በማቴዎስ 4:1—10 በተቀመጠው ዘገባ መሰረት በኢየሱስና በሴይጣን መካከል የተደረገውን የቃላት ምልልስ መፈፀሙን ምን አይነት ምስክር አለ? ማቴዎስ በቦታው አልነበረም? የነበሩት ሴይጣንና ኢየሱስ ብቻ ናቸው። ኢየሱስን እንዳንጠይቀው አርጓል።ምናልባት ምድርን እየገዛ ያለው ሴይጣን ይረዳን ይሆን?
የማቴዎስ ወንጌል 4
1 ከዚያ ወዲያ ኢየሱስ ከዲያብሎስ ይፈተን ዘንድ መንፈስ ወደ ምድረ በዳ ወሰደው፥
2 አርባ ቀንና አርባ ሌሊትም ከጦመ በኋላ ተራበ።
3 ፈታኝም ቀርቦ፦ የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ በል አለው።
4 እርሱም መልሶ፦ ሰው ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣ ቃል ሁሉ እንጂ በእንጀራ ብቻ አይኖርም ተብሎ ተጽፎአል አለው።
5 ከዚህ በኋላ ዲያብሎስ ወደ ቅድስት ከተማ ወሰደውና እርሱን በመቅደስ ጫፍ ላይ አቁሞ፦
6 መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል እግርህንም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ፥ ወደ ታች ራስህን ወርውር አለው።
7 ኢየሱስም፦ ጌታን አምላክህን አትፈታተነው ተብሎ ደግሞ ተጽፎአል አለው።
8 ደግሞ ዲያብሎስ እጅግ ረጅም ወደ ሆነ ተራራ ወሰደው፥ የዓለምንም መንግሥታት ሁሉ ክብራቸውንም አሳይቶ፦
9 ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ አለው።
10 ያን ጊዜ ኢየሱስ፦ ሂድ፥ አንተ ሰይጣን ለጌታህ ለአምላክህ ስገድ እርሱንም ብቻ አምልክ ተብሎ ተጽፎአልና አለው።