القناة التعليمية الرسمية للدعوة السلفية في الحبشة


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


☞ዋናውን የቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት @AbuYehyaAselefy በዚህ ይቀላቀሉ!!
➲የዩቲዩብ ቻናላችንን ለማግኘት እና ቤተሰብ ለመሆን ⬇️
https://youtube.com/channel/UCrHkOu8UyG5-TDewqfcQG5Q
💡☞ለአስተያየት ወይንም ለጥቆማ እንዲሁም ስህተት ካያችሁብኝ በፍጥነት በዚች ይጠቁሙኝ ☞ @AbuYehyabot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ተሳትፎው በጣም ደስ የሚል ነው። በተጀመረው የቆራጦች ብቻ የአምስተኛው ዙር የ200 ብር ዘመቻ 20 ሰዎች ተሳትፈዋል። የቀረው የ668 ቆራጥ ሰዎች ተሳትፎ ነው። እንደውም አንዳንዶች እየጨመሩ 1000 እያስገቡ ነው። አንዳንዶች ደግሞ ስማቸውን ሳይለንት አድርገው ሳይናገሩ ገቢ በማድረግ አካውንቱን የሚደግፉ የጀግኖች ኮከቦች አሉ። ስለዚህ ወንድሜ ከበጎ አድራጊዎች ተሳተፍ። እንደዚህ አይነት ቀላል ብለህ የምትሰራቸው በጎ አድራጎቶች ምናልባትም ለነገ ቀብር ህይወት ተስፋህ ሊሆን ይችላል። አብሽር ወንድሜ አብሽር እህቴ ተሳተፉ። ነጌያችንን ዛሬ እናሳምረው ዛሬ እንገንባው።

በዚህ ታላቁ ወር ትልቅ አሻራ እንጣል።

የባንክ ሂሳብ ቁጥር
ንግድ ባንክ 1000619092175
አቢሲኒያ 192421349
ሙሀመድ፣ አብዱልሀሚድና ኢብራሂም


ያ አሏህ እንዴት ያለ የሚገርም ፍጥነት ነው?

ዛሬ የረመዷን 13 ኛው ለሊት ነው ይህ ማለት ከነገ ወዲያ የረመዷን ግማሽ ነው በሉኛ ።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
اعملوا في رمضان كأنكم لا تحيون بعده
|| 🎙 الشيخ د. صالح بن عبدالله العصيمي

📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


ጥንቃቄ! ⚠️

ቀጥታ አካወንታችሁን ነው የሚጠልፉት ይህን
ሊንክ ተጭናቹ እንዳትገቡ አደራ ከምታምኑት  ሰውም ጭምር ቢላክላችሁ  እንዳትነኩት የነዛ ሰዎች አካወንት ተጠልፎባቸው ነው።

ጥንቃቄ ጥንቃቄ ለሁሉም ሼር አድርጉት ይህ የነካችሁ ካላችሁ በቀጥታ አካወንታቹ ሀክ ተደርጓል ማለት ነው።
scam ነው

➲ ይህን ሁለተኛ ፎቶ ላይ ያለውን setting በማስተካከል የተጠለፈባችሁን አካወነት አስመልሱ

Settings -> devices -> በቀይ የተፃፈውን Terminat All Other session  የሚለውን ተጭናቹ  ok በማለት 24  ሰአት ሳይቆይ አስወግዱት 24  ሰአት ከቆይ እናንተን ሙሉ ለሙሉ የማስወገድ ሀይል አለው

ለሁሉም ሼር አድርጉት

📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


Forward from: በኡስታዝ አቡ ጀዕፈር ❨አቡ አነስ❩ ሙሐመድ አሚን ተቀርተው የተጠናቀቁ ደርሶች መገኛ ቻናል
||- አዲስና ወቅታዊ የሆነ ተቀርቶ የተጠናቀቀ ደርስ
📢 ረመዷንን በእውቀት እንፁም!
 ➩➪➩➪➩🔎

📖📖📖 اسم الكتاب:- «تذكرة الصوام بشيء من فضائل الصيام والقيام وما يتعلق بهما من أحكام»
📖📖 የኪታቡ ስም፦
«ተዝኪረቱ አስ’ሱዋም ቢሸይኢን ሚን ፈዷኢሊ ’ሲያሚ ወልቂያም ወማ የተዓለቁ ቢሂማ ሚን አሕካም»
===========>

🎙በውዱ ኡስታዛችን በኡስታዝ አቡ ጀዕፈር [አቡ አነስ] ሙሐመድ አሚን አላህ ይጠብቀውና

🕌 በሸዋሮቢት ከተማ የሰለፍዮች ፉርቃን መስጂድ የተሰጠ ወሳኝ አንገብጋቢ የሆነ ትምህርት

📱↯↯↯↯ ከክፍል 01 እስከ 17

💡⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Durusu_Abu_Anes/1189
https://t.me/Durusu_Abu_Anes/1189


👉 ቁኑትን ማስረዘም
  
እንደ ሚታወቀው ረመዳን የዒባዳ ወር ነው። በዚህ ወር ከሚሰሩ ዒባዳዎች በተለይ በለሊቱ ከፍለ ጊዜ ሶላተል ተራዊሕ ነው። የተራዊሕ ሶላት ሱና መሆኑ ጥርጥር የለውም። ስንት ረካዓ በሚለው ውዝግቦች ቢኖሩም። በለሊት ሶላት የተወደደውና ከነብዩ በተግባር የተገኘው 11 ወይም 13 ረካዓ ሲሆን በንግግራቸው የለሊት ሶላት ሁለት ሁለት ረካዓ ነው ፈጅርን የፈራ ስው በዊትር ይዝጋው ብለው ልቅ ያደረጉት ስለሆነ ከተጠቀሱት ቁጥሮች መጨመር አይቻልም የሚለው ሚዛን የሚደፋ አይደለም። ነገር ግን ቁጥሩንም አሰጋገዱንም እሳቸው ሲሰግዱ በነበረበት ሁኔታ እሰግዳለሁ የሚል ከሆነ ይህ በላጭ ነው።

💡ወደ ርእሴ ስመለስ በተራዊሕ ሶላት ዊትር ላይ ዱዓእ ማድረጉም ሱና ነው። አንዳንድ የኢስላም ሊቃውንቶች ከረመዳን ግማሽ በኋላ ነው የሚቻለው የሚል እይታ ያላቸው ሲሆን አመዛኙና ከመረጃ አንፃር ከመጀመሪያ ጀምሮ ማድረጉ ሱና መሆኑ ነው።

በዚህ ቁኑት ላይ የሚደረገው የዱዓእ አይነት የተገደበ ነው ወይስ ኢማሙ በፈለገው የዱዓእ አይነት ማድረግ ይችላል የሚለው ሰፊ ውዝግብ ያለበት ሲሆን አንዳንዶች ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ለሑሴን ካስተማሩት ዱዓእ መጨመር አይቻልም ይላሉ። ሐሰን ኢብኑ ዐልይ ከነብዩ የተማረው የቁኑት ዱዓእ የሚከተለው ነው፦

📜 اللَّهُمَّ اهْدِني فِيمَنْ هَدَيْتَ وعَافِني فِيمَنْ عَافَيْتَ وَتَوَلّني فِيمَن تَوَلَّيْتَ وبَارِكْ لِي فِيما أَعْطَيْتَ وَقِني شَرَّ ما قَضَيْتَ فإنَّكَ تَقْضِي وَلا يُقْضَى عَلَيْكَ وَإِنَّهُ لا يَذِلُّ مَنْ وَالَيْتَ تَبَارَكْتَ رَبَّنا وَتَعالَيْتَ.“
       📚قال الترمذي : هذا حديث حسن

📜ሌሎች ደግሞ ዑመር ኢብኑል ኸጣብ ያደረገውን መጨመር ይቻላል ይላሉ። ዑመር ያደረገው ዱዓእ የሚከተለው ነው፦

📜 ”اللَّهُمَّ إنَّا نَسْتَعِينُكَ وَنَسْتَغْفِرُكَ وَلاَ نَكْفُرُكَ وَنُؤْمِنُ بِكَ وَنَخْلَعُ مَنْ يَفْجُرُكَ، اللَّهُمَّ إيَّاكَ نَعْبُد ولَكَ نُصَلِّي وَنَسْجُد، وَإِلَيْكَ نَسْعَى وَنحْفِدُ، نَرْجُو رَحْمَتَكَ وَنَخْشَى عَذَابَكَ إنَّ عَذَابَكَ الجِدَّ بالكُفَّارِ مُلْحِقٌ. اللَّهُمَّ عَذّبِ الكَفَرَةَ الَّذِينَ يَصُدُّونَ عَنْ سَبِيلِكَ ويُكَذِّبُونَ رُسُلَكَ وَيُقاتِلُونَ أوْلِيَاءَكَ. اللَّهُمَّ اغْفِرْ للْمُؤْمِنِينَ وَالمُؤْمِناتِ والمُسْلِمِيَ والمُسْلِماتِ وأصْلِح ذَاتَ بَيْنِهِمْ وأَلِّفْ بَيْنَ قُلُوبِهِمْ وَاجْعَلْ فِي قُلُوبِهِم الإِيمَانَ وَالحِكْمَةَ وَثَبِّتْهُمْ على مِلَّةِ رَسُولِ اللَّهِ صلى اللّه عليه وسلم وَأَوْزِعْهُمْ أنْ يُوفُوا بِعَهْدِكَ الَّذي عاهَدْتَهُمْ عَلَيْهِ وَانْصُرْهُمْ على عَدُّوَكَ وَعَدُوِّهِمْ إِلهَ الحَقّ وَاجْعَلْنا مِنْهُمْ "
  📚وقال الإمام الترمذي : وهذا صحيح موقوفا
   
ከፊል ዑለሞች ሁለቱን አንድ ላይ ማድረግ አይሆንም ምክንያቱም ሁለቱም ከነብዩ የተገኙ ስለሚመስል እንዲሁም ስለሚረዝም ይላሉ።

ዋናው ነጥብ እዚህ ጋር ነው እነዚህ ዑለሞች ሁለቱን አንድ ላይ ማድረግ አይቻልም ያሉበት ምክንያት አንዱ ይረዝማል የሚል ነው። ምናልባት ሁለቱም ዱዓኦች አንድ ላይ በቁኑት ቢቀሩ 5 ደቂቃ ቢወስዱ ነው ከመሆኑም ጋር ይረዝማል ነው ያሉት። ታዲያ እነዚህ ዑለሞች አሁን ያሉት ኢማሞች የሚሰሩትን ቢያዩ ምን ይሉ ነበር?!!!!!

አብዛኞቹ ከሶላቱ ይልቅ ለቁኑቱ ሲጨነቁ ፣ ሲጠበቡ ፣ ድምፅ ሲቀያይሩ ፣ በግድ ለማልቀስና ለማስለቀስ ሲሞክሩ ነው የሚታየው። ብዙዎች ሰጋጆች  ወገባቸው እስኪንቀጠቀጥና መቆም እስኪያቅታቸው ያረዝማሉ። የሚገርመው ይህን ተግባር የሶላቱ ማማር መለኪያ ማድረጋቸው ነው።‼

➽በዚህ መልኩ ማስረዘም በፍፁም የማይቻልና ሰጋጆችን የሚያሰለች ከኹሹዕ የሚያወጣ ተግባር ነው። ከተጠቀሱት ዱዓኦች ውጪ በተለያየ አይነት ዱዓእ ማድረግን አስመልክቶ ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያ ዚክርና ዱዓእ ዒባዳዎች ናቸው ዒባዳ ደግሞ ተውቂፍይ ነው በመሆኑም ለማንም ከሻሪዑ ከተገኙ ዱዓእና አዝካር ውጪ ለሰዎች ዱዓእና አዝካር አድርጎ መያዝ አይፈቀድለትም። በተለይ ደግሞ በዚህ መልኩ የሚዘወትር ከሆነ ይላል።

