TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
አምባ መፅሐፍ

23 Aug, 20:15

Open in Telegram Share Report

✨✨✨ፍቅር ቅብ....5✨✨✨




ፍቅር ይሁን መላመድ እንጃ....ብቻ አንዳች ከዚህ ቀደም የማላውቀውን ነገር ከተበኝ....


በየሄድኩበት ሁሉ እንዳስታውሰው አይኔ ላይ ምስሉን ሳለ...ቦታው ሁሉ የእርሱ ግዛት መሰለኝ...


በተለይ ፒያሳ አፄዎቹ በቅርስ ያወረሱት እስኪመስለኝ ድረስ ፤ ከግዛቴ ዘወር በይ ይለኛል ብዬ እስክሸሽ ድረስ ፤ በምንይልክ ፈረስ ላይ በእሳቸው ፈንታ እርሱ ተቀምጧል ብዬ እስክሟገት ድረስ ፤ ወደ እኔ ሽቅብ እንዳይጋልብ እስክፈራ ድረስ ...ፒያሳን የግሉ አደረግኩት...


ከቅፅበት ባጠረች የአብሮነት ጊዜያችን ፤  ሽርፍራፊ ሰከንድ በምትመስል ፍቅር ብለን በሰየምነው ነገራችን ከአዲስ አበባ ከተሞች እግራችን ያልረገጠው ፔንሲዮን የለም ብዬ ብናገር ግነት አይሆንብኝም...ከተወደደ ጠይቀን በችግራችን ስቀን አቅማችንን ካማከለ ደግሞ ጉድጉድ ብለን መውጣት ልማዳችን ነበር....



**

የቡና ሰአቴን ከማሳልፍ ፊት አውራሪ በሆንኩት የታስሲ ሰልፍ ከጀርባዬ ያሉ ሀምሳ ሰዎችን ባሳልፍ ይቀለኛል......

ቡና የምጠጣበትን ቤት በጥንቃቄ ነው የምመርጠው....ወደውስጥ ገባ ያለ....ጫጫታ ማይበዛው....ያልሞቀም ያልቀዘቀዘም አየር ያለው....ረጋ ያለ ሙዚቃ የሚከፈትበት.....ቡና ደግሞ ብቻውን አይደለም.....ጭሱ....ቀጤማው ከነቡና ቁርሱ....የኔ የቡና ፉል ፓኬጅ መስፈርት ይሄ ነው....


ከጫጫታው እና ከግርግሩ ውጪ ሌላው መስፈርቴን የሚያሟላ "ኑ ቡና ጠጡ" ቤት ፒያሳ መሀል ያገኘሁ ሰሞን ነበር ዮናስንም ያገኘሁት....


መፅሀፉን ይዞ የሚቀመጥባት ስፓት ነበረችው.....እልፍ ሲል ንፁህ ንፁህ የሚሸት ሰው ነበር....ንፅህና ይማርከኛል....."እድል" ብሎ ሳይጠራኝ ነው "አቤት" ያልኩለት.....ከአካሄዱ ጀምሮ ግርማ ሞገሱ ሌላ ነበረ....ቡናውን እንዴት ካናቷ ፉት እንደሚላት እያየሁ ሁላ  እደነቅ ነበር(አሁን ከሰዉ የተለየ አጠጣጥ ጠጥቶ ነው ሲያዝብኝ እንጂ)

እንዳየው የሚሆናቸውን ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር እንዳምታታው ያስተዋልኩት ዘግይቼ ነው.....


ቤቱ እዚም እዚያም በኳስ መልክ ተጠቅልለው የተወረወሩ ቆሻሻ ካልሲዎቹን ሳይ ነው ድራማው የተገለፀልኝ....

የበረሮ መናሀሪያ የሆነው እና የተቆለለውን ቆሻሻ መመገቢያ ሳህን ሳይ ነው ትንሽ ትንሽ የገባኝ.....ቦክሰር  ከማጠብ መገረብ እንደሚቀለው ሲነግረኝ ነው እንደመባነን ያልኩት።


ትዝ ይለኛል እኔ ነበርኩ ከፊት ለፊቱ ያለችውን ዱካ ወንበር ባለቤት ያላት እንደሆነ የጠየቅኹት.....


ወሬ ለማስጀመር ያህል ስለሚያነበው መፅሀፍ እንደጠየቅኩትም ትዝ ይለኛል.....ሌላ ጊዜ በሰፊው እንደሚያብራራልኝ እና አሁን ስለቸኮለ መሄድ እንዳለበት ሲነግረኝ አምኜው ነበር....."በጣም ገራሚ መፅሀፍ ነው ....አሁን ስራ ገቢ ስለሆንኩ ሌላ ጊዜ በሰፊው አብራራልሻለሁ.....".....ብሎኝ ከወጣ ቀን ጀምሮ ስለዛ መፅሀፍ አንስቶም አያውቅም....


እኔም ሳነሳበት "ይሄ የእኔ እና ያንቺ ግዜ ነው....ስለገፀባህሪያት የምናወራበት አይደለም....".....ይለኝ ነበር.....ለምናሳልፋት ጊዜ ዋጋ እንደሰጠ እንጂ መፅሀፍ የደረሰበት ደርሶ እንደማያውቅ የነገረኝ አልነበረም(ሲያውርብኝ እንጂ ሶስት ወር ሙሉ አንድ መፅሀፎ ይዞ ሲቀመጥ እንዴት አልጠረጥርም)



ዮናስ ለአልጋ አላመቻቸኝም ነበር.....ያኔ ነው ሁለቴም ሳላስብ ጨዋ ነው ብዬ የደመደምኩት.....


ለዚህ ጨዋ ምንስ ቢሰጠው ብዬ ነበር ጭኔን የከፈትኩለት.....ያልፈለጉ በመምሰል ሴት ላይ እርግጠኝነት የመፍጠር የጭንቅላት ጨዋታ እንደተጫወተ የገባኝ እንደተለመደው ዘግይቶ ነው።


ዮናስን መርሳት አልቀለለኝም.....


እንዴትስ ሊቀለኝ ይችላል.....


ነጋ ጠባ የማስበው እንዴት አይደውልልኝም የሚለውን ነው....."እንደዚህ ይደረጋል" ብዬ በሌለበት የምጯጯኧው በየደቂቃው ነው.....


ብላክ ሊስት ውስጥ ባስገባውም አንድ አስራ አራት ጊዜ "ሞክሮ ገርጥቷል" የሚለውን ዝርዝር እንደማይ እርግጠኛ ነበርኩ...


...ከ2 ወር ምጥ በኃላ ብላክ ሊስት ወዳስገባሁት contact ልደውል እጄን አነሳሁ...ደወልኩ...ስልኩ ተነሳ።


አላለቀም......

✍ሸዊት

አቅራቢ:- 📚@ambabooks

📢 ቻናሎቻችንን ይቀላቀሉ፦
📖 ማቆያ ➤
@amba_pdf_books
🎭 ትረካ ➤
@amba_treka
🎓ትምህርት➤
@yetmhrt_pdf
🎵  ሙዚቃ ➤
@ambamusic1
━━━━━━━━━━━━━━
   ❤️React ያድርጉ | ሼር ያድርጉ

1.2k 0 5 1 12
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot