FastPay የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ
• ከ30 በላይ የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር ጥምረት ፈጥሯል ተብሏል
የሀገርን ችግር በሀገር ልጅ መፍታት በሚል መርህ የበለጸገው FastPay ቴክኖሎጂ፤ ከሀገር ዉጪ ለሚደረጉ ማናቸውም የገንዘብ ዝውዉሮች ፍቱን መፍትሄ እንዲሆን ታልሞ መበልጸጉ ተጠቁሟል፡፡
አዲሱን የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂ በተመለከተ የFastPay ቡድን፣ ዛሬ ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3 ሰዓት ላይ በስካይ ላይት ሆቴል ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡
FastPay እ.ኤ.አ በ2021 ዓ.ም ሃሳቡ የተጠነሰሰው በዋሺንግተን ዲሲ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፤ ከእልህ አስጨራሽ አድካሚ ጉዞ በኋላ ዉድ የሆነውን የገንዘብ ማስተላለፊያ ፈቃድ በአሜሪካና በኢትዮጵያ ማግኘት ችሏል፡፡
የዲያስፖራውን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደተዘጋጀ የተነገረለት አፕሊኬሽኑ፤ በተጨማሪም የሃገሪቱን የውጭ ምንዛሬ እጥረት ለመቀነስም ያለመ ባለ ብዙ መፍትሄ አፕሊኬሽን ነው ተብሏል፡፡
FastPay ከ30 በላይ ጠንካራ የኢትዮጵያ ባንኮች ጋር ጥምረት መፍጠሩ የተገለጸ ሲሆን፤ ከባንኮቹም መካከል የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ሥራ ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ አዋሽ ባንክ፣ ዳሽን ባንክ ይገኙበታል፡፡
ተጠቃሚዎች በፋስትፔይ ኢቲ ተጠቅመው ገንዘብ ሲልኩ፣ ምንም ዓይነት የመላኪያ ክፍያ አለመጠየቃቸውና ከዕለቱ የባንኮች ምንዛሪ ከፍ ያለውን ማቅረቡ መተግበሪያውን ልዩ ያደርገዋል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም፣ መተግበሪያው ለዕርዳታ ተቋም ወይም ለግለሰብ ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ በቀላሉና በቀጥታ ገንዘብ ማስተላለፍ የሚያስችል እንደሆነም ተጠቁሟል፡፡
⬇️