📝ለማጠቃለል በቁኑት ዱዓእ ላይ የሚወደደው
–  በተገኙት ዱዓኦች ማድረጉ
ከነብዩ የተገኘውና ከዑመር የተገኘውን አንድላይ አለመቀላቀል ሁለቱም ከነብዩ የተገኙ እንዳይመስል
በተለያየ ጊዜ በሁለቱም አይነት ዱዓኦች ማድረግ
– በተቻለ መጠን የሰጋጆችን ሁኔታ ማየትና አለማስረዘም
ዋጂብ እንዳይመስል አልፎ አልፎ መተው ምክንያቱም ሰዎች ዋጂብ ይመስላቸውና ከተተወ ሶላቱ ትክክል አይደለም ወይም አጅሩ ይቀንሳል ሊሉ የተወዉን ሰው ሊወቅሱትና እንዳበላሸ ሊያዩት ይችላሉና!

➡️  ከነብዩና ከዑመር ከተገኙት ውጪ ቁርኣንና ሐዲስ ላይ በመጡ ዱዓኦች ሳይረዝም ማድረግ እንደሚቻል የብዙ ዑለሞች እይታ ነው።

🔹 ሌላው ተሀጁድ መስገድ የሚፈልግ ሰው  ኢማሙ ዊትር ሰግዶ ሲያሰላምት ተነስቶ ሁለት አድርጎ ጨርሶ ዊትሩን ተሀጁድ ላይ መስገድ ይኖርበታል በአንድ ለሊት ሁለት ዊትር ስለሌለ።

አላህ አውቀው ከሚሰሩት ያድርገን።

➘➘➘➘➘
https://t.me/bahruteka


📜 ማርች 8 የማጭበርበሪያ እና የትዝብት ቀን!

     በጎርጎሮሳዊያኑ አቆጣጠር ማርች 8 (እንደሚሉት ከሆነ) በየአመቱ እንደ አለም አቀፍ የሴቶች ቀን ተብሎ የሚከበርበት ቀን ነው። በዚህ ቀን በርካታ መድረኮች እና ማህበራዊ ሚዲያዎች ስለ ሴቶች ክብር፣ መብት እና እኩልነት የመሳሰሉትን ያወራሉ። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ኢስላምን እና ከሴቶች ጋር ያለው የተባረኩ ህግጋቶችን ይተቻሉ። ይህንን የኢስላም ህግን የሚጠብቁ ሀገሮችን፣ ተቋሞችን እና ቤተሰቦችን በጭቆና እና በመብት መንፈግ ይተቻሉ።

ኢስላም ማለት በየትኛውም ቦታ፣ ዘመን እና ሁኔታ ለሰው ልጆች የሚመጥ እና ዘመን የማይሽራው ሀይማኖት ነው። በዱንያም ይሁን በአኼራ ለሰው ልጆች መንፈሳዊም ይሁን ገሀድዊ ደስታ እና ስኬት መሰረት ነው። ከኢስላም ውጪ የሰዎች ጥቅም የሚያስጠብቅ ጉዳትን ደግሞ የሚያስወግድ እና የሚከላከል ሀይማኖት በጭራሽ የለም። ፈጣሪም ዘንድ ተቀባይነት ያለው ከአደም ጀምሮ ከሰማይ የተዘረጋ ብቸኛ ሀይማኖት ኢስላም ነው። አይሁዳዊነት፣ ክርስትና እና ሌሎችም ሀይማኖቶች በሰውልጆች ጠባብ አእምሮ መሰረት የተፈበረኩ ድርሰቶች ናቸው።

ኢስላም ለሴቶች (በተለይም ለእናት) ለየት ያለ እይታ አለው። ለሴቶች ወደር የሌለው እንክብካቤ አለው። ለመጀመርያ ግዜ የድንቁርናውን ዘመን የጭቆና ቅንበርን ከሴት ልጅ ጫንቃ ላይ ያነሳው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለው ትኩረት ትልቅ ለመሆኑ በቁርአን ውስጥ በነሱ ስም «የሴቶች ምእራፍ» የሚባል ምእራፍ መኖሩ ማሳያ ነው። በየትኛውም ሀይማኖት ውስጥ ባልታየ መልክ በመርየም ስምም ሱራ አለ። ለሴት ልጅ የሚገባትን እንክብካቤ እና ክብር እንዲሰጣት ያደረገው ኢስላም ነው። ኢስላም ለሴቶች ያለውን ክብር እና ቦታ ለማወቅ የፈለገ ሰው የታላቁን ፈጣሪ መፅሀፍ ቁርአንን እንዲሁም የነብያዊ ጥቅሶችን በንፁህ አእምሮ ያጥና። በተጨማሪም በርካታ የሆኑ የሊቃውንቱን ድርሰቶችን ያጥና።

ምእራባውያን የኢስላምን ትልቅነትንና መለኮታዊነት ባወቁ ግዜ የሚችሉ መስሏቸው ኢስላምን ለማጣጠል እና ለማንቋሸሽ ብለው ካጠመዷቸው በርካታ ወጥመዶች መካከል አንዱ ማርች 8 ነው። ብዙ ሰዎች (በተለይም ሴቶች) በዚህ ቀን ማላዘብ የምር ለሴቶች ክብር እና መብት የተጨነቁ ይመስላቸዋል። አመቱን ሙሉ የሚደረገው የመብት መግፈፍ እና ጭቆናን በአንድ ቀን መዝሙር ይረሱታል። በተቃራኒ ደግሞ ያለውን ተጨባጭ እና እውነታ የሚያውቁ በርካታ ሰዎች አመቱን ወደሃላ በማሰብ ይህንን ቀን እና የዚህ ቀን ወሬን ታዝበው ያልፋሉ።

ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጭቆናዎች በጣም በርካታ ናቸው። በየቦታው የሚታየው የብዙሀኑን ሴት መብት የገፈፈው የኒቃብ መልበስ እገዳ እና ከሱ ጋር ተያያዥ የሆኑ በርካታ እገዳዎች (ለምሳሌ የት/ት እገዳ) ማሳያ ናቸው። መልበስ ተፈጥሯዊ እና ሰብአዊ መብታቸው አልነበረም ለምን ይታገዳሉ?! በብስለት ላጤነ ሰው ሴት ልጅን እንድትራቆት፣ ከተቃራኒ ፆታ ጋር ልቅ የሆነ መስተጋብር እንዲኖራት እና ከወንደንዶች ጋር የተለያዩ መድረኮችን እንድትጋራ መፍቀድ ከዚህ በላይ ክብሯን ዝቅ ማድረግ የለም። ከዚህም ባሻገር በየሆስፒታሉ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ተገቢውን ክትትል ባለማግኘት እና የሴት አዋላጆች እጥረት ምክንያት በርካታ እናቶች ህይወታቸው ያልፋል። በየመስሪያ ቤት ስራ ፍለጋ ከቀረበች ወይ ውድድር ውስጥ ከገባች በተለይ ሙስሊም ከሆነች ካልተገላለጠች፣ ሴትነቷን ካልሸጠች ወይም ሌላ መጥፎ ነገር ውስጥ ካልገባች ስኬታማ አትሆንም። አረ በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጭቆና ብዙ ነው። ይሄ ሁሉ በሚታይበት የሴቶች መብት እያሉ ማላዘብ ማጭበርበሪያ እንጂ ምንም አይደለም።

በዚህ ዘመን የሴት ልጅን መብት እናስከብራለን በሚል ሽፋን እንድትገላለት፣ እንድትራቆት፣ ከወንድ ጋር እንድትቀላቀል፣ ሚዲያ ላይ እንድትወጣ፣ በቴሌ-ቪዥን መስኮት እንድትታይ ወዘተ የሚያደርጉ ሰዎች እያረከሷት ነው። ከዚህም አልፎ በተለያዩ ምርቶች ላይ ፎቶዋን በመለጣጠፍ ማሻሻጪያ ብልጭልጭ አድርገዋታል። ይሄ ሁሉ ባለበት ማርች 8 የበለጠ ከዚህ በላይ እንድትረክስ የሚደረግበት እንጂ ሌላ አይደለም። ሴትን ልጅ ወደ ክብሯ ወደ ልእልትነቷ መመለስ የሚቻለው ወደ ኢስላም በመዞር ቢቻ ነው። የሷን መብት እና ልቅናን ማስጠበቅ የሚቻለው ወደ መሸፋፈኗ፣ ከጥፋት ስፍራ በመራቋ፣ ሴትነቷን በመጠበቋ እንዳጠቃላይ የኢስላምን መርህ በጠበቀ መልኩ ሲሆን ቢቻ ነው።


ሙሀመድ አል-ወልቂጢይ

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


Forward from: Muhammed Mekonn
በዚህ አመት በየካቲት ወር ብቻ የተደረጉ ሙሐደራወች!
▱▰▱📌

ቀደም ሲል በጥር ወር ብቻ የተደረጉትን ማጠናቀራችን ይታወሳል።
👉 ይ  ሄ   ው   ➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9812

⚙ በዚህ ጥንቅር ደግሞ በተገባደደው የካቲት ወር በተለያዩ ቦታዎች በተለያዩ መሻይኾች  ኡስታዞች እና ዱዓቶች የተሰጡ ትምህርቶችን እናቀርብላችኋለን።

▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰

➊ኛ በስልጤ ዞን ምዕራብ አዘርነት ወረዳ ሌራ ከተማ በኢማሙ አህመድ መስጂድ ላይ የተሰጡ ትምህርቶች

«የረመዳን ወር ትሩፋቶች»
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9835

➧ “እንግዳን በክብር ማስተናገድ
       በኢስላም አስተምሮ
!!!”
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9825

➧ ፅናት እና ከሙብተዲዕ መለየት
🎙በሸይኽ መህቡብ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9933

“ኢኽላስ ስራን ለአላህ ማጥራት”
🎙 በሸይኽ ሙባረክ ሁሰይን حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9934

🏝 بَيَانٌ عَنِ التَّوْحِيْدِ وَالْأَسْمَاءِ وَالصِّفَاتِ
🏝 ስለ አላህ አንድነት ስለ ስሞቹ እና ባህሪያቶቹ ዙሪያ ማብራሪያ

🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9936

    ➧ ተውሂድ (የአላህ አንድነት)
🎙
በኡስታዝ ባህሩ ተካ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9941

    ➧ ወደ አላህ ጥሪ ማድረግ
🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9943

  ➧ አል-ኢስቲቃማህ ❴ፅናት❵
🎙
በሸይኽ ኑሪ «حَفِظَهُ الله»
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9949

    ➧ በሌራ የተሰጠው ፈታዋ
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
✅      ➘➘➘➘➘➘

https://t.me/AbuImranAselefy/9952

➋ኛ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በኬሌ ከተማ አስተዳደር በከላቡልቱ ኑር መስጅድ ላይ የተሰጡ ትምህርቶች

ሀ, እስልምና ትክክለኛው ጎዳና
🚥——————————🚦
🏝                 ➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9971

ለ, የዒልም እና ዓሊሞች ልቅና
🚥——————————🚦 
🏝                 ➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9980

ሐ, ተውሒድ የአምልኮ መሰረት ነው።
🚥——————————🚦
🏝                 ➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9983

መ, እስልምና ቀጥኛ መንገድ
🚥—————————🚦
🏝                 ➘➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/10031

▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰

❸ኛ በቀቤና ልዩ ወረዳ በጀብዱ ቀበሌ እና በእጉማ መንደር ከቀን 13/06/2017 ጀምሮ የተሰጡ ትምህርቶች

✅ ፆም ከኢስላም መሰረቶች ነው።
🚥——————————-👌
🎙በሸይኽ ሙባረክ ሁሰይን حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9988

✅ ተውሒድ እና ሽርክ ጉዳይ
🚥—————————-👌
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9989

✅ እስልምናን በአግባቡ መገንዘብ
🚥——————————-👌
🎙 በኡስታዝ ባህሩ ተካ حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9990

✅ የተፈጠርንበት ዋና አላማ!
🚥——————————-👌
🎙በሸይኽ  ሙባረክ حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9993

✅ የአላህ ስራ እና ተውሒድ
🚥—————————-👌
🎙 በኡስታዝ ዐብዱልቃድር حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/9994

✅ ዳዕዋ በጉራጊኛ ቋንቋ
🚥—————————-👌
🎙በኡስታዝ ጀማል حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/10010

✅ ዕውቀት የስኬት መሰረት
🚥—————————-👌
🎙በኡስታዝ አብዱልቃድር حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/10011

✅ አላህን እና ነብዩን መውደድ
🚥—————————-👌
🎙በኡስታዝ አብዱልጀሊል حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/10012

✅በቀቤና የተሰጠው ፈታዋ
🚥—————————-👌
🎙በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حَفِظَهُ الله
🏝               ➘➘➘
https://t.me/AbuImranAselefy/10014

▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰

❹ኛ በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው አል-ኢስላህ መድረሳህ ከየካቲት 16/2017 E.C የተሰጡ ምክሮች

◉እስልምና የስኬቶች ሁሉ ቁልፍ
⛱^^^^^^^^^^^^^^^^^^
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حفظه الله
📲🚦🚥🏖    ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/10028

➧ ወደ አላህ ዲን መጣራት
      🏝🏝🏝🏝🏝
🎙በሸይኽ ሀሰን ገላው حفظه الله
📲🚦🚥🏖    ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9985

◉ፆም 4ኛው የኢስላም ማዕዘን
⛱^^^^^^^^^^^^^^^^^^
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حفظه الله
📲🚦🚥🏖    ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/10029

🔎 የአቂዳችን ምንጮች
⛱^^^^^^^^^^^^^^^^^^
🎙 በሸይኽ ዩሱፍ አህመድ حفظه الله
📲🚦🚥🏖    ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/10009

🔎 የተለያዩ ጥያቄዎች መልስ
   ⛱^^^^^^^^^^^^^^^^^^
🎙 በሸይኽ ዐ/ሐሚድ حفظه الله
📲🚦🚥🏖    ➴➴➴
https://t.me/AbuImranAselefy/9976

▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰

❺ኛ በወራቤ ከተማ ፋብሪካ ሰፈር በሚገኘው አዩብ አል-አንሷሪይ መስጂድ በታላቁ ሸይኻችን ሸይኽ አብዱልሐሚድ ያሲን አል`ለተሚይ የረመዷንን አቀባበል አስመልክቶ የተደረገ ሰፊ ዳሰሳ

ሀ) ➴➴➴➴➴
ስለ ፆም ዝርዝር ዳሰሳ
♻️
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy/10034

ለ)   ➴➴➴➴➴➴
◎ ተጨማሪ የፆም ህግጋቶች
♻️
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy/10035

ሐ)  ➴➴➴➴➴
በወራቤ የተሰጠው ፈታዋ
♻️
🏝 ⇣⇣⇣🍭⇣⇣⇣📲 ⇣⇣⇣↙️
https://t.me/AbuImranAselefy/10036


ወንጀሎቻችንን የሚያሳብስ አጠርና ቀለል ያለ እጅግ ትልቅና አንገብጋቢ የሆነ ዱዓ!
√√√√√√√√👌

🌸 اللهم مغفرتك أوسع من ذنوبي، ورحمتك أرجى عندي من عملي
↪️ አል-ሏ-ሁ-ም-መ መጝፊረቱከ አውሰዑ ሚን ዙ-ኑ-ቢይ ወ-ረህመ
ቱከ አር-ጃ ዒን-ዲ-ይ ሚን ዓመሊ-ይ


ትርጉም፦ አላህ ሆይ ይቅር ባይነትህ ከእኔ ወንጀል የሰፋ (የበለጠና የበዛ) ነው፣ የአንተ (ረህመትህ) አዛኝነትህ ደግሞ እኔ ዘንድ ካለው መልካም ስራ የበዛና የበለጠ ነው።

📢 ያለንበት የተከበረው የረመዷን ወር ነው። እነዚህንና መሰል ዱዓዎች ላይ ልንጠናከር ይገባል።

🤲 ኢላሂ ወንጀሎቻቸው ከተሰረዙሩላቸው፣ መልካም ስራዎቻቸው ተቀባይነት ካገኙላቸው፣ ከጀሐነም እሳት ነፃ ከሚባሉት፣ ወደ ጀነት ከሚገቡት ባሪያዎችህ አድርገን!

📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


🔹 የካቲት 30/2017 በአ/አ ካራ ቆሬ ቢላል ኢብኑ ረባሕ መድረሳ የእስልምና እንግድነት በሚል ርእስ የተደረገ ሙሓደራ ።

↪️ ከተነሱ ነጥቦች ውስጥ :–

– እንግዳ የሆነው ሶላት ፆምና ሐጅ ሳይሆን ተውሒድ መሆኑ ።
– በነብዩ ዘመን እንግዳ የሆነው በጣኦት አምላኪያን መካከል ነበር ።
– ምክንያቱም የአላህ መልእክተኛ ላ ኢላሃ ኢልለላህ በሉ ያሉት ጣኦት አምላኪያንን ነበር ።
– ዛሬ ተውሒድ እንግዳ የሆነው ሙስሊም ነኝ በሚል ማህበረሰብ መካከል ነው ።
– ተውሒዱ ሽርክ ሽርኩ ተውሒድ ተደርጎ ተይዟል ።
– አብዛኛው ሙስሊም ቀብር አምላኪ ነው ።
– ሰዎች ወደተለያየ የመሻኢኾች መውሊድ ብሎ የሚሄደው ጥሬ እቃ ወይም ሸቀጥ ሊያመጣ ሳይሆን ቀብር ለማምለክ ነው ።
– በረመዳን ከምንጊዜውም በላይ ሽርክ ይሰራል ።
– ቁርኣን እንግዳ ሆኖ ከእስልምና የሚያወጣ ሽርክ የያዘው መንዙማ ነግሷል ። የሚሉና ሌሎችም ነጥቦች ተዳሰዋል ።

http://t.me/bahruteka


አላህን ይቅርታ መጠየቅ
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯🏝

🎙 በአቡ ዒምራን حَفِظَهُ الله

🕌 በወራቤ ከተማ በዘሞ ባቲ ሰፈር በዳሩል ሂጅራ መስጂድ የተደረገ ሙሐደራ

🗓 ዛሬ የካቲት 30 / 2017 ወይም
      ረመዷን 9/1446 ሒጅራ

🏝🚥🏖  ➴➴➴➴➴➴👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10110


ረመዷን የመልካም ስራ ወር
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯🏝

🎙 በኡስታዝ አብዱራዛቅ حَفِظَهُ الله

🕌 በወራቤ ከተማ በዘሞ ባቲ ሰፈር በዳሩል ሂጅራ መስጂድ የተደረገ ሙሐደራ

🗓 ዛሬ የካቲት 30 / 2017 ወይም
ረመዷን 9/1446 ሒጅራ

🏝🚥🏖 ➴➴➴➴➴➴👇
https://t.me/AbuImranAselefy/10109


አላህን የመፍራት ትሩፋቶች ብዙ ናቸው።

1, ከተለያዩ ጭንቆች መውጫ መፍትሔ (ቀዳዳ) ማግኘት።
2, ከማናስበው በኩል የአላህ ሲሳይ መምጣት።
3, ጎዳዮችን አላህ ገር ያደርግልናል።
4, የአላህ እርዳታን ማግኘት።
5, እውቀት እና ጥበብን ማግኘት።
6, የወንጀል መማር እና የምንዳ መተለቅ።
7, ከአላህ አስፈሪ ከሆነው ቅጣት መዳን።
8, ለታማኝነት መገጠም።
9, የአላህን ውዴታ ማግኘት።
10, ስኬትን እና ሀሴትን ማግኘት።
11, ለአላህ ፈሪዎች የተዘጋጀውን ጀነት ማግኘት።
12, ምፅዋታችን ተቀባይነት ያገኛል።
13, ከአደጋ መጠበቅ።
14, የእለተ ትንሳኤ የበላይነትና ልቅና ማግኘት።
15, ስጋት እና ፍራቻ መወገዱ።

ወዘተ… በጣም ብዙ ነው። ስለዚህ አላህን እንፍራ።

https://t.me/abuzekeryamuhamed


👉 ረመዳን ሁለተኛው አስር

የተከበራችሁ ምእመናን የአላህ ባሮች እንሆ ረመዳን የመጀመሪያው 10 አልቆ ሁለተኛው ሊገባ ነው ። እስኪ ሁላችንም ራሳችንን እንጠይቅ ።
ከቁርኣን ጋር ምን ያክል ጊዜ አሳለፍን ?
ከዚክር ጋር
ከዱዓእ ጋር
ከሶላት ጋር
ከሶደቃ ጋር
ሁኔታችን ምን ያክል ተቀይሯል
ንግግራችን
ቀልዳችን
ትረባችን
ማሽማጠጣችን
መሳደባችን
ባጠቃላይ ከረመዳን በፊት ከነበረን ባህሪ ምን ያክል ተቀይረናል ? በጊዜያችን ምን ያክል ተጠቅመናል ? በምን እያጠፋነው ነው ?
ጊዚ ከሰከንድ አመልካች ወደ ደቂቃ አመልካች በተሸጋገረ ቁጥር እኛ ደግሞ ከተወሰነልን ጊዜ እየተሸረፈ ወደ ቀብር አየተጠጋን ነው ።
ይህ አላህ ለድክመታችን ማካካሻ የሰጠን ገፀ በረከት ( የረመዳን ወር ) ካልተጠቀምንበት ምንም ሳይዛነፍ ጉዞዉን መጨረሱ አይቀርም ። ቀኑ ለለሊት ለሊቱ ለቀን እየተቀባበሉ ሳምንት እያለ ወር ያልቃል ። የተወሰነው የገፀ በረከት ጊዜ ከዚያም የእድሜ መንገድ ጉዞዉን ይቀጥላል በዱንያ ላይ የተወሰነለት ገደብ እስኪያበቃ
የሚጠብቀን ከሁለት አንድ ነው ። ዘላለማዊ ፀፀት ወይም ዘላለማዊ የተድላ ህይወት
የፈለግነውን መምረጥ እንችላለን ። ግን እጅ በማውጣት ሳይሆን በስራ ነው ።

