Forward from: የእምነት ጥበብ
ከሁለት አካል አንድ አካል ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ሲባል ምን ማለት ነው?
በዚህ ርዕስ ዙሪያ የሚያስቁ የተለያዩ ሀሳቦችን አይቻለሁ።
1ኛ. ባሕርይን እንጅ አካልን አልተካፈለም የሚልና
2ኛው .የመለኮቱ አካል (ሎጎስ) ሰው ለመሆን የጎደለው የሰው አካል ሳይሆን የሰው ባህሪ ነበር። የሚሉ አሰቂኝ ቀልዶች😁
ሲጀመር በየትኛውም መንገድ አካል ሳይኖር
ባሕርይው ሊኖር አይችልም እስትንፋስ ያለውም ይሁን የሌለውም።
‹አካል ሲባል ግዙፍም ሆነ ረቂቅ የባሕርይ መገለጫ ነው፤ ባሕርይ ሲባል ግዙፍም ሆነ ረቂቅ የአካል መገኛ መሠረት ነው፡፡
ስለሰው ባሕርይ ስናወራ ስለ ሥጋ ብቻ አይደለም ስለ ነፍስ ብቻ አይደለም የሰው ባሐርይ የነፍስና ሥጋ አንድ በመሆን የተገኘ ነው ከሁለቱ አንዱ ከጎደለ የሰው ባሕርይ አይደለም ሰው የሚባለው የሥጋና ነፍስ ተዋሕደው አንድ በመሆን ያስገኙት እንጅ ። ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ሥጋና ነፍስን እደነሣ ነው የምናምነው ወይ ነፍስ ከእናትና አባት አትከፈልም ብለው ከሚያመኑት ወይም ደግሞ ለክርስቶስ በነፍስ ፈንታ መለኮት ሆነው ከሚሉት ወገን ካልሆን በስተቀር። የሰው ባሕርይ ከእንስሳት የሚለየው ሕያው የሆነች የማትሞት ነፍስ ስላለችው ነው ። ክርስቶስ ባሕሪያችን ነሣ ስንል ሥጋችንም ነፍሳችንም ነሣ ማለታችን ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም እኔ የምትል ነፍስን ከድንግል ማርያም ተካፍሏል ከባሕርይ ባሕርይን ሲካፈል ከድንግል እኔነት እኔነትን ተካፍሏል ።
እኛ ሰዎች ባሕርይን ከእናትና አባታችን ስንካፈል አካልን ተካፈልን ማለት ነው ። እኔነትን ከእናትና አባታችን በተከፍሎ የምናገኘው እንጅ ከየትም የመጣ አይደለም ። ስለዚህ ክርስቶስ ስንል ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ነው ። ስለዚህ ቃል ሰው ከመሆኑ በፊት ሰዋዊ ባሕርይ እንዳልነበረው ሁሉ ሰዋዊ አካል(እኔነት የለውም) ሰው ሲሆን ግን የእርሱ ያልነበረውን የሰውን ባሕርይ ገንዘቡ ሲያደርግ የእርሱ ያልነበረውን እኔነትም ገንዘቡ አድርጓል ። ስለዚህ ክርስቶስ ሁለት ባሕርይ ነው እንደማንለው ሁሉ ሁለት እኔነትም አንለውም የሰውነት እኔነት ከመለኮት እኔነት በተዋሕዶ አንድ ሆኑ እንል አለን እንጅ ። ስለዚህ ከሁለት ባሕርይ አንድ ባሕርይ ስንል ከድንግል ማርያም የተካፈለውን ባሕርይና የመለኮትን ባሕርይ ማለታችን እንደሆነ ሁሉ ከሁለት አካልም ስንል እንደሁ ነው የሰውነት እኔነት በተከፍሎ የሚገኝ ነው።
@felgehaggnew