ውድድር ማስታወቂያ እንዲሁም የፖለቲካ ድርጅቱ የሚያሰራጨውን የአድራሻ ለውጥ፣ የስብሰባ ጥሪ እና መሰል ማስታወቂያዎችን የሚከለክል አይደለም።)እና ሌሎች በሕግ የተከለከሉ ማስታወቂያዎች፡፡
💎 ገደብ የተደረገባቸው ማስታወቂያዎች
- የአልኮል መጠኑ ከ12 በመቶ በላይ የሆነ ማንኛውንም መጠጥ የሚመለከት ማስታወቂያ ከውጭ ማስታወቂያ እና እለታዊና ሳምንታዊ ካልሆነ ጋዜጣ እና መጽሔት በስተቀር በሌሎች የማስታወቂያ ማሰራጫ መንገዶች (ማለትም በብሮድካስት አገልግሎት፣ በስልክ አገልግሎት ወይም በፖስታ አገልግሎት የማስራጫ መንገዶች) አማካኝነት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ማሰራጨት የተከለከለ ነው፡፡ ሌላው እዚህ ጋር ልብ ሊባል የሚገባው የአልኮል መጠኑ ከ12 በመቶ በላይ የሆነን መጠጥ በውጭ ማስታወቂያ ማሰራጫ መንገድ ለምሳሌ፡- በሕንጻ ወይም በማናቸውም ስትራክቸር ወይም በትራንስፖርት ተሽከርካሪ ላይ በሚፃፍ ወይም በሚለጠፍ፣ በተንጠልጣይ ነገር፣ በፖስተር፣ በስቲከር፣ በብሮሸር፣ ሊፍሌት ወይም በራሪ ወረቀት በመጠቀም ማሰራጨት ቢቻልም በሌላ በኩል ደግሞ እንደ የኤሌክትሮኒክ ስክሪን፣ በድምፅ ማጉያ፣ የድምፅ ካሴት ወይም በሌላ በምስልና በድምፅ በሚሰራጭ የውጭ ማስታወቂያ መንገዶች ማሰራጨት አይቻልም፡፡ ሌላው ማንኛውም የአልኮል መጠጥ ማስታወቂያ የአልኮል መጠጡን መውሰድ ለጤና ተስማሚ እንደሆነ፣ ግላዊ ወይም ማኅበራዊ ስኬትን እንደሚያስከትል፣ የተሻለ ሥነ ልቦናዊ ወይም አካላዊ ብቃት እንደሚያስገኝ ወይም ፈዋሽ እንደሆነ የሚገልጽ ወይም በተደጋጋሚ ወይም ከልክ በላይ እንዲጠጣ የሚገፋፋ፤ ከአልኮል ሱስ መጠበቅን የሚያጣጥል ወይም የሚቃወም፣ አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅ ላይ ትኩረት የሚያደርግ ወይም አካለ መጠን ያልደረሰ ልጅን የማስታወቂያው ተዋናይ አድርጎ የሚጠቀም፤ ወይም ሌላ መሰል መልእክት የሚያስተላልፍ መሆን የለበትም፡፡ በተጨማሪም የአልኮል መጠጥ የውጭ ማስታወቂያ ከልጆች መዋያ ማዕከል፣ ከትምህርት ቤት፣ ከህክምና ወይም ታሪካዊ ተቋም፣ ከሲኒማ ቤት፣ ከቲያትር ቤት ወይም ከስታዲየም በመቶ ሜትር ራዲየስ ውስጥ እንዲቀመጥ መደረግ የለበትም፡፡
የሕግ ተጠያቂነት💎💎
የማስታወቂያ ስራ ሊከተለው የሚገባ ህግና ስርዓት ያለው እንደመሆኑ ህግና ስርዓቱን ባልጠበቀ መልኩ የማስታወቂያ ስራ ላይ መሰማራትም ሆነ ማሰራጨት አስተዳደራዊ፣ ፍትሀ ብሔራዊና የወንጀል ተጠያቂነትን የሚያስከትሉ ሲሆን በዚህ ፅሁፍ ከወንጀል አንፃር ሊኖር የሚችለውን የህግ ተጠያቂነት ሁኔታ እንደሚከተለው ተዳሷል፡-
- በአዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 34/1/ሀ/ መሰረት አንድ ሰው በአዋጁ አንቀፅ 5/1/ እና/2/ መሰረት በማስታወቂያ ስራ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችለውን ፍቃድ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ሳያገኝ በማስታወቂያ ስራ ላይ የተሰማራ እንደሆነ በንግድ ምዝገባና ፍቃድ አዋጅ አንቀፅ 49/2/ መሰረት ለስራው የሚጠቀምበት መሳሪያ መወረስን ጨምሮ ከብር 150ሺ እስከ 300ሺ በሚደርስ የገንዘብ መቀጮ እና ከ7ዓመት እስከ 15ዓመት በሚደርስ የፅኑ እስራት ሊቀጣ ይችላል፡፡
- ከይዘትና ስርጭት አንፃር በመገናኛ ብዙሀን የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ከሌሎች ፕሮግራሞች የተለየ መሆኑ በግልፅ በሚታወቅ መልኩ እና በዜና መልክ ባልተዘጋጀ መልኩ መቅረብ ያለበት መሆኑን፣ የማስታወቂያ ወኪል የአንድን ሰው ምርት፣ አገልግሎት ወይም ሌላ መልእክት የሚያስተዋውቅ የንግድ ማስታወቂያ አዘጋጅቶ ባሰራጨ በሦስት ወራት ውስጥ የሌላ ሰውን ተመሳሳይ ምርት፣ አገልግሎት ወይም ሌላ መልእክት በተመሳሳይ የማስታወቂያ ተዋናይ ምስል ወይም ድምፅ አዘጋጅቶ ማሰራጨት የለበትም በማለት በአዋጁ አንቀፅ 6 ንዑስ አንቀፅ (2)(3) እና(4) የተደነገጉትን መተላለፍ፣ በአዋጁ አንቀፅ 26(3) ስር 12 በመቶ በላይ የአልኮል መጠን ያላቸውን መጠጦች የማስታወቂያ ስርጭት በተመለከተ የተቀመጡ ገደቦችን መተላለፍ ደግሞ በአዋጁ አንቀፅ 34/1/ለ/ መሰረት ከብር 10ሺ በማያንስና ከብር 100ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ እንደሚያስቀጣ ተደንግገዋል፡፡
- በአዋጁ አንቀፅ 6/1/ ስር የተዘረዘሩት የማስታወቂያ ይዘት የተመለከቱ ክልከላዎችን መተላለፍ፣ ህግን ወይም መልካም ስነምግባርን የሚፃረሩ እንዲሁም አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆኑ ማስታወቂያዎች ተብለው በህጉ የተደነገጉትን ማስታወቂያዎች ሰርቶ ማሰራጨት፣ በአዋጁ አንቀፅ 26(1)፣(2) እና (4) የተጠቀሱትን ክልከላዎች በመተላለፍ የአልኮል ይዘታቸው ከ12 በመቶ በላይ የሆኑ መጠጦችን ከተፈቀደው የማስታወቂያ መንገድና ቦታ ውጭ ማስተዋወቅ ከ20ሺ ብር በማያንስና ከብር 150ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡
- በአዋጁ አንቀፅ 25/1/ ስር የተመለከቱትን በህግ ክልከላ የተደረገባቸውን ማስታወቂያዎች ማሰራጨት ደግሞ ከ30ሺ ብር በማያንስና ከብር 250ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡
- በአዋጁ አንቀፅ 34/2/ መሰረት ከፍ ሲል ከተመለከተው የገንዘብ መቀጮ በተጨማሪ ጥፋተኛ የሆነው ሰው ከሕገ ወጥ ማስታወቂያ ሥራው ያገኘው ገቢ ይወረሳል፡፡
ከቅጣት ጋር በተያያዘ ሌላው ከግንዛቤ ልናስገባው የሚገባው ጉዳይ በአዋጁ ላይ በዝርዝር የተጠቀሱት ሌሎች ሁኔታዎች ማለትም የተለየ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ስለሚያስፈልገው ማስታወቂያ፣ አካለመጠን ያልደረሰ ልጅን ስለሚመለከት ማስታወቂያ፣ ስለፀረ አረም ወይም ፀረ ተባይ በተመለከተ የሚተላለፉ ማስታወቂያዎች ወዘተ በተመለከተ የተጠቀሱ ዝርዝር ሁኔታዎችን አለማሟላት በአዋጁ አንቀፅ 34 መሰረት የሚያስቀጡ መሆናቸውን መገንዘብ የሚገባ ሲሆን፡፡ በተጨማሪም ከፍ ሲል ያየናቸው በአዋጁ ላይ ተጠቅሰው የሚገኙት ቅጣቶች ተፈፃሚ የሚሆኑት ድርጎቶቹ በሌላ ህግ የበለጠ የማያስቀጡ እንደሆነ ነው፡፡ ይህም ማለት ድርጊቱ በሌላ ህግ በአዋጁ ከተገለፀው የቅጣት መጠን በላይ የሚያስቀጣ በሆነ ጊዜ ለጉዳዩ የምንጠቀመው የበለጠ የሚያስቀጣውን ህግ ይሆናል ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ በአዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 8(12) መሰረት በትክክለኛ ዋጋው እየተሸጠ ያለን ምርት ወይም አገልግሎት በነጻ እየተሰጠ ወይም በቅናሽ እየተሸጠ እንደሆነ አድርጎ የሚያቀርብ ማስታወቂያ አሳሳች ወይም ተገቢ ያልሆነ ይዘት ወይም አቀራረብ እንዳለው ማስታወቂያ ይቆጠራል፡፡
በአዋጁ አንቀፅ 34(1)(ሐ) መሰረት ደግሞ መሰል አሳሳች ይዘት ያለው ማስታወቂያ ማሰራጨት ከ20ሺ ብር በማያንስና ከብር 150ሺ በማይበልጥ የገንዘብ መቀጮ ያስቀጣል፡፡ በሌላ በኩል በዚሁ ተመሳሳይ ጉዳይ ላይ የንግድ ስራ እና ሸማቾች ጥበቃ አዋጅ ቁጥር 813/2006 አንቀፅ 22(4)(5) መሰረት የንግድ እቃዎችንና አገልግሎቶችን በማስታወቂያ እንደተነገረላቸው አለመሸጥ፣ ስለዋጋ ቅናሽ አሰተኛ ወይም አሳሳች መረጃ መስተላለፍ በአዋጁ አንቀፅ43/3/ ተጠቃሎ ሲታይ ስለ ዋጋ ቅናሽ አሰተኛ ወይም የተሳሳተ መረጃ ማስተላለፍ(ማስተዋወቅ) የአመታዊ ሽያጭ ገቢውን ከ5 እስከ 10 በመቶ የገንዘብ ቅጣት እና ከ1 ዓመት እስከ 5 ዓመት በሚደርስ ፅኑ እስራት እንደሚያስቀጣ ይደነግጋል፡፡ ይሄም ከፍ ሲል በአዋጅ ቁጥር 759/2004 አንቀፅ 34/1/ሐ/ ከተጠቀሰው የቅጣት መጠን ከፍ የሚል በመሆኑ መሰል የዋጋ ቅናሽን በተመለከተ የሚቀርቡ ሀሰተኛ ማስታወቂያዎች ሲሰሩ ክስ ሊቀርብ የሚገባው በንግድ ስራና የሸማቾች ጥበቃ አዋጅ መሰረት ሊሆን እንደሚገባ መረዳት ያስችላል፡፡