*__*
ዮሐንስ ዘሰዋስው ስለ ቀቢጸ ተስፋ ሲያስረዳ፦ "ቀቢጸ ተስፋ የመቀባጠር አንዱ ቅርንጫፍ፣ የእርሱም የበኲር ልጅ ናት። ... ቀቢጸ ተስፋ የነፍስ ልምሾነት (መሰልሰል)፣ የአእምሮ መዛል (መድከም)፣ ተጋድሎን ቸል ማለት፣ ብፅዓትን (ቃል ኪዳንን) መጥላት ነው። ... እግዚአብሔርንም ምሕረት የለሽና ሰዎችን የሚጠላ እንደ ኾነ አድርጋ ትከሳለች። መዝሙራትን ለመዘመር የምትዝል፣ ለጸሎት የምትደክም፣ ለአገልግሎት እንደ ብረት የጸናች (ግትር የኾነች)፣ ለተግባረ እድ የምትተጋ፣ ለመታዘዝ ኹኔታ (ብቃት) ቸልተኛ ናት።" ይላል። (ሳሙኤል ፍቃዱ (ሐተታና ትርጒም)፣ ምዕራግና ድርሳን፣ 2011 ዓ.ም፣ ገጽ 173)። ከዚህ ትርጒም ተነሥተን ተስፋ መቍረጥ ለመንፈሳዊ አገልግሎት ያለንን ስልቹነት፣ ወይም ጥላቻ የሚያመለክት ነው ማለት እንችላለን። ልበ አምላክ ዳዊት "ሰነፍ በልቡ እግዚአብሔር የለም ይላል" እንዳለ በንዝኅላልነታችን ምክንያት እግዚአብሔር የለም ብለን እስከ ማመን የምንደርስበት ክፉ አኗኗር በቀቢጸ ተስፋ ኾኖ መኖር ነው። ተስፋ የሚቈርጥ ሰው ስኬት ላይ መድረስ አይችልም። ሕይወቱን በበጎ ጎዳና መምራት አይኾንለትም። ምክንያቱም ማንኛውም ነገር ጥረትንና ተጋድሎን ይሻልና። አንዴ ወደሚፈልገው መንገድ እየሄደ ውድቀት ካገጠመው ኹሉም ነገር ወዲያ ጨለማ መስሎ ይታየዋል።
በዋናነት ብዙ ሰዎች በተስፋ መቍረጣቸው ምክንያት ራሳቸውን ለማጥፋት ይወስናሉ። ተስፋ መቍረጥ የእግዚአብሔርን ምሕረት የመርሳትና ይሁዳን የመምሰል ሕይወት ነው። ተስፋ የሚቈርጥ ሰው ከዚህ ሐሳቡ ለመውጣት ሲል ወደ ሱስ ይጓዛል። በጽኑ ሱስ ሲያዝ ደግሞ የበለጠ የሕይወትን ጣዕም እያጣ ይሄዳል፤ ኋላም ራስን ማጥፋትን እንደ ቀላል ነገር አድርጎ ሊመለከት ይችላል። ቅዱስ ይስሐቅ ዘሶርያ "በመሰናክልህ ምክንያት ተስፋ አትቍረጥ። ይኸውም ኃጢአትህን በማሰብ አትጸጸት ማለቴ ሳይኾን፥ ነገር ግን የማይድኑ አድርገህ አታስብ ማለቴ ነው።" በማለት የገለጸው ብዙውን ጊዜ ተስፋ መቁረጥ ከኃጢአቴ አልነጻም፣ መዳን አልችልም ብሎ ከማሰብ የሚመጣ ስለ ኾነ ነው። The Ascetical Homilies of St. Isaac the Syrian, Homily 64, “On Prayer, Prostrations, Tears, Reading, Silence, and Hymnody”። ወንድሜ ሆይ! ምንም ዓይነት መሰናክል ሊገጥምህ ይችላል፤ ነገር ግን ከልብህ ተጸጽተህ ንስሓ ከገባህ የሚድን መኾኑን አትዘንጋው። ከማንኛውም ውድቀትህ በላይ እግዚአብሔር የሚያዝንብህ አይምረኝም ብለህ ማመን ስትጀምር ነው። ንስሓ ከተገባበት የማይድን ምንም ዓይነት አደገኛ የኃጢአት በሽታ የለምና። የደማስቆው ጴጥሮስ "ነፍስን የሚገድለውን ተስፋ መቍረጥን፥ ጽኑ ተአጋሲነት ይገድለዋል።" በማለት ያስረዳል። St. Peter of Damaskos, “Book II: Twenty-Four Discourses,” V Patient Endurance, The Philokalia: The Complete Text (Vol. 3)። እንግዲህ ይህ የሊቁ አገላለጽ በአንድ በኩል ተስፋ መቍረጥ ነፍስን የሚገድል መርዝ መኾኑን የሚጠቁም ሲኾን፥ በሌላ በኩል በትዕግሥት ሊነቀል የሚችል መኾኑን ያስረዳል። ስለዚህ ተስፋ መቍረጥ ትዕግሥትን በማጣት የሚበቅል ክፉ አረም መኾኑን በዚህ እናስተውላለን።
ዮሐንስ ዘካርፓቶስ እንዲህ ይላል "ፈርዖን ፈርቶ እንዲህ አለ፦ "ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን በፍጥነት ጠራ፦ አምላካችሁን እግዚአብሔርን እናንተንም በደልሁ፥ አኹን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ፣ አላቸው። ሙሴም ከፈርዖን ፊት ወጣ ወደ እግዚአብሔር ለመነ።" ፈርዖንም ተሰማለት። በተመሳሳይ ኹኔታ አጋንንትም ጌታችንን ወደ ገደል እንዳይከታቸው ለመኑ፥ ጥያቄያቸው ተመለሰላቸው። ሉቃ 8፡31። እንግዲያው አንድ ክርስቲያን ከመንፈሳዊ ሞት ይወጣ ዘንድ ቢለምን ምን ያህል የበለጠ ይሰማለት ይኾን?" በማለት በምንም መንገድ ተስፋ ወደ መቍረጥ መሄድ እንደ ሌለብን ነው።(St. John of Karpathos, For the Encouragement of the Monks in India who had Written to Him: One Hundred Texts (69)። ያን ጨካኙን ፈርዖንን የሰማ አምላክ አንተን እንዴት አይሰማህም? በመስቀል ላይ የሚሰቅሉትን እኒያን አይሁድን የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ የምሕረት ድምፁን ያሰማ እርሱ አይምረኝም ብለህ ስለምን ትጨነቃለህ? ይልቅስ ኃጢአትህን አምነህ ይቅር ይልህ ዘንድ ወደ ፈጣሬ ዓለማት ወደ ኾነው ጌታ በአንብዓ ንስሓ ብትቀርብ አይሻልህምን? ተስፋ ስንቈርጥ ሁሉንም ነገር አጥርተን ማየት አንችልም። ልክ በጨለማ ውስጥ ያለ ሰው በብርሃን አለመኖር ምክንያት ከፊት ለፊቱ ያሉ ነገሮችን አጥርቶ ማየት እንደ ማይችል፥ ተስፋ በመቍረጥ ጨለማ ውስጥ ያለም ሰውም እንዲሁ አጥርቶ ማየት አይችልም።