የቦሊቪያ ፖሊስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መሪን በቁጥጥር ስር አዋለ
በዋና ከተማዋ ላ ፓዝ የሚገኘው ፕሬዚዳንታዊ ቤተ መንግስት በወታደሮች ከተወረረ ከሰዓታት በኋላ የቦሊቪያ ፖሊስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን መሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ይፋ አድርጓል።
የታጠቁ ወታደሮች ቁልፍ የመንግስት ህንፃዎች በሚገኙበት ሙሪሎ አደባባይ ላይ ቆመው ታይተዋል። የአማፂው ወታደራዊ መሪ ጄኔራል ሁዋን ሆሴ ዙኒጋ “ዲሞክራሲን እንደገና ማዋቀር” እንደሚፈልጉ እና ምንም እንኳን ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴን ቢያከብሩ፣ የመንግስት ለውጥ እንደሚመጣ የተናገሩ ሲሆን አሁን በእስር ላይ ይገኛሉ።
ፕሬዝዳንት አርሴ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን አውግዘዋል፣ ህዝቡም "እንዲደራጅ ጥሪ አቅርበዋል። ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት ውስጥ ለሀገሪቱ ህዝብ በቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልእክት "የቦሊቪያውያንን ህይወት ለማጥፋት የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት እንደገና መፍቀድ አንችልም" ብለዋል።
አርሴ አዲስ ወታደራዊ አዛዦችን እየሾሙ መሆኑን አስታውቀው ጄኔራል ዙኒጋ የቦሊቪያ የቀድሞ መሪ ኢቮ ሞራሌስን በግልፅ በመተቸት ከስልጣናቸው መባረራቸውን አረጋግጧል። ሞራሌስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን በማውገዝ በጄኔራል ዙኒጋ እና “በግብረ አበሮቻቸው” ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው አሳስበዋል።
ሞራሌስ ደጋፊዎቻቸው በተለይም በሀገሪቱ የኮክ አብቃይ ንቅናቄ ውስጥ የሚገኙት ገበሬዎች የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራው እንዲያበቃ ወደ አደባባይ በመውጣት እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል። ጄኔራል ዙኒጋ በወታደሮች ከተወሰዱ በኋላ ከሙሪሎ አደባባይ በመሆን “ይህችን የትውልድ አገር ወደ ነበረችበት እንመለሳለን። "ሀገርን ያፈረሱ ወንበዴዎችና ልሂቃን ናቸው ሀገርን ተቆጣጠረው ያሉትም ብለዋል።