TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
አምባ መፅሐፍ

21 Aug, 19:21

Open in Telegram Share Report

✨✨ፍቅር ቅብ....4✨✨



"መነጋገር አለብን...."...አልኩት ባንደኛው ቀን ወደ ነገርየው ልንሄድ ስንል እንደሚሆነው ሲሆን...


"ምነው እድሌ..."...በትንፋሹ እያወራ ነው...የምወድለት አስተያየቱም ተከተለ....እስከ አሁን ፍንክች አላልኩም.....አኳሀኑን ለመናቅ እየተፍጨረጨርኩ ራሴን እገስፃለሁ.....


"ምንድን ነው ግንኙነታታችን...ትርጉም ያጣ አልመሰልህም....?"....ያልጠበቀው ጥያቄ ነበር መሰለኝ ደነገጠ...ውስጤን ሲያራውጠው የነበረ ጥያቄ አፌን ገፍትሮ ሲወጣ እኔ ራሴ ከእርሱ እኩል ደነገጥኩ....


"እንጋባ...."....ይሄን ሲለኝ የስላቅ ሳቄን ልስቅ ቃጣኝ....


"እንጋባ ማለት...."....በምናቤ ቆሎ እየበላን ስንኖር ታየኝ...ለበአል ለበአል ዶሮ ወይ በግ ሳይሆን የተፈጨ በሶ ይዞ ሲገባ....እንደ መናኝ  ያለ እህል እየኖርን እንደ አለመኛ ደግሞ ጉድጉድዱን እያደራን ስንፈስክ እና ለእዜሩም ግራ ስንሆን ታየኝ..


"እንጋባ ማለትማ ያው እንጋባ ነዋ...."


"wow በጣም አስረዳኧኝ...ምን ይዘን ነው የምንጋባው....?...ትዳር ምን እንደሆነ ታውቃለህ ግን...."


"በትንሹ...."...አለኝ ከአይኔ ፈቀቅ እንደማለት እያለ...


"በትንሹ...ካካካካ በትንሹ አይደል...."...የምሬን ነው የተበሳጨሁት...በትንሹ የሚያውቀው ነገር ውስጥ ነው ይዤሽ ካልገባሁ ሲለኝ ያሳነሰኝ መሰለኝ.....


"የትዳር ግማሹን መንገድ እኮ already ሄደናል..."...አለኝ ደግሞ...የባሰው መጣላችሁ...ጉድ አልኩኝ በሆዴ...


"የምን ግማሽ መንገድ ነው...በትንሹ ለምታውቀው ነገር ግማሽ እና ሙሉ ምዕራፍ ለማበጀት አልቸኮልክም...."


"ያልተያየነው ምን ቀረ..."....አለኝ ሰውነቴን በአይኑ ስካን እያደረገ....የአይኑን ማረፊያ ጭኖቼ መሀል እንቁዬ ላይ አድርጎ...እኔ እንቁዬ አልኩት እንጂ በእርሱ አይን ከድንጋይም ቀሏል...


"ድሮም እንካ ያሉት እ*ስ ርካሽ ነው"......ትል ነበር ሀያቴ።


"ምን አልክ..."...አልኩ እያጉረጠረጥኩበት...ወዲያው ደግሞ እንዳይደግመው ጥያቄዬ ላይ ጥያቄ ደረብኩ....


"አላማህ ምንድን ነው....?"


"አንቺን ማግባት...."


"እኔን ማግባት ነው የህይወትህ የመጨረሻ ግብ....እሺ ከዛስ...ከዛስ...ነገስ...."


" ለነገ ነገ ያውቃል..."...አለኝ ፈርጠም ብሎ...በገንኩ...ምንም ባልሰሩበት ነገን ተስፋ ማድረግ ምን ይሉታል...?...ቆይ የዚን ወና ጭንቅላት ባለቤት ነበር ሳፈቅር የኖርኩት....?


"ቆይ ታፈቅረኛለህ....?"


"በጣም...በጣም..."....አለኝና ከሽፋሽፍቴ በላይ ለአይኔ ቀረበ...ከዛ እንደ ድመት ይተሻሸኝ ጀመር....


"እድሌ በጣም አፈቅርሻለሁ...እጅግ በጣም....".....ይሄን ብሎ አፌን ወደሚያዘጋበት አቅጣጫ እጁን ሰደደ....ሰውነቴ እግዜር ይስጠው ያለወትሮው በረዶ ሆነ...


"አታፈቅረኝም...የምታፈቅረው ይሄንን ነው...አሁን እያደረግክ ያለውን ነገር...."...ስለው ከመቅፅበት እጆቹን ከሰካበት ነቀለ....


"ማፍቀር ላንቺ ምንድን ነው...."


"ማፍቀር...ማፍቀርማ ለምታፈቅረው ሰው.....".....ጀምሬ ተውኩት....


"እየሰማሁሽ ነው...ጨርሺልኝ እንጂ...."...ጀምሬ መተዌን አስታወሰኝ.....


"አልጨርሰውም...ይልቅ ማለቅ ያለበት ሌላ ነገር አለ...."


"ምን...."


"ትርጉም የሌለው ግንኙነታችን...."


"ማለት እድሌ እንለያይ እያልሺኝ ነው...."


"መስሎህ እንጂ ቀድሞም አንድ ላይ አልነበርንም....እርማችንን አንድ ቀን ብንነጋገር መግባባት አቅቶን አንተ እንጋባ ትላለህ...ስሙኒ ሳይኖረን ቤተሰብ እንመስርት ትላለህ...ገንዘቡን ተወውና በሞተ የስራ ሞራል አብረን እንኑር ስትል ትንሽ አታፍርም...አልገባህም...አንተ ምኑም አልገባህም...."


"ላስረዳሽ ቆይ"....አለኝ እጄን እንደመያዝ ብሎ...ከተቀመጥኩበት ተነሰቼ በጨርቅ የሞላሁት ቦርሳዬን ሳንጠለጥል....


"ያልገባህን ምን ብለህ ልታስረዳኝ ነው....?"...መልሱን ሳልጠብቅ የያዘኝ እጁን መንጭቄ ሄድኩ።


****


"ወንድ ልጅ ያስስገደደ ሳያስመስል ማስገደድ ይችልበታል...ጠንቀቅ በይ...በቀላሉ ጭንሽን የከፈትሽለት ወንድ ጭንሽን ከቤቱ በር ለይቶ አያየውም..."....ብዬ ታናሽ እህቴን የመከርኳት ምክር እና ስራዬን እያሰብኩ በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ከሄድኩበት "ኧረ ሂሳብ" የሚል ረዳት ድምፅ አባነነኝ.....


ሰባት ቦታ የተጣጠፈች ከሀያቴ የተበደርኩትን ሀያ ብር ከፍዬ አምስት ብር መልሴ ጋር ሀሳቤ ሄደ.....(ትላልቅ ሰዎች ግን ለምን ብር ያለልክ እንደሚያጣጥፉ አላውቅም).....ረዳቱም እግዜር ይስጠው ደጅ አላስጠናኝም.....ወደ ቀደመው ነገሬ ተመለስኩ.....


'ለእህቴ ሌላስ ምን አልኳት....'....ጭንቅላቴን የኃሊት ስልከው እሱም የተመላለስነወን ቃል በቃል ይዞልኝ መጣ.....


"ተከፍቶ የኖረን ጊቢ ሁሉም ቆሻሻውን ያራግፍበታል...."....ስላት


"ግን እኮ እህቴ ተዘግቶ የኖረን ደግሞ ድር ያደራበታል....."....ነበር ያለቺኝ።


"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ስላት አስታውሳለሁ።


አላለቀም.....

✍Shewit

አቅራቢ:- 📚@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ

1.9k 0 8 26
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot