የማስታወቂያ ሕግ⚠️🔽
በዓለም እንዲሁም በሀገራችን እየተስፋፋ የመጣው የዲጂታል ኮሚውንኬሽን ቴክኖሎጂ ሰዎች የሚሰሩትን ምርትም ሆነ አገልግሎት ለሌሎች ሰዎች ተደራሽ ለማድረግና ለማስተዋወቅ እጅግ ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል፡፡ አሁን አሁን መደበኛ በሚባሉት የሚዲያ ማስራጫዎችና ከዚህ ቀደም ከተለመዱት የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገዶች በተጨማሪ
የኢንተርኔት ድረ ገፅ (
ቲክቶክና ፌስቡክ በመሳሰሉት የማህበራዊ ሚዲያዎች) ዋነኛ የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገድ መሆን ጀምረዋል፡፡
⚠️
የማስታወቂያ ሕግን አለማወቅ እና በሂደቱም የሚፈፀሙ የሕግ ጥሰቶች ተጠያቂነት እንደሚያስከትሉ ተገንዝቦ ዘርፉ የሚፈልገውን ተገቢውን እውቀት እና የሚገዛበትን የሕግ ማዕቀፍ ጠንቅቆ ማወቁ በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ከሚመጣብን ተጠያቂነት ሊታደገን ስለሚችል ተገቢውን ትኩረት መስጠት ይገባናል፡፡
🔽🕯📈⁉️
የማስታወቂያ ስራዎች የሚመሩበት ዋነኛው የሕግ ክፍል የሚገኘው በአዋጅ ቁጥር
759/2004 በተደነገገው አግባብ ነው፡፡ በዚህ አጭር ጽሁፍ የማስታወቂያ ምንነት እና ዓላማ፣ በማስታወቂያ ስራ ለመሰማራት ሊሟሉ የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች፣ የማስታወቂያዎች ይዘትና አቀራረብ፣ ክልከላና ገደብ የተደረገባቸው የማስታወቂያ ዓይነቶች እና የሕግ ተጠያቂነት የሚሉትን ጉዳዮች በአጭሩ ለመዳሰስ ተሞክሯል፡፡
የማስታወቂያ ምንነት እና ዓላማ
ማስታወቂያ ማለት አንድን ምርት፣ አገልግሎት፣ ክስተት ወይም ሀሳብ ለህዝብ ለማስተዋወቅ እና ፍላጎት ለመፍጠር የሚደረግ ማንኛውም ጥረት ነው። ይህም በተለያዩ መንገዶች ሊከናወን ይችላል:: ለምሳሌ፡- በህትመት ሚዲያ (ጋዜጦች፣ መጽሔቶች፣ እና ብሮሸሮች)፤ በኤሌክትሮኒክ ሚዲያ (ቴሌቪዥን፣ ሬዲዮ፣ እና
ኢንተርኔት)፤ በማህበራዊ ሚዲያ (📱ፌስቡክ፣ ትዊተር📱፣ ኢንስታግራም📱፣ ቲክቶክ📱 እና ሌሎችም)፤ በውጭ ማስታወቂያዎች (ቢልቦርዶች፣ ፖስተሮች እና ሌሎችም) እና በቀጥታ ግንኙነት (ስልክ፣ ኢሜይል፣ እና ፊት ለፊት ውይይት) መንገዶች የማስታወቂያ ስራ ሊሰራ ይችላል፡፡
በአዋጅ ቁጥር
759/2004 አንቀጽ 2/1/ ድንጋጌ መሠረት ማስታወቂያ ማለት የምርት ወይም የአገልግሎት ሽያጭ እንዲስፋፋ ወይም ስም፣ አርማ፣ የንግድ ምልክት ወይም ዓላማ እንዲተዋወቅ በማስታወቂያ ማሰራጫ መንገድ አማካኝነት የሚሰራጭ የንግድ ማስታወቂያ ሲሆን የሕዝብ አገልግሎት ማስታወቂያንና የግል ማስታወቂያን ይጨምራል፡፡ በሕጉ መሰረት የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገዶች የሚባሉት ደግሞ፡- መገናኛ ብዙሃንን፣ የውጭ ማስታወቂያን፣ የቴሌኮምን፣ የፖስታ፣ የኢንተርኔት ድረ ገፅ እና የፋክስ አገልግሎቶችን፣ ሲኒማን፣ ፊልምን፣ ቪዲዮን እና መሰል የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገድን እንደሚጨምር ተደንግጎ ይገኛል፡፡
የማስታወቂያ ዓላማ ሰዎችን ስለ አንድ ነገር ማሳወቅ፣ ፍላጎት መፍጠር፣ እና ሽያጭ ማሳደግ ነው። ውጤታማ ማስታወቂያ ግልጽ፣ አጭር፣ እና ትኩረት የሚስብ መሆን አለበት።
በማስታወቂያ ስራ ለመሰማራት ሊሟሉ የሚገባቸው ቅድመ-ሁኔታዎች
በማስታወቂያ ስራ ላይ ሊሰማሩ የሚችሉ ሰዎችን በተመለከተ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎች መሟላት የሚገባቸው መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ የመጀመርያው ቅድመ-ሁኔታ ዜግነት ነው፡፡ የማስታወቂያ አዋጁ በአንቀጽ 4(1) እና (2) ስር በግልጽ እንዳስቀመጠው በማስታወቂያ ስራ ላይ ለመሰማራት ፈቃድ ጠያቂው ግለሰብ ዜግነቱ ኢትዮጵያዊ መሆን ያለበት ሲሆን ፍቃድ ጠያቂው ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል በሚሆንበት ጊዜ ደግሞ በኢትዮጵያ ሕግ መሰረት የተቋቋመና በካፒታሉ ውስጥ የውጭ አገር ዜጋ ድርሻ የሌለበት የንግድ ማኅበር መሆን ይጠበቅበታል፡፡ በሌላ ሀገር ዜግነት የተሰጣቸው በትውልድ ኢትዮጵያዊ የሆኑ የውጪ አገር ዜጋ በማስታወቂያ ስራ ላይ የመሰማራት መብት ያላቸው መሆኑን ከአዋጁ መገንዘብ ይቻላል፡፡
ይሁንና ኢትዮጵያዊ መሆን ብቻውን የማስታወቂያ ወኪል ወይም አስነጋሪ ለመሆን ያስችላል ማለት ግን አይደለም፡፡ ይልቁንም በማስታወቂያ ስራ ላይ ለመሰማራት አግባብ ካለው የመንግስት አካል ሕጋዊ ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባ በአዋጁ አንቀፅ 5 ስር ተደንግጎ ይገኛል፡፡
ማንኛውም ማስታወቂያ አሰራጭ ማስታወቂያ በማዘጋጀት ሥራ ላይ ለመሰማራት አግባብ ካለው የመንግስት አካል የማስታወቂያ ሥራ ፈቃድ ማውጣት አለበት፡፡ ይሄም ማለት አሁን አሁን በስፋት እየተለመደ የመጣው በኢንተርኔት ድረ ገፅ እና እንደ ቲክቶክና ፌስቡክ ባሉ መሰል የማስራጫ መንገዶች ላይ ማስታወቂያዎችን በክፍያ እንደሚሰሩ በመግለፅ ብዙ ተከታይ ባላቸው የማህበራዊ ድህረ ገፆቻቸው ላይ አድራሻ በማስቀመጥና የቪዲዮ፣ የፊልም ወይም የሲኒማን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ከሚመለከተው አካል ምንም ዓይነት የማስታወቂያ ስራ ፍቃድ ሳይወስዱ የማስታወቂያ ስራዎችን መስራት የሕግ ተጠያቂነትን እንደሚያስከትል የሚያስገነዝብ ነው፡፡ የማስታወቂያ ፍቃድን በተመለከተ ሌላው ልብ ሊባል የሚገባው ነጥብ ምርቱ፣ አገልግሎቱ ወይም ሌላ መልዕክት እንዲተዋወቅለት የሚፈልግ ማንኛውም ሰው የማስታወቂያ ሥራ ፈቃድ ማውጣት ሳያስፈልገው የራሱን ማስታወቂያ አዘጋጅቶ ማሰራጨት ወይም ማስታወቂያውን አዘጋጅቶ በማስታወቂያ አሰራጭ አማካኝነት እንዲሰራጭለት ማድረግ ይችላል፡፡
የማስታወቂያዎች ይዘትና አቀራረብ
በአዋጁ አንቀፅ 6 መሰረት የማስታወቂያዎች ይዘትና አቀራረብ ተከታዮቹን ነጥቦች ከግምት ያስገባ መሆን ይኖርበታል፡፡ እነሱም፡-
- ማንኛውንም ሕግ ወይም መልካም ሥነ-ምግባር የማይፃረር፣ አሳሳች ወይም ተገቢ ካልሆነ አገላለጽ ነፃ የሆነ፣ የሕብረተሰቡን ማህበራዊና ባህላዊ እሴት የሚያከብርና የሸማቹን ሕጋዊ ጥቅም የማይጎዳ፣ የሚተዋወቀውን ምርት ወይም አገልግሎት እውነተኛ ባህሪ፣ ጥቅም፣ ጥራትና ሌላ መሰል መረጃዎችን የሚገልጽ፣ የሌሎችን ሰዎች ምርት ወይም አገልግሎት የማያንቋሽሽ እና የአገርን ክብርና ጥቅም የሚጠብቅ እንዲሁም የሙያ ሥነ-ምግባርን የሚያከብር ይዘትና አቀራረብ ያለው መሆን አለበት፡፡
- በተጨማሪም ከይዘት አንፃር በመገናኛ ብዙኃን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከሌሎች ፕሮግራሞች የተለየ መሆኑ በግልፅ በሚታወቅ መልኩ እና በዜና መልክ ባልተዘጋጀ መልኩ መቅረብ ያለበት ሲሆን፡፡ በተጨማሪም የማስታወቂያ ወኪል የአንድን ሰው ምርት፣ አገልግሎት ወይም ሌላ መልእክት የሚያስተዋውቅ የንግድ ማስታወቂያ አዘጋጅቶ ባሰራጨ በሦስት ወራት ውስጥ የሌላ ሰውን ተመሳሳይ ምርት፣ አገልግሎት ወይም ሌላ መልእክት በተመሳሳይ የማስታወቂያ ተዋናይ ምስል ወይም ድምፅ አዘጋጅቶ ማሰራጨት የለበትም::
🚫 ክልከላ የተደረገባቸው ማስታወቂያዎች
የሚከተሉትን ማስታወቂያዎች በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በማንኛውም የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገድ አማካኝነት ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡-
- አግባብ ባለው የመንግስት አካል በአደንዛዥ እፅነት የተመደበን ማንኛውንም እፅ የሚመለከት ማስታወቂያ፤ ያለሐኪም ትእዛዝ የማይሰጥ ወይም በጥቅም ላይ የማይውል መድሀኒትን ወይም የሕክምና መገልገያን ተጠቃሚው በቀጥታ እንዲጠቀም የሚገፋፋ ማስታወቂያ፤ ናርኮቲክ መድሐኒትን ወይም ሳይኮቴራፒክ ንጥረ ነገርን የሚመለከት ማስታወቂያ፤ የጦር መሳሪያ ማስታወቂያ፤ የቁማር ማስታወቂያ፤የሕገ ወጥ ምርት ወይም አገልግሎት ማስታወቂያ፤ የአራጣ አበዳሪ ማስታወቂያ፤ የጥንቆላ ማስታወቂያ፤ የሲጋራ ወይም የሌሎች የትምባሆ ውጤቶች ማስታወቂያ፤ የፖለቲካ ግብ ያለው ማስታወቂያ(ነገር ግን አግባብ ባለው ሕግ መሠረት ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ የፖለቲካ ድርጅት ወይም የምርጫ እጩ ተወዳዳሪ በምርጫ ወቅት የሚያሰራጨውን የምርጫ