የመከላከያ ሰራዊት ለሀገራዊ ደኅንነት የመጨረሻው ምሽግ በመሆኑ ለሕዝባችን እና ሀገራችን ደኅንነት ሁልጊዜም እንሠራለን ሲሉ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ፡፡
የኢትዮጵያ አየር ኃይል ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ የአየር ጥበቃ ፖሊስ አባላቱን እና ቴክኒሻኖች አስመርቋል፡፡
በዚሁ ወቅት የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ባደረጉት ንግግር÷ በርካታ ልፋትን አከናውናችሁ የማዕረግ ሽልማትን ያገኛችሁ የአየር ሃይል አባላትና ቤተሰቦች ለዚህ ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡
አየር ሃይል የሀገሪቱ መከላከያ ክንድ መሆኑን ጠቅሰው÷ ይሄንን ኃይል ማጠንከር ብቻ ሳይሆን የባህር ሃይል አቅምንም በመጨመር ከፍ ማለት እንደሆነ ተናግረዋል።
አሁን ላይ ኢትዮጵያ ትልቅ የምድር ሃይል አቅምን ገንብታለች ያሉት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ÷ አየር ሃይላችንንም በከፍተኛ አቅምና ችሎታ የጠነከረ ለማድረግ በከፍተኛ ቁርጠኝነት እየተሰራ ነው ብለዋል።
በዘመነ ህውሓት የአየር ሃይሉን አቅም በአቅሙ ወደታች የሆነ እና የብሄር ብሄረሰብ ተዋጽኦም ያልነበረው ተቋም አድርጎት እንደነበረ አስታውሰው÷ ኢትዮጵያ ለስሙ ብቻ አየር ሃይል አላት ተብሎ ለውድቀት እንድትዳረግ ያደረገ የህውሓት የሴራ ውጤት እንደነበረም ገልጸዋል፡፡
የሀገሪቱን የፓይለት ባለሙያዎች ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን÷ ከውጭም ሌሎቹን ማሰልጠን የሚችል አቅም ተፈጥሯል ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ አየር ሃይል የአፍሪካ የልምድ መውሰጃ ማዕከል እንዲሆን እየተሰራ መሆኑ የተመላከተ ሲሆን÷ ባለፉት ሁለት አመታት በተሰራው ስራም ለውጥ ማምጣት ተችሏል ተብሏል።
አየር ሃይሉ የደረሰበትን ከፍታ በሽብር ቡድኑ ላይ ያከናወነው የጀግንነት ተግባር እና ጀብዱ ማሳያ እንደሆነ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