አምባ መፅሐፍ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Books


🎯 አዲስ እና ጥንታዊ መጻሕፍት በአንድ ቦታ
📥 ሁሉም መጻሕፍት በPDF መልክ
📖 “ማንበብ ሙሉ ሰው አያደርግም፤ ወደ ሙሉነት ያደርሳል እንጂ”
👉 Owner: @AmbaSupport
Buy ads ፡
https://telega.io/c/AmbaBooks
🔗 ቅርንጫፎቻችን፦
@AMBA_PDF_BOOKS
@AMBA_TREKA
@YETMHRT_PDF
@AMBAMUSIC1
🤝 ይቀላቀሉን፣ እውቀትን እናጋራ!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Books
Statistics
Posts filter


📑ውጤት ተለቋል 🔥🔥🔥

እምቢ ላላቹ ከታች ባለው ሊንክ ID ላኩን እናይላችዋለን ፈጠን በሉ👇👇👇

'https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0' rel='nofollow'>https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0
'https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0' rel='nofollow'>https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0
'https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0' rel='nofollow'>https://t.me/addlist/7P6VWV6q3hpmNDE0


#ህልምሽን_ንገሪኝ በትረካ:

በዓለም ላይ በርካታ መፅሐፍቶቹን በብዙ ሚሊየን ቅጂዎች በመሸጥ የሚታወቀዉና ተወዳጁ ደራሲ ሲድኒ ሼልደን ከፃፋቸዉ መፅሐፍት አንዱና ተወዳጁን  Tell me Your Dreams መፅሐፍ ሕልምሽን አጫዉቺኝ/ ንገሪኝበሚል ወደ አማርኛ መተርጎሙ ይታወቃል፤ ተርጓሚዉ ግርማ ሓ/ስላሴ ሲሆን በቻናላችን ባማረ አቀራረብና በጥራት በተከታታይ ይዘንላችሁ ቀርበናል።

#ከመጽሐፉ_ውስጥ_ገጽ_የተወሰደ

ወደ እርስ ቤቱ ግድግዳ እያፈገፈገች ስትል ጮኸች። አይኖቿ በፍርሀት ተሞልተዋል። 
::
አለ ዶ/ር ሳሌም
::

::

::
እያለች ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ሁኔታ ተንሰቀሰቀች። 

⏰ ዛሬ ምሽት 2፡00 ላይ ይጠብቁን!
🎧 ትረካውን ለማዳመጥ አይርሱ!

አቅራቢ:👇
📢
@AMBA_TREKA
📢
@AMBA_TREKA
❤️ React ያድርጉ!


🌅 እንዴት አደራችሁ ውድ ቤተሰቦቻችን! ❤️🙏

☀️ መልካም ሰኞ!

አዲስ ቀን፣ አዲስ ሳምንት፣ አዲስ ተስፋ! ✨
ሰኞን በፈገግታ 😊

ሳምንቱን በተስፋ 🌿

ቀናችንን በመልካም ሀሳብ ❤️

እንጀምር!

🙏 ይህ ሳምንት ለሁላችንም የሰላም፣ የደስታ እና የስኬት ሳምንት ይሁን! ❤️✨

📚 አምባ መጽሐፍ — መልካም የንባብ ሳምንት ! 📖


አሁኑኑ እናድርግ

👉“ከማንኛውም የከበረ ስጦታ ይልቅ ስለ ሕይወት ያለንን አመለካከት የሚያሰፋ አንድ መጽሐፍ ይበልጣል” … ይላሉ የመጽሐፍ ጥቅም የገባቸው!!!

🙏 5 ሰከንድ አይፈጅም ይህንን ሊንክ ለጓደኞቻችን በመላክ የቻናላችንን አባላት ቁጥር እናሳድግ።

"ማንበብ ወደ ሙሉነት ያደርሳል "

ይህው የቻናላችን ሊንክ👇👇👇
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS


✨✨✨ፍቅር ቅብ....5✨✨✨




ፍቅር ይሁን መላመድ እንጃ....ብቻ አንዳች ከዚህ ቀደም የማላውቀውን ነገር ከተበኝ....


