የከበረች ቅድስት ኦርኒም ሃይማኖትን እያስተማረች፣ ድውያንን እየፈወሰች፣ ሙታንን እያስነሣች በታላቅ አገልግሎት ተቀመጠች፡፡ ከዚህም በኋላ 4ኛ ንጉሠሥ መጣና የእርሷን ዜና ሰምቶ ወደ እርሱ አስመጣት፡፡ ለጣዖትም እንድትሰግድ ባስገደዳት ጊዜ ጣዖቱቹንና እርሱን ረገመቻው፡፡ ንጉሡም በዚህ ተናዶ ከእሳት ውስጥ ጨመራት፡፡ እርሷም ከእሳቱ ውስጥ ሆና ስትጸልይ የታዘዘ መልአክ መጥቶ እሳቱን አቀዝቅዞ በሰላም አወጣት፡፡ ከእሳቱም ከወጣች በኋላ የንጉሡን ጣዖታት ዳግመኛ ዘለፈች፡፡ ንጉሡም በእርሷ ላይ የተፈጸመውን ታላቅ ተአምር አይቶ በጌታችን አመነ፡፡ አምስተኛውም የፋርስ ንጉሥ በመጣ ጊዜ ቅድስት ኦርኒን ይዞ በእጁ በያዘው ጦር ወጋትና ሞተች፡፡ የታዘዘ መልአክም መጥቶ ከሞት አስነሣትና ዳግመኛ በጌታችን ስም ማስተማር ጀመረች፡፡ ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ተድላ ደስታ ወዳለበት ገነት ተነጥቃ ወጣች፡፡ ማኅበርተኞቿ የሆኑ 13 ሺህ ሰዎች በዚሁ ዕለት በሰማዕትነት ዐርፈዋል፡፡
የሰማዕቷ የቅድስት ኦርኒ ረድኤት በረከቷ ይደርብን በጸሎቷ ይማረን!
+ + +
ሰማዕቷ ቅድስት ጤቅላ፡- ጤቅላ ማለት ‹‹ልጅ፣ ለግላጋ›› ማለት ነው፡፡ ቅድስት ጤቅላና ከእርሷ ጋር የነበሩ አራት ደናግል ጥር 30 ቀን ፎላ በሚባል ኃጥእ ቄስ እጅ ሰማዕትነታቸውን ፈጸሙ፡፡ ይህም ፎላ የተባለ ቄስ በአመጽ የሰበሰበው ብዙ ገንዘብ እንዳለው በከሃዲው መኰንን ዘንድ ነገሩበት፡፡ ስለዚህም መኮንኑ ገንዘቡን ሁሉ እንዲወርሱ አዘዘ፡፡ ፎላም ወደ መኰንኑ ዘንድ በመሄድ ገንዘቡን ይመልስለት ዘንድ ቢለምነው እምቢ አለው፡፡ ከሃዲው መኰንንም ስለ እነቅድስት ጤቅላ የምግባር የሃይማኖታቸውን ዜናቸውን በሰማ ጊዜ ወደ እርሱ እንዲያመጧቸው አዘዘና አስመጣቸው፡፡ ጌታችንን አስክዶ እምነታቸው አውጥቶ ለጣዖት እንዲገዙ ግድ አላቸው፡፡ እነርሱ ግን በእምነታቸው በጸኑ ጊዜ መኰንኑ ፎላንን ጠርቶ ‹‹እነዚህ ደናግል ለፀሐይ ይሰግዱ ዘንድ እነርሱን ብትሸግልልኝ ገንዘብህን መልሼ እሰጥሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላንም እነ ቅድስት ጤቅላን ይሸነግላቸው ጀመረ፡፡ ደናግሉም ‹‹አንተ የሰይጣን ልጅ የክብር ባለቤት ክርስቶስን እንክደው ዘንድ እንዴት ትፈትነናለህ? አንተ ቀድሞ መምህራችን የነበርክ ስትሆን›› ብለው ዘለፉት፡፡
መኰንኑም ይህን ቃላቸውን ከአንደበታቸው በሰማ ጊዜ በጅራፍ ጽኑ ግርፋትን አስገረፋቸው፡፡ እነዚህ ቅዱሳት ደናግል ግን ስለ ጌታችን ይመሰክሩ ነበር እንጂ ምንም አልፈሩም ነበር፡፡ መኰንኑም ፎላንን ‹‹የበከተ ብትበላ ደምንም ብትጠጣ ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› ባለው ጊዜ እንዳለው አደረገ፡፡ ዳግመኛም ‹‹እነዚህን ደናግል ብትገድላቸው ገንዘብህን እመልስልሃለሁ›› አለው፡፡ ፎላም ይህን በሰማ ጊዜ እንደ አስቆሮቱ ይሁዳ ልቡ በገንዘብ ፍቅር ተነድፏልና ልቡናውን አጽንቶ ቅዱሳት ደናግሉን ሊገድላቸው ሄደ፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉት፡- ‹‹ከሃዲ ሆይ የመድኃኒታችንን የክርስቶስን ቅዱስ ሥጋውንና ክቡር ደሙን በእጅህ ታቀብለን አልነበረምን? ስለ ገንዘብ ፍቅር ብለህ እኛን የክርስቶስን በጎች ልታርድ መጣህን?›› እያሉ በገሠጹት ጊዜ ሰልፍ እንደተማረ አርበኛ ሰው ሆኖ በሰይፍ ራስ ራሶቻቸውን ቆረጣቸው፡፡ መኰንኑም የፎላንን ብላሽነትና ድንቁርናውን አይቶ ወዲያው በሰይፍ ገደለው፡፡ ፎላም ገንዘቡን፣ ሃይማኖቱንና ነፍሱን አጣ፡፡ የእነዚህም ቅዱሳት ደናግል ስማቸው መሪ የሆነቻቸው ጤቅላ፣ ማርያ፣ ማርታ፣ አመታ፣ አበያ ሲሆን ጥር 30 ቀን ሰማዕትነታቸውን በድል ፈጽመው የክብር አክሊልን ተቀዳጅተዋል፡፡ የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ቅድስት ሶፍያ ዘአንጾኪያ፡- በዚህች ዕለት ቅድስት ሶፍያና ሦስት ልጆቿ በሰማዕትነት ያረፉ ሲሆን የልጆቿ ስም ጲስጢስ፣ አላጲስና አጋጲስ ነው፡፡ የስማቸውም ትርጓሜ በቅደም ተከተላቸው መሠረት ‹‹ሃይማኖት፣ ተስፋ፣ ፍቅር›› የሚል ነው፡፡ ዕድሜአቸውም 12፣ 10 እና 9 ነው፡፡ የራሷ የሶፍያ የስሟ ትርጓሜ ደግሞ ጥበብ ማለት ነው፡፡
ይኽችም ቅድስት ሶፍያ ከአንጾኪያ ከከበሩ ወገኖች የተገኘች ናት፡፡ ልጆቿም ባደጉ ጊዜ ወደ ሮሜ ከተማ ወስዳ እግዚአብሔርን መፍራትንና የቤተ ክርስቲያንን ትምህርት አስተማረቻቸው፡፡ የልጆቹም ምግባር ሃይማኖታቸው በከሃዲው የሮም ንጉሥ በአርያኖስ ዘንድ ስለተሰማ ንጉሡ ጭፍሮቹን ልኮ አስመጣቸው፡፡ እናታቸውም ‹‹ልጆቼ ተጠበቁ የዚህን የኃላፊውን ዓለም ክብር በማየት ልባችሁ እንዳይደክምና ከዘላለማዊ ክብር እንዳትርቁ፣ ከሙሽራው ከክርስቶስ ጋር ሆናችሁ ወደ ሰማያዊው ሠርግ እንድትገቡ ጠንክሩ…›› እያለች ትመክራቸውና ታጽናናቸው ነበር፡፡ ከዚህም በኋላ እናታቸው ይዛ ወደ ንጉሡ አቀረበቻቸው፡፡ ንጉሡም ታላቂቱን የ12 ዓመቷን ጲስጢስን ‹‹ስታድጊ ከመንግሥቴ ታላላቅ ባለሥልጣናት ውስጥ ከአንዱ ጋር አጋባሻለሁ፣ ብዙ ስጦታንም እሰጥሻለሁ፡፡ አሁን ግን ለጣዖቴ ለአጵሎን ስገጂ›› እያለ ሊደልላት ሞከረ፡፡ እርሷም ንጉሡንና የረከሱ አማልክቶቹን ረገመቻቸው፡፡
ንጉሡም አማልክቶቹንና እርሱን ስለረገመች ቅድስት ጲስጢስን እጅግ በጽኑ ሥቃዮች አሠቃያት፡፡ በብረት ዘንግ አስደበደባት፤ ጡቶቿን አስቆረጣቸው፤ በብረት ምጣድ አድርጎ ከሥር እሳት አስነደደባት ነገር ግን በእሳቱ ውስጥ ሆና ስትጸልይ እሳቱ እንደጠዋት ጤዛ ቀዝቃዛ ሆነ፡፡ በዙሪያዋ ያሉና ይህንን ተአምር ያዩ ሰዎች ሁሉ ‹‹በዚህች ብላቴና አምላክ እናምናለን›› ብለው ጮኹ፡፡ ወዲያውም ራሶቻቸውን ቆረጧቸውና በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
ከዚህም በኋላ የቅድስት ጲስጢስ አንገት ይቆርጡት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ እንዳዘዘውም አንገቷን ሰየፏትና ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ የክብር አክሊልን ተቀዳጀች፡፡ እናቷም ሥጋዋን አንሥታ ወሰደች፡፡ አሁንም ንጉሡ በሁለተኛይቱ ልጅ በቅድስት አላጲስ ላይም እንዲሁ ተመሳሳይ ሥቃይ አደረሰባትና አንገቷን አስቆረጠው፡፡ አሁንም እናቷ ቅድስት ሶፍያ ሥጋዋን አንሥታ ከወሰደች በኋላ እንዳትፈራ በማሰብ ስለ 9 ዓመቷ ታናሽ ልጇ ስለ አጋጲስ ጸለየች፤ አጽናናቻትም፡፡ ወዲያውም አጋጲስን አንስተው በመንኰራኩር ውስጥ ጨመሯት፡፡ የታዘዘ መልአክም መንኰራኩሩን ሰበረውና በሰላም ወጣች፡፡ ዳግመኛም ነበልባሉ እስከ ሰማይ የሚደርስ እሳትንም አንድደው በዚያ ይጨምሯት ዘንድ ንጉሡ አዘዘ፡፡ ቅድስት አጋጲስም በመስቀል ምልክት አማትባ ወደ እሳቱ ተወርውራ ገባች፡፡ ጌታችንም መልአኩን ልኮ እሳቱ እንደ ውርጭ አቀዘቀዘላት፡፡ በዚያ ተሰብስበው የነበሩ ሰዎችም ሁለት ነጫጭ ልብሶችን የለበሱ ሰዎች በልብሳቸው ሲጋርዷት አይተው እጅግ አደነቁ፡፡ በጌታችንም ስም አምነው ምስክንርነታቸውን ሲሰጡ ራሶቻውን በሰይፍ ቆርጠዋቸው በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡
በመጨረሻም የቅድስት አጋጲስንም አንገቷን በሰይፍ ቆርጠው ሰማዕትነቷን በድል ፈጽማ አክሊልን እንድትቀዳጅ አደረጓት፡፡ የከበረች ሶፍያም የሦስት ልጆቿን ሥጋቸውን ወስዳ ገነዘቻቸውና ከከተማው ውጭ ወስዳ ቀበረቻቸው፡፡ በ3ኛውም ቀን መቃብራቸው ላይ ሄዳ በማልቀስ ነፍሷን ይወስድ ዘንድ ጌታችንን ለመነችው፡፡ ጌታችንም ልመናዋን ሰምቶ ጥር 30 ቀን ነፍሷን ወሰዳት፡፡ መእመናንም መጥተው ገንዘው ከልጆቿ ጋር ቀበሯት፡፡ ከሃዲው ንጉሡ ግን በተአምራት ወዲያው ዐይኖቹ ጠፍተው ሥጋው ሁሉ ተሰነጣጠቀ፡፡ እጆቹም ተቆራርጠው፣ ሰውነቱ ተልቶና ሸቶ ክፉ አሟሟት ሞተ፡፡
የሰማዕታቱ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን በጸሎታቸው ይማረን!
ከገድላት አንደበት
✞ ✞ ✞