በፈተና ሰሞን ለልጆች የሚደረግን ድጋፍ ማጠናከር
እንደሚታወቀው ልጆች ከጨቅለነታቸው ጊዜ ጀምሮ ፈተና ላቀ ስፍራ እንዳለው በተደጋጋሚ የሚሰሙበት አጋጣሚ በርካታ ነው፡፡ ለዚህም ተገቢውን ዝግጅትና ጥረት ማድረግ እንዳለባቸው ከየአቅጣጫው ይነገራቸዋል፡፡
መረጃዎች እነደሚያሳዩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ልጆች ፈተና የሚያስከትልባቸው መጨናነቅ ከልክ በላይ ሲሆን ለከፍተኛ ጭንቀት እና ጤና መታወክ ይዳረጋሉ፡፡ይኸውም የፈተና ሰሞን ውጥረት በጊዜ ተረድቶ በወጉ መቆጣጠር አስፈላጊ መሆኑን ያስገነዝበናል፡፡ወላጆች ልጆች በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸውን ውጥረትና የመጨናነቅ ስሜት ለመቆጣጠር ባላቸው ሚና (role) በመታገዝ ልጆች የዚህ አስከፊ ችግር ሰለባ እንዳይሆኑ ጭምር መርዳት እና ማገዝ ይቻላሉ፤ ይጠበቅባቸዋልም፡፡
ወላጆች ከማንም በላይ ልጆችን በተሻለ ቅርበት የማግኘት ዕድሉ ስላላቸው በፈተና ሰሞን በልጆች ላይ የሚስተዋልን ውጥረትና ጭንቀት ለመቆጣጠር ሚናቸው የገዘፈ ነው፡፡ወላጆች በፈተና ሰሞን ልጆች በቤት ውስጥ ሳሉ ሲያጠኑ ሊከሰት የሚችልን ውጥረትና ጭንቀት መቆጣጠር እንዳለባቸው መረዳትና በዚህ የተነሳ ለከፋ ችግር እንዳጋለጡ ተገቢውን ድጋፍ ማድረግ አለባቸው፡፡፡፡
ልጆች በፈተና ሰሞን የሚሰማቸውን ጭንቀትና የውጥረት ስሜት እንዲቆጣጠሩ ወላጆች ሊያደርጓቸው የሚገቡ ተግባራት መካከል የተወሰኑትን እንመልከት፡-
ልጆችዎ እነዲያጠኑ ይርዷቸው
ወላጆች በማስጠናት አሊያም ለጥናት የሚሆኑ አመቺ አካባቢን በማመቻቸት ልጆች ሳይረበሹ በርትተው እንዲያጠኑ ሊረዷቸው ይገባል፡፡
በፈተና ሰሞን ልጆችዎን ካሉባቸው ሃላፊነቶች ይቀንሱላቸው
ሁላችንም እነደምንረዳው ፈተና በልጆች ላይ ጠንከር ያለ ጫና ይፈጥርባቸዋል፡፡በዚህን ጊዜ ልጆች በቤት ውስጥ በሚከናወኑ በርካታ ሃላፊነቶች እንዳይጠመዱ ወላጆች የተቻለንን ሁሉ ለልጆቻችን ልናደርግ ይገባል፡፡በተለይ በፈተና ሰሞን ከልጆች ጋር የሚከሰት ያለመግባባት ልጆች ላይ የከፋ የአዕምሮ ውጥረት ሊየስከትል ስለሚችል ይህን መሰል ስሜት በልጆች ላይ ከሚፈጥር ተግባርና ንግግር አስፈላጊውን ሁሉ ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
ልጆችዎ ጥናታቸውን በዕቅድ እንዲያካሂዱ ይርዷቸው
በፈተና ሰሞን ልጆችዎ የሚያደርጉት የፈተና ዝግጅት (ጥናት) በዕቅድ የተመራ ይሆን ዘንድ ይተባበሯቸው፡፡ ከዚያም በወጣው የጥናት ፕሮግራም መሰረት ልጆችዎ ለፈተና ተገቢውን ዝግጅት እያደረጉ ስለመሆናቸው መቆጣጠር እንዲሁ የእርሶ ድርሻና ኃላፊነት ነው፡፡
የልጆችዎ የፈተና ዝግጅት (ጥናት) ከመጠን ያለፈ እንዳይሆን ተገቢውን ክትትል ያድርጉ
ልጆች በፈተና ሰሞን ውጥረት ውስጥ ሲገቡና ከልክ በላይ ሲጨንቃቸው የሚያደርጉትን ጥናት ማመጣጠን ይቸግራቸዋል፡፡ጤናማ ከሆነው በላይ ጥናት ሊገቡም ይችላሉ፡፡ በዕርግጥ ልጆችዎ በተለይ በፈተና ሰሞን ማጥናት እንዳለባቸው ምንም ጥርጥር የለውም ፡፡ ሆኖም ግን ጥናቱ (የፈተናው ዝግጅት) ያስከተለው ጫና ልጆችዎ አዕምሯቸውን የሚያዝናኑባቸውን ተግባራት ሁሉ አስወግደው የፈተና ግዞተኛ አድርጎ ሊያስቀር አይገባም፡፡
ለልጆችዎ ነፋሻ እና ንጹህ አየር የሚገኝበትን ሁኔታዎች ያመቻቹ