በየሄድኩበት ሁሉ እንዳስታውሰው አይኔ ላይ ምስሉን ሳለ...ቦታው ሁሉ የእርሱ ግዛት መሰለኝ...


በተለይ ፒያሳ አፄዎቹ በቅርስ ያወረሱት እስኪመስለኝ ድረስ ፤ ከግዛቴ ዘወር በይ ይለኛል ብዬ እስክሸሽ ድረስ ፤ በምንይልክ ፈረስ ላይ በእሳቸው ፈንታ እርሱ ተቀምጧል ብዬ እስክሟገት ድረስ ፤ ወደ እኔ ሽቅብ እንዳይጋልብ እስክፈራ ድረስ ...ፒያሳን የግሉ አደረግኩት...


ከቅፅበት ባጠረች የአብሮነት ጊዜያችን ፤  ሽርፍራፊ ሰከንድ በምትመስል ፍቅር ብለን በሰየምነው ነገራችን ከአዲስ አበባ ከተሞች እግራችን ያልረገጠው ፔንሲዮን የለም ብዬ ብናገር ግነት አይሆንብኝም...ከተወደደ ጠይቀን በችግራችን ስቀን አቅማችንን ካማከለ ደግሞ ጉድጉድ ብለን መውጣት ልማዳችን ነበር....



**

የቡና ሰአቴን ከማሳልፍ ፊት አውራሪ በሆንኩት የታስሲ ሰልፍ ከጀርባዬ ያሉ ሀምሳ ሰዎችን ባሳልፍ ይቀለኛል......

ቡና የምጠጣበትን ቤት በጥንቃቄ ነው የምመርጠው....ወደውስጥ ገባ ያለ....ጫጫታ ማይበዛው....ያልሞቀም ያልቀዘቀዘም አየር ያለው....ረጋ ያለ ሙዚቃ የሚከፈትበት.....ቡና ደግሞ ብቻውን አይደለም.....ጭሱ....ቀጤማው ከነቡና ቁርሱ....የኔ የቡና ፉል ፓኬጅ መስፈርት ይሄ ነው....


ከጫጫታው እና ከግርግሩ ውጪ ሌላው መስፈርቴን የሚያሟላ "ኑ ቡና ጠጡ" ቤት ፒያሳ መሀል ያገኘሁ ሰሞን ነበር ዮናስንም ያገኘሁት....


መፅሀፉን ይዞ የሚቀመጥባት ስፓት ነበረችው.....እልፍ ሲል ንፁህ ንፁህ የሚሸት ሰው ነበር....ንፅህና ይማርከኛል....."እድል" ብሎ ሳይጠራኝ ነው "አቤት" ያልኩለት.....ከአካሄዱ ጀምሮ ግርማ ሞገሱ ሌላ ነበረ....ቡናውን እንዴት ካናቷ ፉት እንደሚላት እያየሁ ሁላ  እደነቅ ነበር(አሁን ከሰዉ የተለየ አጠጣጥ ጠጥቶ ነው ሲያዝብኝ እንጂ)

እንዳየው የሚሆናቸውን ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር እንዳምታታው ያስተዋልኩት ዘግይቼ ነው.....


ቤቱ እዚም እዚያም በኳስ መልክ ተጠቅልለው የተወረወሩ ቆሻሻ ካልሲዎቹን ሳይ ነው ድራማው የተገለፀልኝ....

የበረሮ መናሀሪያ የሆነው እና የተቆለለውን ቆሻሻ መመገቢያ ሳህን ሳይ ነው ትንሽ ትንሽ የገባኝ.....ቦክሰር  ከማጠብ መገረብ እንደሚቀለው ሲነግረኝ ነው እንደመባነን ያልኩት።


ትዝ ይለኛል እኔ ነበርኩ ከፊት ለፊቱ ያለችውን ዱካ ወንበር ባለቤት ያላት እንደሆነ የጠየቅኹት.....


ወሬ ለማስጀመር ያህል ስለሚያነበው መፅሀፍ እንደጠየቅኩትም ትዝ ይለኛል.....ሌላ ጊዜ በሰፊው እንደሚያብራራልኝ እና አሁን ስለቸኮለ መሄድ እንዳለበት ሲነግረኝ አምኜው ነበር....."በጣም ገራሚ መፅሀፍ ነው ....አሁን ስራ ገቢ ስለሆንኩ ሌላ ጊዜ በሰፊው አብራራልሻለሁ.....".....ብሎኝ ከወጣ ቀን ጀምሮ ስለዛ መፅሀፍ አንስቶም አያውቅም....


