የሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ ጠንካራ ሥራ መሠራቱን የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ገለጸ።
በአማራ ክልል ወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፤ የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ የ6 ወራት የሥራ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ የውይይት መድረክ በሁመራ ከተማ አካሂዷል።
በግምገማው የተገኙት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኅላፊ ኢንስፔክተር ጌታቸው ሙሉጌታ የወልቃይት ጠገዴን የወሰን እና የማንነት ጥያቄን አሳልፎ የሚሰጥ መሪ የለም ብለዋል።
ሕዝቡ ወዳጅ እና ጠላቱን ለይቶ ለመብቱ እና ለማንነቱ እንዲቆም ማንቃት ፣ ማደራጀት እና ማንቀሳቀስ እንደተቻለም ተናግረዋል። ከውጭም ሆነ ከውስጥ ያለ ኅይል በጦርነት የሚያመጣው መፍትሄ የለም ያሉት ኢንስፔክተሩ ፍላጎቱን በኅይል ማሳካት የሚፈልግ አካል ላይም የተጠናከረ እርምጃ ይወሰድበታል ብለዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ሕዝብን ነቅቶ የሚጠብቅው የጸጥታ ኀይል፤ ለመብት እና ለማንነቱ የሚታገል መሪ እና ተደራጅቶ የሚያደራጅ ጠንካራ መዋቅር ያለው መኾኑንም ተናግረዋል።
የወሰን፣ የማንነት እና የድንበር ጥያቄዎቹ ለድርድር የሚቀርቡ አለመኾናቸውን አንስተዋል። ዞኑ በስድስት ወራት የጸጥታ ሥራ አፈጻጸሙ የሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ፣ ሕግ እና ሥርዓትን በማጽናት ረገድ ጠንካራ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገልጸዋል።
በክልልሉ የተፈጠረው የጸጥታ ችግር በዞኑ አንዳንድ አካባቢዎችም የተከሰተበት ወቅት እንደነበር ያነሱት ምክትል ኀላፊው በጸጥታ መዋቅሩ እና በዞኑ አጠቃላይ የመሪዎች ቁርጠኝነት ችግሩን ማስተካከል መቻሉንም ተናግረዋል።
ዝርፊያን እና እገታን በማስቆም ፤ ወንጀለኞችንም ተከታትሎ በመያዝ ዞኑ ሰላማዊ እንዲኾን በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ብለዋል።
የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ፖሊስ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሙላት ማሞ የጸጥታ መዋቅሩ ለኅብረተሰቡ ተገቢውን አገልግሎት በመስጠት እና የሕዝቡን ሰላም እና ደኅንነት በመጠበቅ ረገድ ያከናወናቸው ተግባራት በጥልቀት መገምገማቸውን ተናግረዋል።
ኅብረተሰቡ የጸጥታ ኀይሉን በመደገፉ ምክንያት የዞኑ ሰላም እና ደኅንነት የተረጋገጠ መኾኑን ነው የገለጹት። ተሳትፎውን በማጠናከር የሕዝቡን ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጤንነት ማስጠበቅ እንደሚገባም ገልጸዋል።
ዞኑ ኤርትራን እና ሱዳንን የሚያዋስን በመኾኑ ስትራቴጂካዊ ጠቀሜታው ሀገራዊ ስለኾነ ጠንካራ የጸጥታ መዋቅር እንደሚያስፈልግ ታውቆ እየተሠራበት ነው ብለዋል።
የውስጥ እና የውጭ ኀይሎች የቦታውን ወሳኝነት በመረዳት ያልተገባ እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ዞኑ የጸጥታ መዋቅሩን በንቃት ስምሪት እየሰጠ ነው ብለዋል። በመደራጀት ፣ በመተሳሰብ እና በመደጋገፍ የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማጽናት እንደሚገባም አሳስበዋል።
የአውራ ወረዳ አሥተዳዳሪ ፈረደ በሪሁን የሕዝብን ሰላም እና ደኅንነት ለመጠበቅ የማይሰለች የጸጥታ መዋቅር መኖሩን ተናግረዋለ ሲል የዘገበው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ነው።