ﷻ" በራሳቸው ቀዬ በዓይናቸው እያሳያቸው እሳቱንም እየሞቁ ነው።

"ኃያልነትና ልዕልና ግን የአሏህ"ﷻ" ብቻ ነው። እነሱ ባያውቁም እኛ እናውቃለን። እነሱ ባያዩም እኛ እያየን ነው አልሐምዱሊላህ።


"ተረቴን መልሱ አፌን በዳቦ አብሱ" ያው እሱ ረስቶት መሰለኝ😀 ያው በተረት ተረት እና በዐረቄ PHD ሲኖርህ ውጤቱ ይህን ይመስላል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram


"እንኳን አደረሳችሁ" ማለት፦
"ይህንን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ ለጉርብትና ብሎ፣ ለመመሳሰል፣ ይሉኝታ ይዞትም ይሁን አልያም በእነሱ ለመወደድ አስቦ ይህን ከፈፀመ ትልቅ ወንጀልን ሠርቷል።

«ኩፋሮችን ልዩ በሆነ በዓላቸው እነሱን እንኳን አደረሳችሁ ማለት ሐራም ነው። ይህን ያደረገ ሰው ከኩ*ፍ*ር ቢተርፍ እንኳን ለመስቀል መስገዳቸውንና የኩፍር ተግባራቸውን እንደ ማበረታታት ይቆጠራልና ከዝሙት እና ከአስካሪ መጠጥ እንዲሁም ነፍስን ከመግደል በላይ የከፋ ወንጀል ሠርቷል»። {أحكام أهل الذمة ابن القيم}




ኢብን-ሢና"

"ሰሞኑን Islamic Golden Age 800-1400 C.E ከነበሩ ሙስሊም ሳይንቲስቶች ሳጠና ለዘመናዊው ዓለም የሕክምና ሳይንስ ትልቅ ሚና ካበረከቱና ግንባር ቀደም ተጠቃሽ ከሆኑት ሳይንቲስቶች አንዱ «ኢብኑ -ሢና አገኘሁ።

Ibn Sina, በምዕራቡ ዓለም "Avicenna" ይሉታል። ታላቅ"philosopher" እና "physician ነበር። ምዕራባዊያኑ "The Father of early modern medicine" ይሉታል።

"አል-ቃኑን ፊል-ጢቢ"The Canon of Medicine" የተሰኘ ለዓለም ትልቅ መድብለ-ዕውቀት መጽሐፍን አበርክቷል። ይህ "የኢብን ሢና" መጽሐፍ እስከ 18th ክፍለ ዘመን ድረስ ለሕክምና ሳይንስ እንደ ዋና ማጣቀሻ ምንጭ" Encyclopedia of medicine" ሆኖ ለዓለም አገልግሏል።

""ይህ "The Canon of Medicine" የተሰኘው መፅሐፉ እስከ 18th Century ድረስ በአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች ጭምር እንደ ዋና የሕክምና ሳይንስ ማጣቀሻና መማሪያ መጽሐፍ ተደርጎ ነበር።
https://t.me/AbuMahira55

20 last posts shown.