አላህ(ሱ ወ) የሱረቱ ዩሱፍ መጀመሪያ ላይ ትረካውን ሲጀምር :–
نَحْنُ نَقُصُّ عَلَيْكَ أَحْسَنَ الْقَصَصِ
መልካም ዜናዎችን በአንተ ላይ እንተርክልሃለን፡፡ (ዩሱፍ 3) ይለናል ...እስቲ ለትንሽ ደቂቃዎች በዩሱፍ ቦታ እራሳችንን እናስቀምጥና እናስበው
•አባትህ በጣም እንዲወድህ ትፈልጋለህ ?መልስህ አዎ ከሆነ የዩሱፍ በአባቱ መወደድ ግን ጉድጓድ ውስጥ የመጣሉ ምክኒያት ሆኖታል...
•ጉድጓድ ውስጥ መጣልን ትፈልጋለህ ?መልስህ አይ ከሆነ የዩሱፍ ጉድጓድ ውስጥ መጣል ግን ለሌላ ታሪክ ጅማሮ ሆኖታል የንጉሱ አገልጋይ ቤት የመግቢያ ሰበብ ...
•የሚመችህ ቦታ የአባትህን ምትክ አግኝተህ በተድላና በምቾት ማደግ ትፈልጋለህ አዎ ከሆነ መልስህ የዩሱፍ መመቻቸት እና ድሎት ውስጥ መገኘት ግን የእስር ቤት የመግቢያ ሰበብ ሆኖታል
•እስር ቤት ገብተህ ለዘመናት ተረስተህ መኖርን ትፈልጋለህ ?መልስህ እርግጠኛ ነኝ አይ አልፈልግም ነው ...ታውቃለህ ግን የዩሱፍ እስር ቤት ውስጥ መጣል ለንግስናው ሰበብ እንደሆነ ...
★ይሄ ሁሉ የጌታችን አላሁ (ሱ ወ) ጉዳዮችን የማስተናበር መንገድ ነው። አላህ የአንተን ጉዳይ ለማቃናት ሁኔታዎች አይገድቡትም ....
አሊሞች ይናገራሉ "ሱረቱ ዩሱፍን አብዝቶ የሚቀራ አላህ ከልቡ ላይ ሀዘኑና ጭንቀቱን ያስወግድለታል "
لَقَدْ كَانَ فِي قَصَصِهِمْ عِبْرَةٌ لِّأُولِي الْأَلْبَابِ
በታሪካቸው ውስጥ ለአእምሮ ባለቤቶች በእርግጥ መገሰጫ ነበረ፡፡(ዩሱፍ 111)
አብሽር የኔ መልካም!
የተባረከ ጁምዓ ይሁንልን!
Adnan yesofi