#ልቤ_ያውቀዋል
ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝን ነገር
የሰራህልኝን ስራ
መድኃኔዓለም አወጣኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ
መስቀል ተሸክመህ በደም ርሰህ
እኔን በመከራ ዳግም ወልደህ
በክብር ተሻገርኩ ክሰህልኝ
በሕይወት አቆምከኝ ወድቀህልኝ /2/
የበደሌን ጋራ አቀበቱን
የባርነት ሰነድ እዳ ክሱን
አጥፍተኸው ጌታ መዳን ሆነ
እርቃኔ በእርቃንህ ተሸፈነ /2/
በፍቅርህ መዓዛ ረክቷል ልቤ
በማይቆም መውደድህ ተከብቤ
የሕይወቴ ወደብ መስቀልህ ነው
ወጀብ እና ነፋስ የማይነቅለው /2/
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ኤልሻዳይ
እፎይ አለ ልቤ ከስቃይ
ሆኖልኛል መዳን አንተ ታመህ
ነጻ ወጣው ሸክሜን ተሸክመህ /2/
ዙፋንህን አስተወህ የእኔ ፍቅር
ከሰማይ ሀገርህ መጣህ ከምድር
ታየ ስትፈልገኝ ልጄ ብለህ
ፈራጅ እና አጽዳቂ አምላክ ሆነህ
..................................................
📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
•ሼር // SHARE•
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
ልቤ ያውቀዋል ያደረክልኝን ነገር
የሰራህልኝን ስራ
መድኃኔዓለም አወጣኝ ከመከራ
በቃል ጉልበት አይወራ
መስቀል ተሸክመህ በደም ርሰህ
እኔን በመከራ ዳግም ወልደህ
በክብር ተሻገርኩ ክሰህልኝ
በሕይወት አቆምከኝ ወድቀህልኝ /2/
አዝ=====
የበደሌን ጋራ አቀበቱን
የባርነት ሰነድ እዳ ክሱን
አጥፍተኸው ጌታ መዳን ሆነ
እርቃኔ በእርቃንህ ተሸፈነ /2/
አዝ=====
በፍቅርህ መዓዛ ረክቷል ልቤ
በማይቆም መውደድህ ተከብቤ
የሕይወቴ ወደብ መስቀልህ ነው
ወጀብ እና ነፋስ የማይነቅለው /2/
አዝ=====
የእሾህ አክሊል ደፍተህ ኤልሻዳይ
እፎይ አለ ልቤ ከስቃይ
ሆኖልኛል መዳን አንተ ታመህ
ነጻ ወጣው ሸክሜን ተሸክመህ /2/
አዝ=====
ዙፋንህን አስተወህ የእኔ ፍቅር
ከሰማይ ሀገርህ መጣህ ከምድር
ታየ ስትፈልገኝ ልጄ ብለህ
ፈራጅ እና አጽዳቂ አምላክ ሆነህ
..................................................
📥ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ልጆች📥
•ሼር // SHARE•
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
❤️ @Addis_Mezmure ❤️
❤️ @Addis_Mezmure ❤️