እኔም ሳነሳበት "ይሄ የእኔ እና ያንቺ ግዜ ነው....ስለገፀባህሪያት የምናወራበት አይደለም....".....ይለኝ ነበር.....ለምናሳልፋት ጊዜ ዋጋ እንደሰጠ እንጂ መፅሀፍ የደረሰበት ደርሶ እንደማያውቅ የነገረኝ አልነበረም(ሲያውርብኝ እንጂ ሶስት ወር ሙሉ አንድ መፅሀፎ ይዞ ሲቀመጥ እንዴት አልጠረጥርም)



ዮናስ ለአልጋ አላመቻቸኝም ነበር.....ያኔ ነው ሁለቴም ሳላስብ ጨዋ ነው ብዬ የደመደምኩት.....


ለዚህ ጨዋ ምንስ ቢሰጠው ብዬ ነበር ጭኔን የከፈትኩለት.....ያልፈለጉ በመምሰል ሴት ላይ እርግጠኝነት የመፍጠር የጭንቅላት ጨዋታ እንደተጫወተ የገባኝ እንደተለመደው ዘግይቶ ነው።


ዮናስን መርሳት አልቀለለኝም.....


እንዴትስ ሊቀለኝ ይችላል.....


ነጋ ጠባ የማስበው እንዴት አይደውልልኝም የሚለውን ነው....."እንደዚህ ይደረጋል" ብዬ በሌለበት የምጯጯኧው በየደቂቃው ነው.....


ብላክ ሊስት ውስጥ ባስገባውም አንድ አስራ አራት ጊዜ "ሞክሮ ገርጥቷል" የሚለውን ዝርዝር እንደማይ እርግጠኛ ነበርኩ...


...ከ2 ወር ምጥ በኃላ ብላክ ሊስት ወዳስገባሁት contact ልደውል እጄን አነሳሁ...ደወልኩ...ስልኩ ተነሳ።


አላለቀም......

✍ሸዊት

አቅራቢ:- 📚@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ




Forward from: አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
ኤክሶድያ - ሰለሞን አበበ @AmbaBooks.pdf
2.3Mb
📚 ኤክሶድያ 📚

📝ደራሲ:- ሰሎሞን አበበ
📆ዓ.ም:- 2013
📑የገፅ ብዛት :- 162
🖨size :- 2.3MB
👆አቅራቢ:-
@ambabooks
ይሄ መጽሐፍ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልቦለድ ነው።  📚
━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📚 ዋና ቻናል ➤
@ambabooks
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ


Forward from: አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
📚 ኤክሶድያ 📚

📝ደራሲ:- ሰሎሞን አበበ
📆ዓ.ም:- 2013
📑የገፅ ብዛት :- 162
🖨size :- 2.3MB
👆አቅራቢ:-
@ambabooks
ይሄ መጽሐፍ በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ ልቦለድ ነው።  📚

👇 ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS
❤️ React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ


📖 የሳምንቱ ትልቅ ትምህርት #08

መጻሕፍትን በተሻለ መንገድ ለማንበብ እነዚህን መንገዶች ተከተሉ :- 

📖 የሚስባችሁን መጽሐፍ ብቻ  ምረጡ በግዴታ የማትወዱትን  መጽሐፍ አትጀምሩ ። ታሪክ ፣ ስነ-ልቦና ፣ ንግድ ፣ ሃይማኖት ወይም ሌላ የሚስባችሁን ብቻ መርጣችሁ አንብቡ  ።

📖 በትንሽ በትንሹ ጀምሩ በቀን ከ 5 –10 ገጽ  ብታነቡ በቀጣይ ቀናት ደግሞ በእጥፍ በእጥፍ  እያሳደጋችሁ ማንበብ ። በአንድ ቀን ብዙ ለማንበብ ብላችሁ ራሳችሁን አታጨናንቁ ::

📖 ምን ለማለት ፈልጎ ነው በሉ:-  ማንበብ ስትጀምሩ ሐሳባችሁን "ደራሲው ምን ሊነግረኝ ፈልጎ  ነው? " ፣ "ይህ ለሕይወቴ ምን ያስተምረኛል?" ብላችሁ አስቡ ።

📖 የገባችሁን ነገር ጻፉት :- የወደዳችሁትን  ሐሳብ ፣ አዲስ ቃላት ወይም ትምህርት በማስታወሻ ደብተር ላይ መዝግቡት ።

📖 በየቀኑ የተወሰነ ሰዓት መድቡ :- ለምሳሌ ጠዋት 15 ደቂቃ ወይም ከመኝታ በፊት 20 ደቂቃ ።

📖 በእርጋታ አንብቡ :- በፍጥነት አንብቦ መጨረስ  ሳይሆን በእርጋታ መረዳት ዋናውና መሰረታዊ ነገር ነው ::  በፍጥነት አንብቦ ከማለፍ ይልቅ አንዱን ገጽ አንብቦ ለመረዳት 20 ደቂቃ ቢፈጅብህ ይሻላል ::

አምባ መጻሕፍት !
የንባብ ባህል እንዲዳብር እንተጋለን !

( ምክሩን ከወደዳችሁት ለሌሎችም እንዲደርስ ለወዳጅ ዘመድዎ አጋሩልን )


አቅራቢ:- 📚
@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ


ጅንጀና Pro Max

ለፈገግታ 🙏 😂


#7ቱ_የአቡነ_ሺኖዳ_ምክሮች

ከአዲሱ #ሰይጣንን_አስርቡት_መጽሐፍ

#አንድ
#ተንኮለኛው_እባብ_ጠላታችንን_ላስተዋውቃችሁ!

ሰይጣን ወይም ዲያብሎስ ስለሚባለው መንፈሳዊ ፍጡር መጀመሪያ ማወቅ ያለብን ነገር ቢኖር ቀይ ልብስ ለባሽ፣ በራሱ ላይ ቀንዶች ያሉት፣ ጭራ ያለው እና ጦር ያዥ አድርገን እንደምናስበው እንደማናገኘው ማወቅ ነው።

👉 መጽሐፉ ስለ ዲያቢሎስ ማወቅ ተንኮሉን ለማፍረስና በእቅዱ ውስጥ ላለመውደቅ ይረዳናል።

#ሁለት
#ዲያብሎስ_ሰፈራችንን_ያውቃል!

እነዚህ ቃላት በውስጣችን ፍርሃትን እንዲፈጥሩብን መፍቀድ የለብንም። ነገር ግን እውነት መሆኑን ግን እንቀበል! ጠላት ሰፈራችንን ያውቃል! ይህ ማለት ዲያብሎስ በመረጠው ቦታ ለመዋል የሚፈልግን ሰው ሁሉ ጎረቤቱ ለማድረግ ፈቃደኛ ነው ማለት ነው፡፡ ታዲያ ሰፈሩ እየመጣን እንዴት ሰፈራችንን አያውቀውም?

👉 እንዴት ከዲያቢሎስ ሰፈር እንደምንርቅና ሰፈራችንን ፈጽሞ እንዳያውቅ ማድረግ እንደምንችል እንማርበታለን።

ይቀጥላል ....

አቅራቢ:- 📚@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ




👔 ወንድ ልጅ ለራሱ ልብስ ሲገዛ የሚያስበው ስለ ዋጋው ነው፤ 👗ሴት ልጅ ለራሷ ልብስ ስትገዛ ግን የምታስበው ስለ ሌላ ሴት አስተያየት ነው።🤔

📚 ርዕስ፦የወንዶችና የሴቶች ስነ-ልቦና
📝 ደራሲ፦ሮን ቶማስ

👇 እናንተ ምን ትላላችሁ? እውነት ነው ወይስ አይደለም?


✨✨ፍቅር ቅብ....4✨✨



"መነጋገር አለብን...."...አልኩት ባንደኛው ቀን ወደ ነገርየው ልንሄድ ስንል እንደሚሆነው ሲሆን...


"ምነው እድሌ..."...በትንፋሹ እያወራ ነው...የምወድለት አስተያየቱም ተከተለ....እስከ አሁን ፍንክች አላልኩም.....አኳሀኑን ለመናቅ እየተፍጨረጨርኩ ራሴን እገስፃለሁ.....


"ምንድን ነው ግንኙነታታችን...ትርጉም ያጣ አልመሰልህም....?"....ያልጠበቀው ጥያቄ ነበር መሰለኝ ደነገጠ...ውስጤን ሲያራውጠው የነበረ ጥያቄ አፌን ገፍትሮ ሲወጣ እኔ ራሴ ከእርሱ እኩል ደነገጥኩ....


"እንጋባ...."....ይሄን ሲለኝ የስላቅ ሳቄን ልስቅ ቃጣኝ....


"እንጋባ ማለት...."....በምናቤ ቆሎ እየበላን ስንኖር ታየኝ...ለበአል ለበአል ዶሮ ወይ በግ ሳይሆን የተፈጨ በሶ ይዞ ሲገባ....እንደ መናኝ  ያለ እህል እየኖርን እንደ አለመኛ ደግሞ ጉድጉድዱን እያደራን ስንፈስክ እና ለእዜሩም ግራ ስንሆን ታየኝ..


"እንጋባ ማለትማ ያው እንጋባ ነዋ...."


"wow በጣም አስረዳኧኝ...ምን ይዘን ነው የምንጋባው....?...ትዳር ምን እንደሆነ ታውቃለህ ግን...."


"በትንሹ...."...አለኝ ከአይኔ ፈቀቅ እንደማለት እያለ...


"በትንሹ...ካካካካ በትንሹ አይደል...."...የምሬን ነው የተበሳጨሁት...በትንሹ የሚያውቀው ነገር ውስጥ ነው ይዤሽ ካልገባሁ ሲለኝ ያሳነሰኝ መሰለኝ.....


"የትዳር ግማሹን መንገድ እኮ already ሄደናል..."...አለኝ ደግሞ...የባሰው መጣላችሁ...ጉድ አልኩኝ በሆዴ...


"የምን ግማሽ መንገድ ነው...በትንሹ ለምታውቀው ነገር ግማሽ እና ሙሉ ምዕራፍ ለማበጀት አልቸኮልክም...."


"ያልተያየነው ምን ቀረ..."....አለኝ ሰውነቴን በአይኑ ስካን እያደረገ....የአይኑን ማረፊያ ጭኖቼ መሀል እንቁዬ ላይ አድርጎ...እኔ እንቁዬ አልኩት እንጂ በእርሱ አይን ከድንጋይም ቀሏል...


"ድሮም እንካ ያሉት እ*ስ ርካሽ ነው"......ትል ነበር ሀያቴ።


"ምን አልክ..."...አልኩ እያጉረጠረጥኩበት...ወዲያው ደግሞ እንዳይደግመው ጥያቄዬ ላይ ጥያቄ ደረብኩ....


"አላማህ ምንድን ነው....?"


"አንቺን ማግባት...."


"እኔን ማግባት ነው የህይወትህ የመጨረሻ ግብ....እሺ ከዛስ...ከዛስ...ነገስ...."


" ለነገ ነገ ያውቃል..."...አለኝ ፈርጠም ብሎ...በገንኩ...ምንም ባልሰሩበት ነገን ተስፋ ማድረግ ምን ይሉታል...?...ቆይ የዚን ወና ጭንቅላት ባለቤት ነበር ሳፈቅር የኖርኩት....?


"ቆይ ታፈቅረኛለህ....?"


"በጣም...በጣም..."....አለኝና ከሽፋሽፍቴ በላይ ለአይኔ ቀረበ...ከዛ እንደ ድመት ይተሻሸኝ ጀመር....


"እድሌ በጣም አፈቅርሻለሁ...እጅግ በጣም....".....ይሄን ብሎ አፌን ወደሚያዘጋበት አቅጣጫ እጁን ሰደደ....ሰውነቴ እግዜር ይስጠው ያለወትሮው በረዶ ሆነ...


"አታፈቅረኝም...የምታፈቅረው ይሄንን ነው...አሁን እያደረግክ ያለውን ነገር...."...ስለው ከመቅፅበት እጆቹን ከሰካበት ነቀለ....


"ማፍቀር ላንቺ ምንድን ነው...."


"ማፍቀር...ማፍቀርማ ለምታፈቅረው ሰው.....".....ጀምሬ ተውኩት....


"እየሰማሁሽ ነው...ጨርሺልኝ እንጂ...."...ጀምሬ መተዌን አስታወሰኝ.....


"አልጨርሰውም...ይልቅ ማለቅ ያለበት ሌላ ነገር አለ...."


"ምን...."


"ትርጉም የሌለው ግንኙነታችን...."


"ማለት እድሌ እንለያይ እያልሺኝ ነው...."


"መስሎህ እንጂ ቀድሞም አንድ ላይ አልነበርንም....እርማችንን አንድ ቀን ብንነጋገር መግባባት አቅቶን አንተ እንጋባ ትላለህ...ስሙኒ ሳይኖረን ቤተሰብ እንመስርት ትላለህ...ገንዘቡን ተወውና በሞተ የስራ ሞራል አብረን እንኑር ስትል ትንሽ አታፍርም...አልገባህም...አንተ ምኑም አልገባህም...."


"ላስረዳሽ ቆይ"....አለኝ እጄን እንደመያዝ ብሎ...ከተቀመጥኩበት ተነሰቼ በጨርቅ የሞላሁት ቦርሳዬን ሳንጠለጥል....


"ያልገባህን ምን ብለህ ልታስረዳኝ ነው....?"...መልሱን ሳልጠብቅ የያዘኝ እጁን መንጭቄ ሄድኩ።


****


"ወንድ ልጅ ያስስገደደ ሳያስመስል ማስገደድ ይችልበታል...ጠንቀቅ በይ...በቀላሉ ጭንሽን የከፈትሽለት ወንድ ጭንሽን ከቤቱ በር ለይቶ አያየውም..."....ብዬ ታናሽ እህቴን የመከርኳት ምክር እና ስራዬን እያሰብኩ በሀሳብ ጭልጥ ብዬ ከሄድኩበት "ኧረ ሂሳብ" የሚል ረዳት ድምፅ አባነነኝ.....


ሰባት ቦታ የተጣጠፈች ከሀያቴ የተበደርኩትን ሀያ ብር ከፍዬ አምስት ብር መልሴ ጋር ሀሳቤ ሄደ.....(ትላልቅ ሰዎች ግን ለምን ብር ያለልክ እንደሚያጣጥፉ አላውቅም).....ረዳቱም እግዜር ይስጠው ደጅ አላስጠናኝም.....ወደ ቀደመው ነገሬ ተመለስኩ.....


'ለእህቴ ሌላስ ምን አልኳት....'....ጭንቅላቴን የኃሊት ስልከው እሱም የተመላለስነወን ቃል በቃል ይዞልኝ መጣ.....


"ተከፍቶ የኖረን ጊቢ ሁሉም ቆሻሻውን ያራግፍበታል...."....ስላት


"ግን እኮ እህቴ ተዘግቶ የኖረን ደግሞ ድር ያደራበታል....."....ነበር ያለቺኝ።


"ድር እኮ መድሀኒትነት አለው....ቁስልን ለዘብ ያደርጋል....ላፅዳህ ብትዪውም በጄ ይልሻል.....የዘመናት ቆሻሻን ዘወር ብታደርጊው እንኳን ጠረኑ ከርቤም አይበቃውም....."....ስላት አስታውሳለሁ።


አላለቀም.....

✍Shewit

አቅራቢ:- 📚@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ




Forward from: አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
የሺ ሀረጊቱ በደጀኔ ተሰማ .pdf
53.6Mb
📚የሺ ሀረጊቱ 📚

📝ደራሲ፦በደጀኔ ተሰማ
📜ይዘት፦ልቦለድ
⬇️size፦53.6MB
💰የተቀመጠ ዋጋ፦....
🪝Type ፦#ልቦለድ#Pdf
🔔ቻናል፦
@ambabooks

━━━━━━━━━━
📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦

📚 ዋና ቻናል ➤
@ambabooks
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
❤️ ከወደዱት React ያድርጉ