ነፋሻና ንጹህ አየር እንዲሁም የፀሀይ ብርሃን ልጆች በፈተና ሰሞን የሚያጋጥማቸውን ውጥረትና ጭንቀት እነዲቆጣጠሩ ከፍ ያለ ሚና ይጫወታል፡፡ እነዚህ ሁለት ነገሮች ልጆች መልካም ስሜት እንዲሰማቸው ያግዛቸዋል፡፡ እናም በፈተና ሰሞን ነፋሻ አየር እና የፀሀይ ብርሃን ልጆችዎ በበቂ ሁኔታ ስለማግኘታቸው እርግጠኛ ይሁኑ፡፡
ልጆችዎ ተገቢ የሆነ የአካል ብቃት (ስፖርታዊ) እንቅስቃሴ ማድረጋቸውን ይከታተሉ፡፡
ለረጅም ጊዜ ሳይንቀሳቀሱ በአንድ ቦታ ተቀምጦ መቆየት ወደ አካልም ሆነ አዕምሮ ጤናማ ያልሆኑ ስሜቶችን ይጋብዛል፡፡ ይህም ልጅዎች የሚያደርጉት የፈተና ዝግጅትን በንቃት አንዳያከናውኑ ተጽዕኖ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸው በፈተና ሰሞን በሚያጠኑበት ወቅት ተገቢውን የአካል እንቅስቃሴ ያደርጉ ዘንድ በሚገባ ማበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡
የልጆችዎን የአመጋገብ ስርዓት ይከታተሉ
ልጆች በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸው ውጥረት እና መጨናነቅ እየከፋ ሲሄድ ፈተና ዝግጅቱ ላይ ይበልጥ ትኩረት ለማድረግ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ከምግብ ጭምር ሊዘናጉ አንዳንዴም ሆን ብለው ለረጅም ጊዜ መታቀብን ሊመርጡ ያችላሉ፡፡ይህ ደግሞ በአግባቡ እንዳያጠኑ ብቻ ሳይሆን በፈተና ሰሞን የሚገጥማቸውን ውጥረትና ጭንቀት የመቆጣጠር አቅማቸውን ሊያዳክምባቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ወላጆች ልጆቻቸው በፈተና ዝግጅት ላይ ሳሉ ተገቢውን የተመጣጠነ ምግብ በተገቢው ሰዓት የሚያገኙባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት ይኖርባቸዋል፡፡ይህ ሲሆን ልጆች ለፈተናው የሚያደርጉትን ጥናት በተሻለ አቅምና የመንፈስ ብርታት ማካሄድ ይችላሉ፤ውጤታማም ይሆናሉ፡፡
ልጆችዎን በተገቢ መልኩ ያበረታቱ
ልጆች በፈተና ውጤታማ ይሆኑ ዘንድ የሚደረግ ማበረታቻ ተገቢ ነው፡፡ ሆኖም ልጆች በጥናት ይጎብዙ ዘንድ የሚደረግ ከመጠን ያለፈ የማበረታቻ ጋጋታ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ስለሚችል ተገቢውን ጥንቃቄ ልናደርግ ይገባል፡፡
በሚያበረታቱበትም ጊዜ ቢሆን ወላጆች ልጆች ላይ የሚያደርጉት አሉታዊ (negative) ተፅእኖ ልጆች በፈተና ሰሞን የሚሰማቸውን ውጥረትና ጭንቀት ለመቆጣጠር አይጠቅማቸውም፤ቢያባብሰው እንጂ፡፡
ስለዚህ ወላጆች ልጆችን በትክክል የማበረታታት አግባብ እንዴት ያለ እንደሆነ ሊረዱት ይገባል፡፡“ልጄ አጥንቶ ጥሩ ውጤት ሊያመጣ ይገባል፡፡” ከሚል ወላጃዊ ስሜት ብቻ ተነሳስተው ልጆች ላይ በተለይ በፈተና ሰሞን ተገቢ ያልሆነ ጫና ማሳደራቸው ጉዳቱ የከፋ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ እኛም ወላጆች ይህን ከማድረግ ልንቆጠብና ሚዛናዊ ልንሆን ይገባል ስንል ለዛሬ ያዘጋጀነውን በፈተና ዝግጅት ላይ ያተኮረ ወቅታዊ መልዕክት በዚህ እንቋጫለን፡፡
ውድ ተማሪዎቻችን ፡-
በመንፈቀ- ዓመቱ ላሳያችሁት መልካም ስነ-ምግባር እንዲሁም ንቁ የትምህርት ተሳትፎ ከልብ እናመሰግናለን
መልካም የጥናት ጊዜ!! መልካም ውጤት !!!