በትግራይ ክልል ወረርሽኝ በሆነ መልኩ በተከሰተ ከእንስሳት ወደ ሰዎች የሚተላለፍ በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት አለፈ
በደቡብ ምስራቅ ትግራይ በተለይም ህንጣሎ ዋጀራት በተሰኘዉ ወረዳ ከእንስሳት ወደ ሰዉ በሚተላለፍ በሽታ የአራት ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።
በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን እና የጤና ማስተዋወቅ ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሚካኤል ሃጎስ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በሽታዉ ጦርነቱ ካስከተለዉ ቀዉስ መካከል አንዱ ነዉ ብለዋል። በበሽታዉ ከተያዘ እንሰሳ ጋር በሚኖር ንክኪ እና ስጋዉን በመብላት በሚተላለፈዉ በሽታው በወረዳዉ በወረርሽኝ መልክ መከሰቱን ተናግረዋል።
በዚህ በሽታ ቁጥራቸዉ በዉል ያልታወቀ ሰዎች መጠቃታቸዉን የተናገሩት አቶ ሚካኤል ፤ እስከሞት ሊያደርስ እንደሚችልም ገልጸዋል። በዚህ በሽታ የተነሳ የአራት ሰዎች ህይወት ሲቀጠፍ በርካቶች በአዲ ጉደም ሆስፒታል እንዲሁም ከፍ ባለ አስጊ ሁኔታ ዉስጥ ያሉት ደግሞ በዓይደር ሪፈራል ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የህክምና ክትትል ላይ ናቸዉ ብለዉናል።
በሽታዉ በሁሉም የትግራይ ዞኖች ይታይ ነበር ያሉት አቶ ሚካኤል አሁን ግን በወረርሽኝ መልክ በደቡብ ምስራቅ ትግራይ አንድ ወረዳ ላይ መከሰቱን አስረድተዋል።
አንትራክስ የተሰሰነዉ በሽታ በባክቴሪያ የሚመጣ ሲሆን የተጠቃዉ ሰዉ ፤ ከእንስሳት ጋር በሚኖረዉ ንክኪ የቆዳ ላይ ህመም ፣ በበሽታዉ የተጠቃ እና ያልተመረመረ ከብትን የተመገቡ ሰዎች ደግሞ ከአንጀት ጋር የተታያዘ ከፍተኛ ህመምን እንዲሁም የእንሰሳዉ ቆዳ በፋብሪካዎች ከተቀነባበረ ደግሞ በሳንባ ላይ ከፍተኛ ህመምን የሚያስከትል እና በ 24 ሰዓታት ዉስጥ ሊገድል የሚችል ነዉ ብለዉናል።
በአሁኑ ወቅትም በትግራይ ከእንስሳቱ ጋር በሚኖር ንክኪ በቆዳ ላይ የሚከሰተዉ የበሽታ አይነት በስፋት መታየቱን ጠቅሰዉ ያልተመረመረ ስጋን የተመገቡ ሰዎችም በበሽታዉ መጠቃታቸዉን አክለዋል። በሽታዉ ከሰዉ ወደሰዉ አይተላለፍም የተባለ ሲሆን ከእንስሳት ጋር የሚኖር ንክኪን ግን መገደብ አስፈላጊ መሆኑንም ጠቅሰዋል።
ከ 20 አመታት በፊትም በሽታዉ ተከስቶ ነበር የተባለ ሲሆን በወቅቱ በቁጥጥር ስር የነበረ ቢሆንም ከጦርነቱ በኋላ በተፈጠረዉ የጤና አገልግሎት ስርዓት መጓደል የተከሰተ መሆኑን አመላክተዋል።
በበሽታዉ የተያዙ ሰዎች በቆዳ ላይ የማሳከክ እና አብጦ የመፈንዳት እንዲሁም የእንስሳት ስጋን ተመግበዉ የታመሙትን ሰዎች ደግሞ እንደማንኛዉም የሆድ ህመም የቁርጠት እና የህመም ምልክት ያለዉ ሲሆን በአንጀት ላይ ግን ቁስለትን የሚያስከትል መሆኑንም ተናግረዋል።
በሽታው በቶሎ የህክምና ክትትል ከተደረገለት የሚድን እንደሆነም በትግራይ ክልል ጤና ቢሮ የጤና ኤክስቴንሽን እና የጤና ማስተዋወቅ ኤክስቴንሽን ፕሮግራም አስተባባሪ የሆኑት አቶ ሚካኤል ሃጎስ ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።