📢 አንዘናጋ! ያለፈው አልፏል የተቀሩትንም
የተቆጠሩ ውድ የረመዷን ቀናቶች ከዘመናዊ
ሌባ እንጠብቅ‼️
√√√√√√√√√👌
↪️ ሶሻል ሚዲያ (𝕤𝕠𝕔𝕚𝕒𝕝 𝕞𝕖𝕕𝕚𝕒) ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ዋነኛ እና ግንባር ቀደም ችግር ሆኗል፡፡ በብዙ ቦታዎች በቤትም፣ በመስሪያ ቤትም፣ በመስጂድ፣ ስንበላ እና ስንጠጣ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ገንዘባችንን እያፈሰስንበት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከተለያዩ ዒባዳዎች ቁርኣን ከመቅራት፣ ደርስ ከመከታተል፣ ከዚክር፣ ከዱዓ፣ መልካም ስራዎችን ከመስራት..... እንድንርቅ እና እንድንራቆት አድርጎናል። የሞቱ ሰዎች በመቃብሮቻቸው ዉስጥ ናቸው። ጥሩም ይሁን መጥፎ ከሥራዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ተመልሰውና ወደ ዱንያ መጥተው መልካም የመሥራት ዕድላቸው ዜሮ ነው። እዚያ ሆነው በዋዛ ፈዛዛ ስላሳለፉት የምድር ላይ ጊዜያቸው ይቆጫሉ። በሚገባ ስላልተጠቀሙበት ዕድሜያቸው ይፀፀታሉ። ምን አልባት ወደ ዱንያ ብትመለሱ ምን ታደርጋላችሁ ተብለው ቢጠየቁ «ከረመዷን አንድ ቀን አገኝተን ብንፆም» ብለው መመኘታቸው አይቀርም። እኛ ደሞ የአላህ ፍቃድ ሆኖ እነዚህን ቀናቶች አገኝተናል እና ውዶቼ… እንደ ዋዛ አልፈው ነገ ላይ እንዳንፀፀት እንጠንቀቅ! ጊዜያችንን በአግባቡ እና በፕሮግራም እንጠቀም።
✅ ሶሻል ሚዲያ ላይ ደርቀን አፍጠን እንደምንዉለው ሁሉ ቁርኣን ላይ ብናፈጥ ኑሮ በተወሰኑ ቀናት ዉስጥ ቁርኣንን እናኸትም ነበር።
✅ የሞባይላችን ባትሪ ሲጎድል ተጨንቀን፣ ተስገብግበን እንደምንሞላው ሁሉ የኢማናችንን ቻርጅ ለመሙላት ጉጉት ቢኖረን የኢማን ድሃ ሆነን አንቀርም ነበር።
✅ በየጊዜው ለኢንተርኔት ዳታ ከምናወጣው ገንዘብ ለችግረኞች ጥቂት ብንለግስ ወይም ለመልካም ሥራ ብናዉል ምንዳችን ይበዛ ነበር።
➲ ስልክ ይዞን እየጠፋ ነውና መንቃት አለብን። ረመዷን ደግሞ የትርፋማ ንግድ ወር ነው። ስለዚህ እንዳያዘናጋን በዒባዳዎች እንጠናከር አደራ! አደራ! አደራ!
📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy