ተዘርፎ የነበረን ጤፍ በማስመለስ ለባለቤቱ ማስረከቡን ፖሊስ ገለፀ።
በታጣቂዎች ተወስዶ ታግቶ የነበረን ንብረትነቱ የአቶ ዋጋነህ መንግስቴ የሆነን የጭነት መኪና እስከጫነው 250 ኩንታል ጤፍ ማስመለሱን የበባህርዳር ከተማ አስተዳደር ፖሊስ መምሪያ የ7ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ገልጿል።
እንደ ጣቢያው የወንጀል ምርመራ ክፍል ኀላፊ ኢንስፔክተር ክንድየ ይማም ገለፃ ተሽከርካሪው ጥቅም 10 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9:30 አካባቢ 250 ኩንታል ጤፍ በመጫን ለንግድ ስራ ከደቡብ ጎንደር ዞን አንዳቤት ወረዳ ወደ ባህርዳር እየተጓዘ እያለ ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ሮቢት ባዕታ ላይ ሲደርስ በታጠቁ ሀይሎች ተይዞ ሹፌሩን እና አብረው የነበሩ ግለሰቦችን በመያዝ ወደማይታወቅ ስፍራ ይዘዋቸው ይሄዳሉ።
ኢንስፔክተር ክንድየ እንደሚሉት ተሽከርካሪውን ከነጤፉ ወደ ባህርዳር ከተማ አፄ ቴዎድሮስ ክ/ከተማ በራሳቸው ሹፌር በማምጣት ማራኪ ቀበሌ ልዩ ቦታው ኪዳነ ምህረት ቤተክርስቲያን አቃኔ አድማሴ ከተባለ ግለሰብ አንድ መጋዘን ውስጥ ጤፉን በማራገፍ መኪናውን እዛው አካባቢ ታርጋውን በመፍታት ያስቀምጡታል።
ፖሊስም የደረሰውን ጥቆማ መሰረት አድርጎ መኪናውን ካገኘ በኃላ የአካባቢውን መጋዘን ሲፈትሽ ጤፉን ሊያገኘው ችሏል ይላሉ ኢንስፔክተር ክንድየ ይማም ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም ባለ መጋዘኑን ጨምሮ አራት(4)ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር በማዋል አስፈላጊውን ምርመራ በማጣራት ለሚመለከተው የፍትህ አካል መላኩን ኢንስፔክተር ክንድየ አክለው ገልጸዋል።