አላህ ካገራላቸው ባሮቹ ያድርገን ።

http://t.me/bahruteka


📢 አንዘናጋ! ያለፈው አልፏል የተቀሩትንም
የተቆጠሩ ውድ የረመዷን ቀናቶች ከዘመናዊ
ሌባ እንጠብቅ
‼️

√√√√√√√√√👌

↪️ ሶሻል ሚዲያ (𝕤𝕠𝕔𝕚𝕒𝕝 𝕞𝕖𝕕𝕚𝕒)  ዛሬ ላይ የብዙዎቻችን ዋነኛ እና ግንባር ቀደም ችግር ሆኗል፡፡ በብዙ ቦታዎች በቤትም፣ በመስሪያ ቤትም፣ በመስጂድ፣ ስንበላ እና ስንጠጣ ሳይቀር ትልቅ ትኩረት ሰጥተነው ጊዜያችንን እየጨረስንበት ገንዘባችንን እያፈሰስንበት ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከተለያዩ ዒባዳዎች ቁርኣን ከመቅራት፣ ደርስ ከመከታተል፣ ከዚክር፣ ከዱዓ፣ መልካም ስራዎችን ከመስራት..... እንድንርቅ እና እንድንራቆት አድርጎናል። የሞቱ ሰዎች በመቃብሮቻቸው ዉስጥ ናቸው። ጥሩም ይሁን መጥፎ ከሥራዎቻቸው ጋር ተገናኝተዋል። ተመልሰውና ወደ ዱንያ መጥተው መልካም የመሥራት ዕድላቸው ዜሮ ነው። እዚያ ሆነው በዋዛ ፈዛዛ ስላሳለፉት የምድር ላይ ጊዜያቸው ይቆጫሉ። በሚገባ ስላልተጠቀሙበት ዕድሜያቸው ይፀፀታሉ።  ምን አልባት ወደ ዱንያ ብትመለሱ ምን ታደርጋላችሁ ተብለው ቢጠየቁ «ከረመዷን አንድ ቀን አገኝተን ብንፆም» ብለው መመኘታቸው አይቀርም። እኛ ደሞ የአላህ ፍቃድ ሆኖ እነዚህን ቀናቶች አገኝተናል እና ውዶቼ… እንደ ዋዛ አልፈው ነገ ላይ እንዳንፀፀት እንጠንቀቅ! ጊዜያችንን በአግባቡ እና በፕሮግራም እንጠቀም።

ሶሻል ሚዲያ ላይ ደርቀን አፍጠን እንደምንዉለው ሁሉ ቁርኣን ላይ ብናፈጥ ኑሮ በተወሰኑ ቀናት ዉስጥ ቁርኣንን እናኸትም ነበር።

የሞባይላችን ባትሪ ሲጎድል ተጨንቀን፣ ተስገብግበን እንደምንሞላው ሁሉ የኢማናችንን ቻርጅ ለመሙላት ጉጉት ቢኖረን የኢማን ድሃ ሆነን አንቀርም ነበር።

✅ በየጊዜው ለኢንተርኔት ዳታ ከምናወጣው ገንዘብ ለችግረኞች ጥቂት ብንለግስ ወይም ለመልካም ሥራ ብናዉል ምንዳችን ይበዛ ነበር።


ስልክ ይዞን እየጠፋ ነውና መንቃት አለብን። ረመዷን ደግሞ የትርፋማ ንግድ ወር ነው። ስለዚህ እንዳያዘናጋን በዒባዳዎች እንጠናከር አደራ! አደራ! አደራ!

📱👇👇👇👇👇
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


አቡ ሑራይራ (ረዲየሏሁ አንሁ)እንዲህ ብሎዋል...

ሐሜት ጾምን ይቀደዋል። ኢስቲግፋር ይሰፋዋል። (የቂያማ ቀን) የተሰፋ ጾም ይዞ ለመምጣት የቻለ ያድርግ (የተሰፋ ጾም ይዞ ይምጣ)። ”

📚 ለጣዒፍ | ኢብኑ ረጀብ


t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk
t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk


ጫት የዱዓ መሳሪያ ሳይሆን የውድመት መሳሪያ ነው!

⚠️ ጫት ውድ የሆነውን ግዜ ይገድላል።
⚠️ ጫት ያጀዝባል።
⚠️ ጫት ያጃጅላል።
⚠️ ጫት አላማ ቢስ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ነዝናዛ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ኪስን ያከሳል።
⚠️ ጫት ወንድነትን ያከስማል ብልት ያኮላሻል።
⚠️ ጫት ቤተሰብን ይበትናል።
⚠️ ጫት ያልከሰክሳል።
⚠️ ጫት ሌባ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ወስላታ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ልብን ያደርቃል።
⚠️ ጫት የሰው እጅ ያሳያል/ለማኝ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ያደሀያል።
⚠️ ጫት ያሳብዳል።
⚠️ ጫት እንቅልፍ ይከላክላል።
⚠️ ጫት ለቢድዓ እና ሽርክ ይዳርጋል።
⚠️ ጫት ፈሪ ያደርጋል።
⚠️ ጫት ጥርስን ያዳሽቃል።
⚠️ ጫት አፍን ያገማል።
⚠️ ጫት ቡቱቶ ያስለብሳል።
⚠️ ጫት ጨጓራ በሽታ ያመጣል።
⚠️ ጫት ውበት ያበላሻል።
⚠️ ጫት ያደነዝዛል።
⚠️ በዲንህ ደዩስ እንዲትሆን ያደርግሃል።

📌 በጥቅሉ ጫት ትውልድ ገዳይ አደገኛ ቅጠል ነው። ወጣቶቻችን ሆይ ንቁ ኤሄን ቅጠል እያኘካችሁ ውድ የሆነውን ግዜያችሁን አታውድሙ። ለጉዳቶቹ ሰለባ አትሁኑ።

👌 የሆነ ቦታ ዞር ዞር ስል ያገኘሁት ነው የተወሰነ ጨማምሬበት አቀረብኩላችሁ። እስቲ ለጫት ቃሚዎች ከእውቀታቸው ላይ ይጨምሩበት ላኩላቸው። እንጂማ ጉዳቱን የማያቁ ሁነው አይደለም

t.me/abuzekeryamuhamed
t.me/abuzekeryamuhamed


የቁርአንን ገፅ ለመግለጥ ጣትን ምራቅ ማስነካት
√√√√√√√√√√ 👌

✅ የሻፊዒያ ዑለማዎች ቁርአንን ምራቅ በነካው ጣት ማስነካት ሐራም ነው ይላሉ።
📖 ቱህፈቱል ሙህታጅ ( 2/150 )

➡️ የማሊኪያ ዑለማዎች ደግሞ ጣቱን ምራቅ በማስነካቱ የፈለገው ገፁን ለመገልበጥ ከሆነ ሐራም ከመሆኑም ጋር ወደ ኩፍር ደረጃ ማድረሱ አስፈላጊ አይደለም ምክንያቱም ቁርአን ማዋረድ ስላላሰበ ይላሉ።
📖 ሸርሁል ከቢር ( 4/301 )

👉 ኢብኑል ዐረቢ ረሂመሁላሁ እንዲህ ይላል፦ «ሰዎች ቁርአን ለመቅራት ሲፈልጉ ጣታቸውን በምራቅ ይለዉሱና እንዲቀላቸው የቁርአንን ገፆች ያገላብጣሉ ይህ በጣም ቆሻሻና ቁርአንን ማዋረድ ነው ለሙስሊሞች ይህን ለዲናቸው ሲሉ ሊተዉት ይገባል»።
📖 ሸርህ ሱነን አትቲርሚዚ (10/240 - 241)

  
👉 ኢብኑል ሃጅም እንዲህ ይላል፦
«ህፃናትን ለሚንከባከብ ግዴታ የሚሆንበት ህፃናቶችን ሰዎች ከለመዱት ጣትን በምራቅ እያስነኩ የቁርአንን ገፆች ከመንካት ሊከለክል ነው። ምክንያቱም ቁርአን መከበር አለበት ይህ ደሞ ቆሻሻና ማዋረድ ነው»።
📖 አል’መድኸል  ( 2/318 )
  
🔎 በአሁኑ ጊዜ በረመዳን ምክንያት ሰዎች ፊታቸውን ወደ ቁርኣን ማዞራቸው በጣም የሚያስደስት ሲሆን በዛው ልክ በሙሉ ማለት በሚቻል መልኩ የቁርኣንን ገፅ ለመክፈት ጣታቸውን ምራቅ ማስነካታቸው ሲታይ ይሰቀጥጣል። ዱዓቶችና ኡስታዞች ለአማኞች ግንዛቤ ሊያስጨብጡና ከዚህ ተግባር እንዲከለከሉ ሊያደርጉ ይገባል።

http://t.me/bahruteka


💡ረመዷናዊ ትምህርቶች📢

➡️ ከታች ሊንኩን በመጫን በወንድም ጅብሪል ሱልጧን አላህ ይጠብቀውና በረመዳን ዙሪያ የተፃፉ ጠቃሚና አጫጭር ትምህርቶች ናቸው ተከታተሉ!

🔸ተኝቶ ቁርዓን መቅራት እና ሱጁድ...
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3280

🔸በረመዳን ቀን ሚስትን መሳም እና ማቀፍ!
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3282

🔸ስንት ኪሎ ሜትር መንገድ ስንጓዝ ፆማችንን እናጥፋ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3283

🔸ኢማሙ ሃያ ሶስት ረከዓ እያሰገደ እኔ አስራ አንዱን ሰግጄ ቢወጠስ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3287

🔸ቁርዓን ሃፊዝ አይደለሁም ግን ተራዊህ አሰጋጅ ኢማም ነኝ እና ቁርዓን ይዤ በእሱ እያየሁ እያነበብኩ ማሰገድ እችላለሁ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3289

🔸ተራዊህን ከኢማማችን ጋር ሰግጄ ዊትርን ደሞ ቆይቼ ለመስገድ ፈለኩኝ...
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3291

🔸ፆመኛ ሆኜ ሳለሁ ጥም ሲያስቸግረኝ ጥሙን ሊቀንስልኝ ብዬ ሻወር ቢወስድስ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3292

🔸መሸት ሲል የሆነ ድምፅ ሰምቼ አዛን ያለ መስሎኝ ቢበላና ከዛም ያ ድምፅ አዛን ባይሆንስ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3293

🔸ተራዊህን ለብቻዬ በቤቴ ውስጥ ቢሰግድስ?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3295

🔸ቁርዓን ድምፄን ሳላወጣ በእይታ ብቻ እያስተነተንኩ ቢቀራ አጅር አገኝበት ይሁን?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3299

🔸አንድ ሰው ሌላን ሰው ቢያማ ወይም ነገር ቢያዋስድ ፆሙ ይጠፋ ይሆን?
📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Abumuseab/3300

🌿🛎ሼር በማድረግ ተደራሽነቱን እናስፋው! ባረከሏሁ ፊኩም
======>
🏴🏴🏴🏴🏴

📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy
https://t.me/AbuYehyaAselefy


💡«ስለ ረመዷን ጠቅለል 💡
ያሉ ምክሮች!»
   

🎙الأسـتاذ أبو أنس أبو جعفر محمد أمين السلفي «حفظه الله»
🎙
በውዱ ኡስታዛችን በኡስታዝ አቡ አነስ ❨አቡ ጀዕፈር❩ ሙሐመድ አሚ አላህ ይጠብቀውና!

=> በውስጡ፦
ሽቶ መጠቀም
ምግብን መቅመስ
ረስቶ የበላ ሰው ሑክሙ
➩ ኒያን በተመለከተ
ምራቅን እና አክታን መዋጥ በተመለከተ
የማስታወክ  ፍርዱ
መርፌ መወጋት ፆምን ያበላሻልን?💉
➩መፋቂያ መጠቀም🪥
oxygen (ኦክስጅን) የመጠቀም ሑክሙ
ሐይድ እና ኒፋሳ
በሰፈር ላይ ያለን ሰው የተመለከቱ ፍርዶች
በረመዷን በቀኑ ክፍለ ጊዜ ጎንኙነት መፈፀም
ሲጋራ እና መሰል ጭሶችን መጠጣትን የተመለከቱ ሑክሞች🚬
በረመዷን ባለቤቱን መደባበስ፣ መሳምን የተመለከቱ ፍርዶች
በረመዷን መጉመጥመጥ፣ ገላን መታጠብ ይቻላልን?🚿
ዋግምት እና ሑክሙ.....

📝ወቅታዊ እና አንገብጋቢ የሆነ ትምህርት ስለሆነ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተቋዳሽ ይሁኑ!

📱⇘⇘⇘⇘⇘
https://t.me/Durusu_Abu_Anes
https://t.me/Durusu_Abu_Anes
https://t.me/Durusu_Abu_Anes

20 last posts shown.