Forward from: አምባ መጻሕፍት ማቆያ 📚
📚የሺ ሀረጊቱ 📚

📝ደራሲ፦በደጀኔ ተሰማ
📜ይዘት፦ልቦለድ
⬇️size፦53.6MB
💰የተቀመጠ ዋጋ፦....
🪝Type ፦#ልቦለድ#Pdf
🔔ቻናል፦
@ambabooks

📌ማጋራት አይዘንጋ
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS
📢
@AMBABOOKS


❤️ ቤተሰብ፣ ጥያቄ ስንጠይቃችሁ ተሳትፎ አድርጉ፤ ዝም አትበሉ! 😍👇

📚 @Amba_Books ግሩፕ ነው፤ ግሩፑን በመቀላቀል ተሳትፎ አድርጉ። አዲስ የመጣችሁም እንተዋወቅ! ❤️


📚❤️ ቤተሰብ፣ ለእናንተ የምንጊዜም ምርጥ መጽሐፍ የትኛው ነው?

👇 ኮሜንት ላይ ፃፉልን፤ ለሌሎችም ጀማሪ አንባቢያን ይጠቅማል! ❤️


" ያ ደግ ሰው በመንገዱ እየኼደ ሳለ ሽፍታ አገኘ፡፡ ያ ደግ ሰው፤ “ሰላም ለአንተ ይኹን! በዚህ ስፍራ ለምን ብቻህን ትዘዋወራለህ?” አለው። ያ ሽፍታም፡ “እኔ ሽፍታ ነኝ! ለዚህም ነው በዚህ ሰዋራ ስፍራ የምዘዋወረው::

ይልቅ ምን ይዘሃል? ወዲህ በል የያዝኸውን ኹላ! አምጣው!” አለው። ያ ደግ ሰው፡ “ለምን ግን ሠርተህ አትበላም? ሰው የደከመበት ገንዘብ ላንተ ምን ያደርግልሃል?" አለው፡፡

ያ ሽፍታ እየሣቀ፡ “ስማ! ማር በልተህ ታውቃለህ?" አለው:: ያ ደግ ሰው፡ “እንዴታ! በደንብ አድርጌ ነዋ የምበላው!" አለው::

ያ ሽፍታ፡ “ሠርተህ ነው ወይስ ከንብ ቀምተህ ነው? በጭስ እያስፈራራህ፣ እንዳትታይ በጭንብል እየተከለልህ ነው ንብ ለፍታ የሠራችውን የምትቀማት” አለው፡፡

ያ ደግ ሰው፤ ኹሉም ስው “ለፋኹበት” በሚለው ጕዳይ ወስጥ መዝረፍ እንዳለበት ዐወቀ። ከዚያም፣ ለሽፍታው “ብዙ ገንዘብ የለኝም:: ምናልባት ይህቺ ኹለት ፈረንካ ከበቃችህ እንካ” አለው፡፡

ያ ሽፍታ፡ “ለዛሬው ምሬሃለኹ፣ ከዚህ በኋላ ግን በማያገባህ ጕዳይ አትግባ" አለው፡፡

ያ ደግ ሰው፡ “እንኳን ማርኸኝ እንጂ በል ደኅና ሰንብት" ብሎት ፈጠን ፈጠን እያለ ተራመደ፡፡ በመንገዱም ላይ ሳለ እንዲህ እያለ እያሰበ ነበር፡፡

“አኹን ግን የእውነት እንቁላልን ዶሮ የምትሸጠው ቢኾን ዋጋው ስንት ይኾን ነበር? ሰው ከዕቅፏ ፈልቅቆ ይወስድባታል እንጂ መቼ ይጠይቃታል። እና፣ ከደምና ከዐጥንቴ ያልሠራኹትን ገንዘብ ሽፍታ ወስዶብኝ እንዲህ ከተንገበገብኹ ልጅ ይኾነኛል ያልኹትን፣ ከብቤ ያኖርኹትን ቢያነሡብኝ ቀድሜ አበድኹኝ” እያለ ኑሮውን እየታዘበ ኼደ፡፡ "

" ግርባብ
ያ ደግ ሰው "

በፍቃዱ አየልኝ

መጽሐፉ በመደብራችን ይገኛል ::

አቅራቢ:- 📚
@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ

20 last posts shown.